Oeiryt Consultancy Services

Oeiryt  Consultancy Services Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Oeiryt Consultancy Services, Consulting Agency, Nifasil Lafto Sub city Wereda 01, Addis Ababa.

Oeiryt Consultancy Services is Ethiopian based firm which provides Business, Investment and Quality consultancy based on international standard (ISO) to manufacturer and service provider.

ብሔራዊ ባንክ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚገኙ ህገወጥ የገንዘብ አስተላላፊዎችን አስጠነቀቀ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መቀመጫቸውን በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (ዱባይ) ያደረጉ ድርጅቶች መደበ...
08/08/2025

ብሔራዊ ባንክ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚገኙ ህገወጥ የገንዘብ አስተላላፊዎችን አስጠነቀቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መቀመጫቸውን በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (ዱባይ) ያደረጉ ድርጅቶች መደበኛውን ገበያ ያፈነገጠ የትይዩ ገበያውን የሚያስፋፉ ህገወጥ ድርጊቶች እንዳሉ ገልጿል። ባንኩም እነዚህን ድርጊቶች ለመግታት አስቸኳይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ በወቅታዊ የውጭ ምንዛሪ ገበያ እንቅስቃሴን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ፤ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ስርዓት ሆን ብለው ለመሸርሸር እና የገበያ ዋጋን ለማዛባት በማለም በውጭ ሀገር የሚገኙ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ላይ የሚወሰደው እርምጃ እንደሚቀጥል በጥብቅ አሳስበዋል።

ማዕከላዊ ባንኩ በህገወጥ መንገድ ኢ-መደበኛ ገበያን የሚጠቀሙ አካላት ከዚህ ድርጊታቸው ካልተቆጠቡ "ገንዘባቸውን እስከመውረስ" የሚደርስ እርምጃ እወስዳለሁ ማለቱን ካፒታል ከመግለጫው ተመልክቷል።

በተጨማሪም፣ የባንክ ስርዓቱን የማይጠቀሙ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በአፋጣኝ ወደ ባንክ ስርዓቱ እንዲገቡ በጥብቅ አሳስቧል።

ይህ እርምጃ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የፋይናንስ ስርዓት ለማረጋጋት እና የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን ለመቆጣጠር የሚያደርገው ጥረት አካል መሆኑም ተመላክቷል።

Source: capitalethiopia

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2017 ዓ.ም. ከኃይል ሽያጭ 75.4 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2017 የበጀት ዓመት ከኃይል ሽያጭ እና ተያያዥ አገልግሎቶች በድምሩ ...
07/08/2025

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2017 ዓ.ም. ከኃይል ሽያጭ 75.4 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2017 የበጀት ዓመት ከኃይል ሽያጭ እና ተያያዥ አገልግሎቶች በድምሩ 75.4 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል። ይህ አጠቃላይ ገቢ 338.7 ሚሊዮን ዶላር እና 28.52 ቢሊዮን ብርን ያካተተ መሆኑን ተቋሙ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

የቋሙ በበጀት ዓመቱ ውስጥ 25.18 ቴራ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል የሸጠ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ አብዛኛው (93%) ለሀገር ውስጥ አገልግሎት የዋለ ነው። ቀሪው 7% ደግሞ ለጎረቤት ሀገራት መሸጡ ተገልጿል።

ለሀገር ውስጥ ከተሸጠው ኃይል 60% ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፣ 27% ለዳታ ማይኒንግ ፣ 6% ለተለያዩ ኢንዱስትሪዎች መቅረብን አመልክቷል።

በሌላ በኩል 5% የኤሌክትሪክ ኃይል ለኬንያ እንዲሁም 2% ለጅቡቲ መሸጡን ሪፖርቱ ያሳያል። ከጠቅላላው የገቢ መጠን ውስጥ፣ 74.05 ቢሊዮን ብር የተገኘው ከኃይል ሽያጭ ሲሆን፣ 1.41 ቢሊዮን ብር ደግሞ ከተጓዳኝ አገልግሎቶች መሆኑን ካፒታል ከመግለጫው ተከታትሏል።

source; CapitalNews

ኢትዮጵያ በማዕድን ኢንቨስትመንት ማራኪነት በአለም የመጨረሻ ደረጃ ላይ ተቀመጠች በካናዳው "Fraser Institute" የተዘጋጀው የ2024 ዓመታዊ የማዕድን ኩባንያዎች ጥናት፣ ኢትዮጵያ በማ...
05/08/2025

ኢትዮጵያ በማዕድን ኢንቨስትመንት ማራኪነት በአለም የመጨረሻ ደረጃ ላይ ተቀመጠች

በካናዳው "Fraser Institute" የተዘጋጀው የ2024 ዓመታዊ የማዕድን ኩባንያዎች ጥናት፣ ኢትዮጵያ በማዕድን ኢንቨስትመንት ማራኪነት ደረጃ ከአለም መጨረሻ ላይ መቀመጧን አመላክቷል። ጥናቱ 82 ሀገራትን ገምግሞ ለኢንቨስትመንት ማራኪ የሚያደርጉ የፖሊሲ መረጋጋት እና ግልጽነት ላይ ችግሮች እንዳሉ በመጠቆም ኢትዮጵያን ከሁሉም በታች አስቀምጧታል።

የኢንቨስትመንት ማራኪነት ደረጃው የሀገሪቱን የጂኦሎጂካል አቅም ከመንግስት የፖሊሲ ማዕቀፎች ጋር በማጣመር የሚሰላ ነው። ምንም እንኳን ኢትዮጵያ በሀብት የበለፀገች ብትሆንም፣ ደካማ የፖሊሲ አሰራር ኢንቨስተሮችን እያራቀ መሆኑን ጥናቱ ያሳያል።

ጥናቱ እንደ የግብር አወሳሰን፣ የህግ ስርዓት እና የፖለቲካ መረጋጋት ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮችን የሚገመግም ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በዚህ ምድብ ውስጥ ካሉ 10 ዝቅተኛ ደረጃ ከተሰጣቸው ሀገራት ውስጥ አንዷ ነች።

የጥናቱ ተሳታፊዎች እንደገለጹት፣ የማዕድን ሀብት መሠረታዊ ቢሆንም፣ 40% ያህሉ የኢንቨስትመንት ውሳኔዎች የሚወሰኑት በፖሊሲ አሰራር ላይ ነው። ይህም ግልፅ ደንቦች፣ የፖለቲካ መረጋጋት እና ፍትሃዊ የህግ ማዕቀፎች የማዕድን ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆኑ ያመለክታል።

ሪፖርቱ ኢትዮጵያ የፖሊሲ ክፍተቶቿን ካልሞላች፣ ኢንቨስትመንቶች ግልጽ እና ባለሀብት ወዳድ ወደሆኑ ሀገራት ሊዞሩ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል።

Read More

Source: capitalethiopia

ለችግር ጊዜ ተብለው ለኢትዮጵያ የሚሰጡ የገንዘብ እርዳታዎች የዋጋ ንረትን እንዲያባብሱ እንደሚያደርግ አንድ ሪፖርት አመለከተ ለችግር ጊዜ ተብለው ለኢትዮጵያ የሚሰጡ የገንዘብ እርዳታዎች የዋጋ...
01/08/2025

ለችግር ጊዜ ተብለው ለኢትዮጵያ የሚሰጡ የገንዘብ እርዳታዎች የዋጋ ንረትን እንዲያባብሱ እንደሚያደርግ አንድ ሪፖርት አመለከተ

ለችግር ጊዜ ተብለው ለኢትዮጵያ የሚሰጡ የገንዘብ እርዳታዎች የዋጋ ንረትን እንዲያባብሱ በማድረግ የድሆችን የኑሮ ሁኔታ የበለጠ እያወሳሰቡት እንደሆነ፣ የ2025 "የዓለም የምግብ ዋስትና እና የተመጣጠነ ምግብ ሁኔታ ሪፖርት አመላከተ።

ይህ ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ የእርዳታ ገንዘቦች የሀገር ውስጥ የምግብ አቅርቦት ውስን በሆነበት ወቅት ወደ ገበያ ሲገቡ፣ የዋጋ ግሽበት እንዲጨምር ምክንያት ይሆናሉ።

በዚህ ሳምንት ይፋ የሆነዉ ይህ ሪፖርት እንደ ምሳሌ የጠቀሰው የኢትዮጵያ ምርታማ የሴፍቲ ኔት ፕሮግራም የሰጠው የገንዘብ ድጋፍ የዋጋ ግሽበትን በመጨመር የድሆችን የመግዛት አቅም እንደቀነሰ ነው።

ይህ ደግሞ በምግብ ዋስትና እጦት እና በጤናማ ምግብ ዋጋ ንረት እየተሰቃየች ባለችው ኢትዮጵያ ላይ ተጨማሪ ጫና ፈጥሯል።

በተመሳሳይ መልኩ እንደተጠቀሰዉ ፤ ኢትዮጵያ በ2024 ዓ.ም. ከፍተኛ የምግብ እጥረት ካለባቸው አምስት ሀገራት አንዷ ነበረች። ከዚህም በላይ፣ የጤናማ ምግብ ዋጋ ከ2017 ዓ.ም. ጀምሮ ከ$2.94 ወደ $4.47 ማደጉ፣ በተለይም ውስን ገቢ ያላቸውን ዜጎች ጤናማ ምግብ ማግኘት ከባድ ፈተና ውስጥ እንደከተታቸው ሪፖርቱ ያሳያል።

ይህንን ችግር ለመፍታት የገንዘብ እርዳታን ከምግብ ዋጋ ጋር ማስተሳሰር ወይም ቀጥተኛ የምግብ እርዳታ መስጠት የበለጠ ውጤታማ እንደሆነ ይመክራል። በተጨማሪም፣ ዘላቂ የግብርና ስርዓቶችን መገንባት እና የዋጋ መረጋጋትን የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎችን መተግበር ዘላቂ መፍትሔዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ይጠቁማል።

Source CapitalNews

አሃዱ ባንክ ከ2.1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ይፋ አደረገአሃዱ ባንክ ከ2.1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በማስመዝገብን ያስታወቀ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ...
30/07/2025

አሃዱ ባንክ ከ2.1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ይፋ አደረገ

አሃዱ ባንክ ከ2.1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በማስመዝገብን ያስታወቀ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ1 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ወይም የ90.9 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ገልጿል።

የባንኩ አጠቃላይ ትርፍ የእርጅና ቅናሽ እና ተያያዥ ወጪዎችን ጨምሮ፣ ለመጠባበቂያ ከተቀመጠው እና ከግብር በፊት 569 ሚሊዮን ብር ማትረፉን በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው ትርፍ በ450 ሚሊዮን ብር ብልጫ ያለው ሲሆን፣ የ278.1 በመቶ እድገት አስመዝግቧል።

የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ 7.8 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው የሒሳብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ68 በመቶ ዕድገት በማሳየቱና በውጭ ምንዛሪ ገቢ ረገድም ከ88 ሚሊዮን ዶላር በላይ መሰብሰብ መቻሉን አስረድተዋል።

የደንበኞች ቁጥር 1.1 ሚሊዮን መድረሱን የገለፀው ባንኩ አጠቃላይ ሀብቱ ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ በማድረስ የ57 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን አስታውቋል።

Source: capitalethiopia

ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ ክልል 4ሺህ 700 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማስገባቱ ተገለጸከሌሎች ማዕድን ምርት 49 ሚሊዮን ብር መሰበሰቡም ተገልጿልቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017 በጀት ዓመት ...
29/07/2025

ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ ክልል 4ሺህ 700 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማስገባቱ ተገለጸ

ከሌሎች ማዕድን ምርት 49 ሚሊዮን ብር መሰበሰቡም ተገልጿል

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017 በጀት ዓመት 1ሺህ 500 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ ለማስገባት አቅዶ 4ሺህ 700 ኪሎ ግራም ወርቅ ማስገባቱን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ አድማሱ ሞርካ፤ ከዕቅዱ በላይ የተከናወነበት ምክንያት መንግስት ለወርቅ አቅራቢዎች ያደረገው “ማበረታቻ እና ህገ-ወጥ ግብይት” መቀነስ ትልቅ አስተዋፅኦ ነበራቸው ሲሉ ለኢዜአ ተናግረዋል።

በተለይም በሀገር አቀፍ ደረጃ በተተገበረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ዘርፉ እንዲነቃቃና አምራቹ ተጠቃሚ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቅሰዋል።

በክልሉ የተመረተው ወርቅ በአነስተኛና ባህላዊ ወርቅ አምራቾች መሆኑን ገልጸው፤ ይህም የህብረተሰቡን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አሳድጓል ነው ያሉት።

ከወርቅ በተጨማሪ የድንጋይ ከሰልና እምነበረድ በስፋት እየተመረተ መሆኑን ጠቅሰው በክልሉ የሚገኙ የማዕድን ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።

አቶ አድማሱ ከማዕድን ምርቱ 49 ሚሊዮን ብር መሰበሰቡንም ጠቅሰው፤ በቀጣይ ትላልቅ ካምፓኒዎችን በመጋበዝ በክልሉ በማዕድን ዘርፍ ለማሰማራት ዝግጅት መጠናቀቁንም አስታውቀዋል።

Source: addisstandardamharic

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፈው የበጀት ዓመት 162 ቢሊዮን ብር ገቢ ማስመዝገቡን አሰታወቀ ኢትዮ ቴሌኮም በቅርቡ ባጠናቀቀው የበጀት ዓመት 162 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማስመዝገብ የእቅዱን 99%...
25/07/2025

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፈው የበጀት ዓመት 162 ቢሊዮን ብር ገቢ ማስመዝገቡን አሰታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም በቅርቡ ባጠናቀቀው የበጀት ዓመት 162 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማስመዝገብ የእቅዱን 99% ማሳካቱን አስታወቀ። ይህ ካለፈው የበጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ72.9% ዕድገትን ያሳያል።

ኩባንያው ይህንን ያስመዘገበው የተለያዩ የንግድ አማራጮችን በመተግበር፣ የደንበኞችን ቁጥር በማሳደግና በማቆየት እንዲሁም ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የፈሰሰባቸውን የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎች በማስፋፋትና በማጠናከር መሆኑን ጠቁሟል።

ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 213.6 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማግኘቱን አስታውቋል፤ ይህም የእቅዱን 84.3% ያሳካ ነው። ይህ አፈፃፀም ካለፈው የበጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ15.44 ሚሊዮን ዶላር (7.8%) ጭማሪ አሳይቷል።

ከተገኘው የውጭ ምንዛሪ ውስጥ 193.11 ሚሊዮን ዶላር ከአለም አቀፍ አገልግሎት የተገኘ ሲሆን፣ 66.6 ሚሊዮን ዶላር ከአለም አቀፍ የትራንዚት ትራፊክ፣ 5.62 ሚሊዮን ዶላር ከመሠረተ ልማት ማጋራት ኪራይ (Infrastructure sharing) የተገኘ ሲሆን፣ ከ14.42 ሚሊዮን ዶላር በላይ ደግሞ በቴሌብር ዓለም አቀፍ የሐዋላ አገልግሎት አማካኝነት ወደ ሀገር ውስጥ የገባ የውጭ ምንዛሪ መሆኑ ተገልጿል።

Source CapitalNews

አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ተግባራዊ መደረግ ተጀመረየገቢዎች ሚኒስትር እንዳስታወቀው አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ከ ሐምሌ 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን ባወጣው ሰርኩላር አስታው...
22/07/2025

አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ተግባራዊ መደረግ ተጀመረ

የገቢዎች ሚኒስትር እንዳስታወቀው አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ከ ሐምሌ 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን ባወጣው ሰርኩላር አስታውቋል።

ይህን ተከትሎ የገንዘብ ሚኒስትር 300 % ጭማሪ ተደርጎበታል ያለዉን ከመቀጠር የሚገኝ ገቢን ጨምሮ የኪራይ ገቢ ግብር ምጣኔ እና የንግድ ሥራ ግብር በአዋጅ ቁጥር 1395/2017 መሰረት እንደሚተገበር አሳስቧል።

Source CapitslNews

ቶምቦላን ጨምሮ በሚደረጉ የዕድል ሙከራ ገቢዎች ላይ የተጣለው ግብር ወደ 20% ከፍ አለበኢትዮጵያ የዕድል ሙከራ ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ ገቢ የሚያገኙ ሰዎች ከሚያገኙት ጠቅላላ ገቢ ላይ የሚከፍ...
19/07/2025

ቶምቦላን ጨምሮ በሚደረጉ የዕድል ሙከራ ገቢዎች ላይ የተጣለው ግብር ወደ 20% ከፍ አለ

በኢትዮጵያ የዕድል ሙከራ ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ ገቢ የሚያገኙ ሰዎች ከሚያገኙት ጠቅላላ ገቢ ላይ የሚከፍሉት የገቢ ግብር መጠን ወደ 20% (ሃያ በመቶ) ከፍ ማለቱን አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ላይ ካፒታል ተመላክቷል።

ይህ ጭማሪ ቀደም ሲል በ2008 ዓ.ም. በወጣው የገቢ ግብር አዋጅ ከተደነገገው 15% የግብር ምጣኔ የጨመረ ነው።

በተሻሻለው አዋጅ መሰረት፣ በዕድል ሙከራ አሸናፊነት የተገኘው ገቢ ሲሰላ፣ ገቢውን ያገኘው ሰው ዕድሉን ለማግኘት ያወጣው ወይም የደረሰበት ማንኛውም ኪሳራ ከታክስ የሚቀነስ አይሆንም። ይህ ማለት አሸናፊዎች የሚያገኙት ጠቅላላ ገቢ ምንም አይነት ቅናሽ ሳይደረግበት ለግብር ተገዢ ይሆናል ማለት ነው።

"የዕድል ሙከራ" ተብሎ ሲገለጽ፣ የጨዋታው ውጤት በተሳታፊው ችሎታ ላይ ሳይሆን በዋነኝነት በዕድል ላይ የተመሰረተ ጨዋታን ያመለክታል። ይህ ትርጉም ሎተሪንና ቶምቦላን የመሳሰሉ የዕድል ጨዋታዎችን ያካትታል።

ይህ አዲሱ የግብር ምጣኔ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄዱ የዕድል ሙከራ ጨዋታዎች ላይ ለሚሳተፉ እና ገቢ ለሚያገኙ ሁሉ ተፈጻሚ ይሆናል።

Source CapitalNews

አስተዳደሩ መዲናዋን ከጎበኙ "አንድ ሚሊየን በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች 143 ቢሊየን ብር አግኝቻለሁ" አለበአዲስ አበባ በበጀት ዓመቱ በተካሄዱ ኮንፈረንሶች እና ከተማዋን ከጎበኙ "ከ1 ሚሊዮን...
14/07/2025

አስተዳደሩ መዲናዋን ከጎበኙ "አንድ ሚሊየን በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች 143 ቢሊየን ብር አግኝቻለሁ" አለ

በአዲስ አበባ በበጀት ዓመቱ በተካሄዱ ኮንፈረንሶች እና ከተማዋን ከጎበኙ "ከ1 ሚሊዮን በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች 143 ቢሊዮን ብር መገኘቱን" የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡

ከንቲባ አዳነች የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም አስመልክተው ለከተማዋ ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት የኮሪደር ልማቱ የአዲስ አበባ ከተማን ገጽታ እየቀየረ በመሆኑ ከተማዋ የስበት ማዕከል ሆናለች ሲሉ አንስተዋል፡፡

በዚህም በርካታ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች በአዲስ አበባ እየተካሄዱ መሆናቸውን የገለጹት ከንቲባዋ፤ አክለውም በከተማዋ በተካሄዱ ኮንፈረንሶች እና ከተማዋን ከጎበኙ "ከ1 ሚሊዮን በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች 143 ቢሊዮን ብር መገኘቱን" ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም ከገቢ ባሻገር የገጽታ ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ "አዲስ አበባ ባስመዘገበችው ውጤት በዓለም አቀፍ የከተሞች ኮንፈረንስ ከ115 አቻ ከተሞች መካከል ቀዳሚ ሆና መነሳቷን እንዲሁም የአፍሪካ ስማርት ሲቲ አሸናፊ መሆኗን" ጠቁመዋል፡፡

በከተማዋ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማትም የሥራ ባሕል አፈጻጻም እና ትብብር የተማርንበት፤ ለብዙ ሺህዎች የሥራ ዕድልን የፈጠረ እና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ያደገበት እንደሆነ መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

Source: addisstandardamharic

የጸደቀው የጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች አዋጅ በፍጥነት ተግባራዊ እንዲሆን ተጠየቀበቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው የጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች አዋጅ ተግባራዊ ሳይሆን መቆየቱ፣ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ከ...
07/07/2025

የጸደቀው የጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች አዋጅ በፍጥነት ተግባራዊ እንዲሆን ተጠየቀ

በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው የጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች አዋጅ ተግባራዊ ሳይሆን መቆየቱ፣ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ኢንተርፕራይዞች እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ቢዝነስ አማካሪ አገልግሎት ሰጪዎች ማኅበር እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መመሪያው በአስቸኳይ ወደ ተግባር እንዲገባና ለሚያስፈጽሙ አካላትም ግንዛቤ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

የማህበሩ ዋና ጸሐፊ :መመሪያው ባለመኖሩ በርካታ ሥራ ፈጣሪዎች ገና በጅምር እንዲጠፉ ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል። ይህ አዋጅ የሥራ ፈጣሪዎችን የፋይናንስ እጥረት፣ የሕግ ግልጽነት ማጣት እና ያልዳበረ የመሠረተ ልማት ችግሮችን ለመፍታት ያለመ እንደሆነም አስረድተዋል።

የብሩህማይንድ ኮንሰልታንት መስራችና ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ደሳለኝ በበኩላቸው፣ የጀማሪዎች ዋነኛ ችግር የመነሻ ካፒታል እጥረት መሆኑን ጠቁመዋል።

አቶ ሰለሞን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (SMEs) ፋይናንስ የሚያገኙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እና ከአበዳሪ ድርጅቶች ጋር ለማገናኘት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

"ፖሊሲ አድቮኬት ነው የምናደርገው" ያሉት አቶ ሰለሞን፣ የተግዳሮቶቹ እንዲታዩ እና በተለይም SMEs የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ይህን ፕሮግራም በሰፊው እንደነደፉት አስረድተዋል።

ለወጣቶች የቢዝነስ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በጋራ እየሰሩ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በቅርቡ በተካሄደ የሶስት ቀናት አውደ ርዕይ ላይም 40 ተሳታፊዎች እና ከ4000 በላይ ጎብኚዎች የተገኙ ሲሆን፣ የፋይናንስ ተቋማትና የመንግስት አካላትም ተሳትፈው ነበር።

Source: capitalethiopia

Address

Nifasil Lafto Sub City Wereda 01
Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251901110086

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Oeiryt Consultancy Services posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Oeiryt Consultancy Services:

Share