ETHIO ገበያ

ETHIO ገበያ የሀገር ውስጥ እና የውጭ የቢዝነስ መረጃዎችን፣የድርጅት እና የተቋማትን ምርት እና አገልግሎት እና አዳዲስ ፈጠራዎችን የሚተዋወቅበት

2% ተጨማሪ ጉርሻ! የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (ሚያዚያ 21 ፣ 2018 ዓ.ም)ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያ...
29/04/2026

2% ተጨማሪ ጉርሻ!
የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተመን (ሚያዚያ 21 ፣ 2018 ዓ.ም)
ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ፋስትፔይ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
April 29, 2026

  የናፍጣ አቅርቦት ከዛሬ ጀምሮ ቀድሞ ወደ ነበረበት እንዲመለስ መንግሥት ወስኗል! - የገንዘብ ሚኒስትር    አሕመድ ሽዴበኢትዮጵያ የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ከመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት ...
29/04/2026

የናፍጣ አቅርቦት ከዛሬ ጀምሮ ቀድሞ ወደ ነበረበት እንዲመለስ መንግሥት ወስኗል! - የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ

በኢትዮጵያ የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ከመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት በፊት ወደ ነበረበት 9 ሚሊዮን ሊትር እንዲመለስ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ አሳውቀዋል።

በመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት ምክንያት በተፈጠረው የዋጋ መጨመር እና የአቅርቦት መስተጓጎል የተነሳ በኢትዮጵያ የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ወደ 4.5 ሚሊዮን ሊትር ወርዶ ነበር።

አሁን የአንድ ቀን የናፍጣ አቅርቦት ወደ ቀደመው 9 ሚሊዮን ሊትር እንዲመለስ መወሰኑን ተከትሎ ከዛሬ ጀምሮ ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ መጓጓዝ እንደሚጀመር የገለጹት የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ወደ ክልሎች ደግሞ ከነገ ጀምሮ መጓጓዝ ይጀምራል ብለዋል።

እስካሁን የቤንዚን እና የአውሮፕላን ነዳጅ ሙሉ በሙሉ ቀድሞ በነበረው መጠን እየቀረበ መሆኑንም የገንዘብ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል ኢኮኖሚው ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለመከላከል መንግሥት በልዩ ግዢ በከፍተኛ ዋጋ ነዳጅ ገዝቶ እያቀረበ መሆኑንም ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ አስረድተዋል።

በዚህም ምክንያት በአሁኑ ወቅት መንግሥት በየወሩ ቀድሞ ከነበረው በተጨማሪ 20 ቢሊዮን ብር እየደጎመ ነዳጅ እያቀረበ መሆኑን ነው የገለፁት።


#ኢትዮጵያ

  #የአፍሪካ ልማት ባንክ ለቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የአበዳሪዎች ኢንሹራንስ አማካሪ እየፈለገ ነውየአፍሪካ ልማት ባንክ (AfDB) በኢትዮጵያ ለሚገነባው የቢሾፍቱ ዓለ...
29/04/2026

#የአፍሪካ ልማት ባንክ ለቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የአበዳሪዎች ኢንሹራንስ አማካሪ እየፈለገ ነው

የአፍሪካ ልማት ባንክ (AfDB) በኢትዮጵያ ለሚገነባው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ገለልተኛ የአበዳሪዎች ኢንሹራንስ አማካሪ ለመቅጠር የፍላጎት መግለጫ ጥሪ አቅርቧል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሚገነባው ይህ አዲስ አውሮፕላን ማረፊያ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምስራቅ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ የአህጉሪቱ ትልቁ የአቪዬሽን ማዕከል እንዲሆን ታቅዶ የተነደፈ መሆኑን ባንኩ ጠቁሟል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ እንደ ዋና አበዳሪ አስተባባሪ በመሆን ከሌሎች አበዳሪዎች ጋር የብድር ሂደቱን የሚያከናውን ሲሆን፣ ተመራጩ አማካሪ ድርጅት በፕሮጀክቱ ኢንሹራንስ መስፈርቶች፣ ሰነዶችና ክትትል ላይ ገለልተኛ ግምገማ የማድረግ ኃላፊነት ይኖርበታል ብሏል።

አማካሪው በቀጥታ ሪፖርት የሚያደርገው ለባንኩ ቢሆንም፣ በብድር ሂደቱ ለሚሳተፉ ሁሉም አበዳሪዎች ተገቢውን የጥንቃቄ አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለበት።

ባንኩ ብቃት ያላቸውን የአማካሪ ድርጅቶች የፍላጎት መግለጫ (EoI) እንዲያቀርቡ የጋበዘ ሲሆን፣ ድርጅቶቹ ያላቸውን የባለሙያ ብቃት፣ ተመሳሳይ ስራዎችን የመስራት ልምድና ከዓለም አቀፍ የልማት ባንኮች ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።


24/07/2025

ኢትዮ ቴሌኮም 162 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ።
ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት 162 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተቋሙን የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በዓመቱ 162 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱን ጠቅሰው ÷ በዚህም የእቅዱን 99 በመቶ ማሳካት ተችሏል ነው ያሉት፡፡

ከባለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጻጸርም የ73 በመቶ እድገት ማሳየቱን የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ÷በዚህም ተጨማሪ 68 ነጥብ3 ቢሊየን ብር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት 76 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ መገኘቱንና በዚህም የእቅዱን 104 በመቶ ማሳካት መቻሉን አመልክተዋል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር ከባለፈው ዓመት 6 ነጥብ 2 በመቶ መጨመሩን ጠቁመው÷ የሕዝብ ሽፋኑም 99 ነጥብ 4 በመቶ መድረሱን አብራርተዋል፡፡

365 ምርትና አገልግሎቶች ለደንበኞች የቀረቡ ሲሆን÷ ከእነዚህ ውስጥም 134ቱ አዳዲስ፤ 157 የሚሆኑት ደግሞ ማሻሻያ የተደረገባቸው ናቸው፡፡

በበጀት ዓመቱ 462 ሺህ የሳይበር ጥቃት ሙከራ መደረጉን ጠቅሰው ÷ በተገነባው የሳይበር ሴክዩሪቲ አሰራርም ሙከራዎችን ማክሸፍ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡



አዋሽ ባንክ ከ22 ቢሊዮን በላይ ብር አተረፈ። #ኤቫ ሚዲያአዋሽ ባንክ ከ22 ቢሊዮን በላይ ብር ማትረፉን አስታወቀ።ባንኩ የ2024/25 የስራ አፈጻጸሙን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።መግለጫውን...
02/07/2025

አዋሽ ባንክ ከ22 ቢሊዮን በላይ ብር አተረፈ።

#ኤቫ ሚዲያ
አዋሽ ባንክ ከ22 ቢሊዮን በላይ ብር ማትረፉን አስታወቀ።

ባንኩ የ2024/25 የስራ አፈጻጸሙን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጸሃይ ሽፈራው እንደገለጹት፤ ባንኩ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻውን መሰረት የተለያዩ አሰራሮች ላይ ለውጥ አድርጎ ሲሰራ ቆይቷል።

በዚህም ዓመቱ በርካታ ስራዎች የተሰሩበትና ለባንኩ ውጤታማ የሆነ ዓመት ነው ብለዋል።

52 አዳዲስ ቅርንጫፎች መከፈታቸው ገልጸው፤ አጠቃላይ የቅርጫፎቹን ቁጥር 989 ማድረስ ተችሏል ነው ያሉት።

እንዲሁም ሶስት ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞች ባንኩን መቀላቀላቸውንና አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር ከ15 ሚሊዮን በላይ ማድረሱን ተናግረዋል።

የዲጂታል ተደራሽነትን ለማሳደግ በተሰራ ስራ አንድ የትሪሊዮን የሚጠጋ ብር በዲጂታል ተዘዋውሯል ያሉት ስራ አስኪያጁ፤ ባንኩ ከሚሰጠው 77 በመቶ የሚሆነው አገልግሎት በዲጂታል እየተሰጠ ነው ብለዋል።

የባንኩን ተቀማጭ ገንዘብ ለማሳደግ በተሰራ ስራም የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ 106 ቢሊዮን ብር ደርሷል።

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ42 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ገልፀዋል።

ከወለድ ነጻ የሆነ የባንክ አገልግሎት ተቀማጭ ገንዘብ 37 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መሆኑንም ተናግረዋል።

ስራ አስኪያጁ ባንኩ በዓመቱ መጨረሻ ከታክስ በፊት 22 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር አትርፏል ብለው፤ በዚህ ዓመት ብቻ 7 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የካፒታል እድገት መመዝገቡን ገልፀዋል።
#አዋሽባንክ

02/07/2025
ተጨማሪ ጉርሻ !ውድ ደንበኛችን ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ወርልድ ሬሚት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከ...
01/07/2025

ተጨማሪ ጉርሻ !
ውድ ደንበኛችን ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ወርልድ ሬሚት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!
አቢሲንያ
የሁሉም ምርጫ!
የባንካችን ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች
Facebook: https://lnkd.in/eHmPTGdR Instagram: https://lnkd.in/dRwfk_P5 LinkedIn: https://lnkd.in/etnBf_r5 Twitter: https://lnkd.in/ecxYNgf Website: https://lnkd.in/ei3nRNA Tikok: https://www.tiktok.com/?_t=ZM-8xInZoUoBRo&_r= Telegram: https://t.me/BoAEth

የብሄራዊ ባንክ ዛሬ ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ በአማካኝ አንድ ዶላር 131.70 ብር ተሸጠ።ባንኩ በየ15 ቀናት አወጣዋለው ባለው የውጭ ምንዛሬ በጨረታ የመሸጥ አሰራር መሰረት ዛሬ 50 ሚ...
01/04/2025

የብሄራዊ ባንክ ዛሬ ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ በአማካኝ አንድ ዶላር 131.70 ብር ተሸጠ።

ባንኩ በየ15 ቀናት አወጣዋለው ባለው የውጭ ምንዛሬ በጨረታ የመሸጥ አሰራር መሰረት ዛሬ 50 ሚሊየን ዶላር ባንኮች እንዲገዙ አቅርቦ ነበር።

በዚህም 12 ባንኮች የውጭ ምንዛሬውን መከፋፈል እንደቻሉ ነው ብሄራዊ ባንክ ያስታወቀው።

ከአንድ ወር በፊት 60 ሚሊየን ዶላር ለጨረታ ቀርቦ በአማካኝ 135.6 ብር ለአንድ ዶላር መግዣ ቀርቦ ነበር።

ዛሬ በወጣው ጨረታ የቀረበው አማካኝ ዋጋ ካለፈው አንፃር የ 3 በመቶ አካባቢ ቅናሽ የታየበት ነው።

ሰኞ ብሄራዊ ባንክ ከባንክ መሪዎች ጋር ባደረገው ስብሰባ የውጭ ምንዛሬ ህጎች እንዲከበሩ አስጠንቅቆ ነበር።

በተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ግብይት ላይ የሚታሰብ ኮሚሽን እና የአገልግሎት ክፍያ እንዳይጋነን ነው ባንኮችን ያሳሰበው።

ባንኮች በቀደመው ጨረታ ከፍ ያለ ዋጋ ማቅረባቸው መወያያ ሆኖ ነበር።

ባሳለፍነው ሳምንት የተሰበሰበው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴም የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው መግለፁ አይዘነጋም።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መደበኛና ተከታታይ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ሊያወጣ ነው።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንቱ መደበኛና ተከታታይ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ሊያወጣ መሆኑን አስታወቀ፡፡ባን...
31/03/2025

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መደበኛና ተከታታይ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ሊያወጣ ነው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንቱ መደበኛና ተከታታይ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ሊያወጣ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ባንኩ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ÷ ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንት መደበኛ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታ ማካሄድ እንደሚጀምር ገልጿል፡፡

ጨረታዎቹም ለሚቀጥሉት በርካታ ወራት እንደሚካሄዱ ያመላከተ ሲሆን÷ዓላማውም የማዕከላዊ ባንኩን የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት ግብን ለማሳካት ነው ብሏል፡፡

የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ከተጀመረ ወዲህ የወጪ ንግድ በመስፋፋቱ፣ የውጭ ሐዋላ በመጨመሩና የካፒታል ፍሰት በማደጉ ምክንያት የኢትዮጵያ የውጭ ክፍያ ሚዛን በከፍተኛ ደረጃ የመሻሻል አዝማሚያማሳየቱ ተጠቁሟል፡፡

የማዕከላዊ ባንኩ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በታሪኩ ከፍተኛው መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው÷ በሀገሪቱ ውስጥ ብቸኛው የወርቅ ገዢ ለሆነው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቀረበው የወርቅ መጠን ከፍተኛ መሆን የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት ከተገመተው በላይ እንዲጨምር ማድረጉን አንስቷል፡፡

ከዚህ ከተጠበቀው በላይ ከሆነው የውጭ ምንዛሪ ግኝት አንጻር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቀጣይ ወራት በመደበኛነት በየሁለት ሳምንቱ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታዎችን ለማካሄድመወሰኑን ነው የተገለጸው፡፡

ይህ አካሄድ በማዕካላዊ ባንክ እየተከማቸ ካለው የውጭ ምንዛሪ የተወሰነውን መጠን ለግሉ ዘርፍለማቅረብና የማዕከላዊ ባንኩን የገንዘብ ፖሊሲ ዓላማ ለማሳካት እንደሚያግዝ ተመላክቷል፡፡

የውጭ ምንዛሪ ጨረታው የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማረጋጋትና ሪፎርሙ ከተጀመረ ወዲህ መሻሻል እያሳየ የመጣውን የውጭ ክፍያ ሚዛን በይበልጥ ለማጠናከር እንደሚረዳ ታምኖበታል ተብሏል፡፡

በመሆኑም ፍላጎቱ ያላቸው ባንኮች በተሰጠው የጊዜ ሰሌዳና በተቀመጠው አካሂድ መሰረት የጨረታ ሰነዶቻቸውን እንዲያስገቡ ባንኩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ለጨረታ የቀረበው የውጭ ምንዛሪ መጠን 50 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን÷ ጨረታው ማክሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተመላክቷል፡፡

27/01/2025

&marketing
#0904341787

27/01/2025

Address

Addis Ababa

Telephone

+251912706059

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ETHIO ገበያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ETHIO ገበያ:

Share