05/07/2023
ተማሩ ሳትማሩ እየገባችሁ ኢትዮጵያ ሗላ ቀር እና ድሃ አደ!!ኢትዮ ቴሌኮም የአንድ ብሄር ተወላጆች በበላይነት እንዲቆጣጠሩ እየተደረገ መሆኑን ሰራተኞች ገለፁ።
================================================
ሾልኮ ኦ ኤም ኤን የደረሰው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የአመራር የብሄር ስብጥር መረጃም ከአንድ ብሄር የመጡ አመራር ሰንሰለት ፈጥረው የሚሰሩበት ድርጅት መሆኑንም አመላክቷል።
በኢትዮ ቴሌኮም በዋና ስራ አስፈፃሚ የሚመመራ ሲሆን፣ ከዋና ስራ አስፈፃሚ ቀጥሎ ቺፍ፣ ዳሬክተር፣ ማናጀር፣ ሱፐርቫይዘር የሚባሉ የአመራር እርከን ይገኛሉ።
ሰሞኑን ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ ባለው የአመራር እርከን ላይ ባለው የብሄር ተዋፅዖ አስመልክቶ የተደረገው ጥናት ውጤት ለኦ ኤም ኤን ደርሷል።
ጥናቱ እንዳመለከተው ከዋና ስራ አስፈፃሚ ቀጥሎ ባለውና ቺፍ በመባል የሚታወቀው የአመራር ቦታ 10 በአማራ ተወላጅ፣ 6 በኦሮሞ ተወላጅ፣ 2 በካምባታ ተወላጅ እንዲሁም 1 በትግራይ፣ በጉራጌና በጋሞ ተይዟል።
ምክትል ቺፊ የሚባለው የአመራር ቦታ ደግሞ 4ቱ በአማራ ተወላጆች ተይዟል።
ዳይሬክተር የሚባል የሚባል ቦታ ደግሞ 57 በአማራ ተወላጅ፣ 11 በኦሮሞ ተወላጅ፣ 9 በትግራይ ተወላጅ፣ 5 በጉራጌ ተወላጅ፣ 3 በስልጤ፣ 1 በፋር ተወላጅ መያዙን ሰነዱ አመላክቷል።
በሰነዱ መሰረት የማናጀርነት ቦታን በተመለከተ ደግሞ 242 በአማራ ተወላጆች የተያዘ ሲሆን 50 በኦሮሞ፣ 26 በትግራይ፣ 6 በጉራጌ፣ 2 በስልጤ እንዲሁም አንዳንድ በጋሜ፣ በሀረሪ፣ ሀዲያ፣ ዎላይታ ተይዘዋል።
በአጠቃላይ ድምሩ ኢትዮ ቴሌኮም ውስን ቦታ ላይ ያለው የአመራር ስብጥር 313 የአማራ ተወላጆች ሲሆኑ፣ 67 የአሮሞ፣ 36 የትግራይ፣ 12 የጉራጌ፣ 5 የስልጤ፣ 2 የጋሞ፣ 2 የካምባታ ተወላጆች እንደሆኑ ተመላክተዋል።
አንዳንድ የአፋር፣ የሀረሪ፣ የሀድያና ዎላይታ ተወላጆችም እንዳሉ ሰነዱ አመላክቷል።
ጉዳዩን በተመለከተ ኦ ኤም ኤን ያነጋገራቸው የድርጅቱ ሰራተኞች በበኩላቸው ድርጅቱ ውስጥ የተዘረጋው የአንድ አካባቢ ሰዎች የአመራር ሰንሰለት ድርጅቱን የዘረፋና ምዝበራ ማእከል አድርጓል ብለዋል።
በአከባቢ በመደራጀት የተፈጠረው የአመራር ሰንሰለት ሁሉም ብሄሮችና ብሄረሰቦች በድርጅቱ ውስጥ በፍትሃዊነት እንዳይሳተፉ አድርጓል ይላሉ።
የሀገሪቷ ተቋማት ሁሉንም ህዝቦች መምሰል እያለባቸው ዛሬም እንደአሮጌ ዘመን በአንድ አካባቢ ሰዎች በበላይነት እንዲያዙ ማድረግ አሳዛኝ ነው ብለዋል።
በዚህ ላይ በድርጅቱ ውስጥ የተንሰራፋው የሙስናና ዘረፋ ሰንሰለት በጊዜ መላ ካልተበጀለት አደጋው የከፋ መሆኑን ተናግረዋል።
ኦ ኤም ኤን ያነጋገረው ማህበራዊ ኣንቂ በበኩሉ የአማራ ፅንፈኛ የፖሊትካ ቡድኖች በፌዴራል ተቋማትና በፊንፊኔ ከተማ ውስጥ ያለውን ጉድ ለመሸፋፈን አስቀድሞ ሌላውን በውሸት ይወነጅላሉ ብሏል።
በፌዴራል መንግስቱና በፊንፊኔ ከተማ የመንግሥት መዋቅር ውስጥ የያዙትን የበላይነትና ኢፍትሃዊ ተጠቃሚነታቸውን ለመከላከል ቀድመው ተረኛ በማለት የኦሮሞ ህዝብን ባልዋለበት ለመውቀስ እየሞከሩ ነው ይላሉ።
ለእነዚህ ፅንፈኛ ቡድኖች እኩልነትና ፍትሃዊ ተሳታፊነት ተሸናፊነት ይመስላቸዋል ብሏል።
ይህ በፌዴራል መንግስቱና በፊንፊኔ ከተማ የመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሚስተዋለው ችግር በአፋጣኝ መፈታት እንዳለበት መክረዋል።