19/05/2017
ከዚህ በታች በፎቶ የምትመለከቱት ወጣት አማኑኤል አሰፋ ይባላል። የአእምሮ ህመምተኛ ነው የመጣው ከደብረ ታቦር 04 ቀበሌ
ሥላሴ አካባቢ አራዳ ገበያ ሰፈር ነኝ ይላል የ12ኛ ክፍል ት/ቱን በዳግማዊ ቴዎድሮስ ት/ት ቤት እየተከታተለ በግንቦት ወር 2008
ዓ.ም መግቢያ ላይ እንደወጣ አእምሮው መለስ ሲልለት ይናገራል።የቤተሰቡንም ስም አባቱ አሰፋ ንጉሴ ፣እናቱ የኔወርቅ
፣ወንድሞቹ ዳንኤል እና ይነበብ እህቶቹ መሉ አሰፋ ባህር ዳር universty ተማሪ እና ትነበብ አሰፋ እዛው ደብረ ታቦር ታቦር የሚባል
ት/ት የምትማር እንዳለችው ይናገራል የቤተሰብ ስልክ ስጠን ስንለው መናገር አይፈልግም ።በአሁኑ ሰዓት በአዋሽ 7 ኪሎ ቅድስት
ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ይገኛል የአማኑኤል ቤተሰብ ወይም ጓደኛ የሆናችሁ መጥታችሁ ማግኘት ትችላላችሁ። እባካችሁ
ይህን ፅሁፍ የምታነቡ ሁላችሁ ሼር በማድረግ ከቤተሰቡ እናገናኘው ።