SEEN Consulting Architects PLC

SEEN Consulting Architects PLC Grade 1 Construction consulting Firms

The new sister company
01/05/2022

The new sister company

Bravo Senegal
06/02/2022

Bravo Senegal

24/01/2022
for general knowledge
07/12/2021

for general knowledge

03/06/2021

/ /

========================

👉በኮንስትራክሽን ውል ሁለት አይነት የግንባታ ስራ ርክክብ ያለ ሲሆን ይሄውም ግዚያዊ ርክክብ(provisional acceptance) እና የመጨረሻ ርክክብ(final acceptance) የሚያካትት ነው፡፡

👉በዚህ ጽሁፍ በዋናነት በኮንስትራክሽን ውል ህግ እውቅና የተሰጣቸውን የርክክብ አይነቶች ምንነትና ተያያዥ ውጤታቸውን አስመልክቶ የህግ ድንጋጌዎችን እና አሁን ላይ በመንግስት ተቋማት እየተሰራበት ያለውን የፒፒኤ 2011 ጀኔራል ኮንዲሽን ድንጋጌዎችን ባካተተ ሁኔታ ለማብራራት ተሞክሯል፡፡

/ /

👉ግዜአዊ ርክክብ በተለይ በኮንስትራክሽን ውል የተመለከቱ የግንባታ ስራዎች ተከናውነው ካበቁ በኋላ ወዲያውኑ ሁለቱ ወገኖች ማለትም አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በስራው ላይ የሚደረግ የምርመራ ማረጋገጫ ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3274(1) ይደነግጋል፡፡ ይሄውም አሰሪው በትክክል የተገነባውን ግንባታ በእጁ አግብቶ መያዙን ጭምር ያረጋግጣል፡፡ ስለዚህ ጊዜአዊ ርክክብ በዋናነት የተሰራውን የግንባታ ስራ አሰሪው መብቱን ጠብቆ በመጀመሪያ የሚረከብበት ሂደት ነው ማለት ነው፡፡በስራው ላይ ምርመራ መደረጉንም የሚያረጋግጥ ነው፡፡

👉ፒፒኤ 2011 ክሎስ 84.1 ላይ የስራ ምርመራ/verification and test/ በመሀንዲሱ ተቋራጭ ባለበት ሊደረግ እንደሚገባ በመርህ ደረጃ ተቀምጧል፡፡ሆኖም ግን ተቋራጩ ምርመራው ከሚካሄድበት እለት ከ30 ቀን በፊት በተገቢ ሁኔታ እንዲያውቀው ተደርጐ በምርመራው እለት ያልተገኘ እንደሆነ የስራ ምርመራው ተቋራጩ በሌለበት ሊካሄድ እንደሚችል ይፈቅዳል፡፡

👉እንግዲህ መሀንዲሱ ስራውን ከመረመረ በኋላ ያላመነበትን የስራ ክፍል ፈርሶ እንደገና እንዲሰራ ወይም እንዲጠገን ተደርጐ የጥራት ደረጃውን ባሟላ ሁኔታ እንዲከናወን ለማዘዝ እንደሚችል ፒፒኤ ክሎስ 85 ይፈቅድለታል፡፡

በዚህም መሰረት ግንባታው የስራ ምርመራውን ካለፈ አሰሪው ግንባታውን የሚረከበው ይሆናል ማለት ነው፡፡

👉ስለዚሁም የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት ለተቋራጩ የሚሰጠው ይሆናል፡፡በመሰረቱ ተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት እንዲሰጠው መጠየቅ ያለበት ስራው ሊጠናቀቅ ይችላል ብሎ ከሚያስብበት ከ15 ቀን በፊት መሆን ይኖርበታል፡፡ከዚያም መሀንዲሱ ጥያቄው በደረሰው በ30 ቀን ውስጥ የስራ ምርመራውን አጠናቆ ሰርተፍኬቱን መስጠት ወይም ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ ይኖርበታል፡፡መሀንዲሱ ሰርተፍኬቱን ሳይሰጥ ወይም ጥያቄውን ውድቅ ሳያደርግ 30 ቀኑ ያለፈ እንደሆነ ለተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት እንደተሰጠው ግምት እንደሚወሰድ ፒፒኤ ክሎስ 87 ያስቀምጣል፡፡

👉ሌላው ተቋራጩ በስራው ላይ ያደረገው መሻሻል/መለወጥ ቢኖር እንኳ በዝምታ ግዜአዊ ርክክብ ከተደረገ መሻሻሉ ተቀባይነት እንዳገኘ የህግ ግምት እንደሚያስወስድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(2) ይደነግጋል፡፡እዚህ ላይ ተቋራጩ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት የመስራት ግዴታ ያለበት መሆኑ ይታዎቅ፡፡ ስለዚህ የህግ ግምቱ እሳቤ ተቋራጩ ከዲዛይኑ በመውጣት አሻሽሎ የሰራው ስራ ኖሮ በግዜአዊ ርክክብ ወቅት በዝምታ አሰሪው ካለፈው እንደተቀበለው ይቆጠራል ነው፡፡

እንዲሁም ግዜአዊ ርክክብ መደረጉ የመድህንነት ጊዜው(warranty period) መጀመሩን እንደሚያመለክት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(3) ይደነግጋል፡፡

( / )

(warranty period) የሚባለው ከጊዜአዊ ርክክብ እስከ መጨረሻ ርክክብ ያለው ጊዜ ሲሆን አሰሪው ግንባታው በተቋራጩ በደህና ሁኔታ ስለመሰራቱ ለመመርመርና ለማረጋገጥ የሚያስችለው ጊዜ ነው፡፡የጊዜው ርዝማኔም በውላቸው ላይ የሚወሰን ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3277 ይደነግጋል፡፡ ሆኖም በውሉ ላይ የመድህንነት ጊዜው ርዝማኔ ያልተጠቀሰ እንደሆነ ከጊዜአዊ ርክክብ ቀን ጀምሮ 365 ቀን ስለመሆኑ የፒፒኤ ክሎስ 88.7 ያስቀምጣል፡፡

👉ተቋራጩ በዚሁ በመድህንነት ጊዜ በተለይ የተበላሹ ስራዎችን እንዲያድሳቸው በአሰሪው በታዘዘ ጊዜ የማስተካከል ግዴታ እንዳለበት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3278 ይደነግጋል፡፡ ለዚህም ለጥገና ወጭ ሲባል ከተቋራጩ ክፍያ ላይ ሪቴንሽን ገንዘብ(retention money or bond) 5% እየተቀነሰ በአሰሪው ይያዛል፡፡

👉በመድህንነት ጊዜ ውስጥ የተለዩ ብልሽት ያለባቸው ስራዎችን እንዲያስተካክል ተቋራጩ ተጠይቆ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ያላስተካከለ እንደሆነ አሰሪው የማስተካከያ ስራውን በተቋራጩ ወጭ በራሱ ወይም ሌላ ቀጥሮ ሊያሰራው ወይም ውሉን ሊያቋርጥ ስለመቻሉ ፒፒኤ ክሎስ 88.3 ለአሰሪው መብት ይሰጠዋል፡፡

/ /

👉በፒፒኤ ክሎስ 86 ላይ የግንባታ ስራው በከፊል እርክክብ የሚደረግበትንም አማራጭ ያስቀምጣል፡፡ይህ ማለት የተወሰነውን የስራ ክፍል(part of the work) ከአጠቃላይ ውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ በውል ላይ ከተቀመጠ ተቋራጩ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከአጠቃላይ የውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ ይገደዳል ማለት ነው፡፡በዚህም በአንድ ውል ውስጥ በተለያየ ጊዜ ጊዜአዊ ርክክብ ሊደረግ የሚችልበትን ሁኔታ ይፈጥራል ማለት ነው፡፡
****** ****** ******
/ /

👉የመጨረሻ ርክክብ/Final Acceptance/ በተለይ የመድህንነት ጊዜ ካለቀ በኋላ እና ተቋራጩ ጠቅላላ ግዴታዎቹን በደህና ሁኔታ የፈጸመ መሆኑን አሰሪው ሲያረጋግጥ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በእጁ የሚያደርግበት(definitively appropriate) ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279 ይደነግጋል፡፡

👉የመጨረሻ ርክክብ አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት በአስገዳጅ ሁኔታ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279(2) ላይ ተደንግጓል፡፡ሆኖም ጊዜአዊ ርክክብ/ Provisional Acceptance/ በሚመለከት ግን በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት የሚያስገድድ ግልጽ ህግ የለም፡፡ስለዚህ ስራው ተጠናቆ አሰሪው ግንባታውን በእጁ ካስገባ ጊዜአዊ ርክክብ መደረጉን የሚያስገነዝብ ይሆናል ማለት ነው፡፡በእርግጥ በጽሁፍ መደረጉ ይመከራል፡፡

👉በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3282 ላይ እንደተቀመጠው ከመጨረሻ ርክክብ በኋላ ተቋራጩ እስከ 10 አመት ድረስ ስለስራው አሰራር ጉድለት ተቋራጩ ሀላፊነት አለበት፣መድህን ሆኖ ይቀጥላል፡፡በመጨረሻ ርክክብ ወቅት የሚታዩ ለነበሩ ጉድለቶች(apparent defect) ግን ተቋራጩ ሀላፊነት የለበትም፡፡ሀላፊነቱ የሚመለከተው ግንባታው በውሉ የተመለከተውን የታለመለትን ጥቅም እንዳይሰጥ የሚያደርጉ ወይም አጠቃቀሙን በጣም ውድ የሚያደርጉና አክሳሪ የሚያደርጉ ጉድለቶችን ነው፡፡

👉የመጨረሻ ርክክብ መደረጉ የተቋራጩን መሰረታዊ ግዴታ የሚያወርድለት ሲሆን ቀሪ ክፍያ ካለው እንዲከፈለው እና ዋስትና እንዲወርድለትና የዋስትና መያዣ ገንዘብ ካለም እንዲለቀቅለት ለተቋራጩ መብት የመስጠት ውጤት እንደሚኖረው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3281 ይደነግጋል፡፡

👉ፒፒኤ ክሎስ 89 በተመሳሳይ ስለመጨረሻ ርክክብ የደነገገ ሲሆን የመጨረሻ ርክክብ ሰርተፍኬትም በመሀንዲሱ ለአሰሪውና ለተቋራጩ እንደሚሰጥ ያስቀምጣል፡፡

((((((((((በጉባኤ አሰፋ))))))))))

https://www.facebook.com/216094568731497/posts/1473834362957505/

የአ/አ/ከ/አ/ኮንስትራክሽን ቢሮ ግንቦት 26/2013

22/05/2021

- ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳዎቅ ፍፁም በጎነት ነው ። ሼር ሼር

safety alert!😃
27/02/2021

safety alert!😃

Address

Megenagna
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 15:00

Telephone

+251911970105

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SEEN Consulting Architects PLC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to SEEN Consulting Architects PLC:

Share