Hailemichael Tadesse Authorized Accountant

Hailemichael Tadesse Authorized Accountant We worked on Any Accounting services and prepare Financial statement Reports, VAT, Income Tax, Month

25/02/2026

ለክቡራን ግብር ከፋዮች
ለ2017 ግብር ዘመን ጠቅላላ ከከፈላችሁት ንግድ ሥራ ትርፍ ግብር ላይ (ዊዝሆልዲንግ ታክስ ያቀናነሳችሁትና በቅድመ- ኦዲት [Pre- Audit] የተደረገዉን ማስተካከያ ግብር ጨምሮ) 25%ቱን በማስላት፤ ከሀምሌ/2017 ዓም እስከ መስከረም/2018 ዓ.ም ዊዝሆልድ የተደረጋችሁትን ቅድመ- ግብር በመቀነስ ለ2018 ግብር ዘመን ቅድሚያ ግብር ክፍያ እስከ የካቲት 25/2018 ዓ.ም ባለዉ ጊዜ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ በቅ/ጽ/ቤታችን ስም AACGRA LARGE TAX PAYERS BRANCH OFFICE ወደተከፈተ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000277732088 ገቢ አድርገዉ Bank Deposit Slip እንዲያቀርቡ እንዲሁም ከሀምሌ/2017 ዓም እስከ መስከረም/2018 ዓም ድረስ ዊዝሆልድ የተደረጋችሁትን ቅድመ- ግብር በEXCEL- SHEET በሠንጠረዥ ሞልታችሁ እንድታቀርቡ እንዲሁም የዊዝሆልዲንግ ደረሰኝ ኮፒ በተጨማሪም ፕሪ ኦዲት የተሰራበትን ወረቀት ኮፒ በማድረግ እንድታቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የአዲስ አበባ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት (AALTO)

28/01/2026

በ2018 ግብር ዘመን በየሶስት ወሩ የሚከፈል ቅድመ ግብር መቼ መቼ ይከፈላል ?
በፌዴራል የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀጽ 89 ከተያዘው የግብር ዓመት በፊት በነበረው የግብር ዓመት የተከፈለውን ግብር 25 በመቶ እንደሚከፍል ተደንግጓል፡፡ በዚህ መሰረት የ2018 ግብር ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ግብር በየሩብ ዓመቱ (በየሶስት ወሩ) በማሳወቅ የሚከፍሉበት የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የመክፈያ ጊዜ ከየካቲት 1 እስከ የካቲት 30
• ከሐምሌ 1 እስከ መስከረም 30 የተቀነሰ 3% ቅድመ ግብር (Withholding ) በዚህ ወር ከሚከፈለው ክፍያ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል፡፡
የሁለተኛ ሩብ ዓመት የመክፈያ ጊዜ ከግንቦት 1 እስከ ግንቦት 30
• ከጥቅምት 1 እስከ ታህሳስ 30 የተቀነሰ 3% ቅድመ ግብር (Withholding ) በዚህ ወር ከሚከፈለው ክፍያ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል ፡፡
የሶስተኛ ሩብ ዓመት የመክፈያ ጊዜ ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 30
• ከጥር 1 እስከ መጋቢት 30 የተቀነሰ 3% ቅድመ ግብር (Withholding )
በዚህ ወር ከሚከፈለው ክፍያ ላይ ተቀናሽ ይደረጋል ፡፡
በ2019 ከሐምሌ 1 እስከ ጥቅምት 30 አጠቃላይ የ2018 ግብር ዓመት የትርፍ ግብር ቀድመው የከፈሉትን በመቀነስ ቀሪውን ይከፍላሉ፣ በትርፍ የተከፈለም ካለ ተመላሽ ይጠይቃሉ፡፡

Address

Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 08:30 - 18:00
Tuesday 08:30 - 18:00
Wednesday 08:30 - 18:00
Thursday 08:30 - 18:00
Friday 08:30 - 18:00
Saturday 09:00 - 17:00

Telephone

+251913143025

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hailemichael Tadesse Authorized Accountant posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hailemichael Tadesse Authorized Accountant:

Shortcuts

Share