Nati Sw

Nati Sw Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Nati Sw, Business service, Wolaita S**o, Addis Ababa.

የመለያየቱ መፍትሔ መወያየት ነው።😂😂😂😀
31/12/2023

የመለያየቱ መፍትሔ መወያየት ነው።😂😂😂😀

29/12/2023
ስማኝ ልጄ!!!!!!! ተነቦ ሼር ይደረግ1. ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!!2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ...
29/12/2023

ስማኝ ልጄ!!!!!!! ተነቦ ሼር ይደረግ

1. ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!!

2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!!!!

3. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!!!!

4. አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!!!!

5. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!!

6. ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ!!!

7. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!!!!

8. ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ስራ ውደድ ማለት እንጂ!!!!

9. ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!!!!

10. ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ስትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!!!!

11. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ግዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!!!!

12. እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነትተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት ማለት እንጂ!!!!

13. አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!!!!

14. ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!!!

15. ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክህ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ!!!!

16. አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!!

የማፍቀር መስፈርቱ ፍቅር ብቻ ነው!! በዚህ ቻናል 👉 በኔ የተፃፉ ግጥሞች 👉 እንዲሁም ከሌሎች 👉 ህይወት ቀያሪ እና አሰተማሪ ፅሁፎች 👉 አጭር ልብወለዶች ይቀርቡበታል ሀሳብ አሰተያየት ....

29/12/2023
😂😂😂😂😀
29/12/2023

😂😂😂😂😀

29/12/2023
1-. አልበርት አንስታይን አንስታይን ከ1879-1955 የኖረ ታላቅ የሳይንስ ሊቅ ነበር። በተለይ ሁለት ግኝቶቹ የሳይንስ እይታችንን በእጅጉ የቀየሩ ሲሆን አንስታይን ምድራችን ካፈራቻቸው የሳ...
21/12/2023

1-. አልበርት አንስታይን

አንስታይን ከ1879-1955 የኖረ ታላቅ የሳይንስ ሊቅ ነበር። በተለይ ሁለት ግኝቶቹ የሳይንስ እይታችንን በእጅጉ የቀየሩ ሲሆን አንስታይን ምድራችን ካፈራቻቸው የሳይንስ ሊቆች ውስጥም ሆነ ወደፊት ከሚወለዱት ውስጥ ተወዳዳሪ አይገኝለትም የሚባል ብርቅዬ ሳይንቲስት ነው።

አንስታይን በልጅነቱ ዳይስሌክሊስ (ሲያነቡ ወደ ግራ የሚያነቡ) የነበረ ሲሆን በትምህርቱ ደካማ በመሆኑ አስተማሪዎቹ ደደብ አድርገው ይገምቱት ነበር።

በ15 ዓመቱ ትምህርቱን አቁሞ ከዓመት በኋላ ዙሪክ የሚገኝ አንድ ፖሊ ቴክኒክ ለመግባት አመልክቶ የመግቢያ ፈተናውን ወድቋል።

ይህ ሰው ግን በፊዚክስ ንድፈ ሃሳብ ዓለምን በመቀየሩ የኖቬል ሽልማት ለመሸለም የበቃ ድንቅ ሳይንቲስት ነው።

2- ቤንጃሚን ፍራንክሊን

ይህ ሰው የሂሳብ ትምህርት አይሆነውም ነበር። እናም አባቱ ከትምህርት ቤት አስወጥቶ ሻማና ጧፍ ሲያሰራው አደገ። ነገር ግን ይህ ሰው አሜሪካ ካፈራቻቸው ታላላቅ ሰዎች አንዱ በመሆን ታዋቂ ፖለቲከኛ፣ ሳይንቲስት፣ ጸሐፊ እና የፔንሲልቫኒያ ፕሬዚዳንትና የአሜሪካ መስራች አባት ለመባል የበቃ ሰው ነው።

3- ቻርለስ ዳርዊን

ወጣቱ ዳርዊን በትምህርቱ በመድከሙ አባቱ "አንተ ከአደን እና ውሻ በስተቀር የምትወደው ነገር የለም፤ ስለዚህ ለራስህም ሆነ ለቤተሰብ ውርደት እንዳትሆን" ብሎ ከትምህርት ቤት አስወጣው።

የህክምና ትምህርት ሞከረ አስጠላው። የሃይማኖት ትምህርትም ሞክሮ ነበር አልሆነለትም። ብዙውን ግዜውን ግን ከስፖርተኞች ጋር ነበር የሚያጠፋው።
ይህ ሰው ግን በመጨረሻ አጠቃላይ የስነ-ህይወት ሳይንስን ለመቀየር ችሏል።

4- ሴናተር ኤድዋርድ ኤም ኬኔዲ

ይህ የማሳቹሴትስ ሴናተር በአንድ ወቅት ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ሁሉ ተወዳድሯል። ግን ፈተናውን ጓደኛው ሲፈተንለት ተይዞ ከሚማርበት ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተባርሮ ነበር።

5- ሰር ዊንስተር ቸርችል

ይህ ሰው ታላቅ እንግሊዛዊ ፖለቲከኛ፣ ገጣሚ፣ ደራሲና ሰዓሊ ሲሆን እንግሊዝን በአንደኛ እና ሁለተኛ የዓለም ጦርነት በተለያየ የመንግስት ስልጣን ደረጃ የመራ ታላቅ የፖለቲካ ሰው ነው። (በአገራችን መዲና አዲስአበባ ጎዳና በስሙ ተሰይሞለታል)

ቸርችል ይህቺ ምድር ካፈራቻቸው ድንቅ የፖለቲካ ሰዎች አንዱ ቢሆንም በትምህቱ ደካማ ስለነበር ሮያል የውትድርና ኮሌጅ ለመግባት ከአንዴም ሁለት ግዜ ተፈትኖ በመውደቁ መግባት አልቻለም ነበር።

6- ቶማስ ኤድሰን

ይህ ታላቅ ፈላስፋ ትምህርት ቤት የሄደው ለሶስት ወራት ብቻ ነበር። ምክንያቱም በስምንት ዓመቱ አስተማሪው "ደደብ" ብሎ ስለሰደበው እናቱ ከትምህርት ቤት አውጥታ ቤት ውስጥ አስተማረችው። በዘጠኝ ዓመቱ ይሞክራቸው የነበሩት ነገሮች ከእናቱ አቅም በላይ ሆኖ ተገኝቷል።

ቶማስ ኤድሰን በህይወት ዘመኑ አንድ ሺህ አዳዲስ ግኝቶችን የፈለሰፈ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የኤሌክትሪክ ብርሃን እና ሸክላ ማዘፈኛ ሲኖሩበት ያሻሻላቸው ነገሮች ደግሞ ፊልም ማሳያ፣ ቴሌፎን ይገኙበታል።

7- አይዛክ ኒውተን

ይህ ሰው ደካማ ውጤቶች ስለነበሩት ከትሪንቲ ኮሌጅ ሆነ ከካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ሲመረቅ የክብር ወይም የማዕረግ ተመራቂ አልነበረም።

ነገር ግን በታሪክ ከታወቁት ታላላቅ የሳይንስ ፈጣሪዎች አንዱ በመሆን የዘመኑ ሳይንስ በእርሱ ስራዎች ላይ ለመመርኮዝ በቅተዋል።

---------------------------------

Address

Wolaita S**o
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nati Sw posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share