Tame TK

Tame TK Media and news page

ህዩዋ...ባላ ህዩዋ…. እንኳን አደረሳችሁ፡፡ ጳጉሜ 1 በታላቅ ድምቀት የሚከበረው "ህንግጫ" የልምላሜው መልክ፤ የኮንታ ብሔረሰብ አዲስ ዓመት፤የኮንታ ብሔረሰብ በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ...
06/08/2026

ህዩዋ...ባላ ህዩዋ…. እንኳን አደረሳችሁ፡፡

ጳጉሜ 1 በታላቅ ድምቀት የሚከበረው "ህንግጫ" የልምላሜው መልክ፤ የኮንታ ብሔረሰብ አዲስ ዓመት፤

የኮንታ ብሔረሰብ በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ባህላዊ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ቅርሶችና ዕሴቶች ባለቤት መሆኑ እሙን ነው፤ ከእነዚህ ውብ ዕሴቶች አንዱ የሆነው የብሔረሰቡ የዘመን መለወጫ/ህንግጫ/ በዓል አንዱ ነው።

የኮንታ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ /ህንግጫ/ በዓል በብሔረሰቡ ዘንድ በየዓመቱ በታላቅ ጉጉት ተጠብቆ የሚከበር ልዩ በዓል ሲሆን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሻገር ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ ነው፡፡ እሴቱ ሳይጎድልና ውበቱ ሳይደበዝዝ እዚህ የደረሰ የብሔረሰቡ የማንነት መገለጫም ነው፡፡

ህንግጫ በኮንታ ብሔረሰብ አጠራር ያማረ፣ ያጌጠ፣ የለመለመ ማለት ሲሆን አደይ አበቦች ፈክተው የሚታዩበት፣ የክረምቱ ወራት አልፎ የጠራ ሰማይ የሚታይበት፣ አርሶ አደሮች የክረምት አዝመራቸውን አገባደው ከአረምና ኩትኳቶ ስራ አርፈው ለመልካም ፍሬ ተስፋ የሚሰንቁበት ወቅት በመሆኑ በብሄረሰቡ ዘንድ በልዩ ትኩረትና በተስፋ የሚከበር ልዩ በዓል ነው።

የህንግጫ በዓል ሲከበር ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት መሸጋገሪያ እንደመሆኑ በዕለቱ ሁሉም ጠግበው፣ ጎዶሎው ሞልቶ፣ ያለው ለሌለው አካፍሎ የሚበላበት፣ ድሃ ከሀብታም እኩል የሚያከብሩት፣ መጥፎ ነገር ሁሉ ቀርቶ መልካም መልካሙ እንዲሸጋገር ፈጣሪውን የሚለምንበት የጥጋብና ሙሉ የመሆን አስተምህሮ የሚገለፅበት የተስፋ በዓል ነው።

እንደ ባህሉ ትውፊት ህንግጫ ከጳጉሜ የመጨረሻዋ ቀን እስከ መስከረም 30 ድረስ ደምቆ ይከበራል። ከቤት እስከ ደጃፍ አካባቢ ይፀዳል፤ ከአሮጌው ዓመት የሚሻገር እድፍና ጉድፍ እንዳይኖር ይጠረጋል፤ ምድር ትዋባለች፡፡

ህንግጫ ከ12 ዓይነት በላይ የሆነው የኮንታ ባህላዊ ምግብ ተዘጋጅቶ የሚቀርብበት የባህል አውድም ነው፡፡ የዘመን መለወጫ በዓል ማብሰሪያ እሳት የሚወጣው ጳጉሜ የመጨረሻዋ ቀን ነው፡፡

በህንግጫ ወቅት ‹‹ሙጬ ›› ማለት ከጳጉሜ 1 እስከ ጳጉሜ 5/6 ድረስ ያሉ ቀናትን የሚያመላክት ሲሆን በእነዚህ ቀናት ዉስጥ እህል በተለይም ጤፍ ቢዘራ የማይበቅልና ቢበቅልም እንኳን ከግንዱ ተቆርጦ የሚወድቅና እንዲሁም ሳያድግ ቀጭጮ ስለሚቀር ወቅቱ ‹‹ ሙጬ ›› ተብሏል፡፡

በመሆኑም ‹‹ ሕንግጫ ›› የሚለዉ የብሔሩ የዘመን መለወጫ በዓል እንደሆነ የዕድሜ ባለፀጋዎችና የተለያዩ የታሪክ መጽሐፍቶች ይመሰክራሉ፡፡

የኮንታ ህዝብ የዘመን መለወጫ በዓል ማክበር የጀመረዉ በኦሞ፣ በጎጀብ እና በዝግና ተፋሰስ መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በዓሉን ሲያከብሩ እንደ ነበረ ይነገራል፡፡

ሆኖም በዓሉ መቼና እንዴት ተጀምሮ እያደገ እንደመጣ ትክክለኛውን ጊዜ የሚጠቁም የጽሑፍ መረጃ ባይኖርም ለበዓሉ ታሪካዊ አመጣጥ የራሱ አመልካች መረጃዎች እንዳሉ ቀደምት አባቶች በአፈ-ታሪክ ያረጋግጣሉ፡፡

ይህም በኮንታ መንግሥት ተመስርቶ ግዛቱን ተቆጣጥሮ መኖር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ማለትም የመጀመሪያው የአራ የዘር ግንድ ቀዳሚ ንጉስ “ከካቲ ኤማዶ” ዘመነ መንግስት በ12ኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ይበልጥ በተጠናከረ ሁኔታ በቤተሰብ ደረጃም ሆነ ከጎረቤት ጋር በጋራ በመሆን በዓሉን እያከበሩ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ መሆኑ በታሪክ ይነገራል፡፡

‹‹ህንግጫ›› ማለት እንደ ብሔሩ አባቶችና የታሪክ ምሁራን አገላለጽ የሁለት ቃላት የ‹‹ሂን›› እና የ‹‹ጊጫ›› ዉህድ ሲሆን ‹‹ሂን›› ማለት ወደዚያ አስፋ/ፊ ሲሆን ‹‹ጊጫ›› ማለት አሳምር፣ ጥረግ፣ አጽዳ፣ ፋቅ (Giid’ara) የሚል ትርጉም ይሰጣል፡፡

በመሆኑም ከዕለቱ በዓል ጋር የሚያ

የኮንታ ብሄር ዘመን መለወጫ "ህንግጫ" በዓልን ማክበር የብሄሩን መልካም እሴት የማስተዋወቅና ለመጪው ትውልድ የማስተላለፍ ታላቅ ኃላፊነት ነው፤ አቶ ታከለ ተስፉየኮንታ ዞን ባህል ቱሪዝም እና...
24/07/2026

የኮንታ ብሄር ዘመን መለወጫ "ህንግጫ" በዓልን ማክበር የብሄሩን መልካም እሴት የማስተዋወቅና ለመጪው ትውልድ የማስተላለፍ ታላቅ ኃላፊነት ነው፤ አቶ ታከለ ተስፉ

የኮንታ ዞን ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ የ2019 ዓ.ም የኮንታ ብሄር ዘመን መለወጫ "ህንግጫ" በዓል አከባበር ዕቅድ ዙሪያ ከዞን፣ ከወረዳና ከተማ አስተዳደር አመራር አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በዓሉ ከነሀሴ 25 - 30/2018 ዓ.ም ድረስ በየመዋቅሩ እንደሚከበር የተገለፀ ሲሆን በዞን ደረጃም ለ3 ተከታታይ ቀናት በሩጫ፣ በፋናል ውይይት እና በሌሎች ኩነቶች ተከብሮ ማጠቃለያው ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም በአደባባይ በደመቀ ሁኔታ እንደሚከበር ታውቋል።

የዘንድሮውን የኮንታ ብሄር ዘመን መለወጫ "ህንግጫ" ከወትሮ በተሻለ ድምቀት ለማክበር ከወዲሁ ሁሉም መዘጋጀት እንደሚገባ ተጠይቋል።

በመድረኩ የተገኙት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ የህዝብ የማንነት መገለጫ የሆነውን የኮንታ ብሄር ዘመን መለወጫ "ህንግጫ" በዓልን ስናከብር ሰፊውን ህዝብ በማሳተፍ በደማቅ ሁኔታ ማክበር እንደሚገባ አስረድተዋል።

ለዚህም በዓሉ ከቀደሙት ጊዜያት በተሻለ እንዲከበር በየደረጃው አስፈላጊ ዝግጅቶች ሊደረጉ እንደሚገባ በማስገንዘብ ይህም የብሄሩን መልካም እሴት የማስተዋወቅና ለመጪው ትውልድ የማስተላለፍ ታላቅ ኃላፊነት ስለመሆኑ አስረድተዋል።

የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ ባለፈው ዓመት የነበሩ ጥንካሬዎችን በማጎልበትና የተስተዋሉ ክፍተቶችን በማረም የዘንድሮውን በዓል ከፍ አድርጎ ማክበር እንደሚያስፈልግ ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል።

ከከተማ ጽዳትና ውበት ማስጠበቅ ጀምሮ የህዝብ ተሳትፎ በማሳደግ በየደረጃው የተዋቀሩ ኮሚቴዎችና አመራሮች ከወዲሁ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸውም አቶ ታከለ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የዞኑ ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አበበ ደምሴ የኮንታ ብሄር ዘመን መለወጫ "ህንግጫ" በዓል በብሄሩ ተወላጆች ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠውና ከጥንት ጀምሮ እየተከበረ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የአዲስ ዓመት መለወጫ በዓል ስለመሆኑ አብራርተዋል።

የበዓሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ያነሱት አቶ አበበ የዘንድሮውን በዓል ለማክበር የሚያስችሉ ዝግጅቶችን የሚያስተባብሩና በየደረጃው የተዋቀሩ የተለያዩ ኮሚቴዎች ከወዲሁ ሚናቸውን በትኩረት ሊወጡ እንደሚገባ አስረድተዋል።

በዓሉ በየደረጃው እየተከበረ ዞናዊ ማጠቃለያ በአመያ ከተማ እንደሚደረግ ያመላከቱት ኃላፊው ከተሞችን ለእንግዶች ምቹና ሳቢ ማድረግ እንደሚገባም አንስተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች የብሄሩ የማንነት መገለጫና ከማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ የሚመደበው ይህ በዓል የብሄሩን ባህል፣ ታሪክ፣ እሴት እና ማንነት ለዓለም የሚያስተዋውቅ መሆኑን በመገንዘብ በተገቢው ማልማትና ማስተዋወቅ እንደሚገባ ገልፀዋል።

የበዓሉ አከባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ያወሱት ተሳታፊዎች በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶችና ሚዲያዎች በሰፊው ማስተዋወቅ ያሻልም ብለዋል።

ለበዓሉ ስኬት የተደራጁ የኮሚቴ አባላት እና የሚመለከታቸው አካላት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በውጤታማነት መፈፀም እንደሚገባቸው የተገለፀ ሲሆን መላው የዞኑ ነዋሪዎችና ተወላጆች እንዲሁም ሌሎች ደጋፊዎችና በጎ ፍቃደኞች ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል።

የ"ህንግጫ"ን በዓል በድምቀት ማክበር የሚያስችል መነሻ ዕቅድ በዞኑ ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ በአቶ አበበ ደምሴ በኩል ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

ዘገባው የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

  !! #የድልቀመር |1: ስያበሳጩሁ/ ሲፈትኑህ ዝም በል።*አንገትህን የሚያስደፋ ክርክር ውስጥ አትግባ። እውነተኛ ሃይልበቃላት ሳይሆን በድርጊት ይታያል። ንዴትህን ዋጥ።2: ሲሰድቡህ ዝም በ...
24/07/2026

!!

#የድልቀመር |1: ስያበሳጩሁ/ ሲፈትኑህ ዝም በል።*
አንገትህን የሚያስደፋ ክርክር ውስጥ አትግባ። እውነተኛ ሃይል
በቃላት ሳይሆን በድርጊት ይታያል። ንዴትህን ዋጥ።

2: ሲሰድቡህ ዝም በል።*
አንበሳ ከውሻ ጋር አይጫወትም፡፡ ዋጋህን የማያውቅ ሰው ላይ
ጊዜህን አታባክን፡ ዝምታህ መልስህ ነው፡፡

3: ሲያወዳድሩህ ዝም በል።*
ሩጫህ ከራስህ ጋር ነው፡፡ የሌላውን ሰዓት ተመልክተህ የራስህን
አታበላሽ። ንጉስ ነህ። የራስህን ዙፋን ስራ።

*አስታውስ፦ የወንድ ዝምታ ፍርሃት አይደለም፡፡ ቁጥጥር ነው፡፡
ጥበብ የተሞላበት...

በድጋሚ የተሰጠ መግለጫየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስ...
01/06/2026

በድጋሚ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሂደት ላይ እንደነበር ይታወቃል። ቦርዱ በሥምሪት ላይ ያለው የክትትል ቡድኑ ያቀረበለትን ሪፖርት ተመልክቶ የሚከተለውን ወሥኗል።

በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 49(4) መሠረት ቦርዱ የምርጫው ነፃና ፍትሐዊነት ይበልጥ ያሰፍናል ብሎ ካመነ የድምፅ መስጫ ሰዓቱን ሊያራዝም እንደሚችል በግልጽ ይደነግጋል። በመሆኑም የድምፅ መስጫ ሂደት ባልተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ ዕኩለ ለሊት 6:00 ሰዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን ቦርዱ ያሳውቃል።

ማሳሰቢያ: የተመዘገቡ መራጮች መርጠው የተጠናቀቁባቸው ጣቢያዎች ላይ አስፈጻሚዎች የድምፅ ቆጠራ ሂደቱን እንዲያከናውኑ ቦርዱ ያስታውሳል።
#ኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ #

ለኮንታ ዞንና ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን የተላለፈ ጥሪ!በቅድሚያ እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!በሁሉ ነገር የረዳን እግዚአብሔር  ስሙ ለዘላለም ይክበር ይመስገን!ከዚህ በፊት በኢ/ኦ...
28/05/2026

ለኮንታ ዞንና ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን የተላለፈ ጥሪ!

በቅድሚያ እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!

በሁሉ ነገር የረዳን እግዚአብሔር ስሙ ለዘላለም ይክበር ይመስገን!

ከዚህ በፊት በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን በዞን ቤተ ክህነት መዋቅር ስትተዳደር የቆየችው ኮንታ፤ አሁን ላይ ታሪካዊ ለውጥ ተደርጎ ራሷን ችላ የ“ኮንታ ሀገረ ስብከት” ሆና በይፋ መፅደቋ ታላቅ የደስታና የክብር ዜና ሆኗል።

ይህ ታሪካዊ እድል ለመላው የኮንታ ሕዝብ፣ ለምዕመናን እና ለቤተ ክርስቲያኒቱ ታላቅ መንፈሳዊ ምዕራፍ መከፈቱን ያመላክታል።

ከዚህም ጋር በተያያዘ የመንበረ ጵጵስና ምርቃትና የሀገረ ስብከቱ ይፋዊ ማቋቋም ሥነ-ሥርዓት ከሐምሌ 11–12/2018 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ይከናወናል።
በዚህም ታላቅ መርሃ-ግብር ከተለያዩ አካባቢዎች ታላላቅ እንግዶች እና ከሦስት በላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ይካሄዳል።

በመሆኑም ለቀሪ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች:-የዙሪያና የመሀል አጥር ግንባታ፣ መፀዳጃ ቤቶች ግንባታ፣ የብፁዓን አበው መኝታ ክፍል ቁሳቁሶች፣ የሊቀ ጳጳሱ ቢሮ ቁሳቁስ፣ የመሀል አጥር ሥራ፣ እንግዶችን ለመቀበል የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለማሟላት ድጋፍ በማስፈለጉ መላው የኮንታ ሕዝብ፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ያላችሁ ወገኖች በፀሎት፣ በሐሳብ እና በገንዘብ ድጋፍ እንድትተባበሩ በልዑል እግዚአብሔር ስም በክብር ተጋብዛችኋል።

ለድጋፍ
🏦 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)
የሂሳብ ቁጥር: 1000652033068 ይጠቀሙ፣

“ቤቴን ሥሩ፤ በእርሱም ደስ ይለኛል፤ እከብርማለሁ” እንዲል የጌታ ቃሉ፤

በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ሥራ የሚትሳተፉ ሁሉ የእግዚአብሔር በረከት አይለያችሁ።

ጽ/ቤት

ዘገባዉ:- የኮንታ ሀገረ ስብከት የመገናኛ ብዙኃን ነዉ።

 #ኮርማ (Kormma)፦ በኮንታ ምድር የሚፈስ የባህልና የጥበብ ጣዕም !ኮርማ ዝግጅቱ የሚጀምረው በአንጮቴ ነው። አንጮቴው በስልት ተቀቅሎ ከበሰለ በኋላ ቃንጫ የሌለው ተመርጦ በንጹህ ቢላዋ ...
04/04/2026

#ኮርማ (Kormma)፦ በኮንታ ምድር የሚፈስ የባህልና የጥበብ ጣዕም !

ኮርማ ዝግጅቱ የሚጀምረው በአንጮቴ ነው። አንጮቴው በስልት ተቀቅሎ ከበሰለ በኋላ ቃንጫ የሌለው ተመርጦ በንጹህ ቢላዋ በጥንቃቄ የመፋቅ ሂደት ይከናወናል። ይህ ሂደት ምግቡ ለቀጣዩ ደረጃ ንጹህና ዝግጁ እንዲሆን መሠረት ይጥላል።

የኮርማን ልዩ የሚያደርገው ግን የአደቃቅ ስልቱ ነው። አንጮቴው ምንም አይነት ያልደቀቀ ክፍል እንዳይኖረው ተደርጎ በማጭድና “በቀጭኑ በተገመደ ቃንጫ ዩደቲዲ/Yuudetedi በደንብ እንዲደቅ ይደረጋል። ይህ ጥንታዊ ዘዴ አንጮቴው ቅቤን በብዛት የመምጠጥ አቅም እንዲኖረው በማድረግ ምግቡ ልዩ ጣዕምና ልስላሴ እንዲላበስ ያደርገዋል።

የኮርማ የመጨረሻውና የጣዕሙ ምስጢር የሚገለጠው በቅመማ ቅመም አዘገጃጀቱ ላይ ነው። ይህ በቅቤ የራሰ ምግብ በቆጮ ቂጣ ታጅቦ በቡድን ይበላል። ይህም ኮርማ ከግል ምግብነት ባለፈ የህብረት፣ የፍቅርና የአንድነት ምልክት መሆኑን ያሳያል።

ኮርማ በተለይ በአዝመራ ወቅት ወይም #“ዱርዱሩዋ” (Durduruwa) ተብሎ በሚጠራው የደስታ ጊዜ በስፋት ይዘጋጃል። ይህ ወቅት የምድር በረከት ለቤት የሚተርፍበት በመሆኑ ኮርማ የብዛትና የማካፈል ባህል መገለጫ ይሆናል።

ይህንን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ በኮንታ የሚገኘው ባህላዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ ይዘት ያለቸውን እሴቶች/መረጃዎች ያግኙ በተጨማሪ እርሰዎም አከባቢውን የማስተዋወቅ ኃላፊነት ለመወጣት #ሸር ያድርጉ !!
#

04/04/2026
 – የጀግንነት ቀለም የለበሰ ታሪክ !በኮንታ ዞን ውስጥ ከታሪክ ጥልቀት የተነሳ የሚያምር የባህል ተምሳሌት አለ ( #ዳባላ ዳንጩዋ) ። ይህ የቁሣዊ የባህል ቅርስ ብቻ አይደለም፤ የጀግንነት ...
30/03/2026

– የጀግንነት ቀለም የለበሰ ታሪክ !

በኮንታ ዞን ውስጥ ከታሪክ ጥልቀት የተነሳ የሚያምር የባህል ተምሳሌት አለ ( #ዳባላ ዳንጩዋ) ። ይህ የቁሣዊ የባህል ቅርስ ብቻ አይደለም፤ የጀግንነት መለያ፣ የሉዐላዊነት ምልክት እና የትውልድ ክብር የተጠቀሰበት የታሪክ መግለጫ ነው።


በቀድሞ ዘመን የኮንታ ብሔረሰብ በራሱ ንጉሳዊ ሥርዓት ሲኖር የመከላከያ መለያ ነበር። ከውጭ ጥቃት ሲመጣ ወታደሮች መሪ ይህንን ልብስ ህዝቡ መርቆ በአደራ የሚሰጡትን በመልበስ ዳር ድንበራቸውን ይጠብቁ ነበር። ልብሱ እስከ 40 ክንድ የሚደርስ ይረዝም ነበረ፤
በውጊያ ላይ የተወደቀ ጀግና የጦር መሪ ካለ ሰውነቱ በዚሁ ልብስ ከእግር እስከ ራስ ይጠቀለል ነበር፤ ይህም ሞቱን እንደ ክብር እንጂ እንደ ኪሳራ አይቆጠርም የሚለውን የባህል እምነት ያሳያል። በሌላ በኩል ጦርነትን አሸንፎ ስመለሰ ይህንን ልብስ ከፍ አድርጎ እያውለበለቡ ወደ ህዝብ መቀላቀሉ የተለመደ እንደሆነ ይነገራል ።

#ከማህበራዊ እና አንፃር
ይህ ልብስ የጦርነት መለያ ብቻ አልነበረም፤ የህብረተሰቡ አንድነትን የሚያጠናክር መርሃ ግብር ነበር። ህዝቡ ከንጉሡ ጋር ተመካክሮ የጋራ ውሳኔ በማድረግ ለመከላከል ይዘምታል፤ ይህም የተባበሩ ማንነትና እምነት ምልክት ነው።

#የእደ-ጥበብ ክብርና #የዘመናዊ አገልግሎት
እስከ ዛሬ ድረስ በእደ-ጥበብ ሙያተኞች ተጠብቆ የሚሰራው መነሻ ያደረገ የብሔረሰቡ የኢንዱስትሪ እድገትን የሚያመለክት ታላቅ ምልክት ነው። ዛሬም ባህላዊ እሴቱን በመጠበቅ ከዘመናዊ አልባሳት ጋር ተዋህዶ ለኢኮኖሚ እና ለቱሪዝም ዋጋ ያለው ነው።

ዳባላ ዳንጩዋ የአባቶች የመከላከል መንፈስን፣ የአካባቢ ፍቅርን እና የማንነት ክብርን በቀለም የሚነግር መልዕክት ነው። ዛሬ በሙዚየም ውስጥ በክብር ተቀምጦ ቢታይም፤ ከልብ ውስጥ ያለው ክብሩ አይጠፋም።
#

የተወዳጁ የክልላችን የቀድሞ አመራር አቶ ተዘራ ወልደማርያም 2ተኛ ሙትዓመት፤የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እንደ ክልል እጅግ ተወዳጅ እና ጠንካራ አመራር አቶ ተዘራ ወልደማርያምን ያ...
29/03/2026

የተወዳጁ የክልላችን የቀድሞ አመራር አቶ ተዘራ ወልደማርያም 2ተኛ ሙትዓመት፤

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እንደ ክልል እጅግ ተወዳጅ እና ጠንካራ አመራር አቶ ተዘራ ወልደማርያምን ያጣው ልክ የዛሬ 2 ዓመት ነበር። እኚህ የተወደዱ አመራር መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ነበር በሥራ ባሉበት በድንገት በገጠማቸው የጤና እክል በድንገት ያረፉት።

በ1973 ዓ.ም በኤላ አውራጃ አመያ ከተማ ከሃምሳ አለቃ ወ/ማርያም ሱራ እና ከወ/ሮ በላይነሽ ጮቤ የተወለዱት አቶ ተዘራ፣ ከታችኛው የመምህርነት እርከን ተነስተው እስከ ከፍተኛ የክልል አመራርነት የደረሱበት የሕይወት ጉዟቸው ለብዙዎች ተምሳሌት የሚሆን የፅናት መንገድ ነበር።

ከአርባ ምንጭ መምህራን ኮሌጅ ተመርቀው በኦሽካ ዴንቻ፣ በኮንታ ኮይሻ፣ በጨበራ ሻሾ እና በሌሎችም ገጠራማ አካባቢዎች በመምህርነትና በርዕሰ መምህርነት ሲያገለግሉ የነበራቸው ቅንነትና ታማኝነት፣ በኋላ ላይ ተሸክመውት ለነበረው ትልቅ የፖለቲካ ኃላፊነት መሰረት የጣለ ነበር።

በትምህርት ላይ የነበራቸው ልዩ ፍላጎትም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አስተዳደር እንዲያገኙ አስችሏቸዋል።

አቶ ተዘራ የኮንታ ዞን (የቀድሞው ልዩ ወረዳ) ዋና አስተዳዳሪ እና የደቡብ ክልል የፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ፣ በህዝቡ ዘንድ የነበራቸው ተቀባይነትና ተግባቢነታቸው ልዩ መለያቸው ነበር።

በተለይም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሲመሰረት የነበራቸው ሚናና በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው፣ ለክልሉ ሰላማዊ ምስረታና ዕድገት የከፈሉት መስዋዕትነት ሁሌም የሚታወስና በክልሉ ታሪክ በደማቅ የተጻፈ ሁልጊዜ የሚዘከር ታሪካቸው ነው።

በሥራ ገበታቸው ላይ እያሉ በገጠማቸው ድንገተኛ የጤና እክል ከሁለት ዓመት በፊት ቢያልፉም፣ እንደ መሪ ጠንካራ፣ እንደ ወንድም መካሪ፣ እንደ ጓደኛ ደግሞ ተጫዋችና ተግባቢ የነበሩት አቶ ተዘራ፣ በሦስት ልጆቻቸውና ባስቆጠሩት መልካም ስም ዛሬም በመካከላችን አሉ።

ለህዝብ ጥቅምና ክቡር የኖሩ፤ በፍቅር ከራስ ህዝብን እና የህዝብን ሥም ያከበሩ ሁሉ ለዘለአለሙ እየተዘከሩ ይኖራሉ። አቶ ተዘራም ሁሌም የሚዘከሩ የክልሉ ህዝቦች የሁል ጊዜ ጀግና ናቸው።

ነብስዎ በሠላም ትረፍ!
HD #

 #ኡልቱዋ፦ የኮንታ ብሔረሰብ የታሪክ መለከትና የማህበራዊ እሴት ተምሳሌትበኮንታ ዞን ለምለም ምድር ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረውና የብሔረሰቡን ጥንታዊ ሥልጣኔ በድምፅ የሚመሰክረው ...
29/03/2026

#ኡልቱዋ፦ የኮንታ ብሔረሰብ የታሪክ መለከትና የማህበራዊ እሴት ተምሳሌት

በኮንታ ዞን ለምለም ምድር ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረውና የብሔረሰቡን ጥንታዊ ሥልጣኔ በድምፅ የሚመሰክረው "ኡልቱዋ" ከመሣሪያነት ባለፈ የሕዝቡ የልብ ትርታና የታሪክ ማህደር ነው። ይህ ቁሳዊ የባህል ቅርስ ከቀንድና በኮንቲኛ ኢሮሼ ከሚባለው ውስጡ ክፍት ከሆነው እንጨት ተበጅቶ የኮንታን ሕዝብ ትናንት፣ ዛሬና ነገ በአንድነት ያስተሳስራል።



ኡልቱዋ በኮንታ ጠቢባን እጅ በጥንቃቄ የሚሠራ የጥበብ ውጤት ነው። ከተመረጠ ትልቅ የከብት ቀንድና በኮንቲኛ ኢሮሼ ከሚባል እንጨት ዝሪያ የሚበጀው ይህ መሣሪያ ቀንዱ ተጠርቦና ታሽቶ እንደአስፈላጊነቱ በቆዳ ተለብጠው እንዲያምር ከተደረገ በኋላ በሹል ጫፉ በኩል ተበስቶ ከ50 ሳንቲ ሜትር እስከ አንድ ሜትር በሚረዝም ኢሮሼ እንጨት እንዲጣበቅ ተደርጎ ይዘጋጃል። ይህም የብሔረሰቡን ተፈጥሮን የመጠቀም ጥበብና ውበትን የማጣመር ምጡቅነት በግልጽ ያሳያል።

በጥንት ዘመን የኮንታ #ካቲዎች (ነገሥታት) እና የሥር ሹማምንት የኡልቱዋን ድምፅ እንደ ዋነኛ የመገናኛ ዘዴ ይጠቀሙበት ነበር። ሕዝቡን ለማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ውይይቶች ለመጥራት፤ የጦርነት ቅስቀሳን ለማብሰር፤ ለአደን እወጃና ለግብር አሰባሰብ ጥሪ ለማድረግ ኡልቱዋ ቀዳሚው የመንግሥታዊ ተግባቦት መሣሪያ ሆኖ አገልግሏል።

በተጨማሪም በሐዘን ወቅት የታዋቂ ሰዎችን ሥርዓተ-ቀብር በማጀብ፤ በደስታ ጊዜ ደግሞ የብሔረሰቡን ባህላዊ ሙዚቃ ከሌሎች የምትና የትንፋሽ መሣሪያዎች ጋር በመቀናጀት ልዩ ድምቀት ይሰጣል።

!

ዛሬም ድረስ ኡልቱዋ ሕዝቡን ለልማት ሥራዎች በማነቃቃት ረገድ የማይተካ ሚና አለው። በሥራ ሜዳዎች ላይ በመገኘት በሚሰጠው የሞራል ድምፅ ወጣቱንና አምራቹን ኃይል ለሥራ በመቀስቀስ የልማት አጋዥነቱን እያስመሰከረ ይገኛል።

ባጠቃላይ ኡልቱዋ በኮንታ ብሔረሰብ የታሪክን አሻራ ከባህላዊ እሴት ጋር አቆራኝቶ የያዘና የሕዝቡን ማንነት በአንድ ዜማ የሚያስተጋባ ሕያው ቅርስ ነው።
#

Address

Addis Ababa

Telephone

+251967095778

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tame TK posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tame TK:

Shortcuts

Share