Kuriftu Dairy Farm/KDF

Kuriftu Dairy Farm/KDF Hybrid/Cross Bred calves from HF and Boran and Milk

22/12/2025
22/12/2023

ስለ PSEUDOCOWPOX Virus በሽታ ምን ያህል ያውቃሉ???
በጥሬ ትርጉሙ ''ለዘብተኛ'' ወይም "Pseudo" ማለት "False" የሚለውን ትርጉም የሚሰጥ ይህም ማለት False cowpox/የፈንጣጣ በሽታን የሚመስል በተለይ የላሞችን ጡት እና ተጓዳኝ የእንስሳትን እንዲሁም ሰውን ሊያጠቃ የሚችል በቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት በሽታ ማለት ነው።

Pseudocowpox በሀገራችንና በአብዛኛዎቹ የአለም ሀገራት የተለመደ የከብቶች በሽታ ነው።
በሽታው በብዛት የሚከሠተው በሚታለቡ ላሞች ላይ ሲሆን በተጨማሪም በበሽታው የተያዙ ላሞችን ጡት በሚጠቡ ጥጆች የአፍ ዙሪያ የሚከሠት ነው።
የpseudocowpox ቁስሎች በ "ቀለበት/ክብ ቅርፅ" ወይም "የፈረስ ጫማ" ቅርፅ ባላቸው ቅርፊቶች ተለይተው ይታወቃሉ።
ኢንፌክሽኑ/በሽታው የሚተላለፈው
[ ] ጥጆች የተለያዩ ላሞችን እንዲጠቡ በመፍቀድ በሽታውን ወደ ጤነኛዋ ላም የሚያሠራጭ ሲሆን ሌሎችም እንደ በአግባቡ ባልተፀዱ ማለቢያ ማሽን ወይም ንፁህ ባልሆነ እጅ እና ምናልባትም በዝንቦች አማካኝነት ሊሆን ይችላል።
መፍትሔ
[ ] በወተት አለባ ወቅት ለንፅህና አጠባበቅ ትኩረት መስጠት (የእጅና የማለቢያ ማሽኖችን ንፅህና መጠበቅ)
[ ] ከአለባ በኋላ የላሞችን ጡት ዲስኢንፌክት ማድረግ/ ፀረ ጀርሞችን በመጠቀም ጡትን መንከር የበሽታውን አደጋ ይቀንሳል.
ይህ ቫይረስ ከእንስሣት ወደ ሠውም የመተላለፍ እድሉ ከፍ ያለ በመሆኑ በሚያልቡ ሠዎች ላይ የእጅ ላይ እብጠትና ለሌሎች ውሥብሥብ ጉዳቶችን ያሥከትላል።
Kuriftu Dairy Farm, KDF

Keep Recording!!
10/12/2023

Keep Recording!!

Incalf Heifers for saleእርጉዝ ጊደሮች በሽያጭ ላይ፥ ከ125k ጀምሮ
07/12/2023

Incalf Heifers for sale
እርጉዝ ጊደሮች በሽያጭ ላይ፥ ከ125k ጀምሮ

19/11/2022

የተወደዳችሁ የኩሪፍቱ ዴይሪ ቤተሰቦች ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ አቅሙ ኖሯቸዉ እርባታ መጀመር ለሚፈልጉ ባለሐብቶች የቅርብ ክትትል በማድረግ ውጤታማ ስራዎችን እየሠራን እንገኛለን::
ይደውሉልን በቂ ልምድ ባላቸው ባለሞያዎች ድጋፍ እናደርጋለን::

KDF

 # #. በተሻሻሉ የከብቶች መመገቢያ ( ግርግም) እቃዎችና ከዝናብ እና ከፀሀይ ሊከላከል የሚችል የመኖ ማከማቻ ቦታን ብቻ በአግባቡ በመጠቀም ሊባክን የሚችለውንከ30 -50 %  የእንስሳት መ...
25/07/2022

# #. በተሻሻሉ የከብቶች መመገቢያ ( ግርግም) እቃዎችና ከዝናብ እና ከፀሀይ ሊከላከል የሚችል የመኖ ማከማቻ ቦታን ብቻ በአግባቡ በመጠቀም ሊባክን የሚችለውን
ከ30 -50 % የእንስሳት መኖ ብክነት ሊቀንሱ እንደሚችሉ ያውቃሉ??
በተጨማሪም: 👇👇
- የጡት በሽታን
- የእግር በሽታን እና
- መሠል ከምግብ መበስበስና ተያያዥ የእንስሳት በሽታዎች ይታደጎታል::
👉👉 እንዲሁም ከአላስፈላጊ ወጪም ይድናሉ::

ልፌ ወይም Datura Stramonium' እያልን የምንጠራው አረም በዚህ የክረምት ወቅት በብዙ የሀገራችን ክፍል ይበቅላል:: ይህ አረም ዘሩ፣ አበባው እና ቅጠሉ ከእንስሳት መኖ ጋር ተደባልቆ...
18/07/2022

ልፌ ወይም Datura Stramonium' እያልን የምንጠራው አረም በዚህ የክረምት ወቅት በብዙ የሀገራችን ክፍል ይበቅላል:: ይህ አረም ዘሩ፣ አበባው እና ቅጠሉ ከእንስሳት መኖ ጋር ተደባልቆ ለከብቶች መኖነት ከቀረበ ለእንስሳት ሞት ምክንያት ይሆናል::
👉 ስለዚህ:-
1. ሣር ለከብቶቻችን አጭደን የምንሠጥ ከሆነ ይህንን አረም ከሣሩ መለየት ይኖርብናል
2. በከብቶች የግጦሽ ቦታም ይህ አደገኛ አረም ካለ ነቅሎ ማስወገድ ያስፈልጋል (በእርግጥ እንስሳት በተፈጥሮ አደገኛ አረሞችን በሽታና በጣዕም የመለየት ተሰጥዖ ቢኖራቸውም ከተራቡ እንደዛ የማድረግ አቅማቸው ይቀንሣል)

Acidosis አሲዶሲስ/አሲዳማነትአሲዶሲስ የሩመን ፒኤች መጠን ከመደበኛ በታች ሲወድቅ የሚከሰት የሜታቦሊክ በሽታ ነው። ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው ላሞች በትክክል ወደ ከፍተኛ ስኳር/ስታርች መኖ...
28/05/2022

Acidosis አሲዶሲስ/አሲዳማነት
አሲዶሲስ የሩመን ፒኤች መጠን ከመደበኛ በታች ሲወድቅ የሚከሰት የሜታቦሊክ በሽታ ነው።
ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው ላሞች በትክክል ወደ ከፍተኛ ስኳር/ስታርች መኖ ላይ ካልተሸጋገሩ ወይም ከፍተኛ መጠን ያለው ከፍተኛ የስኳር/የስታርች መኖ በአመጋገብ ውስጥ ሲካተት ነው።

Kuriftu Dairy Farm/KDF

23/04/2022

ጥቂት ስለ ወተት ላሞች

Address

Wonji
Adama

Telephone

+251910248101

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kuriftu Dairy Farm/KDF posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Kuriftu Dairy Farm/KDF:

Share