AAAE የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት/Addis Ababa Abattoirs Enterprise

AAAE   የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት/Addis Ababa Abattoirs Enterprise short code 8868

10/09/2026
10/09/2026

እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ፣ አደረሰን!!

ዘመን ከፈጣሪ ለሰው የተሰጠ የመሥሪያ መጽሐፍ ነው። ይህ የመሥሪያ መጽሐፍ ለእያንዳንዱ ሰው የተሰጡ የተወሰኑ ገጾች አሉት። የመጨረሻው ገጽ ተጠናቅቆ የማጠቃለያው ሽፋን እስኪከደን ድረስ የፈለግነውን የመጻፍ መብት በእጃችን ነው። አንዳንዶች ዓለምን የቀየሩ ሐሳቦችንና ሥራዎችን፤ ሌሎች ታሪክን የቀየሩ ዕሳቤዎችንና ቴክኖሎጂዎችን ጽፈውበታል። በተቃራኒው ዓለምን ያወደሙ፤ ሕዝብ የከፋፈሉና የጨረሱ፤ ተፈጥሮን ያዛቡ፤ ክፋትንና ጭካኔን ያስተማሩ ሐሳቦችንና ተግባራትን የጻፉበትም ጥቂት አይደሉም። ስንፍናንና ድንዛዜን፣ ዕንቅልፍንና ሐኬትን የጻፉም አሉ።
ኢትዮጵያውያን በዚህ የዘመን መጽሐፍ ውስጥ ምን እየጻፍን ነበር? አሁንስ ምን እየጻፍን ነው? ወደፊትስ ምን ለመጻፍ እናስባለን? ከኋላችን ያሰናበትነው አሮጌ ዓመት እና ከፊታችን የምንቀበለው አዲስ ዓመት እነዚህን ጥያቄዎች እንድንመልስ ያስገድዱናል። ዓለምን ያስደነቁ የንግድ፣ የግብርና፣ የሥነ ሕንጻ፣ የዘመን አቆጣጠር፣ የሥነ ከዋክብት፣ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር፣ ሥነ ሥዕልና ሥነ ዜማ፣ ሃይማኖትና ፍልስፍና - በዘመን መጽሐፋችን ውስጥ የጻፍንባቸው የዘመን ገጾች አሉን። በተቃራኒው ረሃብና ቸነፈር፣ ጦርነትና እልቂት፣ መከፋፈልና መለያየት፣ ማነስና መድከም፣ የጻፍንባቸው የዘመን ገጾችም አሉን።
የትናንቱ ዘመን ጠባሳውንም ዐሻራውንም፣ ዕዳውን ምንዳውንም ሰጥቶን አልፏል። አሁን ወሳኙ ነገር በቀሩን ዘመናት ምን ቁም ነገር እንሰራለን? የሚለው ነው።
ኢትዮጵያውያን ዛሬ ለትውልድ የሚተርፍ አስደናቂ ታሪኮችን እየሰራን ነው። አረንጓዴ ኢኮኖሚን በአረንጓዴ ዐሻራ፤ ቱሪዝምን በገበታ ፕሮጀክቶች፤ የምግብ ሉዓላዊነትን በበጋ ስንዴና በሌማት ትሩፋት፤ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪን በኢትዮጵያ ታምርት እየገነባንና እያጸናን ነው። የኢነርጂ ዐቅማችንን በተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክትና ኑክሌር ቴክኖሎጂ ለማሳደግ፤ የአፈር ማዳበሪያ ግብአቶችን በሀገር ውስጥ ለመሸፈን፤ የአየር መንገድ አድማሳችንን በግዙፉ የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ፕሮጀክት ለማስፋት፣ ነገን አስበን ዛሬ እየተጋን ነው።
የሕዳሴ ግድብን ፍጻሜ፤ የመስኖ ግድቦችን ፍሬ፤ የሩዝ ምርትን ከፍታ፤ የፍራፍሬ ምርትን ተአምር፤ የወጪ ንግድን ጭማሬ፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያችንን ውጤት፤ በአፍሪካ የፈጠርነውን የኢነርጂ ትሥሥር፤ ዲጂታል 2030ን ስኬት፤ የኮሪደር ልማታችን የኢትዮጵያን ሀብትና ውበት መግለጥ፤ የዘመን መጽሐፋችን እየመዘገበ ነው። የወንዝ ዳርቻ ልማታችን አፈራችንንም፣ ከተማችንንም፣ ጤናችንንም፣ ውኃችንንም እየጠበቀ መሆኑን፤ መድኃኒት የማምረት ደረጃና ዐቅማችም እያደገ መሄዱን፤ የማዕድን ፍለጋችን፣ ምርታችንና ሽያጫችን የዘመናት ስብራትን እየጠገነ መምጣቱን፤ የባሕር በር አጀንዳችን ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት ማግኘቱን፤ የኢትዮጵያ የተጽዕኖ አድማስ መስፋቱን - የዚህ ዘመን የመጽሐፉ ገጾች እያሠፈሩ ናቸው።
እነሆ የዘመን መጽሐፋችንን የ2019 አዲስ ምእራፍ የምንጀምረው ሀገራዊ ምክራችንን በስኬት አጠናቅቀን ነው። ይሄንን ምክክር ለዘመናት ኢትዮጵያውያን ይጠይቁት ነበር። ችግራችንን በጦርነት ከመፍታት ይልቅ ለምን አንመካከርም ይሉ ነበር። በየብሔረሰቡ ያለውን የመነጋገርና የመመካከር ባህል ለምን ወደ ፖለቲካው አናመጣውም ይሉ ነበር። የዘመን መጽሐፍ ገጾችን ስናነባቸው ይሄን ጥያቄ ያቀረቡ ወገኖች ብዙ ዋጋ መክፈላቸውን ያስነብቡናል። እኛ ግን ሐሳቡን አመንንበት፤ አምነንም ተቀበልነው፤ ተቀብለንም ተገበርነው። ማመናችንና መተግበራችን ትክክል እንደሆነ የሚያሳዩ ውጤቶችንም ምክክሩ አስገኘልን።
የመጀመሪያው ውጤት “የጠላት ሟርት መክሸፉ” ነው። ኢትዮጵያውያን ሊመካከሩ አይችሉም፤ ቢመካከሩን ወደ ተቀራቢ ሐሳብ አይደርሱም የሚለውን ሟርት አክሽፈነዋል። ለመመካከር እንደምናቅድ፤ አቅደን እንደምንጀምር፤ ጀምረን እንደምንጨርስ በሀገራዊ ምክክር አስመስክረናል። ብዝሃ ሐሳቦቻችን በሀገር ጉዳይ የጋራ አቋም ከመያዝ እንደማያግዱን በተግባር አይተናል።
ሁለተኛው “ባህሉ” ነው። ከፀሐይ በታች ባሉ ጉዳዮች የመወያየት፣ የመነጋገርና የመግባባት ፖቲካዊ ባህልን ማዳበራችን ታላቅ ስኬት ነው። ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የልሂቃን ጉባኤ አድርጋ ይሆናል። ለሕዝቡ “እኛ እናውቅልሃለን” የሚሉ ልሂቃን፥ የሀገርን ችግሮች በመፍታት ስም የሥልጣን ክፍፍል የሚያደርጉባቸው ጉባኤዎች ተካሂደዋል። የዘመናት ጥያቄዎቻችን ግን መፍትሄ አላገኙም። ከልሂቃን ድርድር ይልቅ ሕዝባችን ራሱ መክሮ ራሱ መፍትሔ የሚያመለክትበት ሀገራዊ ምክክር ማድረግ ያስፈለገን በዚህ ምክንያት ነው። በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ በደማቅ ብዕር የሚጻፍ ታላቅ ጉባኤም ተናወነ።
በተካሄደው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሕዝባችንን ዋና ባለቤትና ዋና ተዋናይ በማድረግ ተጠናቅቋል። ሁሉንም አካባቢዎች፤ ሁሉንም ብሔረሰቦች፤ ሁሉንም እምነቶች፤ አብዛኞቹን የፖለቲካ አመለካከቶች፤ ሀገር ቤቱንና ዳያስፖራውን፤ ገበሬውን፣ አርብቶ አደሩንና ወዛደሩን፤ የሥራ ኃላፊዎችንና መደበኛ ዜጎችን፤ የተማሩትንና ያልተማሩትን፤ ወንዶችንና ሴቶችን፤ በዚህ መጠን በአንድ ጉባኤ በአንድ ቦታ ማገናኘት አዲስ ታሪካችን ነው። በዘመን መጽሐፍም በወርቅ ቀለም ተጽፏል።
ሦስተኛው “ውጤቱ” ነው። በአጀንዳዎች ላይ ተግባብተናል። እነዚህ ስምምነት የተደረሰባቸው ጉዳዮች አንድ በአንድ ወደ ተግባር የሚወሰዱ ናቸው። ባህል የሚሆኑ አሉ። ሥርዓት የሚሆኑ አሉ። አሠራር ተደርገው የሚዘረጉ አሉ። ዕሳቤ ሆነው የምንመራባቸው አሉ። ዐዋጅ ሆነው የሚወጡ አሉ። የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ሐሳቦች የሚሆኑ አሉ። የመዋቅር ማሻሻያ የሚሆኑ አሉ። የነገዎችን ትእምርቶች፣ ሐውልቶች፣ ስያሜዎችና ሀገራዊ ብራንዶች የሚወስኑ አሉ። የትናንት ጉዟችንን የሚያርሙ፣ የሚያስታርቁና በተሻለ መግባባት የሚተረጉሙ አሉ።
መንግሥት ሁሉንም ሐሳቦች በተገቢው መንገድ ይጠቀምባቸዋል። የኢትዮጵያን የነገ ጉዞ በሚያቃና መልኩ ግብአት ሆነው ያገለግላሉ። በየጊዜው የሚጠቀሱ፣ የሚወሱና የሚነሡ ዕሳቤዎች ይሆናሉ። የኢትዮጵያ የዘመን መጽሐፍ ከሀገራዊ ምክክሩ በፊትና በኋላ የተለየ ነገር እንደሚጽፍ አምናለሁ። የመግባባት፣ የመስማማትና የመሰናኘት ጉዟችን እየሠመረ መሄዱን ይመዘግባል። የተግባባንባቸው ሐሳቦች መሬት ወርደው፣ ሥር ይዘው፣ ፍሬ ማፍራታቸውን ይተርካል።
ሀገራዊ ምክክራችን ገደ መልካም መሆኑን በምክክሩ ብቻ ሳይሆን በውጤቱም እያሳየ ነው። በአዲስ ዓመት ዋዜማ በመቶ የሚቆጠሩ ታራሚዎችን መንግሥት በምሕረት እንዲፈቱ አድርጓል። ይሄንን ያደረገበት ዓላማ ሁለት ነው። የመጀመሪያው የሀገራዊ ምክክሩን ውጤት በፍቅር፣ በይቅርታና በሰላም ለመጀመር ነው። ወደ ሀገራዊ ምክክር የመጡ ልዩ ልዩ ወገኖች በአንድም በሌላም ስሕተት የታሠሩ ወገኖች በይቅርታ እና በህግ አግባብ እንዲፈቱ ጠይቀው ነበር። መንግሥት ይሄንን ተቀብሎ በሂደቱ የተስማሙትን ፈትቷል። የምክክሩም ዓላማ ኢትዮጵያውያን በጉዳዮች ላይ እንዲነጋገሩ የተግባቡባቸው የመፍትሔ ሐሳቦች እንዲያቀርቡ ነው። መንግሥትም ለምክክሩ ሐሳቦች ትግበራ ያለውን ቁርጠኝነት በዚህ የይቅርታ ሂደት ማሳየት ጀምሯል።
በዚህ የይቅርታ ሂደት የተፈቱ ወገኖች በሀገራዊ ምክክር ምክረ ሐሳቦች ላይ አዎንታዊ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ ይታመናል። ካለፈው መንገድ በመማር የወደፊቱን መንገድ የሰላምና የዴሞክራሲ መንገድ ያደርጉታል ተብሎ ተስፋ ተደርጓል። ማኅበረሰቡም እነዚህ ወገኖች በሀገር ሰላምና ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ ማገዝና መምከር አለበት።
መነጋገር፣ መከራከርና መፎካከር ሲቻል ግጭትና ጦርነት አዋጪ አይደለም። የብዕርና የሐሳብ ጊዜ እንጂ የጠመንጃ እና የጉልበት ጊዜ አልፏል። የኢትዮጵያ የዘመን መጽሐፍ ካሁን በኋላ የጠመንጃና የጉልበት ታሪክን አይመዘግብም። በታሪካችን ውስጥ በቂ ግጭቶችና ጦርነቶች መኖራቸውን የዘመን መጽሐፋችን አሳይቶናል። ቀጣዩ ምእራፍ አዳዲስ መንዶችን እንጂ አሮጌ አካሄዶችን አይመዘግብም።
ቀጣዩ ዓመት የጉባ ብሥራቶችን የበለጠ ተግባራዊ የምናደርግበት ዘመን ይሆናል። የፖለቲካ ምኅዳሩ ሰፍቶ የተለያዩ ዕሳቤዎችንና አካሄዶችን በብሔራዊ ጥቅም አስተሣሥረን የምንጓዝበት ዓመት ይሆናል። ሁለንተናዊ ሉዓላዊነታችን ይበልጥ የሚከበርበት፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ይበልጥ የሚጸናበት፣ በሁሉም ዘርፎች የጀመርነው ምርታማነት በዓይነትና በጥራት የሚጨምርበት፣ ሀገራችንም የቀጣናውና የአፍሪካ መሪነቷን ሥር መሠረት የምታስይዝበት፤ የኢትዮጵያ ብልጽግና ትውልድ ተሻጋሪ እንዲሆን ተደርጎ የሚገነባበት ዓመት ይሆናል።
ይህ እንዲሳካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ፣ የልሂቃን ሚና፣ የሃይማኖት አባቶች ጸሎት፣ የጸጥታ ተቋማት ጥንካሬና ቁርጠኝነት፣ የአምራች ኢንዱስትሪው ትጋትና ብርታት፣ የንግዱ ማኅበረሰብ ቅልጥፍናና ለሕዝብ አሳቢነት፣ የገበሬውና የአርሶ አደሩ አይበገሬነት፣ የወጣቶችና ሴቶች ያላሰለሰ ጥረት፣ የሚዲያዎች ሐቀኝነት፣ የዲጂታል ዘርፉ ዘመናዊነት፣ የሲቪል ሰረቫንቱ ንጽሕናና አገልግሎት፣ እጅግ ወሳኞች ናቸው።
አዲሱ ዓመት በኢትዮጵያ የዘመን መጽሐፍ ላይ አዲስ ታሪክ፣ አዲስ ሐሳብና አዲስ ሥልጣኔ የምንጽፍበት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ። ይህ እንደሚሆንም አምናለሁ። ፈጣሪም እንደሚረዳን እተማመናለሁ።
መልካም አዲስ ዓመት።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ጳጉሜን 5፣ 2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የእርድ ክፍሎቻችንና የስጋ ስርጭት መኪኖቻችን ለበዓሉ ድንበኞቻችንን ለማስተናገድ  ዝግጁ ተደርገዋል!!
10/09/2026

የእርድ ክፍሎቻችንና የስጋ ስርጭት መኪኖቻችን ለበዓሉ ድንበኞቻችንን ለማስተናገድ ዝግጁ ተደርገዋል!!

የአቃቂ ቅርንጫፍ ቄራ የአካባቢው የስጋ ፍላጎት ለማሟላት ንፅህናውን የጠበቀ የእርድ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተገለፀ!የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኮሚሽነር አህመድ መሃመድ...
10/09/2026

የአቃቂ ቅርንጫፍ ቄራ የአካባቢው የስጋ ፍላጎት ለማሟላት ንፅህናውን የጠበቀ የእርድ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተገለፀ!

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኮሚሽነር አህመድ መሃመድ ዛሬ በአቃቂ ቅርንጫፍ ቄራ በመገኘት ከሰራተኞች ጋር ውይይት አደረጉ።

በውይይቱ የቅርንጫፉ የስራ አፈፃፀም፣ የአገልግሎት ሁኔታና በስራ ሂደቱ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ተነስተዋል። ሰራተኞችም ያሏቸውን ሃሳቦችና ጥያቄዎች በማቅረብ በውይይቱ ተሳትፈዋል።

አቃቂ ቅርንጫፍ ቄራ የአካባቢውን የስጋ ፍላጎት በማሟላት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ሲሆን ቅርንጫፉ በሚሰጠው አገልግሎት ለአካባቢው ህብረተሰብ የስጋ አቅርቦት እንዲሻሻል የራሱን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል።

ኮሚሽነር አህመድ መሃመድ የቅርንጫፉን አገልግሎት ይበልጥ ለማሻሻል የሰራተኞች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልፀው፣ የተነሱ ሃሳቦችና ጥያቄዎች በተገቢው እንደሚታዩ አስገንዝበዋል።

ለተጨማሪ መረጃ 👇

ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/AAAEKERA

ቲውተር፡-https://twitter.com/AAAEkera

ቴሌግራም፡- https://t.me/AAAEKERA

ጳጉሜን 3 የፅናት ቀን የኢትዮጵያ ብቸኛ ወር የሆነችው የጳጉሜ ወር በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ሀገራዊ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። የፀናች ሀገር መሠረት የተቋማት ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን፣ የህ...
08/09/2026

ጳጉሜን 3 የፅናት ቀን

የኢትዮጵያ ብቸኛ ወር የሆነችው የጳጉሜ ወር በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ሀገራዊ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።

የፀናች ሀገር መሠረት የተቋማት ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን፣ የህዝብ አንድነት፣ኃላፊነትና ተሳትፎ ሲሆን ፅናት በፈተና ጊዜ አለመሸነፍ፣በችግር ውስጥ ተስፋን መጠበቅና የተጀመረን የለውጥ ጉዞ በጥራት እስከ መጨረሻ መፈፀምና ማስፈጸም ነው።

የዛሬ ፈተና የነገ ድል መሠረት በመሆኑ በጋራ በመተጋገዝ፣ በትዕግስትና በቁርጠኝነት ችግሮችን በመሻገር የተሻለ ነገን መገንባት እንችላለን።

07/09/2026
07/09/2026

ጳጉሜን 2፤2018 - ለአዲስ አመት ከ4 ሺህ በላይ የእርድ እንስሳትን እንደሚያቀርብ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አስታወቀ

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የዘንድሮውን የአዲስ አመት በዓል አስመልክቶ በዛሬው እለት ለመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች መግለጫ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ ለብስራት ሬድዮ እንደገለፁት ተቋሙ በመጪው የአዲስ ዓመት በዓል 4 ሺህ 500 የቁም የእንስሳትን እርድ ለማከናወን ዝግጅት አጠናቋል።

ከእነዚህም መካከል ከ3 ሺህ በላይ በሬዎች እና ከ1 ሺህ 500 በላይ በግና ፍየሎች እርድ እንደሚከናወን ተገልጿል።

የከተማዋ ነዋሪዎችም በግና ፍየልን በ300 ብር፣ እንዲሁም በሬዎችን ደግሞ በ2ሺ 100 ብር የቄራ የእርድ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ነው የተጠቀሰው።

ሕብረተሰቡ ጥራታቸውና ደህንነታቸው የተጠበቁ ሥጋዎችን እንዲያገኝ ወደ ቄራዎች ድርጅት መምጣት እንደሚገባው ጥሪ ቀርቧል።

በበዓሉ የአቅርቦት እጥረት እንዳይኖር እና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪን ለመከላከል በአዲስ አበባ በሚገኙ የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሥጋ ቤቶች 1 ኪሎ የበሬ ሥጋ 1 ሺህ 200 ብር ሆኖ ለሽያጭ እንደሚቀርብ ተቋሙ ገልጿል።

በቅድስት ደጀኔ



የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61577130725400
Website: https://www.bisrattv.com/
Telegram: https://t.me/Bisrat101fm
YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB
Twitter: https://twitter.com/Bisrat101

Address

From Mxico To Kera, አዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AAAE የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት/Addis Ababa Abattoirs Enterprise posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share