Tigst

Tigst Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Tigst, Business service, Merkto, Addis Ababa.

29/07/2026
26/07/2026
23/04/2026

አዲሱ ሙሽራ በሚስቱ የቀድሞ ፍቅረኛ ተገደለ !

​በጌዴኦ ዞን ገደብ ከተማ የአቢሲኒያ ባንክ ሰራተኛ የሆኑት አቶ ተመስገን ዳንኤል፣ ዛሬ ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ገደማ ወደ ስራ በመጓዝ ላይ ሳሉ በአደባባይ በተተኮሰባቸው ጥይትና በደረሰባቸው የስለት ጥቃት ህይወታቸው አልፏል።

ግድያውን ፈጽመዋል የተባሉት ተጠርጣሪ ግለሰብ በአሁኑ ሰዓት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል።

​የአይን እማኞች እና የሟች የቅርብ ቤተሰቦች እንደገለጹት፣ ጥቃቱ የተሰነዘረው አቶ ተመስገን ከሁለት ወራት በፊት ካገቧቸው ከወይዘሮ ምህረት ደስታ ጋር በተያያዘ በደረሰ የቂም በቀል ተነሳሽነት ነው።

ተጠርጣሪው አቶ አቡሽ ታደሰ ሁጤሳ የሟች ባለቤት የቀድሞ ፍቅረኛ እንደነበሩ የተጠቀሰ ሲሆን፣ "ሚስቴን አገባህብኝ" በሚል ሰበብ ግድያውን እንደፈጸሙት ተነግሯል።

​ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት አቶ ተመስገን "አድኑኝ፣ ሊገድለኝ ነው" በማለት የእርዳታ ጥሪ ቢያሰሙም፣ በአካባቢው ከነበሩ ሰዎች ፈጣን ምላሽ ባለማግኘታቸው ....

ተጠርጣሪው በሽጉጥ በመተኮስ እና በመቀጠልም በስለት መሳሪያ አስክሬኑን በመቆራረጥ አሰቃቂ ጥቃት ሊያደርሱባቸው ችለዋል።

​ፖሊስ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ ዝርዝር ምርመራ እያከናወነ ሲሆን፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በድርጊቱ ከፍተኛ ድንጋጤና ሀዘን ተሰምቶታል።

ማህበረሰባችን ወዴት እየሄደ ነው ሰው ሲገደል እንዴት ቆም ያያል መገላገል እየቻለ እረ ወዴት እየሄድን ነው የግዮን ማለዳ ቤተሰቦች😭

ለቤተሰቦቹ ለወዳጅ ዘመዶቹ በግዮን ማለዳ ስም መፅናናትን እንመኛለን ። ነብሱን ይማርልን !

ግዮን ማለዳ

ፍትህ ለዚህ ወጣት 😭 😭 አመሟቱ በጣም አሰቃቂ ነው የማየት አቅሙ ያላችሁ ቴሌግራም ቻናላችን ላይ ተመልከቱት 👇

ቴሌግራም 👉 T.me/GhionMaleda

15/04/2026

በህጻኗ ላይ የተፈጸመ ድብቅ ጥቃት ይፋ ሆነ

በአዲስ አበባ አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ለረጅም ጊዜ በታማኝነት ስታገለግል የነበረች የቤት ሰራተኛ፣ የ1 አመት ከ8 ወር ህጻን ላይ የፈጸመችው አሳዛኝ ጥቃት በድብቅ ካሜራ ተመዝግቦ ይፋ ሆኗል።

ወላጆቹ ሰራተኛዋን እንደ ቤተሰብ አባል አምነው ለረጅም ጊዜ ከእነርሱ ጋር ቢኖርችም፣ በህጻኗ ላይ በተደጋጋሚ የሚታዩ የመውደቅ አደጋዎች እና በመጨረሻም የእጅ መሰበር ከፍተኛ ጥርጣሬ አስከትሎባቸዋል።

እውነቱን ለማረጋገጥ በቤቱ ውስጥ የተገጠመ የድብቅ ካሜራ ያሳየው ግን እጅግ አስደንጋጭ ነበር።

የተመዘገቡ ጥቃቶች፦
-ህጻኗን ከፍተኛ አካላዊ ጥቃት መፈጸም
-ከቤት እቃዎች ጋር በመጣል እና በጭካኔ መጎዳት

-የህጻኗን እርዳታ እጥረት ተጠቅመው ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች መፈጸም

ተከሳሽዋ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከተያዘች በኋላ ለ9 ቀናት ቆይታ ካደረገች በኋላ፣ በ4,500 ብር ዋስትና መፈታቷ ተነግሯል። ይህም በወላጆቹ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ እና ስጋት አስከትሏል።

ተከሳሽዋ ሸጋዬ ምንይች (የመታወቂያ ስም ዝያን) መሆኗ ሲገለጽ፣ በአዲሱ ገበያ አካባቢ ሌላ ስራ ጀምሯል ተብሏል።

የወላጆች ጥንቃቄ፦ ይህ ክስተት ለማኅበረሰቡ ትልቅ ትምህርት ሲሆን፣ ወላጆች የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች እንዲወስዱ ተመክሮባቸዋል፦

-የህጻናትን ደህንነት በካሜራ (CCTV) በመከታተል መጠንቀቅ
-ድንገተኛ የፍርሃት ስሜት፣ አካላዊ ጉዳት ወይም እንግዳ ባህሪ ካሳዩ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል

እንደዚህ ያሉ ጥቃቶች በህግ እንዲቀጡ ማህበረሰቡ ድምጹን እንዲያሰማ ለተጎጂዋ ህጻን ፈጣን ፈውስ እየተመኘን፣ ወላጆች ለልጆቻቸው ደህንነት ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል።

04/04/2026

ራሷን መከላከል በማትችልበት ሁኔታ እና ባለቤቱ በሌለችበት ወቅት የገዛ ልጅን የግብረ ስጋ ድፈረት ወንጀል የፈፀመው አባት

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ቤንች ሸኮ፣ ሲዝ ከተማ በገዛ ልጁ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል የፈጸመ ግለሰብ በ12 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱ ከክልሉ ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ጥር 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ነው።ተከሳሹ ዳንኤል ወልዴ የሚባል ሲሆን እድሜዋ 14 ዓመት የሆናትን የገዛ ልጁን...

ራሷን መከላከል በማትችልበት ሁኔታ እና ባለቤቱ በሌለችበት ወቅት ኃይል በመጠቀም የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል መፈጸሙ ተገልጿል።

ዓቃቤ ሕግ ከፖሊስ የተሰበሰቡ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ለችሎቱ አቅርቧል። የሲዝ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከሳሹ በቀረበበት የወንጀል ክስ ላይ መከላከል ባለመቻሉ ጥፋተኛ ብሎት በ12 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ይህን ፍጹም ኢሰብዓዊ፣ ኢሞራላዊ የአውሬና የጭካኔ ድርጊት በገዛ ልጁ ላይ የፈጸመውን ወንጀለኛ 12 ዓመት እስራት ብቻ ተፈርዶበታል።

የችሎቱ ዳኛ አማረ ገበየ " ፍርዱ ተከሳሹን የሚያርምና ለሌሎችም ትምህርት የሚሰጥ ውሳኔ " ብለውታል።

ከዚሁ መረጃ ጋር በተያያዘ ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ " የፍርድ ውሳኔው እውነት ማስተማሪያ ነው ? " የሚል ጥያቄና ቅሬታ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ተነስቷል።

በተለያዩ ጊዜ የሚተላለፉ ውሳኔዎች የወንጀሉን ክብደት መመዘን ሲሳናቸው የፍትህ ስርአቱ ላይ ጥያቄ ይነሳል።

የህፃናት ስነልቦና እና የወደፊት ህይወት ላይ የሚደርሰው ጥፋት በዓመታት እስራት ብቻ ሊለካ የማይችል በመሆኑ ቅጣቱ በደሉን ይመጥናል ወይ ? የሚለው በብዙዎች ዘንድ ቁጣን የቀላቀለ ጥያቄ ያስነሳል።

በህፃናት ላይ የሚፈጸሙ መሰል ጥቁር ጠባሳዎች በማህበረሰቡ ዘንድም የሚፈጥሩት ቁስል ጥልቅ ነው።

ግዮን ማለዳ በተከታታይ መሰል የሴቶች ጥቃቶች መረጃዎች የሚጋራው ድርጊት ትኩረት እንዲሰጠውኛ የህግ ማሻሻያ ተደርጎ አስተማሪ የሆነ ቅጣት እንዲሰጥበት ነው።

ህብረተሰቡ ህግን እንደ ጋሻ ማየት የሚፈልገው ወንጀለኞች በድርጊታቸው እንዲጸጸቱ ብቻ ሳይሆን ሌሎች መሰል ሀሳብ ያላቸው ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የሚያደርግ " #አስፈሪ " ቅጣት ሲኖር ነው።

ለሚፈጸሙ ዘግናኝ ወንጀሎች የሚተላለፉ የቅጣት ውሳኔዎች ወንጀሉን የሚመጥኑ ካልሆነ ተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው በህግ ጥላ ስር መጠለልን ትተው በዝምታ እንዲሰቃዩ ፤ በፍትህ ስርዓቱ ተስፋ እንዲቆርጡ በር ይከፍታል።

ፍትህ "ተሰጥቷል" ብቻ ሳይሆን " እንደተሰጠ የሚታወቀው" ውሳኔዎቹ የህዝቡን የሞራል ስብራት የሚጠግኑና የወንጀሉን ክፋት የሚመጥኑ ሆነው ሲገኙ ብቻ ነው።

እንደ ግዮኝ ማለዳ የቅጣት ማነስ የሴቶችን አስገድዶ መድፈር እያበባሰ ነው ብለን እናምናለን ! የሴቶች ጥቃት ይቁም !

እናንተ የፍርድቤቱ ቤቱ ውሳኔ አስተማሪ ኘው ብላችሁ ታስባላችሁ ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን እስኪ?

ግዮን ማለዳ

በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች ቴሌግራም ላይ ያገኛሉ👇

https://t.me/GhionMaleda

07/03/2026

አስሸኳይ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ !
✍ ሙሉ ስሙ ኢምራን ሙራድ ሱሩር ይባላል።ዕድሜ 15 ሲሆን የመኖሪያ አከባቢው ዘሞ ባቴ ትምህርት ቤት ጀርባ የማህበር ቤት ሰፈር ነው።ኢምራን በዕለቱ ከቤት ሲዮጣ ሮዝ ከለር ባለኮፍያ ሹራብና ሲልቨር ከለር ሱሪ የለበሰ ሲሆን ኤርጌንዶ ጫማ አድርጓል።
✍ኢምራን ትላንትና እሁድ 22/06/2018 ከቀኑ 6፡00 አከባቢ ከቤት እንደወጣ እስካሁን ወደ ቤት አልተመለሰም።
✍ ስለሆነም ቤተሰቦቹ በጣም እየተጨነቁ በመሆኑ ልጁን ያገኘ/ ያለበት ጥቆማ በመስጠት ተባበሩን።
አድራሻ፦
✅ 0939743771
✅ 0942152208
✅ ዐ913396600
ስልክ ላይ በመደወል ተባበሩን ይላሉ ቤተሰቦቹ።

Address

Merkto
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tigst posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share