STAR GATE Accountancy

STAR GATE Accountancy This page will provide the most important issues about accounting and Tax related issues in Ethiopia

CONTACT US THROUHT
18/06/2024

CONTACT US THROUHT

18/06/2024

ማንኛውም ታክስ ከፋይ በታክስ ሕግ መሠረት በማንኛውም የታክስ ጊዜ ማቅረብ የሚገባውን የታክስ ማስታወቂያ ያላቀረበ እንደሆነ ባለሥልጣኑ በማንኛውም ጊዜ የሚያገኘውን ማስረጃ መሠረት በማድረግ ለታክስ ጊዜው ታክስ ከፋዩ ሊከፍል የሚገባውን ታክስ በግምት (የግምት ስሌት" ተብሎ የሚጠራ) ማስላት የሚችል ሲሆን የግምት ስሌቱ የሚከተሉትን ይመለከታል፦

ሀ) በፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ ሠንጠረዥ "ለ" ወይም “ሐ” ኪሳራን በሚመለከት የታክስ ጊዜውን የኪሳራ መጠን፤
ለ) በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ መሠረት በግብዓት ላይ በብልጫ የተከፈለ የተጨማሪ እሴት ታክስን በሚመለከት ለታክስ ጊዜው በግብዓት ላይ በብልጫ የተከፈለውን የታክስ መጠን፤
ሐ) በሌላ ማንኛውም ሁኔታ ዜሮ መጠንን ጨምሮ በታክስ ጊዜው ሊከፈል የሚገባውን የታክስ መጠን፡፡

ባለሥልጣኑ ታክሱ በግምት ለተሰላው ታክስ ከፋይ የሚከተሉትን ዝርዝር ነጥቦች ያካተተ የታክስ ግምት ስሌት ማስታ ወቂያ መስጠት አለበት፡-

U) እንደሁኔታው የተሰላውን የታክስ መጠን፤ ወደፊት የሚሸጋገር የኪሣራ ወይም በብልጫ የተከፈለን የግብዓት ታክስ መጠን፣
ለ) በተሰላው ታክስ ላይ ሊከፈል የሚገባ የቅጣት መጠን ካለ፣
ሐ) በተሰላው የታክስ መጠን ላይ ሊከፈል የሚገባ የዘገየ ክፍያ ወለድ መጠን ካላ፤
መ) የታክስ ስሌቱ የሚመለከተውን የታክስ ጊዜ
ሠ) ማስታወቂያው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በ፴ (በሰላሳ) ቀናት ውስጥ ታክሱ፣ ቅጣቱ እና ወለዱ የሚከፈልበትን ቀን፤
ረ) ቅሬታ ማቅረብ የሚችልበትን የጊዜ ገደብ ጨምሮ በታክስ ግምት ስሌቱ ላይ ቅሬታውን የሚያ ቀርብበትን አኳኋን፡፡

የታክስ ግምት ስሌት ማስታወቂያ ታክሱን በሚጥለው የታክስ ሕግ መሠረት በተዘጋጀው የታክስ ግምት ስሌት ሊከፈል የሚገባው ታክስ የሚከፈልበትን ጊዜ ( "የመጀመሪያው የታክስ መክፈያ ጊዜ" ተብሎ የሚጠቀስ) ሊለውጥ የማይችል ሲሆን፣ የታክስ ክፍያው በመዘግየቱ ምክንያት የሚጣል ቅጣትና ወለድ መታሰብ የሚጀምሩት ከመጀመሪያው የመክፈያ ጊዜ አንስቶ ይሆናል፡፡

•ይህ አንቀጽ ተፈጻሚ የሚሆነው በታክስ ስሌት ለሚሰበሰብ ታክስ ብቻ ነው።
•ይህ አንቀጽ በባለሥልጣኑ የተዘጋጀ የታክስ ግምት ስሌት የደረሰው ማንኛውም ታክስ ከፋይ የግምት ስሌቱ የሚመለከተውን የታክስ ማስታወቂያ የማቅረብ ግዴታውን አያስቀርም፡፡
•በባለሥልጣኑ የተዘጋጀ የታክስ ግምት ስሌት ማስታወቂያ ለታክስ ከፋዩ ከደረሰው በኋላ ለዚያ የታክስ ጊዜ. ታክስ ከፋዩ የሚያቀርበው የታክስ ማስታወቂያ ለታክስ ጊዜው እንደቀረበ በታክስ ከፋዩ የተዘጋጀ የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያ ሆኖ አይቆጠርም፡፡
•ባለሥልጣኑ በማንኛውም ጊዜ በግምት ላይ የተመሠረተ የታክስ ስሌት ሊያዘጋጅ ይችላል።
•ባለሥልጣኑ ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም የሚያግዙ መመሪያ ዎችን ሊያወጣ ይችላል፡፡

13/06/2024
የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) የተንከባላይነት ባህሪ****የተጨማሪ እሴት ታክስ የመክፈል ሸክም በአንድ ደረጃ ብቻ የተገደበ ሳይሆን በተለያዩ ደረጃዎች የተከፈለ ነው፡፡ ግዴታውም ከአስመጪው ...
26/03/2024

የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) የተንከባላይነት ባህሪ
****
የተጨማሪ እሴት ታክስ የመክፈል ሸክም በአንድ ደረጃ ብቻ የተገደበ ሳይሆን በተለያዩ ደረጃዎች የተከፈለ ነው፡፡ ግዴታውም ከአስመጪው እና አምራቹ ጀምሮ እስከ ችርቻሮ ሻጩ የሚሄድ ነው፡፡

ከላይ የተዘረዘሩትን ነጥቦች የበለጠ ግልጽ ለማድረግ የሚከተሉትን ምሳሌዎች ማየቱ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

ምሳሌ፡- አንድ ዕቃ አምራች በ200,000ብር የጥሬ ዕቃ ግዢ ቢፈጸምና ዕቃውን ለጅምላ ሻጭ በ250,000 ብር ቢሸጥ፤ ጅምላ ሻጩ 280,000ብር ቢሸጥ፤ አንዲሁም ችርቻሮ ሻጩ ዕቃውን ለሸማቹ 300,000ብር ቢሸጥ እና የታክስ ማስከፈያ መጣኔው 15 በመቶ ቢሆን የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ስሌቱ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

1.ጥሬ ዕቃ አቅራቢው እቃውን ሲሸጥ የሚሰበስበው የተጨማሪ እሴት ታክስ 200,000*15/100=30,000 ይህ ማለት ጥሬ እቃ ሻጩ ዕቃውን ለአምራቹ ሲሸጥ 30,000 ብር ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሰብስቦ ለመንግስት ገቢ ያደርጋል ማለት ነው፡፡

2.አምራቹ ዕቃውን ለጅምላ ሻጩ ሲሸጥ የሚሰበስበው የተጨማሪ እሴት ታክስ ደግሞ 250,000*15/100=37,500 ሲሆን ለታክስ አስገቢው ባለስልጣን የሚከፍለው ታክስ 37,500-30,000 =7,500 ወይም በዚህ ደረጃ እሴቱ 250,000-200,000 =50,000*15/100=7,500 ይሆናል ማለት ነው፡፡

3.ጅምላ ሻጩ ዕቃውን ለችርቻሮ ሻጩ ሲሸጥ የሚሰበስበው የተጨማሪ እሴት ታክስ ደግሞ 280,000*15/100=42,000 ሲሆን ለታክስ አስገቢው ባለስልጣን የሚከፍለው ግን 42,000-37,500=4500 ይሆናል፡፡ በሌላ አገላለጽ 280,000-250,000=30,000*15/100=4500 ይሆናል ማለት ነው፡፡

4.ችርቻሮ ሻጩ ደግሞ ለሸማቹ እቃውን በብር 300,000 ሲሸጥ የሚሰበሰበው ተጨማሪ እሴት ታክስ 300,000*15/100=45,000 ሲሆን ችርቻሮ ሻጩ ለታክስ አስገቢው ባለስልጣን የሚከፍለው ግን 45,000-42,000=3,000 ይሆናል በሌላ አገላለጽ 300,000-280,000=20,000*15/100=3,000 ይሆና ማለት ነው፡፡

 ከላይ በተጠቀሰው መሠረት መንግስት ከጥሬ ዕቃ አቅራቢው 30,000ብር
 ከአምራቹ 7,500 ብር
 ከጅምላ ሻጩ 4500 ብር
 ከችርቻሮ ሻጩ 3,000 ብር

በአጠቃላይ 45,000 ብር ተጨማሪ እሴት ታክስ ይሰበሰባል ማለት ነው፡፡ የታክሱን አጠቃላይ መጠን ዕቃው ለሸማቹ የተሸጠበትን ዋጋ በአስራ አምስት ፐርሰንት በማባዛት ማወቅ ይቻላል፡፡ ይህም 300,000*15/100=45,000 ብር ይሆናል፡፡ በዚህም መሠረት የተጨማሪ እሴት ታክስ በአንድ ደረጃ ብቻ የሚከፈል ሳይሆን በእያንዳዱ ደረጃ የሚከፈል እና ከአንዱ ወደ ሌላው የሚንከባለል ታክስ መሆኑን ከምሳሌው በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡

For more information join
Our Telegram channel👎👎👎

 #ከሽያጭ ታክስ/Turn over tax/ ክፍያ ነፃ ግብይቶች :- •  ቢያንስ ሁለት ዓመት ያገለገለ የመኖርያ ቤት ሽያጭ እና የመኖርያ ቤት ኪራይ •  የፋይናንስ አገልግሎቶች•  ለሳንቲሞችና...
20/03/2024

#ከሽያጭ ታክስ/Turn over tax/ ክፍያ ነፃ ግብይቶች :-

• ቢያንስ ሁለት ዓመት ያገለገለ የመኖርያ ቤት ሽያጭ እና የመኖርያ ቤት ኪራይ
• የፋይናንስ አገልግሎቶች
• ለሳንቲሞችና መዳልያዎች ጥናት አገልግሎት ከሚውሉት በስተቀር የአገር ውስጥና የውጭ አገር ገንዘቦች እና የዋስትና ሰነዶች ማሰራጨት
• በሃይማኖት ድርጅቶች የሚሰጡ የእምነት ወይም ከአምልኮ ጋር የሚገናኙ አገልግሎቶች
• የሕክምና አገልግሎቶች እና አግባብ ባለው የመንግስት መሥርያ ቤት በሚወጣ መመርያ መሠረት ነፃ የተደረጉ አገልግሎቶች
• በትምህርት ተቁዋማት የሚሰጡ የማስተማር አገልግሎቶች እንዲሁም ለሕፃናት ጥበቃ በመዋእለ ሕፃናት የሚሰጡ አገልግሎቶች
• ለሰብአዊ ዕርዳታ የሚውሉ ዕቃዎችና አገልግሎቶች፣ የኤሌክትሪክ፤የኬሮሲን እና የውሃ አቅርቦት፣ የትራንስፖርት አገልግሎቶች
• ማንኛውም የስራ እንቅስቃሴ ለማከናወን ለሚስጥ ፈቃድ ለመንግስት የሚሰጥ ክፍያ
• ከ60% በላይ ሠራተኞቹ አካል ጉዳተኞች የሆኑበት አካል ጉዳተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራ ድርጅት የሚቀርባቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች
• መፃሕፍት( ወደ ሀገር የሚገቡ፣ በሀገር ውስጥ የሚሸጡ እና መጻህፍትን ወቅታዊ ለማድረግ የሚወጡ እትሞች )
• የምግብ እህል (ጤፍ፤ ስንዴ፣ ገብስ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ዘንጋዳ ፣ዳጉሳ ፣ አጃ፣ እንዲሁም የነዚህ ዱቄት ከጥራጥሬ አተር ፣ባቄላ፣ምስር ፣አኩሪ አተር፣ሽንብራ ፣ግብጦ ፣ጓያ )
• የቅባት እህሎችም ሆኑ ፕሮሰስ የተደረጉ ምግቦች፣ ፉርሽካም ጭምር የታክስ መነሳት አይመለከታቸውም፡፡ for more information Please subscribe the following Telegram channel

01/07/2022

ይደውሉልን

Address

ADDIS ABABA ETHIOPIA AROUND DEMBEL CITY CENTER
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30
Saturday 08:30 - 00:30

Telephone

+251970212101

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when STAR GATE Accountancy posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share