04/08/2026
#ከሬናይሰንስ (Renaissance) ጀምሮ እስከ ዘመናዊው ዓለም ድረስ ያለው የጥራት ታሪክ ፣ የወጡ ሕጎች ፣ ታላላቅ ክስተቶች እና በጥራት መጓደል ምክንያት የደረሱ ውድቀቶች
#1የሬናይሰንስ ዘመን (Renaissance Era: ከ14ኛው እስከ 17ኛው ክፍለ ዘመን)
በሬናይሰንስ ዘመን የጥራት አስተሳሰብ በወቅቱ ከነበሩት የእጅ ሙያ ማህበራት (Craft Guilds) ጋር የተያያዘ ነበር። ጥራት የሚለካው በባለሙያው ድንቅ ሙያና ጥበብ (Craftsmanship) ነበር፡፡
የወጡ ሕጎችና የነበሩ ታላላቅ ክስተቶች ቀዳሚው የጀርመን የቢራ ጥራት ሕግ (Reinheitsgebot – 1516) በዓለም ታሪክ ውስጥ እስካሁን ሥራ ላይ ካሉ የጥራትና የምግብ ደህንነት ሕጎች አንዱ ሲሆን ፣ ቢራ የሚሠራባቸውን ጥሬ ዕቃዎች (ውሃ ፣ ገብስና ሆፕስ) ብቻ በማድረግ ጥራቱን ለመጠበቅ የወጣ ሕግ ነበር፡፡ የመረጃ ምንጭ Quality Management: Introduction to Total Quality Management for Production, Processing, and Services ጸሐፊው David L. Goetsch እና Stanley Davis
#2የመካከለኛው ዘመንና የኢንዱስትሪ አብዮት (Middle Era to Industrial Revolution: ከ18ኛው እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ)
በኢንዱስትሪ አብዮት መምጣት ምክንያት የጥራት አስተሳሰብ ከእጅ ሙያ ወደ ጅምላ ምርት (Mass Production) እና ምርመራ (Inspection) ተሸጋገረ።
በወቅቱ የወጡ ሕጎችና ታላላቅ ክስተቶች መሀከልም ተለዋዋጭ ክፍሎች (Interchangeable Parts) Eli Whitney እ.ኤ.አ. በ1798 ለጦር መሣሪያዎች የሚሆኑ ተመሳሳይ ክፍሎችን በመሥራት የመጀመሪያውን የደረጃ መደብ (Standardization) አስተዋወቀ፡፡ የሳይንሳዊ አስተዳደር ቲዮሪ (Scientific Management) Frederick Winslow Taylor የሥራ ሂደቶችን በመከፋፈልና በመለካት ምርታማነትና ጥራትን ለማሳደግ መንገድ ጠረገ፡፡ የዚህ መረጃ ምንጭ Out of the Crisis sihone ፀሐፊው W. Edwards Deming የዘመናዊ ጥራት አባት በመባል የሚታወቀው ነው፡፡
#3የዘመናዊው ዓለም የጥራት አስተሳሰብ (Modern Era: ከ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ እስከ ዛሬ)
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የጥራት አስተሳሰብ ከቀላል ምርመራ (Inspection) ወደ ስታቲስቲካዊ የሂደት ቁጥጥር (Statistical Process Control) ፣ አጠቃላይ የጥራት አስተዳደር (TQM) እና የዓለም አቀፍ ደረጃዎች (ISO) አደገ።
በዘመኑ አደረጃጀቶች ፣ የወጡ ሕጎች እና ደረጃዎች ISO 9001 (በ1987 የተዘረጋ)፦ በዓለም አቀፍ ደረጃ ድርጅቶች የጥራት አስተዳደር ሥርዓታቸውን የሚመሩበት ዋና መለኪያ ሆኖ ማገልገል ጀመረ፡፡ በዚህም የጃፓን የጥራት አብዮት በW. Edwards Deming እና Joseph Juran ድጋፍ ጃፓን "የካይዘን" (Continuous Improvement) ፍልስፍናን በመከተል በዓለም የጥራት መሪ ሆነች፡፡ የዚህ መረጃ ምንጭ (መጽሐፍ) Juran's Quality Handbook ሲሆን ደራሲ Joseph M. Juran እና A. Blanton Godfrey
#4በጥራት መጓደል ምክንያት በዓለም ላይ የተከሰቱ ታላላቅ አደጋዎችና ኪሳራዎች
በታሪክ ውስጥ የጥራትና የደህንነት መጓደል በሰው ሕይወት ፣ በሀገርና በድርጅቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል።
#በቀዳሚነት የቸርኖቢል የኑክሌር አደጋ /Chernobyl Disaster - በ1986 የተከተሰ
የአደጋው ምክንያት የሪአክተር ዲዛይን ጉድለት (Design flaw) እና በጥራት የተደገፈ የደህንነት መመሪያ አለመከተል ነበር፡፡ በሰዎች ላይ ያደሰው አደጋ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለካንሰርና ለሞት ተዳርገዋል። በአካባቢው የሚኖሩ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለዋል፡፡ በሀገርና ድርጅት ላይ ያደሰው ኪሳራ ሲታወስ ደግሞ በወቅቷ የሶቭየት ህብረት ላይ ከ200 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ያደረሰ ሲሆን ፣ ለሶቭየት ህብረት መፍረስም እንደ አንዱ ምክንያት ይጠቀሳል፡፡ የመረጃውን ምንጭ ለምትሹ Chernobyl: History of a Tragedy – Serhii Plokhy
#ቀጣዩ የቦይንግ 737 Max የኤርፕሌን አደጋዎች (2018 - 2019)
የአደጋው ምክንያት በሶፍትዌር ዲዛይን (MCAS) እና በጥራት ቁጥጥር መጓደል እንዲሁም ለፓይለቶች በቂ ስልጠና አለመስጠት ነው ተብሎ ተዘግቧል፡፡ በሰዎች ላይ ያደሰው አደጋ በሁለት አደጋዎች (በኢትዮጵያና በኢንዶኔዢያ) የ346 ንጹሃን ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ በድርጅቱ ላይ ያደሰው ኪሳራ ቦይንግ ከ20 ቢሊዮን ዶላር በላይ direct cost (የካሳና የጥገና) ያጣ ሲሆን ፣ ምርቶቹ ለአመታት ከበረራ በመታገዳቸው በስሙና በገበያ ድርሻው ላይ ትልቅ ውድቀት ደርሶበታል፡፡ የመረጃው ዋና ምንጭ፦ Flying Blind: The 737 MAX Tragedy and the Fall of Boeing – Peter Robison
#ሌላኛው አደጋ የቻሌንጀር ስፔስ ሻትል ፍንዳታ (Space Shuttle Challenger - 1986)
የዚህኛው አደጋ ምክንያት የ"O-ring" የተባለው የጎማ ክፍል በቅዝቃዜ ወቅት የመለጠጥ አቅሙ በመቀነሱ (የዲዛይንና የቁሳቁስ ጥራት ጉድለት) የተከሰተ ነው፡፡ በሰዎች ላይ ያደሰው አደጋ የ7 ጠፈርተኞች ሕይወት ወዲያውኑ አልፏል፡፡ በሀገርና ድርጅት ላይ ያደሰው ኪሳራ ደግሞ የናሳ (NASA) ተአማኒነት ላይ ትልቅ ጥቁር ነጥብ የጣለ ሲሆን፣ የአሜሪካን የጠፈር ምርምር ፕሮግራም ለዓመታት አስተጓጉሏል። ምንጭ The Challenger Launch Decision – Diane Vaughan ነው፡፡
#ማጠቃለያ
#የጥራት ታሪክ እንደሚያሳየው፣ ጥራት ቀደሞ ምርትን ከመፈተሽ ተነስቶ ዛሬ የድርጅቶችና የሀገራት የስትራቴጂ አካል ሆኗል። በጥራት ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት የወደፊት አደጋዎችንና ውድቀቶችን የመከላከያ ዋና መሣሪያ ነው፡፡ ማሽኖች ሲንቀሳቀሱ ፣ ምርቶች ሲመረቱ ፣ አገልግሎቶች ሲሰጡ ፣ በትምህርት ፣ በጤና ፣ በግብርና በሁሉም መስክ ሙያተኞች ለጥራት ትኩረት በመስጠት ውጤታማ ምርትና አገልግሎት ለመስጠት መትጋት አለባቸው! የሰው ልጅ በሙሉ አእምሮው ሊከውናቸው የምገባቸው ጉዳዮ ለአንድ ሰከንድ ከነገሩ ትኩረቱን ቢያነሳ የከፋ አደጋ ይከሰታል፡፡ ትላልቅ ኪሳራዎች ይደርሳሉ፡፡ በጥራት አይቀለድ፡፡ በጥራት መዘናጋት የለም፡፡ ሀገራችን ከሰለጠኑት የዓለም ሀገራት ተርታ እንድትመደብ የምንሻ ከሆነ ምርታማነትና ጥራት ላይ ትኩረት መስጠት መቻል አለብን፡፡ በዓለም ላይ በኛ ሀገር የተገኘውን ቡና ወስዳ በዓለም አንደኛ አምራች የሆነችው ብራዚል ፣ የጃፓኖች የስልጣኔ ልህቀት ሊያስቀናንና በቁጭት ሊያስነሳን ይገባል፡፡
#ኢትዮጵያን የሚመጥን ጥራት!
#በኢትዮጵያ ታሪክ ልክ በተገነባ ስብዕና!