All works business group

All works business group Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from All works business group, Business service, Addis Ababa.

02/04/2021

የስኬታማ ግለሰቦች ልምድ ሀብት ማካበት የብዙ አመታትን ብልሃት የተሞላበት ውሳኔ ይጠይቃል፡፡በሙያም ይሁን በገንዘብ በኩል ማለት ነው፡፡በመቶ የሚቆጠሩ ሚሊየነሮችን ያነጋገረ አንድ ....

25/10/2020

የቁጠባ ባህላችንን እንዴት እናሳድግ?
=======

አንዳንዴ ገንዘብ የመቆጠብ አስቸጋሪው ጉዳይ መጀመሩ ነው፡፡ የሚከተሉትን ሰባት ነጥቦች በቅደም ተከተል መተግበር ገንዘብ ለመቆጠብ ያግዛል፡፡

1. ወጪን መመዝገብ
ቁጠባን ለመጀመር የመጀመሪያው ተግባር ወጪን ማወቅ ነው፡፡ በወር ውስጥ ከሻይ ቡና ጀምሮ ለቲፕ አስከምንሰጠው ሳንቲም ደረስ እያንዳንዷን ወጪ በአግባቡ መዝግቦ መያዝ፡፡

2. ለቁጠባ በጀት መመደብ
ወርሃዊ ወጪ ከታወቀ በኋላ፣ የወጪ ዝርዝሩን በአይነት በመከፋፈልና በማደራጀት ወደበጀት መቀየሩ ቀጣይ ተግባር ነው፡፡ በጀቱ ወጪያችን ከገቢያችን አንፃር ምን እንደሚመስል ያሳያል፡፡ ይህም በቀጣይ የተጋነነና አላስፈላጊ ወጪን በማስቀረት ገቢና ወጪን ለማጣጣም ይረዳል፡፡ አዘውትረው የማይመጡ ነገር ግን የማይቀሩ ወጪዎች መዘንጋት የለባቸውም፡፡
የበጀት ዝርዝሩ ላይ ቢያንስ የገቢን ከ10-15 በመቶ ለቁጠባ መመደብ፡፡

3. ለወጪ ቅነሳ የሚረዱ መንገዶችን መፈለግ
ወጪ ከፍተኛ ሆኖ የሚፈለገውን ያክል መቆጠብ የማያስችል ከሆነ ወጪ ቅነሳ ላይ መስራት ግድ ሊሆን ይችላል፡፡
• እንደ መዝናኛ እና ከቤት ውጪ መመገብን የመሳሰሉ መሠረታዊ ያልሆኑና ወጪያቸው ሊቀነስ የሚችሉትን መለየት፡፡

• የስልክ የአየር ሰዓት ግዢ የመሳሰሉ ቋሚ የሆኑ ወጪዎችን መቀነስ፡፡

4. የቁጠባ አላማ ማስቀመጥ

የቁጠባ አላማን ማስቀመጥ ለቁጠባ ወሳኙ መንገድ ነው፡፡ ቁጠባ ለምን አላማ ሊያስፈልገን እንደሚችል በማሰብ መጀመር - ጋብቻ መፈፀም አስበናል? ትምህርታችንን መቀጠል እንፈልጋለን? መኪና ወይም ቤት መግዛት እንመኛለን? ጉዞና መዝናናት አስበናል? ለእርጅና ዘመናችን ጥሪት መቋጠር እንፈልጋለን?
አላማን ከለዩ በኋላ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያስፈልግና ለቁጠባው የሚወስደውን ጊዜ ለይቶ በማወቅ የአጭር፣ የመካካለኛ እና የረጅም ጊዜ የቁጠባ እቅድ ማውጣት ቀጣዩ ሥራ ነው፡፡

5. ቅደም ተከተል ማስቀመጥ
ከገቢና ወጪ ቀጥሎ የቁጠባ አላማ የቁጠባ በጀት ድልድል ላይ ትልቅ ተጽእኖ አለው፡፡ ረጅም ጊዜ የሚወስዱ የቁጠባ አላማዎችን ባለመዘንጋት ነገር ግን ቅድሚያ መስጠት ያሉብንን የቁጠባ አላማዎች በመለየት መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡

6. ትክክለኛውን የቁጠባ ሂሳብ አገልግሎት መምረጥ
እንደቁጠባ አላማና የሚወስደው ጊዜ ተስማመሚውን የቁጠባ አገልግሎት አይነት ለይቶ መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተለያዩ አላማዎች የሚውሉ የቁጠባ አገልግሎት አይነቶችን ከተሻለ ወለድ እና ሌሎች ጥቅሞች ጋር ይሰጣል፡፡

7. የቁጠባውን እድገት መከታተል
በየወሩ የበጀት አፈፀፀምን በመከታተል በእቅድ መሠረት እየሄደ መሆን አለመሆኑን ማረጋጋጥና የተፈጠረ ልዩነት ሲኖር በአፋጣኝ ማረም ተገቢ ነው፡፡ ቁጠባ እየገባን እና ቁጠባችን እያደገ ሲሄድ የበለጠ ለመቆጠብ እና አላማችንን ቶሎ ለማሳካት ተነሳሽነታችን ይጨምራል፡፡

አብረንን ተያይዘን በ cross እንደግ💱💰
24/10/2020

አብረንን ተያይዘን በ cross እንደግ💱💰

23/10/2020

ራስህን መገንባት፤ ራስሽን መገንባት (Personal development)

በህይወታችሁ መድረስ የምትፈልጉት ነገር ወይም ማሰካት የምትፈልጉት ነገር ኣለ ?
በሁሉም የህይወታችን አንቅስቃሴ ጥበብ የተሞላበት አኗኗር ይፈልጋል፡፡ ለዚህ ጥበብ የተሞላበት አኗኗር ደግሞ ዋናው መነሻው ክህሎት (Skill) ነው፡፡ በትዳር፣ በትምህርት፣ በስራና በፍቅር በነዚህ ሁሉ ስኬት ለመጎናፀፍ ክህሎት ያስፈልገናል፡፡ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ ነገሮች አንድ ሰው በተለያየ መልኩ ማሳካት ይችላል፡፡ ከነዚህ አንዱ መደበኛና መደበኛ ባልሆነ መንገድ ከሳይኮሎጂ ባለሞያ በሚያገኘው ሰልጠና ወይም ትምህርት ነው፡፡

እንግድያውስ አሁን እየኖራችሁት ካላችሁት ንሮ የተሻለ ህይወት የምትሹ (Psychology-ሳይኮሎጂ) ገፅ ይህንን ሰልጠና በተለያዩ መንገዶች ያቀርብላችኋል፡፡ ስልጠናው አንድ ለኣንድም በቡድን ይሰጣል የሚሰጥበት መንገድ በ zoom meeting, Imo video chat, whatsApp, messenger ስልጠናው መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
በዚህ ፔጅ የሚሰጡ ስልጠናዎች
• Develop self-confidence (በራስ መተማመን)
• Assertiveness (ሌሎችን ሳትጎዳ ሀሳብህ በድፍረት መግለፅ)
• Public speaking (ህዝብ በተሰበሰበት ንግግር የማድረግ ክህሎት)
• Time management (የጊዜ አጠቃቀም)
• Developing a Mindset of Success (የስኬት ማይንድ ሴት ማዳበር)
• Reaching Your Potential ብቃትህን መድረስ
• Interpersonal Relationships ከሰዎች ጋር ግንኙነት የመመስረት ክህሎት
• Overcoming Bad Habits and Addictions መጥፎ ልሞደችንና ሱስን የማስወገድና መቀነስ ክህሎት
• Communication Skill የንግግር ክህሎት
• Anger Management ንዴትን የመቆጣጠር ክህሎት
• Positive Thinking (አወንታዊ ኣተሓሳስብ)

ራሰህን ለመቀየር ጊዜ የለገኝም ኣይባልም፤ ለራስህ ጊዜ ካልሰጠህ ታድያ ለማን ልትሰጥ ነው ?
ራስህን ለመቀየር ከሁሉም ጊዜ የተሻለ አሁን ነው፡፡

ባላችሁበት ቦታ፣ ሀገር ሆናችሁ ይህንን ስልጠና መማር ትችላላችሁ
ማንኛውም ጥያቄ ለመጠየቅ በውስጥ መስመር ይጠቀሙ !!

ዳንኤል ገብረህይወት
ክሊኒካል ሳይኮሎጂሰት፣ MSc

ከ ገንዘብ ሀሳብ ይቀድማል ሀሳብ ተግባር ላይ ሲውል ገንዘብ ይሆናል
13/10/2020

ከ ገንዘብ ሀሳብ ይቀድማል ሀሳብ ተግባር ላይ ሲውል ገንዘብ ይሆናል

Address

Addis Ababa

Telephone

+251983758615

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when All works business group posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to All works business group:

Share