Seket Business Consulting / ስኬት ቢዝነስ አማካሪ

Seket Business Consulting / ስኬት ቢዝነስ አማካሪ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Seket Business Consulting / ስኬት ቢዝነስ አማካሪ, Business consultant, Olympiya, Addis Ababa.

14/11/2020

Available in our store for only 4900 birr only

14/11/2020
28/07/2020

የግል ተቋማት አሰሪዎች ሰራተኞቻቸውን ከኮቪድ-19 ለመጠበቅ የሚያደርጉት ድጋፍ ቀንሷል-ኢሰማኮ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመጣበት በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የግል ተቋማት አሰሪዎች ቸልተኝነት እየታየባቸው መሆኑን የኢትዮዽያ ሰራተኞች ማህበር ኮንፌዴሬሽን አስታወቀ።

የኢትዮዽያ ሰራተኞች ማህበር ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ÷የግል ተቋማት አሰሪዎችም ሆነ ሰራተኞች ስለኮሮና ቫይረስ አደገኝነት የክልል ኤፍኤሞች ጨምሮ በተለያዩ የሚድያ ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

ሆኖም በግል ተቋማትም ሆነ በሰራተኞች ዘንድ የቸልተኝነትና የጥንቃቄ ጉድለት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚስተዋል ተናግረዋል።

ችግሩ እየተባባሰ ሲመጣ በሰራተኛና ማህበራዊ ሚኒስትር ወደ ሚመራው የሶስትዮሽ የስራ ቦታ ፕሮቶኮል ኮሚቴ ከሰራተኞች ለቀረበው ቅሬታ በማስማማት በርካታ ችግሮች የተፈቱ ቢሆንም በሁሉም ቦታ ግን ተደራሽ አይደለም ሲሉም ጠቁመዋል።

ነገር ግን ህጉን አክብረው ለሰራተኞቻቸው የንፅህና መጠበቅያ የሚያቀርቡ ተቋማትና ርቀታቸውን ጠብቀው የሚያሰሩ እንዳሉ ገልፀው÷ አንዳንድ ቁጥራቸው ከፍ ያሉ ተቋማት ግን ህጉን ቸል በማለትና ለሰራተኞቻቸው አስፈላጊውን ጥንቃቄ ባለማድረጋቸው ለቫይረሱ እንዲጋለጡ ምክንያት ሆነዋል ብለዋል።

በምሳሌነትም አንድ ስሙን መጥቀስ ያልፈለጉት የውጭ አገር የግል ተቋም ለሰራተኞቹ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ባለመደረጉ በርካታ ሰራተኞች በቫይረሱ መያዛቸውን ተናግረዋል።

ቫይረሱ በሀገራችን ከተከሰተበት ወቅት ጀምሮ ውሃና የንጽህና መጠበቂያ ሳሙና ለሰራተኞች ሲያቀርቡ የነበሩ ድርጅቶችም የቫይረሱ ስርጭት ከፍ ባለበት በአሁኑ ወቅት ቸልተኝነት እየተስተዋለ ይገኛል ብለዋል።

የሚመለከተው አካል ለድጋፍና ክትትል ወደ ተቋማት ሲሰማራ ለታይታ የሚቀመጡ የንፅህና መጠበቂያዎች በሌላው ጊዜ እንደማይቀርቡ ከሰራተኞቹ ለማወቅ መቻሉም ነው የጠቆሙት።

ሰራተኞች በግል አሰሪዎቻቸው ላይ ቅሬታ ሲያቀርቡ ቀደም ብሎ በወጣው የሶስትዮሽ የስራ ፕሮቶኮል መሰረት ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጋር በመሆን የማስማማትና የማስተካከል ስራዎች መሰራታቸውንም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በስምምነት መቋጨት ያልቻሉ ቅሬታዎች በየወረዳው ወደ ተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈፀምያ ማእከላት ቢላክም ተገቢውን ምላሽ እየተሰጠው አይደለም ሲሉም ያስረዳሉ።

ሰው በጤናና በህይወት ሲኖር ነው ሃብት ማፍራትም ሆነ ማደግ የሚችለውና አሰሪዎች ከጥንቃቄ ጉድለት ሰራተኞቻቸው ሊጎበኝ የሚችለው ኮቪድ-19 ለእነሱም እንደሚተርፍ በመገንዘብ ቆም ብለው ሊያስቡ ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።


የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Stay Safe. Make sure to keep your distance. Wash your hands regularly.
15/07/2020

Stay Safe. Make sure to keep your distance. Wash your hands regularly.

Sample is available around StadiumTo get pictures of the certificates0940096111
26/06/2020

Sample is available around Stadium
To get pictures of the certificates
0940096111

Address

Olympiya
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Seket Business Consulting / ስኬት ቢዝነስ አማካሪ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share