Robsen D. wake advocacy page

Robsen D. wake advocacy page Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Robsen D. wake advocacy page, Business service, Addis Ababa.

12/05/2024

Concerning today's game the Gunners do not give a s**t care for the Noisy red Devil's man united....this is my heartily prediction!!!!!!

As soon as the Gunners win Trophy of England perime league the Ironic coach going to  huck......
12/05/2024

As soon as the Gunners win Trophy of England perime league the Ironic coach going to huck......

31/01/2023

ijibbaataa mana murtii waliigala federaalaa murtii hin maxxanfamin lakk, galmee 215762 irratti waliigalteen gurgurtaa manaa alatti osoo bu'uura SHH keewwata 1723(1) tiin qaama Aangoo qabu biratti hin galmaawin raawwatamu qabdiin kan itti kafalame tahullee seera duratti fuudhatama kan hin qabne tahuu fi waxinee akka tahe murtii dirqisiisaa kenneee jira

31/01/2023

በፍትሓብሔር_ክርክር_የመጀመሪያ_ደረጃ_መቃወሚያ_አቀራረብና_እልባት_አሰጣጥ_ሥነ_ሥርዓት
================================
✔️ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በሰጠው መልስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማቅረቡን ማጣራት ይኖርበታል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ቀርቦ ከሆነ ከሳሽ መልስ እንድሰጥበት እድል ይሰጠዋል፡፡ በተቻለ መጠን ፍርድ ቤቱ ለቀረበው መቃወሚያ ወድያውኑ ወይም በአጭር ጊዜ ውስጥ እልባት ልሰጥ ይገባል፡፡

✔️በመጀመሪያ ደረጃ ክርክር ላይ የሚቀርቡ መቃወሚያዎች በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.244 (2(ሀ-ረ)) የተዘረዘሩት ሲሆኑ ነገር ግን ሙሉ ዝርዝር አይሆንም፡-
➥1ኛ/ ፍ/ቤቱ ነገሩን ለመስማት ሥልጣን ከሌለው፤
➥2ኛ/ ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ ከሆነ፤
➥3ኛ/ ክስ የቀረበበት ጉዳይ በሌላ ፍ/ቤት በመታየት ላይ የሚገኝ ከሆነ፤
➥4ኛ/ አንደኛው ተከራካሪ በነገሩ ውስጥ አያገበውም የሚል መቃወሚያ፤
➥5ኛ/ ክሱ በይርጋ የሚታገድ ነው የሚል መቃወሚያ፤
➥6ኛ/ ክስ የቀረበበት ጉዳይ በዕርቅ አልቆ በስምምነት የተፈጸመ እንደሆነ ወይም ለዕርቅ የተቀጠረ እንደሆነ የሚያስረዳ ነገር ቀርቦ መቃወሚያ የተጠየቀ እንደሆነ ናቸው፡፡

✔️ ከዚህ በላይ ከቀረቡት መቃወሚያዎች አንዱ ወይም ከዚያ በላይ የቀረቡ እንደሆነ በቀረቡት መቃወሚያዎች ላይ ከዚህ በታች በተቀመጠው ሁኔታ ብይን ይሰጥባቸዋል፡-
➥1. ማስረጃ ተቀብሎ ከመመረመሩ ወይም ምስክሮችን ከመስማቱ በፊት ፍርድ ቤቱ አስቀድሞ ማናቸውም ተከራካሪ ወገን ላቀረበው መቃወሚያ ውሳኔ መስጠት አለበት (ቁጥር 244(1)) ፡፡
➥2. መቃወሚያዎቹ ከአንድ በላይ ከሆኑ ሁለም አንድ ላይ መቅረብ አለባቸው፡፡
ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት የሚያሰናክል ካልሆኑ በቀር መጀመሪያ ያልቀረቡ መቃወሚያዎች በኃላ መቅረብ አይችሉም፡፡ (ቁጥር 244(3))
➥3. መቃወሚያ መቅረብ ያለበት ከመከላከያ መልስ ጋር ነው እንጂ መጀመሪያ መቃወሚያ ብቻ ቀርቦ ሙለ መልስ በኃላ የሚቀርብበትን አሠራር ፍርድ ቤቱ
መፍቀድ የለበትም፡፡ ስለዚህ ሙለ መልስ ተሟልቶ ሳይቀርብ መቃወሚያው ብቻ የቀረበለት ፍርድ ቤት በቁጥር 338 መሠረት የመከላከያ መልሱን ሲመረምር እንድህ አይነቱን ያልተሟላ መልስ አለመቀበል ወይም ተሰተካክል እንድቀርብ
ማዘዝ አለበት፡፡
➥4. ክሱ ትክክለኛውን ፎርም አልተከተለም የሚል ክርክር እንደመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መቅረብ አይችልም (ቁጥር 244)፡፡ (ክሱ ፎርሙን መከተልን
የሚያጣራው ሪጅስትራር ስለሆነ ነው፡፡)
➥5. ፍርድ ቤቱ የቀረበውን መቃወሚያ እንዲሁም የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ በቁጥር 245 መሠረት ተገቢውን ውሳኔ ይሰጣል፡፡
➥6. የቀረበው መቃወሚያ ክሱ የተነሳበት ጉዳይ በይርጋ የታገደ መሆኑን፣ ወይም አስቀድም በፍርድ የተወሰነ መሆኑን፣ ወይም በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈጸመ መሆኑን፣ ወይም ለዕርቅ የተቀጠረ መሆኑን የሚገልፅ ከሆነና ይህም
በማስረጃ ከተረጋገጠ ፍርድ ቤቱ ክሱን ዘግቶ ባለጉዳዮቹን ያሰናብታል (ቁጥር 245(2))፡፡
➥7. ከላይ በቁጥር 6 ስር ከተገለፀው ውጪ ያለ መቃወሚያ ሲቀርብና በማስረጃ ሲረጋገጥ ግን ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ዘግቶ ተገቢ መስሎ የታየውን ትዕዛዝ
ይሰጣል፡፡
➥8. ከላይ በቁ. 7 ሥር በተጠቀሰው ሁኔታ መዝገቡ ሲዘጋ ካሳሽ ክሱን አሻሻሎ በዚያው ወይም በሌላ ፍርድ ቤት ክሱን እንደገና ለማቅረብ ይችላል፡፡ ከላይ
በቁጥር 6 ሥር በተጠቀሰው ሁኔታ ክሱ ሲዘጋ ግን ከሳሹ በዚያው ጉዲይ ላይ ክስ ለማቅረብ አይችልም (ቁጥር 245 (3))፡፡
➥9. መዝገቡ የተዘጋው ፍርድ ቤቱ ሥልጣን በማጣቱ ከሆነ ከሳሹ ከከፈለው የዳኝነት ገንዘብ ላይ በደንቡ መሠረት ከሚከፈለው ሂሣብ የቀረው ይመለስለታል (ቁጥር 245 (4)) ፡፡

31/01/2023

ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረ ሰራተኛ ሰ/መ/ቁጥር 212420

አሰሪው ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረን ሠራተኛ ለስራው ተስማሚ አለመሆኑን ሳይመዝን ካሰናበተ ስንብቱ ህገ- ወጥ ነው።

ስንብቱ ህገ-ወጥ በመሆኑ ካሳ የሚከፈለው ሲሆን የስንብት እና የማስጠንቀቂያ ክፍያዎች ግን አገልግልትን ታሳቢ ተደርገው የሚሰሉ በመሆኑ አይከፈሉትም።

የካሳው መጠን ሰራተኛው የሙከራ ጊዜውን (60 ቀናት) ቢጨርስ ሊያገኝ ይችል የነበረውን የ2 ወር ደመወዝ ብቻ ነው።

31/01/2023

ተከሳሽ የመከላከያ መልሱን አቅርቦ ክሱ ሊሰማ በተቀጠረበት ዕለት ባለመቅረቡ በፍ/ሥ/ሕ/ቁ 70(ሀ) መሰረት ክርክሩ በሌለበት እንዲታይ ብይን ከተሰጠ የመከላከያ ክርክር የማቅረብ መብቱን ከማሳጣት አልፎ በቀሪዎቹ የክርክር ሂደቶች ከመሳተፍ አያግደውም።

  mana murtii waliigala federaalaa lakk galmee 212950 taheen gaafa 30/9/2014 murtii hin maxxanfamin kenneen madaallii ra...
31/01/2023

mana murtii waliigala federaalaa lakk galmee 212950 taheen gaafa 30/9/2014 murtii hin maxxanfamin kenneen madaallii ragaa ilaalchisee himatamaa irraa kan eegamu ragaan ittisaa inni dhiheeffatee shakkiin olitti irraa ittisuu osoo hin taane ragaa Abbaa Alangaa shakkii keessa galchuu qofaatu irraa eegama kana jechuun wanti ragaa Abbaa Alangaa shakkii keessa galchu dhiheessuun qofti himatamaa bilisa baasu dandaya jechuun murtii dirqiisaa kennee jira.

31/01/2023

ስህተት ያለበት ውሳኔ ስለማስተካከል
⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️💥

💥ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔና ትዕዛዝ ላይ የአጻጻፍ ስህተት፣ የቁጥር አጻጻፍ ጉድለት ወይም ያልታሰበና ባለማስተዋል የተዘለለ ድንገተኛ የቃል ስህተት እንዲታረም በተከራካሪዎች የሚቀርብ አቤቱታ

💥አንድ ፍርድ ቤት በክርክሩ ዋነኛ ጭብጥ ላይ አከራክሮ የሰጠውን ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ ስህተትን ማረም በሚል ሊያሻሽል ወይም ሊለውጥ አይችልም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 37303 ቅጽ 8፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 208

💥በማንኛውም ፍ/ቤት በሚካሄድ ክርክር ሥነሥርዓቱን ያልተከተለ ክስ የቀረበ እንደሆነ ወይም በክሱ ሂደት ሕጉ ያስቀመጣቸው የሥነሥርዓት ደንቦች በአግባቡ ያልተፈፀሙ እንደሆነ ፍርድ ቤት ሥርዓቱ ከሚያዘው ውጪ የተሠራውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ሊሰርዝ ይችላል፡፡ ይህም የሚከናወነው በተከራካሪዎች አመልካችነት ብቻ ሳይሆን በፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነትም ጭምር ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ መርህና ደንብ መሠረት በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ ዳኞች በሚያካሂዱት የዳኝነት ሥራ የሥነሥርዓቱን ደንብ ያልተከተለ ክንውን በራሳቸውም ሆነ በአስተዳደር ክፍሉ መፈፀሙን ሲያውቁ ወይም ሲደርሱበት ስህተቱን እንዲያርሙ ይጠበቅባቸዋል፡፡
💥በፍርድ ቤቶች አካባቢ የሚታየው የተለመደው አሠራር ዳኛ የሰጠውን ትዕዛዝ መቀየር አይችልም፣ መቀየር የሚችለው የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ብቻ ነው የሚል ቢሆንም ይህ በተለምዶ የዳበረው አሠራር የሥነሥርዓቱ ሕጉ ያሰፈረውን መሠረታዊ መርህ የሚጻረር ነው፡፡ ሥነ ሥርዓት ነክ የሆነን ጉዳይ የሚመለከት እስከሆነ ድረስ ባለጉዳዮች ወደ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት መሄድ ሳያስፈልጋቸው ስህተቱን ለፈፀመው ፍርድ ቤት ማመልከት ይፈቀድላቸዋል፣ ዳኞችም እርግጥም ሰህተት መሠራቱን ካመኑበት ስህተቱን የማረም ሥልጣንም አላቸው፡፡
አብርሐም ዮሐንስ
ሰ/መ/ቁ. 17352 ቅጽ 1

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Robsen D. wake advocacy page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share