23/08/2026
በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመምህርነት ለመቀጠር ለተመዘገባችሁ አመልካቾች የጽሑፍ ፈተና ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
ለጽሑፍ ፈተና የተመረጣችሁ መምህራንን ዝርዝር ለማየት 👇 https://www.facebook.com/share/p/1ERW65Q7sr/
ፈተናው የሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች፦
➫ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
➫ ወሎ ዩኒቨርሲቲ
➫ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
➫ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
➫ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ
➫ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
➫ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ
➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ
➫ መቐለ ዩኒቨርሲቲ
በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ፈተናው በሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች የሚቀርባችሁን በመምረጥ በአካል በመገኘት እንድትፈተኑ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።
ለውድድር የተመዘገባችሁበትን መለያ ቁጥር (Reference Number) በመጠቀም የፈተና መግቢያ መለያ ስም እና የይለፍ ቃል (Username and Password) ማግኘት ትችላላችሁ ተብሏል። በተጨማሪም ለፈተና በምትሔዱበት ቀን በየዩኒቨርሲቲዎቹ ከሚመደቡ የፈተና አስተባባሪዎች ዘንድ ማግኘት ትችላላችሁ።
ለፈተና ወደምትመርጡት ዩኒቨርሲቲ ስትሔዱ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይኖርባችኋል።
🔗 Join our Telegram Channel for more job opportunities:
https://t.me/+awJByPcwqdthNTA0