Addis Info Center

Addis Info Center Y
E
S

We Can🙏
(1)

19/06/2026
19/06/2026
19/06/2026
19/06/2026
19/06/2026

የህወሓት መጨረሻ ተቃረበ

19/06/2026

የክረምት በጎ ባህሎቻችንን ወደ ላቀ መገለጫነት እናሻግራለን፡፡

ሰኔ 12 /2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያውያን ባለፉት የለውጥ ዓመታት ክረምት በመጣ ቊጥር የምንከውናቸው ሁለት አንኳር ባህሎችን እየገነባን መጥተናል፤ ኢትዮጵያን አረንጓዴ ማልበስ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፡፡

ኢትዮጵያ የደን ሀብቷ እየተመናመነ፣ የዐፈር መሸርሸር እና ድርቅ ተጋላጭነቷ እየጨመረ መምጣቱን በመገንዘብ መንግሥት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን በሚሊዮን ችግኞች ተከላ በማብሰር ከጥቂት ዓመታት በፊት ጀምሯል፡፡

ኢትዮጵያውያንም ይህንን በጎ ጅምር እና የመዳረሻ ትልም በላቀ ደረጃ በመገንዘብና የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብሩን በተነሣሽነት በመተግበር ዓለምን ያስደመሙ ስኬቶችን አስመዝግበናል፡፡ በሂደቱ የምግብ፣ የደን እና የውበት ችግኞችን በመትከል ዐሻራችን እያኖርን ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ ባህላችንን በእጅጉ አጎልብተናል፡፡

በየዓመቱ በርካታ ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የዓለም ሕዝብን ከአምስት እጥፍ የሚበልጥ ከ48 ቢሊዮን ላይ ችግኞች ተክለናል፤ በዚህም የኢትዮጵያን የደን ሽፋን ትርጒም ባለዉ መጠን አሳድገናል፤ ለምግብ ሉዓላዊነታችን መሠረት መጣል ጀምረናል፤ የፍራፍሬ የወጪ ንግዳችን አሳድገናል።

ከሁለት ዓመታት በፊት ይፋ በተደረገ የጥናት ውጤት መሠረት የደን ሽፋናችን እጅግ ከተመናመነበት በከፍተኛ ፍጥነት አገግሞ ወደ 23.6% አድጓል፡፡

በልዩ ኹኔታ የኢትዮጵያውያንን የተቀናጀ እና የተሰናሰነ ተነሣሽነት በሚጠይቁ የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሮችም የዓለምን ትኩረት በሳበ መልኩ ሚሊዮኖች በአንድ ጀምበር እየወጣን በመትከል የራሳችንን ክብረ ወሰን በራሳችን ደጋግመን እያሻሻልን መጥተናል፡፡

በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የተከልናቸው የምግብ፣ የደን እና የውበት ችግኞች የኢትዮጵያን ኹለንተና የሚቀይሩ፣ የምግብ ሉዓላዊነታችንን የሚያረጋግጡ፤ የአበባ እና ፍራፍሬ ወጪ ንግዳችንን ዕድገት እየለወጡ ያሉ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም ዐቅም ያጎለበቱ ናቸው፡፡

በመኾኑም ይህ ክረምት በመጣ ቊጥር በንቅናቄ የሚከናወን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ባህል የበለጠ እንዲጠናከርና እንዲጎለብት በትጋት መሥራታችንን እንቀጥላለን፤ ኢትዮጵያን አረንጓዴ በማልበስ ንጹሕ አየር ለዓለም እናበረክታለን፡፡ ዘንድሮም የራሳችንን ክብረ ወሰን በራሳችን የላቀ የሚሊዮኖች ተሳትፎ በማሻሻል ጭምር ከ8 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን እንተክላለን፡፡

የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትም ሌላኛዉ ዐዲስ እያደገ የመጣ ልምምዳችን ነው፡፡ ወጣቶች ዕውቀታቸዉን እና ከትምህርት የተረፈ ጊዜያቸውን፣ ባለሀብቶች ደግሞ ሀብታቸውን በማዋጣት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉ ዐቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በመገንባት፣ ማዕድ በማጋራት እጅግ የተዋጣለት ልምምድ አዳብረዋል፡፡

የመንግሥት ተቋማትም በቁጠባ ከሚጠቀሙት ሀብታቸው በማዋጣት ይህንን የበጎ አድራጎት ልምድ የማስፋት እና ወደ ላቀ ባህል ደረጃ የማሳደግ ኃላፊነትን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡

በለውጡ ዓመታት በአዲስ አበባ እና በክልሎች የበርካታ ዐቅመ ደካሞች ቤት ታድሷል፤ በዐዲስ መልክ ተገንብቷል፤ ሕይወታቸዉ እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡ በከተሞች የተጀመረዉ የኮሪደር ልማት ወደ ገጠር ተስፋፍቷል። ኢትዮጵያውያን ችግሮቻችንን ተጋግዞ የመፍታት ባህል እያዳበርን መጥተናል፡፡

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደየአካባቢያቸው በመሄድ እና በወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ታናናሾቻቸውን እያስተማሩ፣ እንደ ደም ልገሳ ያሉ ሕይወት አዳኝ ተግባራትን እያስተባበሩ፣ ዐቅመ ደካሞችን በማገዝ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው፡፡

በመኾኑም በየክረምቱ በበጎ ልምድነት እያሳደግናቸው የመጡ የአረንጓዴ ዐሻራ እና የበጎ ፈቃድ ሥራዎች የበለጠ ሀገራዊ መገለጫችንና ባህላችን እንዲኾኑ ዘንድሮም ካለፉት ዓመታት የላቀ ተሳትፎ የሚጠይቅ ዕቅድ ተዘጋጅቷል፤ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል።

በተደመረ ዐቅማችን የኢትዮጵያን ዕቅድ በሚገባ ለማሳካት ቅድመ ዝግጅት ጨርሰን ወደ ትግበራ ገብተናል። ድላችንን በጋራ የምናበስርም ይኾናል።

የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

19/06/2026
ቃላት በማሳመር ህገ-ወጥነትን መሸፈን ፈፅሞ አይቻልም። ሁሉም ህግና ስርዓት አለው። በተገኘው ሶሻል ሚድያ ቃላት አሳምሮ በመናገር ከህግ ተጠያቂነት አያድንም።
18/06/2026

ቃላት በማሳመር ህገ-ወጥነትን መሸፈን ፈፅሞ አይቻልም።

ሁሉም ህግና ስርዓት አለው። በተገኘው ሶሻል ሚድያ ቃላት አሳምሮ በመናገር ከህግ ተጠያቂነት አያድንም።

ሰበር ዜና! = = = የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ሰላም በሚያደፈርሱ ግለሰቦች ላይ የቪዛ እገዳ ጣለ!በቅርቡ በጽንፈኛ የህወሓት (TPLF) አባላት እና በኢትዮጵያ መንግስት መካ...
18/06/2026

ሰበር ዜና!
= = =
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ሰላም በሚያደፈርሱ ግለሰቦች ላይ የቪዛ እገዳ ጣለ!

በቅርቡ በጽንፈኛ የህወሓት (TPLF) አባላት እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የተፈጠረው ውጥረት በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት ሊቀሰቅስ ይችላል የሚል ስጋት በማሳደሩ፤ አሜሪካ የታለመ የቪዛ ክልከላ እርምጃ ወስዳለች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እንዳስታወቁት፣ ይህ የቪዛ እገዳ በትግራይ ክልል ያለውን የሰላም ሂደት በማደናቀፍ ኃላፊነት በተጣለባቸው ጽንፈኛ የህወሓት አባላት እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ ያነጣጠረ ነው።

📌 **ዋና ዋና ነጥቦች፦**
🔹 **እገዳው በማን ላይ ነው?** በዋናነት ሰላምን በማደናቀፍ ተሳታፊ በሆኑት የህወሓት አመራሮች እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ የተጣለ ነው።

🔹 **የአሜሪካ አቋም፦** አሜሪካ በሰላም እና በክብር መኖር ለሚፈልገው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ (የትግራይን ህዝብ ጨምሮ) ያላትን አጋርነት አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጣለች።
🔹 **ተጠያቂነት፦** አሜሪካ ቀጠናውን ከሚያተራምሱ አካላት ተጠያቂነትን ለማስፈን መስራቷን እንደምትቀጥልም አስታውቃለች።

ሙሉ መግለጫውን ከታች ባለው ሊንክ ማንበብ ትችላላችሁ፦
🔗 [https://www.state.gov/releases/office-of-the-spokesperson/2026/06/announcement-of-targeted-visa-restrictions-for-individuals-involved-in-undermining-peace-in-ethiopia/]

#ኢትዮጵያ #ሰላም #አሜሪካ #ህወሓት #ትግራይ #ዜና

18/06/2026

በትምህርት ሥርዓታችን ውስጥ ትልቅ ለውጥ!

Address

Addis Ababa Ethiopoa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Info Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share