30/08/2023
ተግባቦት በአገልግሎት አሰጣጥ ውስጥ መሰረታዊ ጉዳይ ነው።ከደንበኞች ጋር ባለን ተግባቦት በተቻለ መጠን መጠቀም የሌለብን ቃላትና ሀረጎች እንዳሉ ሁሉ (ከዚህ ቀደም የለጠፍኩትን ይመልከቱ)፤ በተቻለ መጠን አዘውትረን መጠቀም የሚመከሩ ቃላት፣ ሀረጎችና አባባሎች አሉ።
ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉት ይገኙበታል።
• ምን ማድረግ እንደምንችል አብረን እናያለን ፣አብረን መፍትሄ እንፈልጋለን
• መረጃ ለማግኘት፣ ለማወቅ እሞክራለሁ
• የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ
• ልረዳህ የምችለው ወይም ላደርግ የምችለው እንዲህ ነው
• ምን ማድረግ እንደምንችል አማራጮችን እንፈትሽ
• በእውነቱ ከልቤ አዝናለሁ
• ይቅርታ
• ከደቂቃዎች በኋላ አንተ ጋር ነኝ፣ ልረዳህ ዝግጁ ነኝ
• መልሸ እደውላለሁ እባክዎት ስልክዎንና ስምዎትን ይስጡኝ
• ይቅርታ ምን ልታዘዝ
• አይዞን
• እሽ
• ይቻላል
• በደስታ
• ችግር የለም
• እናመሰግናለን፣ ማመስገን ያለብን እኛ ነን
• ትክክል ነው፣እውነት ነው
• ስራችን ነው
• እናመሰግናለን
• ይልመድባቹህ
• ምን እናስተካክል፣ አስተያየት ካለዎት…