23/10/2022
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በስራ አመራር ቦርድ ሲያገልግሉ ለቆዩ ሶስት የቦርድ አባላት የምስጋናና የሽኝት እንዲሁም ለአዳዲስ የቦርድ አባላት የአቀባበል መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡
የምስጋናና የእውቅና ሰርተፊኬት እና ሽልማት የተበረከተላቸው አቶ ዘመዴ ተፈራ ፣አቶ በዛብህ ገብረየስ እና ወ/ሮ ማህዳ ኡመር ናቸው፡፡
አዳዲስ ቦርዱን የተቀላቀሉት እና እንኳን ደህና መጣችሁ የተባሉት አቶ ደበሌ ቃበታ - የጉምሩክ ኮምሽን ኮምሽነር፣ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ -ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ዶ/ር እመቤት መለሰ - ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ- ከገቢዎች ሚኒስቴር እና አቶ ሳሙኤል ሃላላ- ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ናቸው፡፡
በስነ ስርአቱ ላይ የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢና የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አብረሃም በላይ ሽኝት የተደረገላቸውና እውቅና የተሰጣቸው የቦርድ አባለት ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ጊዜያቸውን በመሰዋት የሰሩ በመሆናቸው ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል፡፡አዲሶቹም የላቀ ሚና እንደሚጫወቱ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በበኩላቸው ለግሩፑ ስትራቴጂካዊ አመራር ከመስጠት ባሻገር ጠንካራ የክትትልና ድጋፍ ሚና ሲጫወቱ እንደነበርና በዚህም ሊመሰገኑ እንደሚገባ በመናገር አዳዲስ የቦርድ አባላትም ለግሩፑ ሁለንተናዊ ስኬት የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
Three management board members seen off,five welcomed saturday 22 october 2022,Addis Ababa,Ethiopia:The Ethio-Engineeering Group(EEG)sees three of its board members here yesterdday at a cermony organized to recognizeand certify thier contributions, it also welcomed new ones. It was Ato Zemedie Tefera,Ato Bezabehe Gebereyes and w/ro Maheda Oumer who were seen off,while Ato Debele Kabeta ,from Custums Commission,Ato Tarekegn Bululuta, from the Ministry of Industry, Dr.Emebet Melese, from Commercial Bank of Ethiopia, w/ro Meseret Meskelie ,from the Ministry of Revenue, and Ato Samuel Halala,from the ministry of Industry. Speaking on the occassion ,Minister of Defence and Board chairman of EEG, Dr.Abereham Belay,noted that the out going board members need to be thanked and recogniyed for their relentless efforts to take the group to a better level.He also expressed his belief that the incoming ones too follow suits.EEG CEO,Ambassador Meseganu Arga on his part rehiterated that apart from giving strategic leadership,they were giving support .And as such, they deserve apreciation.I belive the new ones would also do the same he said.
source: EEG