SYT Dreams Business Center

SYT Dreams Business Center SADAM ABDU YIMAM / ሳዳም አብዱ ይማም
World Together / Ethiopia branch at LG-KOICA Hope T

11/12/2024
10/10/2024
 !መራራ ላንዳንዶች ለሌሎች መታደል፣መሳቅና ማልቀስ በሙላትም መጉደል፣ለስንቶች መነሳት ለእልፎችም መውደቅ፣የነበረው ዘመን ላይመለስ ሊርቅ!ያውና እንደሮጠ ጭኖን እንደገሰገሰ፣ሊቋጭ ሊያከትም ዛ...
10/09/2024

!

መራራ ላንዳንዶች ለሌሎች መታደል፣
መሳቅና ማልቀስ በሙላትም መጉደል፣
ለስንቶች መነሳት ለእልፎችም መውደቅ፣
የነበረው ዘመን ላይመለስ ሊርቅ!
ያውና እንደሮጠ ጭኖን እንደገሰገሰ፣
ሊቋጭ ሊያከትም ዛሬ ላይ ደረሰ።
አዎ ላይደገም ሊቀር እንዳለፈ፣
አልቆ ሊያስጀምረን ቋመጠ ከነፈ፣
እኛን አሳልፎ ሊቀረው ለራሱ፣
አሮጌው አበቃ ዘመን ግብስብሱ።
እናም ወገኖቼ ነገም ስለመጣ፣
አዲስ የተባለው ለዛሬ ልወጣ፣
እኛም እንዘጋጅ ላለመድገም ጣጣ!
ጥለነው ለመሄድ ያረጀውን ዕጣ።
አዎ የነበረው አንዳንዱ እጣችን፣
ለሀገር ለትውልድ እንደሰው የጎዳን፣
ነበር ያከሰረን ሆኖብን ፈተና!
ያልበጀን ያልሆነን ፍፁም ብልፅግና።
"የትኛውን እጣ?
የሆነብን ጣጣ?"
ብሎ ለጠየቀ በቅፅበት ላንዳፍታ፣
ሲዘረዘር ቢውል ከጧት እስከማታ!
ዘልቀን ለማንዘልቀው ሁሉን ብናወጋው፣
ይልቅ በጥቂቱ በምሳሌ እንየው።
ጥልና ጥላቻ ቂምና ቅሬታ፣
ሞትና ግድያ ጦርነት በሽታ፣
መደፈር መሰደድ መነጠቅ መበደል፣
በህፃን ባዛውንት በመንግሥትም በግል፣
በሰው በተፈጥሮ የሆነው በሙሉ፣
ቢነገር ቢዘከር ግፍና በደሉ።
አያልቅም እናንተው አንዘልቀውምኮ!
ታዝለን ያሳለፍነው በዘመን ሽኮኮ።
ይልቁን ትተነው ጥለነው ላሮጌ፣
አማራ ኦሮሞ ትግሬና ጉራጌ፣
ጋምቤላ ሱማሌ ስልጤውና ጋሞ፣
ሀረርና ወሎ ጎጃም ከሲዳሞ፣
ደቡብም አኝዋክ አሩሲና ጎንደር፣
ድሬና አዲስ አበባ አርጎባና አፋር።
ብቻ ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡቡ ጫፍ፤
ከምስራቅ ጫፍ እስከ ምዕራብ ጫፍ፣
እንዲሁም በመላው በሀገር ያላችሁ፣
የኢትዮጵያውያ ልጆች በዓለም ላላችሁ።
ያለፈውን ሁሉ በዛሬ ቋጭተነው!
አሮጌውን ዘመን በቃ ሸኝተነው፣
ለወርቃማው ጊዜ እድሉን ሰተነው፣
ተሻግሮ አሻጋሪ ለመሆን እንብቃው።
ጳጉሜ ላይ ስላለን ልንጨርስም ደህና፣
እናም ለምንገኝ በተስፋ ጎዳና፣
በተለይ ላለነው ታሪካዊቷ ቀን፣
አዎ ባስባለችን "የነገ ቀን!"
ደምቃ ባስዋለችን በተስፋ ስያሜ!
በዚች በአጭሯ በአሮጌዋ ጳጉሜ፣
"የዛሬ ትጋት ለነገ ትሩፋት!"
ብላ ላዋለችን ነገን ለምትሹ፣
ተመኘሁ በፅኑ እኔም በምላሹ።
የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የብልፅግና፣
የስኬት፣ የመልካሟ ሕይወት እንዲሁም የጤና፣
ጅማሮ እንዲሆን ዘመኔ ዘመናችሁ!
ከልቤ ተመኘሁ!!
እንኳን አደረሳችሁ።

👉መጪው ጊዜ መልካም ነው!👈

* Peace to mankind! * Peace to the world! * Peace to Africa! * Peace to Ethiopia !!

Long live for Ethiopia !!
💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️❤️
*ሰላም ለሰው ልጆች! *ሰላም ለዓለም! *ሰላም ለአፍሪካ! *ሰላም ለኢትዮጵያ!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!
💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️❤️
Bank Account Numbers፡
1. Buna International Bank – 1939501002548
2. Commercial Bank of Ethiopia – 1000141509067
3. Bank of Abyssinia – 70933322
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Author and poet Sadam Abdu (Sad) / ደራሲና ገጣሚ ሳዳም አብዱ (ሳድ)
World Together / LG-KOICA Hope TVET College / Micom Technology PLC
Emails: [email protected]/[email protected]
FACEBOOK: Sadam Abdu Sad ([email protected])
Mobile: +251935431606
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ጳጉሜ 5/2016 ዓ/ም

 #ተመኘሁ!  ይበዛል ከእዚያኛው መንደር፣  ይደረጋል ከእነንትና ሰፈር፣  ይቀወጣል ከእልፉ ተከታይ፣  እንደዚያው ይዘንባል ከሰማይ።ብቻ አያገባኝም አይደለም ቀንቼ!ይልቁን ለተስፋ ለስኬት ጓጉ...
08/09/2024

#ተመኘሁ!

ይበዛል ከእዚያኛው መንደር፣
ይደረጋል ከእነንትና ሰፈር፣
ይቀወጣል ከእልፉ ተከታይ፣
እንደዚያው ይዘንባል ከሰማይ።
ብቻ አያገባኝም አይደለም ቀንቼ!
ይልቁን ለተስፋ ለስኬት ጓጉቼ፣
አካውቴ አድጎ በለውጥ ከፋታ፣
ለመጪው ቋመጥኩኝ ለማታ የማታ፣
ለዚያ ለታላቁ ለሰውነት ልኩ፣
ለዚያች ለእማማ ምክንያትም በሆንኩ፣
ለድገት ከፍታቸው ሰበባቸው ሆኜ፣
ተመኘሁ ለታሪክ እርሱን አመስግኜ።

ለማንኛውም ከአላህ በታች መልካም ላደረጋችሁልኝ ስለምታደርጉልኝ !

የጉድ ዓመት አልፎ የጉዱ ሳይመጣ
ይኼኔ በጊዜ ሐሳብ እናዋጣ፡፡
የፈሰሰ ውሃ ላይታፈስ ቅጡ
ያለፉትም ጊዜ ዳግመኛ ላይመጡ
ይቅር መባባልን ከልባችሁ አውጡ፡፡

አማራ ኦሮሞ ትግሬ ጉራጌ ጋምቤላ ሱማሌ ስልጤ ሀረሪ ወሎ ጎጃም ደቡብ አኝዋክ ጎንደር አፋር ሲዳሞ ጋሞ አሩሲ አርጎባ አዲስ አበባ ድሬዳዋ ሃዋሳ…. ብቻ ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ ጫፍ፤ ከምስራቅ ጫፍ እስከ ምዕራብ ጫፍ እንዲሁም በመላው ሀገሬ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ዘመኑ፡- የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የብልፅግና፣ የስኬት፣ የመልካም ሕይወት ጅማሮ….እንዲሆንላችሁ ከልቤ ተመኘሁ፡፡

እንኳን አደረሳችሁ !! እያልኩኝ ስራዎቼን ከወደዳችሁልኝ በቀናነት 👉 በማድረግ አብሮነታችን ይቀጥል እላለሁ።

👉መጪው ጊዜ መልካም ነው!👈

* Peace to mankind! * Peace to the world! * Peace to Africa! * Peace to Ethiopia !!

Long live for Ethiopia !!
💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️❤️
*ሰላም ለሰው ልጆች! *ሰላም ለዓለም! *ሰላም ለአፍሪካ! *ሰላም ለኢትዮጵያ!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!
https://www.tiktok.com/?_t=8pYdsWmjmJJ&_r=1
ጳጉሜ 3/2016 ዓ/ም
💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️❤️
Bank Account Numbers፡
1. Buna International Bank – 1939501002548
2. Commercial Bank of Ethiopia – 1000141509067
3. Bank of Abyssinia – 70933322
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Author and poet Sadam Abdu (Sad) / ደራሲና ገጣሚ ሳዳም አብዱ (ሳድ)
World Together / LG-KOICA Hope TVET College / Micom Technology PLC
Emails: [email protected]/[email protected]
FACEBOOK: Sadam Abdu Sad ([email protected])
Mobile: +251935431606
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

95.7k Followers, 9805 Following, 497.7k Likes - Watch awesome short videos created by SADAM ABDU SAD-2

‹‹እንኳን አደረሳችሁ!››የዛሬ ስንት ዓመት በሆነ ዘመን ላይ፣ሲኖር የነበረ በምድር በሰማይ፣ፍጥረታት ባ’ንድ ላይ ጊዜ እየቆጠረ፣አዲስ ዓመት ሲዘልቅ ይቋምጥ ነበረ!በመጪው ሊደሰት ሊቦርቅ በተ...
06/09/2024

‹‹እንኳን አደረሳችሁ!››
የዛሬ ስንት ዓመት በሆነ ዘመን ላይ፣
ሲኖር የነበረ በምድር በሰማይ፣
ፍጥረታት ባ’ንድ ላይ ጊዜ እየቆጠረ፣
አዲስ ዓመት ሲዘልቅ ይቋምጥ ነበረ!
በመጪው ሊደሰት ሊቦርቅ በተስፋ፣
የተሻለ ሆኖ የጊዜው ወረፋ።
ከዓመታት ወዲህ እንዲሁ ቀጥሎ፣
የነበረው ሁሉ በሙሉም ጎደሎ፣
ምኞትና ተስፋው ለ’ሚመጣው ዘመን፣
የተለየ አይደለም ብንፈትሽ መሻቱን።
በተለይ የላቀው ተፈጥረውም ካሉ፣
አዎ ዘረ-አዳም በኒ-ዓደም ሁሉ!
ባ’ዲስ ዘመን ባ’ዲስ ዓመት፣
አዲስ ነገር አዲስ ህይወት፣
ነውና ምኞቱ!
ይጓጓል ለ’ለቱ።
ከአቻምና ወዲያ ወዲህም አቻምና፣
ከዘንድሮም በፊት ከተባለው አምና፣
እንዲሁ መልካሙን አምላኩ እንዲቸረው!
ይመኛል አብዝቶ ዘንድሮም ያለ ሰው።
እኔም እመኛለሁ ለኛና ሀገሬ፣
ሁሉንም ያለፈው ሲከትብ ብዕሬ፣
ባዲስ ዘመን ባዲስ ሃሳብ፣
ከታሪክ መልካሙን በፍቅር በጥበብ!
ለሀገር ለትውልድ ነገንም ሊከትብ።

አዎ ስለአንድነት፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ሰውነት፣ ኢትዮጵያዊነትና ስለመልካሟ ህይወት ለለተተኪው ትውልድ በጥበብ ማቀብል። በቃ ግብርገብነት እና መደጋገፍን የሚከትብና የሚያስተምር የጥበብ አውድማን በተስፋዋ ምድር በትውልድ ማሳ ላይ መዝራት። በጥቅሉ እጅግ አስነዋሪና አስጠያፊ ተግባርን ፈጣሚ ትውልድን ማየትም ማሳየትም አልሻምና ብዕሬም ይኮንነዋል። እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያየን እየመጣን እንዳለው ለመልስም መረዳት አዳጋች ሰቅጣጭ ጥያቄዎች ዓይነት ባዲስ ዘመንም ማየት በታሪክ ተወቃሽ መሆን ነው ትርፉ። አዎ የሰባት ዓመት ጨቅላ ህፃን ደፍሮ እንደ መግደል? ያምስት ዓመት ሀፃን አግቶ መሰዋት? አባት ልጁን መድፈር? ሰውነትን በብሔር? ኢትዮጵያዊነትን በፖለቲካ? ፍጡር ፈጣሪውን መዝንጋት? በወገኑ ለቅሶ መሳቅ? ሰው በልብሱ መለካት? ህግ እና ለውጥ በቃል ወይስ በተግባር? ከህሊና እና ከፈጣሪ ሸሸቶ ሩጫ እስክምን? ወዴት ምልጃ? ማን ከማን እስከመቼ? እኛ ወይስ ዘመን ተወቃሹ? ለምን መጣን? ምን ተጠቀምን? ማነን? እንዴት ሆነልን ከቶ? በቀል ወይስ ምን...? ስሜት ወይስ ስሌት? ፀፀት ወይስ እረፍት? እንዴት .... ለማንኛውም ብዙ ያልተጠየቁና የማይመለሱ ጥያቄዎች አሉ። ለምን ... ??? የሚሉ ዕልፍ ጥያቄዎችን አስነሺና ከስሮ አክሳሪ ተግባራትን ባዲስ ዓመት ባዲስ ዘመን ፈፅሞ መስማትም ማየትም አይገባንምና በዚሁ ፈጣሪ አምላካችን አላህ በቃችሁ ይበለን። እናም እላችኋልሁ፡
ውድ የድረ-ገፄ ተከታዎች፤ ውድ የሀገሬ እንቁ የሐሳብ ልዕልና ባለቤቶች፤ ውድ ዘመድ-ጓደኞቼ፤ ውድ ባገር ቤትና በመላው አለም ዙሪያ ያላችሁ ኢትዮጵያውያንና የጥበብ ባለቤቶች እንዲሁም ለሰው ዘሮች ሁሉ እንኳን ለዓዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ለማለት ወደድኩኝ!
እልፍ ዘመን አልፈን እልፉን አሳልፈን
ስንቱ ጋር ተጋፍጠን ስንቱንም እረተን
የጣልነውን ጥለን የያዝነውን ይዘን
አዲሱን ልንተካ ዛሬ ላይ ተገኘን፡፡
አዎ! ዛሬ ላይ ነው የ336 ቀን መጨረሻ በሆነችው ጳጉሜ 2/2016 ዓ/ም፡፡ አያችሁ ጳጉሜ እንኳ ባቅሟ አምስት/ስድስት እንጂ ሰላሳ አይደለችም፡፡ ከልኳ አታልፍማ!! እስኪ ማነው ወንድ ነኝ የሚል ትናንት ሀሙስ ጳጉሜ አንድን ዛሬ የሚያድርግልኝ!!? በርግጥ የሚችል ካለ እርሱ አላህ፣ አምላክ፣ ፈጣሪ ነህ በሉት፡፡ ሁልህም በእምነትህ….፡፡ ለማንኛውም ‹‹ከመተካትህ›› በፊት መልካምነትህን፣ ፍቅርህን፣ ቅንነትህን፣ ሰውነትህን፣ ሰላምህን፣ እምነትህ፣ ተስፋህን፣ አንድነትህን፣ ዘርህን ተከተህ እለፍ!፡፡
መራራውን እውነት ሃቁን ላትቀይር
ትናንትን ላትመልስ ዛሬንም ሳትኖር
ነገንም ላታውቀው አጉል አትከመር
ጥላቻና ቂምን፣ በደልን አንግበህ፣ ይዘኸው አትዙር፡፡
አስተውል! እየኖርክ በሄድክ ቁጥር እየሞትክ ነው፡፡ ነገ፣ ዛሬ፣ በኋላ፣ እንዲያውም ይህቺን ኢምንት ሐሳብ የያዘች ፅሁፌን አንብበህ ሳትጨርስ ከሴኮንድ በኋላ ምን እንደምትሆን ምን ዋስትና አለህ!? ቶሎ መልስልኛ! አየህ ህሊና ካለህ መልስህ ግልፅ ነው…..፡፡ ታዲያ ጭካኔህን፣ ጉልበትህን፣ ብልጠትህን ያለህን ተጠቅምክ ከሌላው ቀምተህ፤ ከሳቅ ለቅሶ፤ ከስኬት ውድቀት ለስንቱ ሰው ሆነህና ተግተህ ያገኘህው ቁሳቁስም በለው ንበረት፣ ዝናም በለው ሙገሳ አልፎ ተርፎ ስንቱን ተሸካሚ ጫንቃዋን አጉብጠህ የዚህችን ሚስኪን ሀገር ንብረቷን መዝብረህ ለመኖር ትኳትናለህ፡፡ ለየትኛው ሕይወትህ ነው? ለመቼ ነው? ለማን ነው? መልሱ….፡፡
የጉድ ዓመት አልፎ የጉዱ ሳይመጣ
ይኼኔ በጊዜ ሐሳብ እናዋጣ፡፡
የፈሰሰ ውሃ ላይታፈስ ቅጡ
ያለፉትም ጊዜ ዳግመኛ ላይመጡ
ይቅር መባባልን ከልባችሁ አውጡ፡፡
አማራ ኦሮሞ ትግሬ ጉራጌ ጋምቤላ ሱማሌ ስልጤ ሀረሪ ወሎ ጎጃም ደቡብ አኝዋክ ጎንደር አፋር ሲዳሞ ጋሞ አሩሲ አርጎባ አዲስ አበባ ድሬዳዋ ሃዋሳ…. ብቻ ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ ጫፍ፤ ከምስራቅ ጫፍ እስከ ምዕራብ ጫፍ እንዲሁም በመላው ሀገሬ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ዘመኑ፡- የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የብልፅግና፣ የስኬት፣ የመልካም ሕይወት ጅማሮ….እንዲሆንላችሁ ከልቤ ተመኘሁ፡፡
እንኳን አደረሳችሁ !!!!
ጳጉሜ 2/2016 ዓ/ም
👉መጪው ጊዜ መልካም ነው!👈

* Peace to mankind! * Peace to the world! * Peace to Africa! * Peace to Ethiopia !!

Long live for Ethiopia !!
💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️❤️
*ሰላም ለሰው ልጆች! *ሰላም ለዓለም! *ሰላም ለአፍሪካ! *ሰላም ለኢትዮጵያ!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!
💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️❤️
Bank Account Numbers፡
1. Buna International Bank – 1939501002548
2. Commercial Bank of Ethiopia – 1000141509067
3. Bank of Abyssinia – 70933322
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Author and poet Sadam Abdu (Sad) / ደራሲና ገጣሚ ሳዳም አብዱ (ሳድ)
World Together / LG-KOICA Hope TVET College / Micom Technology PLC
Emails: [email protected]/[email protected]
FACEBOOK: Sadam Abdu Sad ([email protected])
Mobile: +251935431606
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

 ከምን’ኛው ጫካ ከየት’ኛው ዘመን፣በየት’ኛው መንግድ እንደምንድን መጣን?እኔ አልገባኝም የገባው ያስረዳ፣ባልገባን ጎዳና እንዴት እንነዳ።ባለሁለት እግር የአራዊት መንጋ፣ስንቱን ‘ሚያሰማን በመ...
17/08/2024

ከምን’ኛው ጫካ ከየት’ኛው ዘመን፣
በየት’ኛው መንግድ እንደምንድን መጣን?
እኔ አልገባኝም የገባው ያስረዳ፣
ባልገባን ጎዳና እንዴት እንነዳ።
ባለሁለት እግር የአራዊት መንጋ፣
ስንቱን ‘ሚያሰማን በመሸ በነጋ፣
ግፍና ተንኮሉ ከሰይጣን የላቀ፤
የነበረ ሁሉ በ’ራሱ አለቀ።
ሰው ከ’ነወዙ ተፈጥሮ ከ’ነመልኳ፣
ፍቅር ከ’ነ’ምቱ ሀገር ከ’ነታሪኳ፣
አደም ከ’ነዝሩ አብሮ እንደገባ፣
በገባበት ጫካ ቀረ እንዳነባ።
“በማን?” አትሉኝም? ትንግርት ይሁናችሁ፣
እንዲሁ ስላችሁ ስራው ይንገራችሁ!
ህፃን ‘ሚደፍር ወገን ‘ሚያሰቃይ፣
እርኩሰት መለያው በምድርም በሰማይ።
ሀገር ያኖረችው አዝላው በአንቀልባ፣
አፈር ያለበሰ ሞቶ የፀነባ፣
ከጌታው አምጦ ከህሊናው ሸሽቶ፣
ጀሰዱም መንፈሱም የተገኘ በክቶ።
ተዋርዶ አዋራጅ ተሰድቦ አሰዳቢ፣
ለማንም ለምንም የሆነ አወዛጋቢ፣
ሰልጥኖ ስንለው ይገኛል ስይጥኖ፣
ሰይጣንም ብንለው ከሰዎቹ ሆኖ፣
ያወዛግበናል ያደናግረናል ሥራና ዓመሉ!
አወቃችሁት ወይ እንዲያው በጥቅሉ?።
ብቻ ካለንበት ከሀገርም ከዘመን፣
አዎ ከጎጇችን የታጎረ አብሮን፣
እንደኛ ያ’ይደለ እኛን የመሰለ፣
ከጫካው ኑሯችን ባ’ብሮነት የዋለ፣
የሆን እሱማ ያልተረዳን አለ።

የሰባት ዓመት ጨቅላ ህፃን ደፍሮ መግደል? አባት ልጁን መድፈር? ሰውነት በብሄር ኢትዮጵያዊነትን በፖለቲካ? ፍጡር ፈጣሪውን መዝንጋት? በወገኑ ለቅሶ መሳቅ? ሰው በልብሱ መለካት? ህግ እና ለውጥ በቃል ወይስ በተግባር? ከህሊና እና ከፈጣሪ ሸሸቶ ሩጫ እስክምን? ወዴት ምልጃ? ማን ከማን እስከመቼ? እኛ ወይስ ዘመን ተወቃሹ? ለምን መጣን? ምን ተጠቀምን? ማነን? እንዴት ሆነልን ከቶ? በቀል ወይስ ምን...? ስሜት ወይስ ስሌት? ፀፀት ወይስ እረፍት? እንዴት .... ለማንኛውም ብዙ ያልተጠየቁና የማይመለሱ ጥያቄዎች አሉ። ለምን ... ???

ቅዳሜ ነሃሴ 11/2016 ዓ/ም

👉መጪው ጊዜ መልካም ነው!👈

* Peace to mankind! * Peace to the world! * Peace to Africa! * Peace to Ethiopia !!

Long live for Ethiopia !!
💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️❤️
*ሰላም ለሰው ልጆች! *ሰላም ለዓለም! *ሰላም ለአፍሪካ! *ሰላም ለኢትዮጵያ!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!
💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️❤️
Bank Account Numbers፡
1. Buna International Bank – 1939501002548
2. Commercial Bank of Ethiopia – 1000141509067
3. Bank of Abyssinia – 70933322
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Author and poet Sadam Abdu (Sad) / ደራሲና ገጣሚ ሳዳም አብዱ (ሳድ)
World Together / LG-KOICA Hope TVET College / Micom Technology PLC
Emails: [email protected]/[email protected]
FACEBOOK: Sadam Abdu Sad ([email protected])
Mobile: +251935431606
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

 !ከሁሉ አስቀድሜ የከበረ ሰላምታዬ በመላው ዓለም ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ወዳጅ ዘመዶቼ ሁሉ ይድረስልኝ። በመቀጠል   እያልኩኝ ከትላልቅ ስኬቶቼ መካከል የሆነውን እና በሰለጠኑ ባለሙያዎ...
16/06/2024

!

ከሁሉ አስቀድሜ የከበረ ሰላምታዬ በመላው ዓለም ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ወዳጅ ዘመዶቼ ሁሉ ይድረስልኝ። በመቀጠል እያልኩኝ ከትላልቅ ስኬቶቼ መካከል የሆነውን እና በሰለጠኑ ባለሙያዎችና ባልደረቦቼ የተቋቋመውን ድርጅት እንሆ እንኩ የምስራቼን እላለሁ። እናም ወገኖቼ ከጌታዬ በታች ከለውጥና ሽልማቶቼ ጎን እንደነበራችሁ ሁሉ አሁንም በዚህኛው ከፍተኛ እንገናኝ ዘንድ https://t.me/micomtechnology ማስፈንጠሪውን በመጫን ቤተሰብና ቢያንስ በውስን ቀናቶች ወደ 5000 members ከፍ በማድረግ የተለመደውን ቀና ትብብራችሁን ዛሬም እሻለሁ።

መፅሐፍ። _2016ን አስከትሎም እየመጣላችሁ ነው። ኢንሻአላህ ***

✅ እናስተዋውቅዎ!
Micom Technology PLC

ምን ማሰራት ይፈልጋሉ?
ለድርጅቶች፣ ለሆቴሎች፣ ለሆስፒታሎች እንዲሁም ለመኖሪያ ቤቶች
Technology
& Electronic Technology
Technology ስራወች ጊዜዉን የጠበቀ ስራ እንሠራለን።

አብረውን ለሚሰሩ ሀላፊወች የተለየ ማበረታቻ ይኖረናል እኛ ጋር ይስሩ ብዙ ያተርፋ።

አድራሻ: ሀያ ሁለት ከመክሊት ህንፃ ከፍ ብሎ ከሚገኘው ኤፍራታ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቁጥር F-09 በአካል በመምጣት መረጃ ማገኘት ይችላሉ።
Follow us
Telegram = t.me/micomtechnology
Facebook = micom technology
contact us
[email protected]
For more info call us
📞 0974044404
📞 0911456642
📞 0946659570

your satisfaction is our satisfaction
☀️መልካም ቀን ይሁንላችሁ

https://t.me/micomtechnology

👉መጪው ጊዜ መልካም ነው!👈

* Peace to mankind! * Peace to the world! * Peace to Africa! * Peace to Ethiopia !!

Long live for Ethiopia !!
💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️❤️
*ሰላም ለሰው ልጆች! *ሰላም ለዓለም! *ሰላም ለአፍሪካ! *ሰላም ለኢትዮጵያ!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!
💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️❤️
Bank Account Numbers፡
1. Buna International Bank – 1939501002548
2. Commercial Bank of Ethiopia – 1000141509067
3. Bank of Abyssinia – 7093332
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Author and poet Sadam Abdu (Sad) / ደራሲና ገጣሚ ሳዳም አብዱ (ሳድ)
World Together / LG-KOICA Hope TVET College / Micom Technology PLC
Emails: [email protected]/[email protected]
FACEBOOK: Sadam Abdu Sad ([email protected])
Mobile: +251935431606
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

02/04/2024

1944 likes, 265 comments. “ with @🤍”

 !!❤❤❤2015❤❤❤2024❤❤❤Dear all and Ethiopian, I wish you and your to all beloved, May this year bring new happiness, new g...
12/09/2023

!!
❤❤❤2015❤❤❤2024❤❤❤
Dear all and Ethiopian, I wish you and your to all beloved, May this year bring new happiness, new goals, new achievements, and a lot of new inspirations on your life. Wishing you a year fully loaded with happiness.
በአንዱ አክለን በሌላው ቀንሰን
ደግሞ ተገናኘን ቆጥረን አስቆጥረን
አዎ ለታደለ ሆኖልን ጭማሪ
ከዚህኛው በኩል የሆነን አብሳሪ።
ብቻ እንቁ-ጣጣዬዋ መጣችልኝ ደግሞ
ዘንድሮን አሁንም ተክታው በከርሞ!
.. አዎ እንቁጣጣሽ ሲመጣ ብዙ ተስፋ እና ትዝታ ሁላችንም አለን። ግን ሰላም ሲኖረን አንድነት ሲያጋምደን ሰውነት ሲያግባባን እምነታችን ሲመራን ክስተት እና ተፈጥሮ ሲያስተምረን...

የሆነው ሆኖ ስለሆነም ስላልሆነም ነገር... ስለሁሉም ነገር #አልሃምዱሊላህ

አምና እንኳን መነነ ካ'ቻምናም እንደ-ዚያው
ዘን-ድሮም ነጎደ እሱስ ምኑን ቀረው!?
ስራና ዕድሚያችን ቀን እየቆጠረ
መንገድ ላይ'ኮ ነው መሔዱ መች ቀረ!
ነገ ያልነው ዛሬ ዛሬም ያልነው ትናንት
እያለ እያለፈ ከነፈ እንደ-ዘበት፡፡

!

👉መጪው ጊዜ መልካም ነው!👈

* Peace to mankind! * Peace to the world! * Peace to Africa! * Peace to Ethiopia !!

Long live for Ethiopia !!
❤️❤️❤️2015❤️❤️❤️2024❤️❤️❤️
*ሰላም ለሰው ልጆች! *ሰላም ለዓለም! *ሰላም ለአፍሪካ! *ሰላም ለኢትዮጵያ!!
https://www.tiktok.com//video/7277882360098606342?lang=en
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!
❤️❤️❤️2015❤️❤️❤️2024❤️❤️❤️
SADAM ABDU YIMAM (SAD) / ሳዳም አብዱ ይማም (ሳድ)
World Together / Ethiopia branch at LG-KOICA Hope TVET College ICT/IT Workshop Technician.
: [email protected] FACEBOOK: Sadam Abdu Sad ([email protected])
Mobile: +251935431606
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

8:15 PM
Tuesday, September 12, 2023
ማክሰኞ: መስከረም 1/2016

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SYT Dreams Business Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share