ቄሮ ወሎ ቦረና

ቄሮ ወሎ ቦረና Qeerroo booranaa
(1)

17/05/2025
ወለጋ የደም መሬት
05/07/2022

ወለጋ የደም መሬት

05/05/2021

ቁርኣን እና ለይለቱል ቀድር
---
አፈንዲ ሙተቂ
----
አዎን! አላህ በለይለቱል ቀድር የሰጠን ትልቁ ስጦታ ቁርኣን ነው። ከመጽሐፎች ሁሉ በላጭ የሆነው ቅዱስ ቁርኣን የወረደው ለይለቱል ቀድር በተባለችው ታላቅ ሌሊት ነው። ይህንንም በቁርኣኑ ውስጥ በግልጽ ነግሮናል።
---
እስቲ በዚህች ታላቅ ሌሊት የወረደውን ቁርኣንን በአጭሩ እንቃኘው።

# ቅዱስ ቁርኣን 114 ምእራፎች (ሱራ) እና 6236 አንቀጾች (አያህ) ያሉት የአላህ ቃል ነው። በየወሩ ለማንበብ በሚያመች መልኩም በሰላሳ ጁዝእ (ክፍሎች) ተከፋፍሏል።

# ረጅሙ የቁርኣን ሱራ "አል በቀራህ" ሲሆን እርሱም 286 አንቀጾች አሉት።

# አጭር የሆኑት የቁርኣን ሱራዎች "አል ዐስር"፣ "አል ከውሠር" እና "አል ነስር" ሲሆኑ እያንዳንዳቸው ሶስት አንቀጾች አሏቸው።

# ረጅሙ የቁርኣን አንቀጽ በሱረቱል በቀራህ የሚገኘው 282ኛ አንቀጽ ነው። አጫጭሮቹ የቁርኣን አያዎች "ጣ ሃ"፣ "ሃ ሚም" እና "ያ ሲን" ናቸው።

# መጀመሪያ የወረደው የቁርኣን ሱራ "አል ዐለቅ" ሲሆን መጨረሻ ላይ የወረደው ሱራ "አል ነስር" ነው።

# በአንቀጽ ደረጃ ደግሞ መጀመሪያ የወረዱት የሱረቱል ዐለቅ አምስት አንቀጾች ሲሆኑ መጨረሻ ላይ የወረደው የሱረቱል ማኢዳ ሶስተኛ አንቀጽ (አያህ) ነው።

# የቁርኣን ሱራዎች በመጽሐፉ ውስጥ የተቀመጡት በወረዱበት ቅደም ተከተል ሳይሆን ለውሀል ማሕፉዝ (ጥብቁ ሰሌዳ) በሚባለው ታላቁ ሰሌዳ ላይ በተጻፉበት መልክ ነው።

# የቁርኣን አወራረድ ሁለት መልሶ አለው። መጀመሪያ ላይ ከለውሐል ማሕፉዝ (የተጠበቀው ሰሌዳ) ላይ ተወስዶ "ለይቱል ቀድር" በምትባለው ታላቋ የረመዳን ሌሊት፣ በቅርቢቷ ሰማይ በሚገኘው ቤይቱል ማእሙር በሚባለው ቤት ወደ መልአኩ ጂብሪል ወርዷል።

# ቁርኣኑ ወደ ጂብሪል የወረደው በተሟላ ሁኔታ እና በለውሐል ማሕፉዝ ላይ ያለውን የሱራዎችና የአያዎች ቅደም ተከተል በጠበቀ መልኩ ነው።

# የነቢዩ ሙሐመድ መልእክተኛነት ከተበሰረ በኋላ ደግሞ ጂብሪል ቁርኣኑን በምእራፎችና በአንቀጾች እየከፋፈለ በ23 ዓመታት ውስጥ በነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ላይ አውርዷል።

# ነቢዩ ሙሐመድም (ሰዐወ) ወሕዩን ከጂብሪል መቀበል የጀመሩት በወርሃ ረመዳን "ለይቱል ቀድር" በምትባለው ትልቋ ሌሊት ነው። "ረመዳን" የወራቶች ንጉሥ የሚባለው በዚሁ ምክንያት ነው።
----
አላህ ለይቱል ቀድርን ከሚወፍቃቸው ያድርገን።
---
(ሼር ብታደርጉት አጅሩ ለእናንተም ለእኔም ነው። ጀዛኩሙላህ)

26/08/2020

የሸሆቼ ልጅ ይናገራል

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቄሮ ወሎ ቦረና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share