25/07/2022
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ታሪክ ከፍተኛውን ሜዳሊያ በማግኘት አጠናቀቀች‼
ላለፉት 10 ቀናት በአሜሪካ ኦሪገን ሲካሄድ የሰነበተውን 18ኛውን የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛውን ሜዳሊያ በማግኘት አጠናቃለች፡፡
በወንዶች እና ሴቶች ማራቶን እንዲሁም በ10ሺ እኛ 5 ሺ ሜትር ሴቶች 4 ወርቅ በማምጣት በሻምፒዮናው ከፍተኛ የሚባል ውጤት ተመዝግቧል፡፡
በ3ሺ ሜትር መሰናክል በሴት እና ወንድ እንዲሁም በወንዶች ማራቶን እና በ1500 ሜትር ሴቶች የብር ሜዳሊያ ተገኝቷል፡፡
ሁለቱ የነሐስ ሜዳያ የመጣው ደግሞ በሴቶች 3ሺ መሰናክል እና በ5ሺ ሜትር ነው፡፡
ኢትዮጵያ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከአፍሪካ ቀዳሚ፣ ከዓለም ደግሞ ከአሜሪካ በመቀጠል 2ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ በሻምፒዮናው ታሪክ ከፍተኛው ሜዳሊያ በማግኘት አጠናቃለች፡፡
ጎረቤት ኬንያ ደግሞ በ2 ወርቅ ፣5 የብር እና 3 የነሀስ በድምሩ 10 ሜዳሊያ በማግኘት በኢትዮጵያ በሁለት ወርቅ ተበልጣ ከአፍሪካ 2ኛደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡