Chilalo Authorized Accounting & Tax Services

Chilalo Authorized Accounting & Tax Services Established to Provide Accountancy & Tax advisory Services, Prepare Financial Statements for general

14/02/2025

የኦዲት መርሆዎች

ማንኛውም የኦዲት ተቋም የኦዲት ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ የሚከተሉትን መሠረታዊ መርሆዎች መከተል ይገባዋል፡፡

-ማንኛውም ኦዲት ሲካሄድ የሂሳብና የኦዲት ደረጃዎችን መሠረት ማድረግ አለበት፤

-በኦዲቱ ሂደት ከፍተኛ የሙያና መልካም የግል ሥነ-ምግባር ሊጠበቅ በሥራም ሂደት ሊገለጽ ይገባል፤

-ሁሉም ኦዲቶች ነጻ በሆነ መንገድ ሊካሄዱና ሪፖርት ሊደረጉ ይገባል፤

-በኦዲት ወቅት የታዩ ትኩረት የሚሹ ማናቸውም ጉዳዮች በሪፖርቱ መካተት አለባቸው፤

-በኦዲቱ ሥራ የሚደረስባቸው መደምደሚያዎችና የሚቀርቡ የማሻሻያ ሃሳቦች ሁሉ በበቂ የኦዲት ማስረጃ ሊደገፉ ይገባል፤

-ኦዲተሮች በኦዲት የሥራ ሂደት ማንኛውንም መረጃ የማግኘት መብት አላቸው፡፡ ምንም ዓይነት ክልከላ ሊደረግባቸው አይገባም፡፡

-የኦዲቱን ዓላማ፣ ወሰን እንደዚሁም በኦዲቱ ሂደት የሚገኙ ግኝቶችን አስመልክቶ የመጨረሻ ሪፖርት ከመውጣቱ አስቀድሞ ከኦዲቱ ተደራጊው ጋር በቂ ውይይት መደረግ አለበት፡፡

05/05/2024
29/09/2023

ሰነዶችን ባለመያዝ የሚጣል ቅጣት

I. የዚህ ተራ ቁጥር (II) እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በታክስ ሕግ መሠረት መያዝ የሚጠበቅበትን ማንኛውንም ሰነድ ያልያዘ ታክስ ከፋይ በታክስ ሕጉ መሠረት ሰነዱ መያዝ በነበረበት የታክስ ዘመን መክፈል ያለበትን ታክስ 20% (ሃያ በመቶ) ቅጣት ይከፍላል፡፡

II. በዚህ ተራ ቁጥር (I) መሠረት ሰነድ መያዝ ሲኖርበት ያልያዘ ታክስ ከፋይ ሰነዱን መያዝ በነበረበት የታክስ ዘመን መክፈል የሚኖርበት ታክስ የሌለ እንደሆነ:-
ሀ) ለገቢ ግብር ሲሆን ታክስ ከፋዩ የሂሳብ ሰነድ ላልያዘበት ለእያንዳንዱ የታክስ ዘመን ብር 20ሺ (ሃያ ሺ ብር)፤ ወይም
ለ) ለሌላ ማንኛውም ታክስ ሲሆን ታክስ ከፋዩ የሂሳብ ሰነድ ላልያዘበት የታክስ ዘመን ብር 2ሺ (ሁለት ሺ ብር)፤ ቅጣት ይከፍላል፡፡

III. በዚህ ተራ ቁጥር (I) መሠረት የሚጣለው ቅጣት በዚህ ተራ ቁጥር (II) ከሚጣለው ቅጣት ያነሰ እንደሆነ የዚህ ተራ ቁጥር (II) ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

IV. የዚህ ተራ ቁጥር(I)፣ (II) እና (III) እንደተጠበቁ ሆነው፣ ማንኛውም ታክስ ከፋይ ከሁለት ዓመት በላይ የሂሣብ ሰነድ ካልያዘ ለታክስ ከፋዩ የንግድ ፈቃድ የሰጠው አካል ከባለሥልጣኑ በሚቀርብለት ማስታወቂያ መሠረት የታክስ ከፋዩን የንግድ ፈቃድ ይሰርዛል፡፡

V. ሰነዶችን ይዞ ማቆየት ላለበት ጊዜ ሳያቆይ የቀረ፤
• የደረጃ ‘ሀ’ ታክስ ከፋይ ብር 50 ሺ (ሃምሳ ሺ ብር) ቅጣት ይከፍላል፡፡
• የደረጃ ‘ለ’ ታክስ ከፋይ ብር 20 ሺ (ሃያ ሺ ብር) ቅጣት ይከፍላል፡፡

VI. በታክስ ሕጉ መሠረት መያዝ የነበረበት ሰነድ ማለት:-

ሀ. የገቢ ግብርን በሚመለከት ለደረጃ ሀ የትርፍና ኪሳራ እና የሀብትና ዕዳ መግለጫ፣ ለደረጃ ለ የትርፍና ኪሳራ መግለጫ እንዲሁም እነዚህን መግለጫዎች ለማዘጋጀት መሠረት የሆኑ ሰነዶች፣
ለ. የተጨማሪ እሴት ታክስና ተርን ኦቨር ታክስ በሚመለከት የግዥና ሽያጭ መዝገብና ታክሱን ለማስላት የሚረዱ ደጋፊ ሰነዶች፣
ሐ. የኤክሳይድ ታክስን በሚመለከት ታክሱን ለማስላት የሚያግዙ የሒሳብ መዛግብትና ደጋፊ ሰነዶች፡፡

VII. ታክስ ከፋዩ በዚህ ተራ ቁጥር v| የተዘረዘሩትን ሰነዶች እንደያዘ የሚቆጠረው ያቀረበው ሰነድ ስለመዝገብ አያያዝ ባለሥልጣኑ በሚጠይቀው መሠረት የቀረበ እና አስፈላጊ ደጋፊ ሰነዶች እንዲያቀርብ ባለሥልጣኑ ሲጠይቀው ያቀረበ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡

VIII. የታክስ ዘመን ማለት:-

ሀ. ለገቢ ግብር ማስታወቂያ የሚቀርብበት ታክስ የሚሸፈነው የአንድ ዓመት ጊዜ፣
ለ. ለተጨማሪ እሴት ታክስ እንደታክስ ከፋዩ የግብይት መጠን አንድ ወር ወይም ሶስት ወር፣
ሐ. ለተርን ኦቨር ታክስ የደረጃ ሀ ታክስ ከፋዮች እንደ ታክስ ከፋዩ የግብይት መጠን አንድ ወር ወይም ሶስት ወር፣ ለደረጃ ለ ታክስ ከፋዮች ሶስት ወር ነው፡፡
መ. ለኤክሳይዝ ታክስ ምርት አንድ ወር ነው፡፡

17/08/2023

ግብር ቀንሶ የመያዝ ስርዓት ተፈጻሚ የማይደረግባቸው ግብይቶች፡-

• የሰው ወይም የእንሰሳት ህክምና አገልግሎት፤
• የመደበኛ ትምህርት አገልግሎት (ስልጠናን አይጨምርም፤
• የፋይናንስ አገልግሎት(ባንክ የደንበኞቹን ንብረት ሲሸጥ የሚቀበለውን ክፍያ አይጨምርም፤
• የኤሌክትሪክ አገልግሎት፤
• የቴሌ ኮሚኒኬሽን አገልግሎት፤
• የየብስ፣ የአየር፣ የባህር እና የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት (ኪራይን አይጨምርም)
• የውሃ አገልግሎት (የታሽገ ውሃን አይጨምርም)፤
• ከገቢ ግብር ነፃ መብት የተሰጣቸው ኢቨስተሮች ከግብር ነፃ በሆኑበት ጊዜ ውስጥ የሚሠጡት አገልግሎት ወይም የሚያቀርቡት ዕቃ፤
• የነዳጅ አቅርቦት ( ቅባትና ዘይቶችን አይጨምርም )፤
• በፌደራልና በክልል የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ መሠረት ለመንግስት መ/ቤት በተሰጠው ትርጉም ውስጥ የሚካተቱ ወይም በተቋቋመበት ህገ መንግስት የመንግስት መ/ቤት የተባሉ የፌዴራል፣የክልል፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት መ/ቤቶች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች፤
• ለትርፍ ያልተቋቋሙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ማህበራት የሚያቀርቧቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች ከተቋቋሙበት አላማ ውጪ በንግድ መልክ የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎችና አገልግሎቶች አይጨምርም፤
• በዲፕሎማቲክና ሌሎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት ለተቋቋሙ የአለም አቀፍ ድርጅቶች የውጭ ዲፕሎማቲክ ወይም ኮንሱላር ሚስዮኖችና ኢምባሲዎች እና ለተባበሩት መንግስታት አካላት የሚፈጸም ክፍያ፤
• ለትርፍ ያልተቋቋሙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ማህበራት የሚያቀርቧቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች ከተቋቋሙበት አላማ ውጪ በንግድ መልክ የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎችና አገልግሎቶች አይጨምርም፤
• በዲፕሎማቲክና ሌሎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት ለተቋቋሙ የአለም አቀፍ ድርጅቶች የውጭ ዲፕሎማቲክ ወይም ኮንሱላር ሚስዮኖችና ኢምባሲዎች እና ለተባበሩት መንግስታት አካላት የሚፈጸም ክፍያ፤
• በገቢ ግብር ህግ መሰረት ከግብር ነፃ የሆነ ገቢ(የሰንጠረዥ “ሠ” ገቢዎች)፣
• ከመንግስት በተሠጣቸው ውክልና መሰረት ዕቃ ወይም አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶች፤
• የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚፈፅምለት ክፍያ፤
• የፋብሪካ ምርት ያልሆነ (የአርብቶ አደር እና የአርሶ አደር የግብርና እና የእንሰሳት ውጤት እንዲሁም ከእንሰሳት የሚገኝ አገልግሎት )፣
• የመኖሪያ ቤት ሽያጭ፤
• በሰው ጉልበት የሚከናወን ዕቃ የመጫን እና የማውረድ አገልግሎት፣
• ቅይጥ ግብይት (አንድ ግብይት ውስጥ ቅድመ ግብር የሚመለከተውና የማይመለከተው ግዥ)፤
• በማቋቋሚያ ህጋቸው ከገቢ ግብር ነፃ የሆኑ ተቋማትን ሚኒስቴሩ ለሌሎች እቃዎች ወይም አገልግሎቶች ግዢ የሚፈጸም ክፍያ የቅድመ ግብር ክፍያ ስርዓት ተፈጻሚ እንዳይደረግበት ሊወስን ይችላል፡፡

27/06/2023

የግብር/ታክስ ሕጋዊ ሥልጣን በኢትዮጵያ

ታክስ የመጣልና የማስተዳደር ስልጣን የፌዴራልና የክልል መንግስታት ነው፡፡ ገቢውም እንዲሁ የፌዴራል፣ የክልልና የሁለቱም የጋራ ገቢ ተብሎ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 95፣ 96፣ 97፣ 98 እና 99 ላይ ተቀምጧል፡፡

የፌደራል መንግስቱ ስልጣን

1. በወጪና ገቢ እቃዎች ላይ የሚጣል የጉምሩክ ቀረጥ፣ ታክስና ሌሎች ክፍያዎች፤
2. በፌዴራል መንግስት ባለቤትነት ስር ከሆኑ የልማት ድርጅቶች ላይ የሚሰበሰብ የንግድ ትርፍ ግብር፣ የስራ ግብር፣ የተጨማሪ አሴት ታክስና የኤክሳይዝ ታክስ፤
3. ከብሔራዊ ሎተሪ እና ሌሎች የእድል ሙከራ ገቢዎች ላይ የሚሰበሰብ ታክስ፣
4. ከአየር፣ ከባቡርና ከባህር ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የሚሰበሰብ ታክስ፤
5. በፌዴራል መንግስት ባለቤትነት ስር ከሚገኙ ቤቶችና ሌሎች ንብረቶች ገቢ ላይ የሚሰበሰብ ታክስ፣
6. የሞኖፖል ታክስ፣ የፌዴራል የቴምብር ሽያጭና ቀረጥ፣ መሰብሰብ ሲሆን፣
7. ከፌደራል መንግስትና ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተቀጣሪዎች የሚሰበሰብ የስራ ግብር (ከ1996 በጀት ዓመት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር እንዲሰበሰብ ተደርጓል)

የክልል መስተዳድሮች ስልጣን

1. ከክልል መስተዳድርና ከድርጅት ተቀጣሪዎች ላይ የሚሰበሰብ የስራ ግብር፤
2. የመሬት መጠቀሚያ ክፍያና በግል ከሚያርሱና በህብረት ስራ ማህበር ስር ከተደራጁ ገበሬዎች ላይ የሚሰበሰብ የንግድ ትርፍ ግብርና የተርን ኦቨር ታክስ፤
3. በክልል ከሚገኙ ግለሰብ ነጋዴዎች ላይ የሚሰበሰብ የንግድ ትርፍ ግብርና የተርን ኦቨር ታክስ፤
4. በክልል ውስጥ በውሃ ላይ ከሚደረግ ትራንስፖርት ከሚገኝ ገቢ ላይ የሚሰበሰብ ግብር፤
5. በክልል መስተዳድር በግል ባለቤትነት ስር ካሉ ቤቶችና ሌሎች ንብረቶች ከሚገኝ ገቢ ግብር፤
6. በክልል መስተዳድር ባለቤትነት ስር ካሉ ቤቶችና ሌሎች ንብረቶች ከሚገኝ ገቢ ግብር፤
7. በክልል መስተዳደር ባለቤትነት ስር ከሚገኙ የልማት ድርጅቶች የሚሰበሰብ የንግድ ትርፍ ግብር፣ የስራ ግብር፣ የተርን ኦቨርና ኤክሳይዝ ታክስ፤
8. በክልል መስተዳድር አካላት ከሚሰጡት ፍቃዶችና አገልግሎቶች የሚመነጩ ክፍያዎች፣
9. ከደን የሮያሊቲ ክፍያ፤
10. ከአነስተኛ የማዕድን ሰራዎች ላይ የሚሰበሰብ የማእድን ገቢ ግብር እና የሮያሊቲና የመሬት ኪራይ ክፍያዎች ናቸው።

የፌዴራልና የክልሎች የጋራ ስልጣን

1. የፌዴራል መንግስትና ክልሎች በጋራ ከሚያቋቁማቸው የልማት ድርጅቶች ላይ የሚሰበሰብ የንግድ ትርፍ ግብር፣ የስራ ግብር፣ የተርን ኦቨርና ኤክሳይዝ ታክስ፣
2. ከግል ድርጅቶች የንግድ ትርፍ ላይ እና ከባለ አክሲዮኖች የትርፍ ድርሻ ላይ የሚሰበሰብ ግብርና የተርን ኦቨር ታክስ፣
3. ከከፍተኛ የማእድን ስራዎችና ከማናቸውም የፔትሮሊየምና የጋዝ ስራዎች ላይ የሚሰበሰብ የገቢ ግብርና የሮያሊቲ ክፍያዎች ናቸው፡፡

18/07/2022

የማኑዋል ደረሰኝ ሲጠፋ ስለሚኖረው አሠራር
የማኑዋል ደረሰኝ ሲጠፋ የሚኖረው አሠራርን በተመለከተ ተፈፃሚነት የሚኖረው አሠራር፤
• ታክስ ከፋዩ ምንም ያልተሠራበት ደረሰኝ የጠፋበት መሆኑን ያስታወቀ እንደሆነ ባለሥልጣኑ በሌላ መንገድ ደረሰኝ የጠፋበት መሆኑን ባስታወቀው ታክስ ከፋይ ስለመሠራቱ የሚገልጽ መረጃ ካላገኘ በስተቀር ታክስ አይወሰንበትም፡፡
• ከላይ የተገለፀው ቢኖርም የጠፋበትን ማንዋል ደረሰኝ ለባለሥልጣኑ ስለመጥፋቱ ሲያሳውቅ የሚከተሉትን መረጃዎች መሠረት በማድረግ ታክሱ ይወሰናል፡፡
☑️ የጠፋው ደረሰኝ በከፊል የተሠራበት ከሆነ ቀሪ ካለው ከቀሪው ላይ የሚገኝ መረጃ፣ ወይም ቀሪ ከሌለው ታክስ ከፋዩ የተሠማራበት የንግድ ዘርፍ ባህሪ ከገዥዎቹ መረጃ የሚኝበት ሲሆን ከገዥዎች የተገኘውን መረጃ፣ ወይም
☑️ ታክስ ከፋዩ የሚያቀርባቸው ዕቃዎች ተመሳሳይ ዋጋና ደረጃ ያላቸው ሲሆኑ በቆጠራ የተሸጠውን ዕቃ ብዛት በመለየት የሽያጭ ደረሰኝ የጠፋባቸውን ዕቃዎችን የሽያጭ ደረሰኝ ባላቸው ዋጋ እንደተሸጡ ተቆጥሮ በማባዛት የሚገኝ ይሆናል፡፡
☑️ የሽያጭ መረጃ ለማግኘት ያልተቻለ እንደሆነ የታክስ ከፋዩ ዕቃ ወይም አገልግሎት ወቅታዊ የገበያ ዋጋ መሠረት ታክሱ በግምት የሚወሰን ይሆናል፡፡
☑️ የጠፋው ደረሰኝ ሙሉ ለሙሉ የተሠራበት ደረሰኝ ከሆነ የሚወክለውን ሽያጭ መጠን ለማግኘት ከላይ የተገለጹትን መንገዶች በመከተል ታክሱ ይወሰናል፡፡
• ታክስ ከፋዩ ምንም ያልተሠራበት ደረሰኝ የጠፋበት መሆኑን ሳያስታውቅ ባለሥልጣኑ በምርመራ ሂደት የደረሰበት እንደሆነ የተሠራበት ደረሰኝ እንደጠፋ ተቆጥሮ በተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ወቅት፣ ንግድ እና አካባቢ የሚገኝ የሦስት ታክስ ከፋይ ያስታወቀውን ወይንም የተወሰነበትን አማካይ ሽያጭ መሠረት በማድረግ ታክሱን በግምት ይወስናል፡፡

02/07/2022

የወጪ ሂሣብ

የወጪ ሂሣብ የኦዲት ግኝት የሚሆነው የሚከተሉት የአሠራር ክፍተቶች ተፈጽመው ሲገኙ ነው፡፡

- እቃው ንብረት ክፍል ገቢ መደረጉ ሳይረጋገጥ በወጪ ሲመዘገብ፤
-የዋጋ ማወዳደሪያና የጨረታ ማስታወቂያ ሳይወጣ የእቃ ግዥ ሲፈፀም፤
- ማስረጃ ሳይቀርብ ወይም ሳይሟላ ሂሣብን በወጪ ሲመዘገብ፤
-በፎቶ ኮፒ ማስረጃ ሂሣብን ሲወራረድ፤
-ከደንብና መመሪያ ውጭ ክፍያ ሲፈጸም፤
-መከፈል ከሚገበው በላይ በብልጫ ክፍያ ሲፈጸም፤
በመስክ ስራ ላይ ለሚገኙ የግንባታ ዕቃዎች ስራ ላይ ሳይውሉ ክፍያ ሲፈጸም፤
-ስልጣን በተሰጠው ኃላፊ ሳይፈቀድ ክፍያ ሲፈጸም፤

08/06/2022

በገደብ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች
☑️የትራንስፖርት አበል:-
• በሥራ ውል መሠረት ሥራውን ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር የሚያከናውን ተቀጣሪ ለአንድ ወር ጉዞ የሚከፈለው የትራንስፖርት ወይም የነዳጅ አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከጠቅላላ የወር ደሞዙ ከ1/4ኛ ባልበለጠ ብቻ ሲሆን የደመወዙ 1/4ኛ ከብር 2ሺ200 በላይ ከሆነ ታክስ ይከፈልበታል፡፡
• አንድ ተቀጣሪ ከመኖርያ ቤቱ ወደ ሥራ እንዲሁም ከሥራ ቦታው ወደ መኖሪያ ቤቱ ለመሄድ የነዳጅ ወጪ ወይም በጥሬ ገንዘብ የሚከፈለው የትራንስፖርት አበል 600 ብር ብቻ ነው፤
• አንድ ተቀጣሪ ሥራውን ለማከናወን ከመደበኛው የሥራ ቦታ ከሚገኝበት ውጪ ሲንቀሳቀስ ለትራንስፖርት ወጪ ከግብር ነፃ የሚሆነው በስራላይ ባለው የትራንስፖርት (የአየር፣የውሃ እና የየብስ) ዋጋ ሊበልጥ አይችልም፡፡
• አንድ የውጭ አገር ዜጋ ስራውን ለማከናወን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣና የውል ዘመኑን ጨርሶ ከሀገር ሲወጣ የሚከፈለው የትራንስፖርት ወጪ ከገቢ ግብር ነፃ ሊሆን የሚችለው በተፈጸመው የቅጥር ውል መሰረት እና የአየር፣ የውሃ እና የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎት ዋጋ ታሪፍ መሰረት ሆኖ ከግብር ነፃ የሚሆነው ለግል መገልገያ ዕቃዎች የሚከፈለው የጭነት ሂሳብ ከ300 ኪሎ ግራም ሊበልጥ አይችልም
☑️የስራ ቦታ አስቸጋሪነት የሚከፈል አበል ፡
• የሥራ ቦታ አስቸጋሪነት ከፍተኛ ሙቀት ወይም ለኑሮ አስቸጋሪ በመሆኑ ወይም በሌላ ተመሳሳይ ምክንያት በተቀጣሪው ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሚደርስ ጉዳት የሚከፈል አበል ሲሆን ፡-
🔹በሥራው ቦታ አስቸጋሪነት ምክንያት የሚከፈል አበል ከግብር ነፃ የሚደረገው የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባወጣው መመሪያ መሠረት(አንደኛ ደረጃ ቆላ ከሆነ ከደመወዙ 40%፣ ሁለተኛ ደረጃ 30% እና ሶስተኛ ደረጃ 20%) የሚከፈል ነው፡፡
🔹በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ማይተዳደሩ መ/ቤቶች እና የግል ድርጅቶች ተቀጣሪ ወይም ሹመኛ ጨምሮ በተመሳሳይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

02/06/2022

ግብር ቀንሶ የመያዝ ስርዓት ተፈጻሚ የማይደረግባቸው ግብይቶች:-
• የሰው ወይም የእንሰሳት ህክምና አገልግሎት፤
• የመደበኛ ትምህርት አገልግሎት (ስልጠናን አይጨምርም፤
• የፋይናንስ አገልግሎት(ባንክ የደንበኞቹን ንብረት ሲሸጥ የሚቀበለውን ክፍያ አይጨምርም፤
• የኤሌክትሪክ አገልግሎት፤
• የቴሌ ኮሚኒኬሽን አገልግሎት፤
• የየብስ፣ የአየር፣ የባህር እና የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት (ኪራይን አይጨምርም)
• የውሃ አገልግሎት (የታሽገ ውሃን አይጨምርም)፤
• ከገቢ ግብር ነፃ መብት የተሰጣቸው ኢቨስተሮች ከግብር ነፃ በሆኑበት ጊዜ ውስጥ የሚሠጡት አገልግሎት ወይም የሚያቀርቡት ዕቃ፤
• የነዳጅ አቅርቦት ( ቅባትና ዘይቶችን አይጨምርም )፤
• በፌደራልና በክልል የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ መሠረት ለመንግስት መ/ቤት በተሰጠው ትርጉም ውስጥ የሚካተቱ ወይም በተቋቋመበት ህገ መንግስት የመንግስት መ/ቤት የተባሉ የፌዴራል፣የክልል፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት መ/ቤቶች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች፤
• ለትርፍ ያልተቋቋሙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ማህበራት የሚያቀርቧቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች ከተቋቋሙበት አላማ ውጪ በንግድ መልክ የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎችና አገልግሎቶች አይጨምርም፤
• በዲፕሎማቲክና ሌሎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት ለተቋቋሙ የአለም አቀፍ ድርጅቶች የውጭ ዲፕሎማቲክ ወይም ኮንሱላር ሚስዮኖችና ኢምባሲዎች እና ለተባበሩት መንግስታት አካላት የሚፈጸም ክፍያ፤
• ለትርፍ ያልተቋቋሙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ማህበራት የሚያቀርቧቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች ከተቋቋሙበት አላማ ውጪ በንግድ መልክ የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎችና አገልግሎቶች አይጨምርም፤
• በዲፕሎማቲክና ሌሎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት ለተቋቋሙ የአለም አቀፍ ድርጅቶች የውጭ ዲፕሎማቲክ ወይም ኮንሱላር ሚስዮኖችና ኢምባሲዎች እና ለተባበሩት መንግስታት አካላት የሚፈጸም ክፍያ፤
• በገቢ ግብር ህግ መሰረት ከግብር ነፃ የሆነ ገቢ(የሰንጠረዥ “ሠ” ገቢዎች)፣
• ከመንግስት በተሠጣቸው ውክልና መሰረት ዕቃ ወይም አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶች፤
• የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚፈፅምለት ክፍያ፤
• የፋብሪካ ምርት ያልሆነ (የአርብቶ አደር እና የአርሶ አደር የግብርና እና የእንሰሳት ውጤት እንዲሁም ከእንሰሳት የሚገኝ አገልግሎት )፣
• የመኖሪያ ቤት ሽያጭ፤
• በሰው ጉልበት የሚከናወን ዕቃ የመጫን እና የማውረድ አገልግሎት፣
• ቅይጥ ግብይት (አንድ ግብይት ውስጥ ቅድመ ግብር የሚመለከተውና የማይመለከተው ግዥ)፤
• በማቋቋሚያ ህጋቸው ከገቢ ግብር ነፃ የሆኑ ተቋማትን ሚኒስቴሩ ለሌሎች እቃዎች ወይም አገልግሎቶች ግዢ የሚፈጸም ክፍያ የቅድመ ግብር ክፍያ ስርዓት ተፈጻሚ እንዳይደረግበት ሊወስን ይችላል፡፡

02/06/2022

በአይነት የሚገኙ ጥቅሞች ላይ ግብር የሚከፈልበት ሁኔታ
የገቢ ግብር ደንብ (410/2009) በዓይነት ለተቀጣሪው የሚሰጥ ጥቅማ ጥቅም ዋጋና ግብር የሚሰላበትን ሁኔታ፡-

🔹ከዕዳ ነጻ የመደረግ፤(ቀሪ የተደረገ የዕዳ መጠን)
🔹የቤተሰብ አገልግሎት ሠራተኞች፤(የቤትሰራተኛ፣ምግብአብሳይ፣ሹፌር፣አትክልተኛ)፣የመኖሪያ ቤት፤
🔹 የቅናሽ ወለድ ብድር፤(ከገበያው የማበደሪያ ወለድ ምጣኔ የሚያንስ)
🔹የምግብ ወይም መጠጥ አገልግሎት፤
🔹የግል ወጪዎች፤(ለተቀጠሪው የግል ወጪ ጥቅም የሚያስገኝ፣የተከፈለ ክፍያ…)
🔹የንብረት ወይም አገልግሎቶች፤
🔹የንብረቱን/አገልግሎቱን እንደመደበኛ የሚያቀርብ ከሆነ የዋጋውን 75% ወይም
🔹በሌላ ሁኔታ የንብረቱን/አገልግሎቱን መሸጫ ዋጋ፣
🔹የአየር ቲኬት ከሆነ ኢኮኖሚ ደረጃ የሚከፈለው ዋጋ
🔹የሠራተኞች የአክሲዮን ዐቅድ፤(ባለ አክስዮን የመሆን መብት/ምርጫ…)
🔹የተሸከርካሪ፤(ተሽከርካሪውን ለማግኘት የወጣ ወጪ ወይም ኪራይ (ሀ)*5%/12)
🔹 ሌላ የዓይነት ጥቅም፡፡
እንደ ዓይነት ጥቅሞች የማይቆጠሩ
• በሠንጠረዥ “ሠ” ከገቢ ግብር ነጻ የሆኑ ገቢዎች መሠረት ከግብር ነጻ የተደረገ ጥቅም፤
• ቀጣሪ ተመሳሳይ ጥቅም የሚያቀርብበትን ድግግሞሽ ከግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋው አነስተኛ ከመሆኑ የተነሳ ማስላቱ ምክንያታዊ ያልሆነ እና ለአስተዳደር የማያመች ጥቅም፤
• በቀጣሪው ወይም በቀጣሪው ስም በሚተዳደር የሠራተኞች ምግብ ቤት፣ ካፊቴሪያ ወይም የመመገቢያ ክፍል ያለምንም ልዩነት ለመደበኛ ሠራተኞች ጥቅም ብቻ ተብሎ የሚቀርብ የምግብና የመጠጥ አገልግሎት ድጎማ፤
• የሥራ አመራር አካል ላልሆነ ተቀጣሪ በሩቅ ሥፍራ የሚቀርብ የማረፊያ ወይም የመኖሪያ ቤት አገልግሎት፤
• ተቀጣሪው እንዲጠቀምበት በቀጣሪው የሚቀርብ ተንቀሳቃሽ ስልክ፤
• በቀጣሪው በቀረበ የተንቀሳቃሽ ስልክ የተደረገን ጥሪ ጨምሮ ቀጣሪ ለተቀጣሪ የሚሸፍነው የተንቀሳቃሽ ስልክ ጥሪዎች ወጪ፤
• በዩኒቨርሲቲ፣ በኮሌጅ ወይም በጎልማሶች ትምህርት በሚሰጥ ሌላ ተቋም የሚሰጥ ትምህርት መከታተል እንዲችል ቀጣሪ ለተቀጣሪ የሚፈጽመው የትምህርት ወይም ሥልጠና ክፍያ፤
• ለተቀጣሪ ጥቅም የሚቀርብ የደህንነት ጥበቃ አገልግሎት፤
• ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች እና የምግብ አገልግሎት የሚያቀርቡ ሌሎች ተቋሞች ለተቀጣሪዎቻቸው የሚያቀርቡት የምግብና መጠጥ አገልግሎት፤
• ለተቀጣሪዎች የሚቀርብ የደንብ ልብስ እና የሥራ መገልገያ ፡፡
• በማንኛውም ሁኔታ በዓይነት ጥቅሞች ላይ የሚከፈለው ጠቅላላ ግብር ተቀጣሪው በወሩ ከሚያገኘው የደመወዝ ገቢ አስር በመቶ (10%) መብለጥ የለበትም፡፡

Address

Adama

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Chilalo Authorized Accounting & Tax Services posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share