ZHA EHS Consultancy Service PLC.

ZHA EHS Consultancy Service PLC. Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ZHA EHS Consultancy Service PLC., Consulting Agency, Addis Ababa.

16/04/2023
16/12/2022

በኢትዮጵያ ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ኮንዶምን የሚጠቀሙት ከ20 በመቶ በታች መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ።

አጥኚዎች Web of Science, Google Scholar ጨምሮ በሌሎች ገጾች ላይ እ.አ.አ ከ2000 - 2019 የነበሩ መረጃዎችን በመተንተን ባገኙት መረጃ መሰረት ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት፣ በምሥራቅ አፍሪካ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ተማሪዎች በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ኮንዶምን የመጠቀም ልምድ ዝቅተኛ ነው ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኤችአይቪ/ኤድስ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ቢኖራቸውም ከአንድ በላይ ወሲባዊ ጓደኛ በመያዝ እና ከልክ በላይ አልኮል በመጠቀም ተጋላጭ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዝቅተኛ የኮንዶም አጠቃቀም (ከ20 በመቶ በታች) ካላቸው ሀገራት መካከል ማዳጋስካር፣ ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ ይገኙበታል ብለዋል።

ኢኮኖሚያዊ ጫና፤ እጾችንና አልኮልን ከመጠን በላይ መጠቀም እና የወሲብ ምስሎችን መመልከት በአብዛኛዎቹ የአለም ሀገራት ለአደጋ አጋላጭ ጾታዊ ባህሪያት አስተዋፅዖ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውን ተመራማሪዎች ለይተዋል።

ከዚህ በተለየ ከሰሃራ በታች ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደግሞ የእኩዮች ጫና፣ የወላጆች ቁጥጥር ማነስ፣ የቤተሰብ ግንኙነት ዝቅተኛ መሆን፣ ደካማ የትምህርት አፈጻጸም እና ከአንድ በላይ ወሲባዊ ጓደኛ መያዝ ለኤችአይቪ እና መሰል ተላላፊ በሽታዎች ለመጋለጣቸው በምክንያትነት ያነሳሉ።

በጥናቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት የኮንዶም አጠቃቀም በምስራቅ አፍሪካ 40.5 በመቶ፣ መካከለኛው አፍሪካ 43.9 በመቶ፣ ምዕራብ አፍሪካ 58.6 በመቶ እና ደቡብ አፍሪካ 50.5 በመቶ ሆኖ ተቀምጧል

29/11/2022

#ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ በተሰበሰበ መረጃ በሀገራችን ባለፈው ዓመት 1.5 ሚሊየን ዜጎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ ይህም ከታሰበው እና ከተገመተው በ 3 ዕጥፍ ከፍ ያለ ሲሆን፣ ባለፈው አመት የተገመተው ወደ 5 መቶ ሰው በቫይረሱ ሊያዝ እንደሚችል ቢሆንም ግን በ3 ዕጥፍ ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል።

ከዚህ በፊት ከነበረው አሁን ላይ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር "በሚያሰጋ ደረጃ እየጨመረ ነው " የተባለ ሲሆን በተደረገ ጥናት ይፋ በሆነ መረጃ እድሜያቸው ከ15-29 ባሉ ሴቶች ቫይረሱ " አስደንጋጭ " በሆነ መልኩ እየተስፋፋ መሆኑን ገልጸዋል።

በየአመቱ እድሜያቸው ከ15-24 ባሉ የማህበረሰብ ክፍልም አዲስ በቫይረሱ ከሚያዙት መካከል ሴቶች 69 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ እንደሚወስዱ ተገልጿል፡፡

በሀገራችን በልጃገረድ እና ወጣት ሴቶች የኤችአይቪ ስርጭት መጠን 0.4 በመቶ እንደሆነ መረጃዎች ቢገልፁም በ2021 እድሜያቸው ከ15-29 ዓመት ያሉ ወጣት ሴቶች በአጠቃላይ አዲስ በቫይረሱ ከተያዙ መካከል 34 በመቶውን ይይዛሉ ነው የተባለው።

ዕድሜያቸው ከ15-24 ባሉ ወጣቶች በወንዶች 39 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ስለ ቫይረሱ መተላለፊያ እና መከላከያ መንገዶች የተሟላ እውቀት ሲኖራቸው በሴቶች ደግሞ 24 በመቶ ብቻ የሚሆኑት ስለ በሽታው ዕውቀት አላቸው።

ይህ ቁጥር ይፋ የሆነው የጤና ሚኒስቴር ከአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ እና ከኤ.ኤች.ኤፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የአለም ኤድስ ቀን ፕሮግራም ላይ ነው።

መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ነው

30/05/2020

ERA ኢመባ:
ይሄን አይታችሁ ዝም እንዳትሉ!! ለምትወዱት ላኩለት!!
=============================.***
በኮሮና ቫይረስ ከተያዝክ በሕይወትህ ገምተህው ፤ አይተህ ፤ የማታውቀውን አይነት ትኩሳት /ንዳድ/ ይሰማሀል፡፡ ከዚህ የተነሳ እድሜ ሙሉህን ቃዥተህ የማታውቀውን ቅዠት ያስቃዥሀል ያልብሀል፤ ጉንፋን ይመስልሀል ግን አይደልም ሁሌ የሚሰማህ አይነት ጉንፋን ወይም ራስ ምታትም አይምሰልህ፡፡
***
እስፖንጅ አፍንጫህ ላይ የተቀረቀረ ይመስል ለመተንፈስ ትቃትታለህ፡፡ ሳንባህን በአየር ለመሙላት በሀይለኛው ትንፋሽህን ስትስብ አየር ያጥርሀል! ያኔ ይጨንቅሀል ፤ ትፈራለህ! በሀይል ከማሳልህ የተነሳ በድካም አእምሮህን ልትስት ትደርሳለህ! ባሳልክ ቁጥር ደረትህ፣ እጆችህ፣ ጀርባህ፣ የእጅና እግር ጣቶችህ .... ነፍስህ እዚያ ጋር ያለ ይመስል በጣም ያሙሃል መገጣጠሚያህ ሁሉ የተነቃቀለ ይመስልሀል፡፡
***
በአፍንጫህ አየር ለማስገባት ስለማትችል ኦክስጂን ይሰጡሀል፡፡ ወዳጄ ያ ደግሞ የአፍንጫህ ቱቦዎች እሳት የተለቀቀባቸው ያክል ስቃይ ይለቅብሀል! አሁንም መተንፈስ ካልቻልክ ሌላ ሀኪም ይመጣና ግማሽ ኢንች የሚሆኑ ሁለት ቱቦዎች በጉሮሮህ በኩል ወደሳንባዎችህ ይሰዳል! ይህን artificial respirator ብለው የሚጠሩት ህክምና ለመተንፈስ የሚረዳህ ነው፡፡
***
ይህ ሁኔታ በጣም ከማስጠላቱና ከመክበዱ በላይ እጅግ አስከፊው ነገር ደግሞ መብላትና መጠጣት አትችልም ይህ አለመሆኑ ደግሞ የባሰ አቅም ያሳጣሀል፡፡ይህ ብቻ አይምሰልህ ከባዱ ነገር ደግሞ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ብቻህን መሆን ስላለብህ አጠገብህ ማንም ሊረዳህ የሚችል ዘመድ አዝማድ ድርሽ አይልልህም ወላ እናትህን፣ አባትህን፣ ልጆችህን፣ ሚስትህን፣ ወንድምና እህትህን ወይም ጓደኛችህን ማየት አይፈቀድልህም፡፡(ይሄ በራሱ ያሳብድሀል)
***
ግራ አይግባህ ለምን ይህ እንደሆነብህ ገብቶሀል ? ምክንያቱም ሊገልህ ባለው በሽታ እንዳትበክላቸው ነው! አንዴ ልድገምልህ? ሊገልህ ያለው ኮሮና በቁምህ ዘመድ አዝማድ ጓደኛህን መንጠቅ ጀምሯል!! በዚህ ስቃይ ውስጥ ብቻህን ከመሆንህ የተነሳ ትፈራለህ፣ ታለቅሳለህ ፣ ሊገልህም እንደሚችል ይገባሀል ! ! ! በነገርህ ላይ ልትሞትም ትችላለህ! የምትወዳቸውን እያሰብክ ካለጠያቂ ነፍስ ለማዳን በሚዋከቡ ሀኪሞች ተከበህ ታለቅሳለህ፤ ከትንፋሽህ ጋር ግብ ግብ እየገጠምክ፡፡
***
ትንሽ ያገገምክ መስሎህ ውስጥህ ተስፋ እየጫረ ባለበት ጊዜ ደግሞ አይንህ እያየ ከተኛህበት ሆስፒታል ካንተው ክፍል ውስጥ ካንተ ቀድሞ የገባ ወይም ካንተ በኋላ የመጣ በነጭ ጨርቅ ተጠቅልሎ አስከሬኑ ሲወጣ ልታይ ትችላልህ! ይህ ደግሞ ቀጥሎ ተረኛ እንደሆንክ እየተሰማህ የባሰ በፍርሀት ታልቃለህ ማለት ነው !!
***
ልክ ይሄንን ስታይ ይቆጭሀል ፤ ያንገበግብሀል ወዲያው ከቻልክ እቤትህ ተቀመጥ፣ ያለምክንያት ከቤት አትውጣ፣ እጅህን በተደጋጋሚ ታጠብ፣ ሳኒታይዘርና አልኮሆል ተጠቀም፣ ርቀትህን ጠብቅ እና ማስክ አድርግ የተባልከው ትዝ የሚልህ! ይሄኔ ነው አሁን የባሰ በቁጭት አለንጋ ትገረፋለህ!! ይፀፅትሀል! እድለኛ ከሆንክ በዚህ ሁሉ አልፈህ ልትተርፍ ትችላለህ ካልሆነ ግን አይንህ እያየ በቸልተኝነትህ ይቺን ምድር በኮሮና ምክንያት ትሰናበታለህ ማለት ነው!!
***
ወዳጄ አንድ ነገር ልምከርህ እኔ ለወላጆቼ ለልጆቼ ለኋደኞቼ ለሚወዱኝ ለምወዳቸው ለሚያከብሩኝ ለማከብራቸው ስል እጠነቀቃለሁ ብለህ ካሁኑ ንቃ! ጥቂት ቀናት ታሪክህን ሊቀይሩ ይችላል!

13/05/2020

As economies close in response to COVID-19, women face significant risks to their health and livelihoods. In the transport sector, where women are already significantly under-represented, they face precarious and vulnerable employment situations that any COVID-19-related economic crisis will accentuate, in a differentiated way to that facing men in the sector.

Any post-COVID-19 response must recognise these gender differences, involve both men and women in its development and be equitable and inclusive in its impact

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911981331

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ZHA EHS Consultancy Service PLC. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share