Sophonias simachew

Sophonias simachew Choose your way.

AWASH
08/08/2022

AWASH

17/10/2020

በተደጋጋሚ ካርቱም፣ ሱዳን ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን

"በካርቱም የሚገኙ ኢትዮጵያን በመታወቂያ ምክንያት በብዛት እየታፈሱ እስር ቤት እየታጎሩ ይገኛሉ። ለመቀጫ እየተባለ መቶ ሺህ የሱዳን ጅኔ ወይም ስድስት ወር እየተፈረደባቸው ነው። ፖሊሶቹ ስልክ እና ገንዘብ ይዘርፋሉ፣ ሴቶች ላይም ወሲባዊ ጥቃት ያደርሳሉ። መንግስት እና ሰብአዊ ድርጅቶች እንዲደርሱልን ጋዜጠኞች አሳውቁልን።"

17/10/2020

ጅማ ዩንቨርስቲ ከቀናት በኋላ የሚቀበላቸውን ተማሪዎች በሁለት ወር ውስጥ እንደሚያስመርቅ አስታወቀ።

የዩንቨርሲቲው ምክትል ፕሬዘዳንት ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ከቀናት በኋላ 4 ሺህ ተመራቂ ተማሪዎችን ይቀበላል።

ኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ የገባው ተማሪዎቹ አንድ ሴሚስተር ሲቀራቸው በመሆኑ መመረቅ የሚያስችላቸውን የአራት ወራት ትምህርት በሁለት ወር ውስጥ መስጠት የሚያስችል ስርዓተ ትምህርት ተዘጋጅቶ መጠናቀቁንም ዶክተር ቀነኒሳ ነግረውናል።

ተማሪዎቹ በኮሮና ቫይረስ እንዳይጠቁ የመማሪያ ክፍሎችን፣ ቤተ መጽሀፍት፣መመገቢያ እና መዝናኛ ስፍራዎች አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መንገድ ማከናወን የሚያስችል የቁሳቁስ እና የሰው ሀይል በሚገባ ዝግጅት መደረጉን ምክትል ፕሬዘዳንቱ ገልጸዋል።

ይህ ሁሉ ዝግጅት ተደርጎም በቫይረሱ የሚጠቁ ተማሪዎች ቁጥር ከጨመረ ህክምና ማካሄድ የሚያስችል ዝግጅቱም ከበቂ በላይ ተዘጋጅተናልም ብለዋል።

ባንድ ክፍል ውስጥ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎችን ከ20-25 ከማድረግ በተጨማሪ ትምህርታቸውን በኦንላየን መከታተል የሚያስችል ዝግጅት ማድረጋቸውንም ዶክተር ቀነኒሳ ተናግረዋል።

ዩንቨርሲቲው ኮሮና ቫይረስ ከመግባቱ በፊት 47 ሺህ ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መስኮች በማስተማር ላይ የነበረ ሲሆን 4 ሺህ ያህሉ ተመራቂ ተማሪዎች ናቸው።

እነዚህ ተመራቂ ተማሪዎች የሚመረቁበት ቀን የዩንቨርሲቲው ሴኔት በቀጣይ በሚያስቀምጠው ውሳኔ መሰረት ይታወቃል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23-30 የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች ቅበላ እንደሚያደርጉ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል።
(ethio fm)

17/10/2020

የሰራተኞች እሮሮ
ለኢትዮጵያን ዲጄ የደረሰው መረጃ:- እንደወረደ አቅርበነዋል ..

“ንግድ ባንክ ሰራተኛ በግዴታ የገበታ ለሐገር መዋጮ አዋጡ እየተባልን ነው፡፡ የወር ደሞዛችንን በሁለት ዓመት ተከፍሎ በሚያልቅ ክፍያ ስጡ ተብለናል፣ ችግሩ በሚድያ ሲገለፅ በስምምነት ላይ የተመሰረተ ነው መባሉ ነው። ይህ ስህተት ነው፣ በማናጀሮች ካላዋጣችሁ እድገት ቢመጣ ላታገኙ ትችላላችሁ ወዘተ እየተባልን ነው፡፡ፕሮጀክቱ ሀገራዊ ስለሆነ ብዙ ሰራተኛ በፈቃደኝነት ሊሳተፍ ይችላል፣ እየሆነ ያለው ግን በተቃራኒው ነው። 'አዋጣለሁ' ወይም 'አላዋጣም' የሚል ፎርም ሙሉ ተብለህ 'አላዋጣም' ብትል የሚከተለውን መገመት ይቻላል። በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ቢሆን ኖሮ ፈቃደኛ የሆናችሁ ብቻ ፎርም ሙሉ ይባል ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የባንኩ ሰራተኛ ማህበር ሰራተኛው በግዴታ ማዋጣት የለበትም በሚል ከማሕበሩ አካውንት 10 ሚሊየን ብር ለመስጠት ፍቃደኛ ቢሆንም የባንኩ ማኔጅመንት ግን ሁሉም ሰራተኛ መሰተፍ አለበት በሚል ሰበብ ሰራተኛውን እያዋከቡ ነው፡፡
1. አብዛኛው ሰራተኛ በቤት ኪራይ የሚኖር የተወሰነውም ቢሆን ቤት የገዛ እና የደሞዙ ½ የሚቀነስበት ሆኖ ሳለ
2. ከፍተኛ የኖሩ ውድነት እና ግሽፈት ባለበት
3. ትምህርት የሚማር ቤተሰብ የሚያስተዳድር ሰራተኛ ባለበት ሆኔታ በወር ከ 1000 ብር ጀምሮ ለሁለት ዓመት ክፈሉ ማለት ስዕተት ነው “

17/10/2020

የአምበጣ ውረርሽ፤
~~~~~~~~~~~~
በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የበረሃ አንበጣ በደረሱ ሰብሎች እና በአርብቶ አደሩ የግጦሽ ሳር ላይ እያደረሰ ያለውን ውድመት ለመከላከል የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።

የተፋሰሶች ልማት ከፍተኛ ምክር ቤት 8ኛ መደበኛ ጉባዔውን በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ጉባኤ አዳራሽ ተካሂዷል።

የጉባኤው ዋነኛ ትኩረትም የአደጋ ምላሽ አሰጣጥ፣ የጎርፍ አደጋንና የእምቦጭ አረምን ማስወገድ ላይ ያተኮረ ነው።

የተፋሰሶች ልማት ከፍተኛ ምክር ቤት ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ የተከሰተው የበረሃ አንበጣ በተለይ በደረሱ ሰብሎች እና በአርብቶ አደሩ የግጦሽ ሳር ላይ ላይ ከፍተኛ ውድመት እያስከተለ ይገኛል ~ ብለዋል።

የአንበጣ ወረርሽኝ በአጭር ጊዜ ለመቆጣጠጥ ከህዝቡ የመከላከል አቅም ጋር በማቀናጀት የተጀመረው ርብርቡ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ሁሉአቀፍ ጥረቶች በየአከባቢው እየተደረጉ ቢሆንም የአምበጣው ወረርሽ ከቁጥጥር ውጭ እንዳይወጣ እንዲሁም በከፋ ደረጃ እንዳይስፋፋ በመረጃ ላይ የተመሰረተ እርምጃ መውሰድ እንደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡

በሃገር ውስጥ ካለው አቅም በተጨማሪ ከውጭ በሚገቡ ድጋፍ ሰጪ አውሮፕላኖች በመታገዝ የኬሚካል ርጭቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡

ችግሩ በስፋት በተስተዋለባቸው አካበቢዎች ለሚኖሩ ዜጎች የዕለት ደራሽ ዕርዳታ የማከፋፈል እና የመልሶ ማልማት ስራ በየደረጃው ባለው አመራር አካላት በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡

በቀጣይ በሃገር ደረጃ መሰል አደጋዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚያሥችል ጠንካራ አቅም የመገንባት ጉዳይ በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ በጣና ሃይቅ ላይ የተንሰራፋውን የእምቦጭ አረም ለማስወገድ በሚጀመረው ሃገር አቀፍ ንቅናቄ ሁሉም ድጋፉን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

በጎርፍ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ የማቋቋም ስራዎች ተገቢ ትኩረት ተሰጥቶ በፍጥነት ምላሽ የመስጠት ጉዳይ ሰፊ ውይይት ተደርጎበት አቅጣጫ ተቀምጧል።

17/10/2020

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራበት ዛሬ ሀገርአቀፍ ምክክር ተደርጓል። በክልሉ መተከል ዞን በተደጋጋሚ ለሚፈጸም ጥቃት ሕወሓት አጥፊዎቹን በመመልመል እና በመደገፍ እንዲሁም በክልሉ የኢንቨስትመንት መሬት ወስደው ሳያለሙ የቀሩ "ባለሀብቶች" እጃቸው እንዳለበት ተረጋግጧል።

ከፌደራል መንግስት እና ከክልሉ አስተዳደሮች ጋር በመሆን የፖለቲካ እና የሕግ እርምጃዎች እየተወሰደ ቢሆንም ያሉትን ጋሬጣዎች በጽናት ተጋፍጦ ማቃናት የሁላችንንም የተቀናጀ ጥረት ይጠይቃል ። የሰው ልጅን አሰቃቂ ህልፈት በተደጋጋሚ እያስተዋሉ የሚያልፍ ጫንቃ የለንም። ስለሆነም ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለመታደግ በኅብረተሰብ ተመልምለው እና ስልጠና ወስደው በአካባቢ ሚሊሺያነት ተደራጅተው አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ ይደረጋል።

የሕዝብ ለሕዝብ ግጭት ሳይሆን በአጥፊዎች የሚፈጸም ጥቃት በመሆኑ ቀደም ሲል ከቀዬአቸው ተፈናቅለው የነበሩ ከ20 ሺህ በላይ የሚቆጠሩ የህብረተሰብ አካላት እንዲመለሱ ተደርጓል። የህዝባችንን በየትኛውም የሀገሪቷ ክፍል በሰላም የመኖር መብት እናረጋግጣለን ።

የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ከአማራ ክልል ጋር በመሆን ጠንካራ ሥራ እየሰራ ይገኛል። የቅርብ ክትትል እያደረግን ማንም በተላላኪነትም ሆነ በውክልና ጦርነት አካባቢውን ለማተራመስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመመከት የክልላችን መንግስት በትኩረት ይሰራል።

የትኛውም ህገወጥ እንቅስቃሴ በትዕግስት እንደማይታለፍ ለወዳጅም ለጠላትም ለማረጋገጥ እወዳለሁ።

# አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳደር በፌስቡክ ገፃቸው

17/10/2020

ኢሳት ቴሌቭዥን በገንዘብ እጥረት ምክንያት ፕሮግራሞቹን አቋርጧል!

"በ2010 ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ኢትዮጵያው ውስጥ ነጻነት እንዲመጣ ሲያረግ የነበረው እንቅስቃሴ የመጨረሻው ምእራፍ ላይ ደርሷል ብለው የሚያምኑ ወገኖች የኢሳት ተልእኮ እንዳበቃም በማመናቸው ለኢሳት የሚደረገው ድጋፍ ቀንሷል። አሁን ላይ ባለው ሁኔታ ኢሳት አየር ላይ ለመቆየት በቂ አቅም ባለመኖሩ ለመቋረጥ ተገዷል" ያለው ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ነው።

Sophonias Evd ( infonans)
05/06/2020

Sophonias Evd ( infonans)

05/06/2020

Address

Arada
Addis Ababa

Telephone

+251921833633

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sophonias simachew posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Sophonias simachew:

Share