Ethiopia le zelalem tinur

Ethiopia le zelalem tinur Ehiopia

24/01/2024
24/01/2024

አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ!
የኦሮሚያ ቤተክህነት ተባለ።
እምቢ አላችሁ።
የኦሮሚያ ሲኖዶስ ተብሎም እርቅ መጣ።
እምቢ አላችሁ።

ቢሆን ኖሮ እርቁ የተሾሙ ጳጳሳት እንዲጸድቁ እና አዳዲስ ጳጳሳት እንዲሾሙ ይደነግጋል። አዳዲስ የመንፈሳዊ ከፍተኛ ትምህርት እንዲቋቋሙ ይደነግጋል። የቤተክርስቲያን አሰራርና መዋቅር ለዘመኑ በሚመጥን መልኩ እንደሚሻሻል ይደነግጋል። ስብከተ ወንጌል በኦሮሚያም ሆነ በደቡብ በሰፊው እንዲስፋፋ ቤተክርስቲያን ተገቢውን እርምጃ እንደምትወስድ ይደነግጋል።

ይህ ሁሉ ድንጋጌ አልተፈጸመም። አባቶች በግፍ እና አለአግባብ አስቀድሞ ከተመደቡበት ሀገረ ስብከት ተፈናቀሉ። በማረፊያ በአታቸውም መቀጠል አልቻሉም። በቢሾፍቱ ከተከራዩበት ቤትም ተወስደው ታሰሩ። ተሰደዱ። የኦሮሚያ ሲኖዶስ ደጋፊዎች ታሰሩ። ከስራቸውም ተባረሩ። ብዙዎች የኦሮሚያ ሲኖዶስ ደጋፊዎች አንገታቸውን ደፉ።

ይህ ሁሉ መሆኑ አለአግባብ እንደሆነ ብንወተውትም በመንደር የሚያስቡ እና ሲኖዶሱን እንዳሻቸው የሚያሽከረክሩ ጥቂት ፊት አውራሪዎች ሊሰሙን አልቻሉም። በሚዲያም ከሚዲያ በመለስም ብዙ አልን። ሰሚ ግን አላገኘንም። ከእነዚህ ብርቱ ጥረቶች በኋላ ዝም አልን።

የኦሮሚያ ሲኖዶስ ዝም ሲል ያበቃለት የመሰላችሁ ተሳስታችኋል። ዝምታው የተዳፈነ እሳት ነበር። እንዲሁም ባስፈለገ ጊዜ የሚያነድ፣ የሚያበስል እና የሚያቃና መንፈስ። የሚመራውም ሦስቱን ሕያዋን በሚያደርጋቸው እሳት መንፈስ ቅዱስ ነው።

እናም ስሙ!
አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ!
መንበረ ጴጥሮስ ተቋቁሞላችኋል!!!
እንኳን ደስ ያላችሁ! እንኳን ደስ ያለን!!!

26/11/2023

እየመጡ ነዉ🤪

09/11/2023

#ለጥንቃቄ

በአዲስ አበባ በከተማ " ጉንፋን መሰል " ህመም መከሰቱና ነዋሪዎች ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው የጤና ባለሙያዎች እየመከሩ ናቸው።

በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሃኪም ዶ/ር ስንሻው አባይ ፤ በአዲስ አበባ በከተማ ለተከሰተው " ጉንፋን መሰል ህመም " ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ጉንፋን መሰል ህመሙ፦
- ከአፍንጫ ብዙ ፈሳሽ መውጣት፣
- ሳል፣
- ራስ ምታት፣
- ጉሮሮን የማቃጠል ስሜት፣
- ድካም፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ የመሳሰሉት እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

ዶክተሩ ፤ ሰሞኑን የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም የላይኛውን የመተንፈሻ አካል ክፍል የሚያጠቃ ነው ብለዋል፡፡

ህመሙን ለመከላከል እና ለማስታገስ ፦
* ፈሳሽ መውሰድ፣
* ከቅዝቃዜ ራስን ማራቅ (ሙቀቱን የተመጣጠነ ማድረግ)፣
* መኖሪያ ቤትን አየር እንዲያገኝ ማድረግ፣
* በቂ የሆነ እረፍት መውሰድ እና የመሳሰሉትን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን መክረዋል።

በሌላ በኩል ፤ በቤት ውስጥ የእፅዋት ዝርያዎችን በፍም (እሳት) ላይ በማጨስ ጭሱን መታጠን ሳንባ እንዲያብጥ ወይም እንዲቆጣ በማድረግ ለጉዳት እንደሚዳርግ ተናግረዋል፡፡

ማህበረሰቡ ፦
° በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ውስጥ መስኮቶችን በመክፈት፣
° በንግድ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ሰው በተሰበሰበበት ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በማድረግ፣
° የእጅን ንፅህና በአግባቡ በመጠበቅ እንዲሁም አስም ያለባቸው ምልክቶቹ እንደታዩባቸው ወደ ህክምና ተቋማት ሄደው መታየት እንዳለባቸው መክረዋል።

የጤና ሚኒስቴር ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በመሆን በ2 ሺህ ያህል ናሙናዎች ላይ ምርመራ አድርጎ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ በሽታ መከሰቱን ከሁለት ሳምንት በፊት ይፋ አድርጓል።

የዝናብ ወራት ማለፉን ተከትሎ በጥቅምትና ህዳር ወቅት ላይ አብዛኛውን ጊዜ የጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ በሽታ ይከሰታል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ምላሽ ግብረ-ሃይል ዋና አስተባባሪ ዶክተር መብራቱ ማሴቦ ፤ ከጥቅምት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ በሽታ መከሰቱን ተናግረዋል።

" እጅን በመታጠብ፣ አፍና አፍንጫን በመሸፈን በሽታውን በቀላሉ መከላከል ይቻላል " ያሉ ሲሆን በበሽታው የተያዙ ሰዎች በቂ እረፍት በመውሰድ፣ ፈሳሽና ትኩስ ነገሮች በመጠቀምና ተገቢውን ህክምና በማግኘት ስርጭቱ እንዳይስፋፋ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የጤና ባለሙያዎች የሚሰጧቸውን ምክረ-ሀሳቦች በመተግበር፣ በርና መስኮቶችን በመክፈት፤ በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር በማድረግ መከላከል እንደሚቻልም ነው የገለፁት፡፡

መረጃው የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና ኢዜአ ነው።

07/10/2023
01/10/2023

🌼🌼🌼
👈
🔊
Numan Events and Promotion 🔥

23/09/2023

በዘጠነኛ ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪ ያገኝው እስራኤል ቤሌማ

"የራሱን የስልክ መስመር ዘርግቶ ሰዎችን በነፃ ስልክ ሲያስጠቅም ነበር"

የተወለደው በምዕራብ ሸዋ ዞን ጊንጪ ከተማ ነው፡፡ ልጅነቱን ከእድሜ እኩዮቹ ጋር በጨዋታ ከማሳለፍ ይልቅ ከእድሜው በላይ በፈጠራ ስራዎች እና በምርምር አሳልፏል፡፡

ያኔ ገና የ7 አመት ልጅ ሳለ ከቴሌ መስመር ጋር ማይገናኝ ቤት ውስጥ መግባት የሚችል ስልክ ሰራ፡፡ የአካባቢው ህብተረሰብም በነፃ በእስራኤል ስልክ ተንበሸበሸ፡፡

ይህ ከቴሌ እውቅና ውጭ የሆነ ስልክ እንዲጣራለት ያዘዘው ቴሌ እስራኤል በፖሊስ እንዲያዝ አደረገ፡፡ ይሁን እንጂ ያገኙት ወንጀለኛ ሳይሆን ባለ ምጡቅ አዕምሮ ባለቤት የሆነውን ታዳጊ ነበር፡፡

በእስር ፈንታ ስራው ተመርምሮ እውቅና እንዲሰጠው ተደረገ፡፡ በኋላም ቴሌ በሰጠው የትምህርት እድል የዘጠነኛ ክፍሉ እስራኤል በጅማ ዩኒቨርሲቲ ከዲግሪ ተማዎች ጋር ተቀላቅሎ በመማር የመጀመሪያ ዲግሪውን ያዘ፡፡

እስራኤል ሙሉ ግዜውን በፈጠራ እና በምርምር ስራዎች ላይ የሚያሳልፍ ሲሆን ሁለት የፓተንት ፈቃድ ያስገኙለት ፈጠራዎች አሉት፡፡ ሌሎች በሂደት ላይ ያሉ ፈጠራዎች እና ምርምሮችም እንዳሉት ይናገራል፡፡

ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለመጀመሪያ ጊዜ ባዘጋጀው የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ ተሳትፎ የ150ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮ ኢኖቬሽን ሴንተር መስራች እና ባለቤት በመሆን ለአስር ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡

ዘገባው የኤፍኤም አዲስ 97.1 ነው።

20/09/2023

Dhugaa ykn Soba Jedhaa Deebisaa!

በጭፍን የኦሮሞን ህዝብ ጥላቻ እስካልቆመ ድረስ ሁሉም የኦሮሞ ህዝብ ካንተ ጋር ነው
04/09/2023

በጭፍን የኦሮሞን ህዝብ ጥላቻ እስካልቆመ ድረስ ሁሉም የኦሮሞ ህዝብ ካንተ ጋር ነው

Address

Addis Abeba
Addis Ababa

Telephone

+69040217

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia le zelalem tinur posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category