Mesfin photo editor

Mesfin photo editor Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mesfin photo editor, Business service, ADDIS ABABA, Addis Ababa.

photo news
24/01/2026

photo news

ከተመሰረተ የ126 አመታት ያስቆጠረው ታዋቂው የፈረንሳይ መነፅር አምራች ሄነሪ ጁሊያን ከጥቂት አመታት በፊት ሊዘጋ ደርሶ የነበረ ካምፓኒ ነው ። ከዛም በኋላ አገግሞ እንደወትሮው የቅንጦት መ...
24/01/2026

ከተመሰረተ የ126 አመታት ያስቆጠረው ታዋቂው የፈረንሳይ መነፅር አምራች ሄነሪ ጁሊያን ከጥቂት አመታት በፊት ሊዘጋ ደርሶ የነበረ ካምፓኒ ነው ።

ከዛም በኋላ አገግሞ እንደወትሮው የቅንጦት መነፅሮችን እያመረተ ቢገኝም ፡ እስከ ባለፉት ሶስት ቀናት ድረስ ግን ይህ ነው የሚባል ከፍተኛ ለውጥ ሳያሳይ ቆይቷል ።...
የዚህ ካምፓኒ ታሪክ የተቀየረው ፡ ሰሞኑን በስዊዘርላንድ ዳቮስ በተካሄደው ጉባኤ ላይ የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት የሄነሪ ጁሊየንን Pacific S 01 የሚባለውን መነፅር አድርገው ከታዩ በኋላ ነበር ።

በወቅቱ ማክሮን ይህንን መነፅር አድርገው ፡ በዳቮስ መድረክ ንግግር ሲያደርጉ የትራምፕን የአሽሙር አድናቆት ጨምሮ የብዙዎችን ትኩረት መሳብ ችለው ነበር ።...
ኢማኑኤል ማክሮን በዚህ መልኩ ከታዩ በኋላ ግን ይህ ነው የሚባል ለውጥ እና ከፍተኛ ሽያጭ ሳያይ አመታትን ያሳለፈው ካምፓኒ ፡ የኦንላይን መሸጫ ዌብሳይቱ መጨናነቅ ጀመረ ።

በተለይ ማክሮን አድርገው የታዩት Henry Jullien Pacific S 01 የሚባለውን መነፅር የሚፈልጉ በሺህ የሚቆጠሩ ሰወች መነፅሩን ለመግዛት በኦንላይን መሻማት ጀመሩ ።...
ከሰአታት በኋላም ፡ ከዚህ በፊት አይቶ የማያውቀው ብዛት ያለው ጎብኚ ማስተናገድ ከአቅሙ በላይ የሆነው የካምፓኒው ዌብሳይት ለበርካታ ሰአታት ክራሽ አድርጎ ሁሉ ነበር ። እንደገና አስተካክለውት ነው ወደስራ የተመለሰው ። ...
በዚህ መልኩ ፡ ባላሰበውና ፡ ባልገመተው ሁኔታ በአውሮፓ መድረክ ላይ ፡ በፈረንሳይ ፕሬዝደንት የነጻ ማስታወቂያ የተሰራለት ይህ ካምፓኒ ፡ በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠሩ ትእዛዞችን ተቀበለ ።

በ126 አመት ታሪኩ አይቶት በማያውቀው ሁኔታ ፡ ሽያጩ በ65 ፐርሰንት የጨመረው ሄነሪ ጁሊያን ፡ አሁን ላይ ከመላው አለም ትእዛዝ እየተቀበለ ሲሆን ፡ ለጊዜው ግን በመጋዘኑ አጭቋቸው የነበሩትን መነፅሮች ፡ በ 770 ዶላር ዋጋ ፡ ( ከ150 ሺህ ብር በላይ) በሰአታት ውስጥ ሽጦ ጨርሷል ።

  (በእውቀቱ ስዩም)ከጅረት አጠገብ ፣ ቆሞ የኖረ ዛፍ መብረቅ ገነደሰውአሁን ድልድይ ሆኖ ፣ ያሻግራል ሰው''አለቀለት'' ያሉት ፤ ተልዕኮው መች አልቆቆሞ የጠቀመ ፣ መላ አያጣም ወድቆ ፤በው...
21/01/2026


(በእውቀቱ ስዩም)
ከጅረት አጠገብ ፣ ቆሞ የኖረ ዛፍ
መብረቅ ገነደሰው
አሁን ድልድይ ሆኖ ፣ ያሻግራል ሰው
''አለቀለት'' ያሉት ፤ ተልዕኮው መች አልቆ
ቆሞ የጠቀመ ፣ መላ አያጣም ወድቆ ፤

በውቄ ❤

ዓለምን ያሳዘነው ዜና:-በደቡብ አፍሪካ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ13 ታዳጊዎች ህይወት አለፈበትላንትናው እለት በደቡብ አፍሪካ Vanderbijlpark (ከጆሃንስበርግ ወጣ ብሎ በሚገኝ ስፍራ)...
20/01/2026

ዓለምን ያሳዘነው ዜና:-በደቡብ አፍሪካ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ13 ታዳጊዎች ህይወት አለፈ

በትላንትናው እለት በደቡብ አፍሪካ Vanderbijlpark (ከጆሃንስበርግ ወጣ ብሎ በሚገኝ ስፍራ) እጅግ ልብ የሚሰብር አደጋ ተከስቷል።

ወደ ትምህርት ቤት በማቅናት ላይ የነበሩ ታዳጊዎችን የጫነ ሚኒባስ ከከባድ መኪና (Truck) ጋር በመጋጨቱ የ13 ህጻናት ህይወት አልፏል።

የ2026 የትምህርት ዘመን ገና መጀመሩ በሆነበት በዚህ ወቅት፣ ልጆቻቸውን ለትምህርት የሸኙ ወላጆች አስከፊውን መርዶ ለመስማት ተገደዋል።

በተለይም ከአንድ ቤተሰብ ሁለት ልጆቿን ያጣችው እናት ሁኔታ የሚይዙት የሚጨብጡትን የሚያሳጣ እና እጅግ ልብ የሚነካ ነው።

በሁሉም ዓለም ያሉ አሽከርካሪዎች የነገ ተስፋ የሆኑ ህጻናትን ህይወት እየመሩ መሆኑን ተረድተው በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያሽከረክሩ ምክር ተላልፏል።

* ፈጣሪ ለወላጆች፣ ለዘመድ አዝማድና ለወዳጅ ዘመድ ሁሉ ብርታቱን ይስጥ።

ለታዳጊዎቹ ነፍስ እረፍትን፣ ለቤተሰቦቻቸው ደግሞ ጽናትን እንመኛለን።

Via :- AP

ጉርሻ page

🌴🌴🌴

18/01/2026

በፑንትላንድ በቁጥጥር ስር ከዋሉት 42 የISIS ታጋዮች መካከል 23ቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተረጋገጠ

የፑንትላንድ የጸጥታ ኃይሎች በሰሜናዊ ሶማሊያ ባካሄዱት መጠነ ሰፊ የካልሚስካድ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር የዋሉ የውጭ ሀገር የISIS ታጋዮችን ዝርዝር ይፋ አድርገዋል በዚህ መረጃ መሠረት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ታጋዮች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ማለትም ሀያ ሶስቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ታውቋል

ይህም ዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡድኑ ISIS በኢትዮጵያ ውስጥ ሰፊ የቅጥር እና የማደራጀት ስራ እየሰራ መሆኑን የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ ነው

በቁጥጥር ስር የዋሉት ኢትዮጵያውያን ስም ዝርዝር እንደሚያሳየው፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ መሆናቸው ስጋቱን ከፍ ያደርገዋል። ከኢትዮጵያውያኑ በተጨማሪ የየመን፣ የቱርክ፣ የሞሮኮ እና የታንዛኒያ ዜጎች በቡድኑ ውስጥ ተሳታፊ ሆነው ተገኝተዋል።

ይህ አሳሳቢ መረጃ እንደሚያመለክተው አክራሪ ኃይሎች በሀገሪቱ ውስጥ በስውር መረባቸውን በመዘርጋት ወጣቶችን ለሽብር ተግባር እያሰለጠኑ ወደ ጎረቤት ሀገራት እያሰማሩ ይገኛሉ

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስት በአሁኑ ወቅት በሃይማኖት አክራሪዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ በመቀጠል ይህንን ውስጥ ለውስጥ እየተካሄደ ያለን አደገኛ እንቅስቃሴ ከወዲሁ ሊታገለው ይገባል

የሀገሪቱን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅም በስውር የሚንቀሳቀሱ የሽብር መረቦችን የመበጣጠስ ስራ የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው

በመሆኑም መንግስት ከጎረቤት ሀገራት የደህንነት ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከር እና በሀገር ውስጥ ያለውን ጥብቅ ክትትል በማስቀጠል ይህንን ስር እየሰደደ የመጣውን የአክራሪነት ስጋት ሳይባባስ ሊያስቆመው እንደሚገባ ተመልክቷል

የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ የሚሰጠውን ይፋዊ ምላሽ እናቀርባለን

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በጸጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የቱሉ ሞዬ የጂኦተርማል (የእንፋሎት) ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን እንደገና ለማስጀመር፣ በመንግስት እና በአልሚ ኩባንያው መካከል ድርድ...
18/01/2026

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በጸጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የቱሉ ሞዬ የጂኦተርማል (የእንፋሎት) ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን እንደገና ለማስጀመር፣ በመንግስት እና በአልሚ ኩባንያው መካከል ድርድር በይፋ መጀመሩን ሪፖርተር እንግሊዘኛው ጋዜጣ ዘግቧል።

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የሚገኘውን ይህን ፕሮጀክት መልሶ ለማስጀመር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የፍትህ ሚኒስቴር እና የማዕድን ሚኒስቴር ተወካዮች የተካተቱበት ኮሚቴ ከአልሚዎቹ ጋር እየተደራደረ ይገኛል። ሆኖም አልሚዎቹ ከዚህ በፊት በነበረው የኃይል ግዢ ስምምነት ላይ ያልነበሩ አዳዲስ ጥያቄዎችን አቅርበዋል። ከጥያቄዎቹ መካከል፡-

ከኤሌክትሪክ ሽያጭ የሚገኘውን ትርፍ ወደ ዶላር ቀይሮ ወደ ውጭ ሀገር ለማጓጓዝ ዋስትና እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያ የፈረመችው የኒውዮርክ የግልግል ዳኝነት ስምምነት በውሉ ውስጥ እንዲካተት ፈልገዋል።

እ.ኤ.አ. በ2017 የተጀመረውና 150 ሜጋ ዋት ያመነጫል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው ይህ የሁለት ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክት፣ እ.ኤ.አ በ2024 ሥራውን አቋርጦ ወጥቶ ነበር። አልሚው ኩባንያ "የኦነግ ሸኔ" ታጣቂዎች በፈጠሩት የጸጥታ ስጋት ምክንያት ሥራውን እንዳቆመ ቢገልጽም፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ግን ምክንያቱ የፋይናንስ እጥረት እና በቦታው ላይ በቂ የጂኦተርማል እንፋሎት አለመገኘቱ ነው ብሏል።

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ አበበ ደገፋ በበኩላቸው፣ በቦታው ላይ የታሰበውን ያህል እንፋሎት አለመገኘቱ እና አበዳሪ ተቋማት ይህንን አይተው ፈንድ ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ስምምነቱን ማሻሻል አስፈላጊ እንዳደረገው ገልጸዋል።

ድርድሩ ከተሳካ ፕሮጀክቱ በታቀደው ልክ 150 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅሙን እንደማ ይቀይር ተገልጿል።

በልጅነቴ ትምህርት ቤት ውስጥ አንድ የክፍል ተማሪ ደብተሬን ቀደደብኝ። እና ለአስተማሪዋ የደረሰብኝ በደል ለመናገር ስሄድ የተማሪው እናት አስተማሪዋ ሆኗ አገኘዋት። ቢሆንም የእኔ ፀባይ ጨዋ ...
17/01/2026

በልጅነቴ ትምህርት ቤት ውስጥ አንድ የክፍል ተማሪ ደብተሬን ቀደደብኝ። እና ለአስተማሪዋ የደረሰብኝ በደል ለመናገር ስሄድ የተማሪው እናት አስተማሪዋ ሆኗ አገኘዋት። ቢሆንም የእኔ ፀባይ ጨዋ የሚባል ስለነበር ሚዛናዊ ፍርድ ትሰጠኛለች ብዬ ጠብቄ ነበር። ነገር ግን ያን ማሰቤ ሞኛሞኝ ከማስባል ውጪ ፋይዳ አልነበረውም። አስተማሪዋ ለበደለኝ ልጇ “ይህ ጥፋት እንዳይደገም እሺ” ብላ አለፈችው።

በዚህ ተራ ንግግር ላሽ የተባለው ተማሪ ያበሽቀኝ ጀመር። ይህንንም ለመቋቋም ስላልቻልኩ እንባዬን ቋጥሬ ወደ ዴክሴ ሄጄ ተቀመጥኩ። በመጨረሻ ግን ማድረግ የምችለው የዛን ልጅ መፅሀፍ ቀዳዶ መጣል እንደሆነ ተገነዘብኩ። ይህንንም ተግባሬን ፈጽሜ ፍትሐዊ ቅጣት አገኘሁ። ከዛ ግዜ በኋላ ይህቺ አለም እንዴት እንደምትንቀሳቀስ ተገለጠልኝ። በተበደልነው ነገር ከማልቀስ ይልቅ በወሰድነው የበቀል እርምጃ የሚደርስብንን ቅጣት ማጣጣም የበለጠ ዲሞክራቲክ ነው!። 🙌🏼😊

''ጠዋት ታይተው ማታ የጠፉ ህልፈታቸው ተመሳሳይ የሆነ ተወዳጅ አርቲስቶች ..............''ጠዋት ለስራ ወተው ታመሙ ሆስፒታል ሲደርሱ አረፉ ከሚል ዜና ውጭ የሞታቸው ምክንያት በዝርዝ...
16/01/2026

''ጠዋት ታይተው ማታ የጠፉ ህልፈታቸው ተመሳሳይ የሆነ ተወዳጅ አርቲስቶች ..............''

ጠዋት ለስራ ወተው ታመሙ ሆስፒታል ሲደርሱ አረፉ ከሚል ዜና ውጭ የሞታቸው ምክንያት በዝርዝር ያልታወቀ እና ለህዝብ ይፋ ያልተደረገው ምርጥ ኢትዮጵያዊ አርቲስቶች ከብዙዎቹ በጥቂቱ.........

ይህ ተመሳሳይ የአርቲስቶቹ ህልፈት እንደት ያዩታል በቅንነት ሀሳብዎን ያካፍሉን?

16/01/2026

ከጠጠሮች ተርታ ወጠህ ከአልማዞች ጎራ መሰለፍ ትሻለህ?

እንግዲያስ የሚያጠነክር ፈተናን እና መከራ ስጠኝ ይሁን ፆለትህ.....

አልማዝ በተፈጥሮ መንገድ እንዴት እንደሚሰራ ልንገራችሁ። አልማዝ የሚሰራው HPHT በሚባል Process ነው። HPHT ማለት High Pressure High Temperature ማለት ነው። አንድ አልማዝ አልማዝ ከመሆኑ በፊት አራት ደራጃዎችን ማለፍ ይኖርበታል። አንደኛ ከምድር በታች ከ300 እስከ 600 ኪሎ ሜትር ዝቅ ብሎ መቀመጥ። ሁለተኛ ከፍተኛ ሙቀት መታደል፣ ከ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬት ቃጠሎ ውስጥ መቀመጥ። ሶስተኛ ከፍተኛ ጭነት ማግኘት። አራተኛ ለረዥም ጊዜ ውስጥ በነዚህ ሁኔታ ውስጥ መቆየት ! እንግዲህ አንድን የድንጋይ ከሰል ወስዳችሁ ከምድር በታች 600 ኪሎ ሜትር ብታወርዱት፣ 1200 ዲግሬ ስንቲ ግሬት ቃጦሎ ውስጥ ብታኖሩት፣ በከፍተኛ ፕሬዠር ውስጥ ብታስቀምጡት እና ለረዥም ጊዚያት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ብትተዉት። ከሱሉ አልማዝ ይሆናል ! ከሰሉ ወደ ዳይመንድ ይለወጣል።

አንዳንዶቻችሁ በህይወታችሁ ግራ ይገባችኋል፣ በጣም የሚወዳችሁ አምላካችሁ ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር አውርዷችሁ ይሆናል። በማይገባችሁ ፈተና 1200 degree cent great ቃጠሎ ውስጥ አስቀምጧችሁ ፤ በማጣት፣ በመገለል፣ በመገፋት ለረዥም ጊዚያት እየፈተናችሁ "ምንድነው እየተካሄደ ያለው" ብላችሁ እስክትጠይቁ ድረስ ለአምስት አመት፣ ለአስር አመት ከሰው፣ ከወዳጅ፣ ከዘመድ፣ ከጓደኛ ዝቅ አድርጓችሁ ይሆናል። ....

"ምን ማለት ነው የሚወደኝ አምላክ ይሄን የሚፈቅደው" ስትሉ .... አልማዝ አድርጎ ሊሰራችሁ፣ ውብ አድርጎ፣ ሊሰራችሁ፣ የምታበሩ አድርጎ ሊያበጃችሁ፣ እንቁ፣ ዳይመንድ፣ አልማዝ ሊያደርጋችሁ ስላሰበ ነው !

አልማዝ ሰባት ባህሪዎች አሉት። አንደኛ ጠንካራ ነው። ወስዳችሁ በድንጋይ ቀጥቅጡት አይሰበርም። በሰይፍ ምቱት አይሰነጠቅም። በመጋዝ ገዝግዙት አይቆረጥም። በአልመዝ ግን ብረት ይቆረጣል፣ በአልማዝ ግን ሰይፍ ይቆረጣል። በአልማዝ ግን ድንጋይ ይፈርሳል። አልማዝ የሚቆረጠው በሌላ አልማዝ ነው። ሁለተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። ከፍተኛ የማንጸባረቅ ባህሪ አለው። refractive index ይባላል። የተቀበለውን ብርሃን መልሶ የማብራት ባህሪ አለው። ያንጸባርቃል። ሶስተኛው የአልማዝ ባህሪ የተቀበለውን የጸሐይ ብርሃን፣ ነጩን ብርሃን ወደ ተለያዩ በርካታ ቀለማት የመበተን ችሎታ አለው። አራተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። እጅግ በጣም ንጹህ ነው። አልማዝ የሚታወቀው በነጹህነቱ ነው። አምስተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። አልማዝ በእሳት አይቃጠልም። አንድ ቤት ውስጥ አልማዝ አለ እንበል ያ አልማዝ ያለበት ቤት ሙሉ ለሙሉ ቢቃጠል አልማዙ ምንም አይሆንም። ምንም። በነበረው ቅርጹ፣ በነበረው ንጽህናው እናገኘዋለን። የሚያስገርመኝን ስድስተኛውን የአልማዝን ባህሪ ልንገራችሁ። ወርቅ ላይ አሲድ ድፉበት ወርቁ ይበላሻል። አልማዝ ላይ አሲድ አፍስሱበት ምንም አይሆንም። አይበላሽም። የመጨረሻው እና ሰባተኛው የአልማዝ ባህሪ በጣም ውድ ነው። በጣም ውድ ነው። የአውራጣትህን ራስ የምታክል ዳይመንድ አንድ ትልቅ ፎቅ ይገዛል። በጣም ውድ ነው።

ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር ወርዳችሁ ፣ በ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬት ስቃይ ውስጥ ያለፋችሁ፣ በፕሬዠር ውስጥ ለበርካታ አመታት ያለፋችሁ እናንተ አልማዝ ሁናችሁ የተሰራችሁ ሰዎች ናችሁ። ሰዎች ጠጠር ብትመስሏቸውም አልማዞች ናችሁ። ዋጋችሁ በጣም ውድ ነው። ... ከተማሩ ሰዎች ይልቅ፣ ብዙ ድግሪ ከተሳካላቸው ሰዎች ይልቅ፤ በመከራ ያለፉ ሰዎችን አከብራለሁ። ዋጋ የከ

በደብረሲና ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ላይ ግድያ ተፈጸመ::​በዛሬው ዕለት የደብረሲና ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ወንድምሲገኝ ማሙዬ በድንገተኛ ጥይት በአሰቃቂ ሁኔታ መገ...
16/01/2026

በደብረሲና ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ላይ ግድያ ተፈጸመ::

​በዛሬው ዕለት የደብረሲና ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ወንድምሲገኝ ማሙዬ በድንገተኛ ጥይት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የአስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

​አመራሩ "ሕዝባቸውን ለማገልገልና የከተማዋን ብሩህ ተስፋ እውን ለማድረግ" ደከመኝ ሳይሉ ሲሰሩ የቆዩ መሆናቸውን ፓርቲው ገልጿል።

​ግድያው "ባልታሰበ ሁኔታ" የተፈጸመና "ትልቅ ሀገራዊ ኪሳራ" መሆኑ ተጠቅሷል።

​እስካሁን ድረስ ጥቃቱን የፈጸመው አካል ማን እንደሆነ በይፋ የተገለጸ ነገር የለም።

​የከተማዋ አስተዳደርና የሥራ ባልደረቦቻቸው በክስተቱ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል።

Via ደብረሲና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት

ጉርሻ page

🌴🌴🌴

Address

ADDIS ABABA
Addis Ababa
171200

Telephone

+251913662475

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mesfin photo editor posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share