Ethio saving and credit corporative society Ltd

Ethio saving and credit corporative society Ltd Our mission is save together to growth together...

28/03/2025
⛔️የኢትዮ ቁጠባ እና ብድር  ኃላ/የተ/መ/ህ/ስ/ማህበር  የትምህርትና ቅስቀሳ ንዑስ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በመገናኘት በቀጣይ ስራዎች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገናል።በቀጣይም ንዑስ ኮሚቴው ማህበ...
27/03/2025

⛔️የኢትዮ ቁጠባ እና ብድር ኃላ/የተ/መ/ህ/ስ/ማህበር የትምህርትና ቅስቀሳ ንዑስ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በመገናኘት በቀጣይ ስራዎች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገናል።

በቀጣይም ንዑስ ኮሚቴው ማህበሩን የተሻለ ደረጃ ለማድረስ ማህበሩ የሚሰራቸውን ስራዎች ለህብረተሰቡ በማድረስ የተሻለ የአባላት ቁጥር እንድኖረው ሁሉም የኮሜቴው አባላት በእኔነት ስሜት እንደሚሰሩ ተግባብተናል።
17/7/2017

22/03/2025

Save today for a better tomorrow

አዳራሽ በመያዙ ምክንያት ስብሰባ ቦታው ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 05 ጎፋ ካምፕ ወጣቶች መዝናኛ ማእከል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
29/01/2025

አዳራሽ በመያዙ ምክንያት ስብሰባ ቦታው ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 05 ጎፋ ካምፕ ወጣቶች መዝናኛ ማእከል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

13/09/2024

ወደ ኢትዮ ገንዘብ ቁጠባ ብድር ኃ/ የተ/ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር የተቀላቀላችሁ ውድ እህትና ወንድሞች እንኳዎን ወደ ህብረት ስራ ማህበራችን ደህና መጣችሁ እያልን ህብረት ስራ ማህበራች በህብረት ስራ በቂ ልምድ ባላቸው አባላት የተመሰረተ እና ከአባላት ቁጠባን በማሰባሰብ የአባላትን ኑሮ ለማሻሻል ትልቅ ራዕይ አንግቦ የሚሰራ ህብረት ስራ ማህበር ሲሆን እርስዎም የህብረት ስራ ማህበራች ( ኢትዮ) አባል በመሆንና በመቆጠብ እንዲሁም በመበደር ብድሩንም ለታለመት አላማ በማዋል እና ብድሩን በወቅቱ እስከነ ወለዱ በመመለስ የአባላት ኑሮ እንዲሻሻል ጥረት የሚደርግ ህ/ስ/ማህበር ነው ። ተጨማሪ መረጃ ቢሮአችን መጥተው ለማግኘት አድራሻችን ጎፋ ገብርኤል አደባባይ ሙላቱ ኬሮ ህንፃ 3 ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 51 ነው ።
የህብረት ስራ ማህበራችን የቁጠባ አካውንት
አቢሲንያ ባንክ 63 86 87 79
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000 47 17 36 787
ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 10 17 4000 66 845 ሲሆን በሚመቸን እና በሚቀርበን በንክ ቁጠባችን ማስገባት እንችላለን ።
ለበለጠ መረጃ 0910350666 ይደውሉልን

13/09/2024

መመዝገቢያ...................1000.00
ቁጠባ................................300.00 ጀምሮ
ዕጣ/ሼር............................2000.00 ጀምሮ
1ዕጣ 500.00 ሲሆን ለአባልነት ከ4 እስከ 500 እጣ መግዛት ይቻላል ።
2 ጉርድ ፎቶ
የአዲስ አበባ መታወቂያ ያለው/ ያላት ሲሆን በተጨማሪም ቢሮ ቀርቦ በቂ ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል ።
ኑ!ለተሻለ ነገ ዛሬ እንቆጥብ!!

13/09/2024

የመስከረም መባቻ ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት የቀደመ ዓመታቸውን አጠናቀው የቀጣዩን አዲስ ዓመታቸው ዑደት አንድ ብለው የሚጀምሩበት ነው፡፡ ቀንና ሌሊቱ እኩል 12 ሰዓት የሚሆንበት የአዲስ ተስፋ ብስራትም ቀን ነው፡፡
አበቦች በምድር ላይ የሚፈኩበት፣ የደፈረሰው የሚጠራበት፣ ምድሩ ሁሉ የሚፈካበት የአዲስ ዓመት፣ የአዲስ ዘመን መለወጫ ነው ።
የተከበራችሁ የኢትዮ ገንዘብ ቁጠባ ብድር ኃ/የተ/ህብረት ስራ ማህበር አባላት እና በህብረት ስራ ማህበራችን የምትቆጥቡ ህፃናት በሙሉ ከነመላ ቤተሰቦቻችሁ እና ወዳጆቻችሁ ጋር እንኳን ለ2017 አዲስ አመት አደረሳችሁ ።
በአዲሱ አመት በ2017 ካሳለፍናቸው አመታት በተሻለ ጠንክረን፤ በአባል ቁጥር በዝተን ፤ ካፒታላችንን አሳድገን ፤ አባሎቻችንን በብድር ተጠቃሚዎች አድርገን ፤አባላት በተለያዩ ኢንቨስትመንት ተሰማርተው እና ተለውጠው የምናይበት ፤ አባላት የምትኮሩበት እና የምትተማመኑበት ተቋም በጋራ አድርገን የምንሰራበት አመት እንዲሆን እንመኛለን።
እነዚህን ለማከናወን የሁላችንም አባላት ተሳትፎና ጥረት የሚያስፈልግ ሲሆን አብረን በህብረት ለተቋማችን ሰርተን የወደፊት ግዙፍ የህብረት ስራ ማህበር በማድረግ ተወዳዳሪና ተመራጭ ተቋም የማድረግ ሀላፊነት በሁላችንም እጅ ላይ ነው ።
የእያንዳንዱ አባላት ግዴታዎች
1. መደበኛ ቁጠባን በየወሩ መቆጠብ
2. ከአባልነት ሼር በተጨማሪ ሼር መግዛት
3.ቢያንስ 3 አባል ማስገባ
4. ብድር መበደር
5.ብድርን በወቅቱ መመለስ እና በተበደሩት ብድር ለውጥ በማምጣት ላልተበደሩ ምሳሌና አርአያ መሆን
6.ባለን እውቀት ፣ ሀብት እና ጉልበት ተቋሙን ማሳደግ
7.በሚኖሩን የጠቅላላ ጉባኤዎችና ስብሰባዎች መገኘትና የነቃ ተሳታፊ መሆን እና በመተዳደሪያ ደንቡ የተቀመጡትን አካቶ

የእያንዳንዱ አባላት መብቶች
1.የምረጥ እና ድምፅ የመስጠት
2.በተሳትፎው ልክ የመጠቀም
3.ብድር የመበደር
4.ጥያቄዎችን የመጠየቅ
5.በስብሰባዎች የመሳተፍ የመሳሰሉት እና በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ የተጠቀሱት አካትቶ

የምንሰጣቸው የቁጠባ አይነቶች
1.መደበኛ ቁጠባ
2.የፍላጎት ቁጠባ
3.የህፃናት ቁጠባ
4. የጊዜ ገደብ ቁጠባ

የምንሰጣቸው የብድር አይነቶች

1.የአጭር ጊዜ ብድር፦ ለማህበራዊ አገልግሎት፣ለቤት እቃ ማሟያ ፣ለትምህርት ....
2.የመካከለኛ ጊዜ ብድር፦ ለንግድ ማስፋፊያና ማስጀመሪያ
3.የረጅም ጊዜ ብድር፦ ለቤት እና ለመኪና መግዣ

ኑ! ለተሻለ ነገ ዛሬ እንቆጥብ!!

Save and gain what u need...... Ethio saving
05/07/2022

Save and gain what u need...... Ethio saving

05/07/2022

ማስታወቂያ
#ትንሹን ዕጣ ማለትም አንድ አባል ሲገባ 4 ዕጣ መግዛት እንዳለበት ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ዕጣውን ገዝታችሁ ያልጨረሳችሁ ዕጣውን ገዝታችሁ እንድትጨርስ እናሳስባለን፡፡
#አራት ዕጣ የገዛችሁ ተጨማሪ ዕጣ መግዛት ስለምትችሉ መግዛት እንዳትረሱ፡፡
#በጉባኤው እደተወሰነው 5000 ዕጣ ለሽያጭ የቀረበ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም አንድ አባል 10% ለገበያ የቀረበውን መግዛት ይችላል፡፡ በዚህም መሠረት አንድ አባል እስከ 500 ዕጣ መግዛት ይችላል፡፡ በየ አመቱ መጨረሻ የቁጠባና የዕጣ ምጥጥን እደተጠበቀ መሆኑን እንዳንረሳ፡፡

05/07/2022

የሐምሌ ወርሃዊ ቁጠባ በመድረሱ እስከ ሀምሌ 8/2014 ድረስ በመቆጠብ የቁጠባ ባህላችንን እናሳድግ፡፡ ሁላችንም የምንቆጥበውን ወርሃዊ ቁጠባ ወር በገባ ከ1-8 በማስገባት ህ/ስ/ማህበራችንን የገንዘብ አቅም በማሳደግ ለአባላችን የብድር ሁኔታዎች እናመቻች፡፡
#ለመበደር የምትፈልጉ አባላት ቢሮ ድረስ በመምጣት ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት መበደር ትችላላችሁ፡፡

30/05/2021

For more information call us on 0910725009 and 0925999412

Address

Gofa Gebreal Adebabay Mulatu Kero Building 4floor
Addis Ababa
1000

Telephone

+251910350666

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio saving and credit corporative society Ltd posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share