MULU production

MULU production Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from MULU production, Professional Service, Addis Ababa.

29/10/2025
ቢያንስ ለ 5,000.000 ኢትዮጵያዊያን ይደርስ ባስቸኳይ ይነበብ!!=============አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ ለመላው ህብረተሰብከ ዶ/ር ሊያ ታደሰ የ ቴሌግራም ገፅካነበባችሁ በሇላ ለሁሉም ...
19/03/2022

ቢያንስ ለ 5,000.000 ኢትዮጵያዊያን ይደርስ
ባስቸኳይ ይነበብ!!
=============
አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ ለመላው ህብረተሰብ
ከ ዶ/ር ሊያ ታደሰ የ ቴሌግራም ገፅ

ካነበባችሁ በሇላ ለሁሉም እንዲደርስ Share ያድርጉ

ሞባይል ስልክ የሚያመጣብን ጣጣ
የአይን ማኩላር እርጅና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እድሜአቸው በገፋ ሰዎች ላይ ብቻ
ነበር የሚታየው።አሁን ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከ30 እስከ 40 አመት የሆኑ ወጣቶች
ሁሉ ‘ማኩላር ዲጀኔሬሽን’ የተባለና ወደ አይነ ስውርነት የሚያደርስ ሕመም
እየተጠናወታቸው መጥተዋል።
ይሄም የሆነበት ማክንያት ብዙ ሰዎች ማታ መብራት ካጠፉ በኋላ ተንቀሳቃሽ ስልክ
እየከፈቱ ያያሉ።በጭለማ ውስጥ ወይም ጨለም ባለ አካባቢ የሞባይል ስልክን ለ30
ደቂቃ እንኳን መጠቀም መታረም የማይችል አደጋ ውስጥ የሚከት ነው።ሕመሙም
ካታራክት አይነት ሕመም ማስከተል ብቻ ሳይሆን የአይን ካንሰርም ያስከትላል።ይህ
ደግሞ መድሃኒት የሌለው በመሆኑ አይን ሲጠፋ ብቻ ቁጭ ብሎ መመልከት ነው ይላሉ
ሃኪሙ።ይህን መልዕክት ያስተላለፉት 254 የሚሆኑ የአይን ስፔሻሊት ሃኪሞች አንድ
ላይ በመሆን ነው።
ብዙ ሰዎች ማታ አልጋቸው ላይ ሆነው መብራት አጥፍተው ወይም ፈዘዝ ባለ መብራት
ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን እንደሚጠቀሙ ስለምናውቅ አደራ፣አደራ፣ራሳችሁን ከማይድን
ሕመም ጠብቁ ብለዋል።
ልብ ያለው ልብ ይበል!!!

ሞባይልን ቻርጅ ላይ አድርገው እንዳይጠቀሙ ተጠንቀቁ ። የአለም ዶክተሮች "
አስጠንቅቀዋል ካንሰር የሚባል ቫይረስ በውስጡ እንዳለ ፈንድቶም ሒወት ሊያጠፋ
እንደሚችል ይመክራሉ ይህ የሞባይል ቫይረስ በዓለማችን ላይ በጣም አደገኛ ቫይረስ
ነው ከፍተኛ የመግደል ፍጥነት አለው። እባካችሁ ይህን በ Telegram ኮንታክት
ዝርዝራችሁ ላይ ላሉ ሰዎች ወይም ለቤተሰብ አጋሩ ሕይወት ወይም ሕይወቶችን
አትረፉ እኔ የኔን ድርሻ ተወጥቻለሁ አሁን የናንተ ተራ ነው ሼር አድርጉ
የእህትህ የወንድምህ
ሀዘን የማያስደስትክ
ከሆንክ/ሽ
ይሄንን ትምህርት ሰጭ ፅሁፍ በየግሩፑ

በማድረግ አስተላልፈው
እናንተም ድርሻችውን
ተወጡ ሜዳውም ፈረሱም ይሄው!!

"ያለሰአቱ የተጠናቀቀው እና የስራ ባልደረቦቿን ያስከፋው የአርቲስት አልማዝ ሀይሌ የቀብር ስነ-ስርአት"😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭ዘመኗን ሁሉ ለኪነ ጥበብ የኖረችው ሁለገብ አርቲስት አልማዝ ሀይ...
26/09/2020

"ያለሰአቱ የተጠናቀቀው እና የስራ ባልደረቦቿን ያስከፋው የአርቲስት አልማዝ ሀይሌ የቀብር ስነ-ስርአት"
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

ዘመኗን ሁሉ ለኪነ ጥበብ የኖረችው ሁለገብ አርቲስት አልማዝ ሀይሌ ዕረፍት ሲሰማ የሙያ ጓደኞቿና አክባሪዎቿ ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ገብተው ነበር። የቀብር ስነስርዓቱም በ ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን በ6:00 ሰአት እንደሚፈፀም በመነገሩ አንጋፋ የሙያ አጋሮቿ ሰአቱን አክብረው የተገኙ ቢሆንም ከጥቂት ባለሙያዎች በስተቀር ከተባለው ሰአት ቀድሞ መፈፀሙን ያወቁት ቤተክርስቲያን ቅጥር ጊቢ ሲደርሱ ነበር። በጥድፊያ የተፈፀመው የቀብር ስነስርዓት ለምን እንደሆነ ያልገባቸው የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ሀዘናቸውን በቅጡ ለመወጣት አለመቻላቸው እንዳሳዘናቸውና የሚመለከታቸው የሙያ ማህበራት አለመገኘታቸው ሙያተኛዋንም ባላከበረ ስነስርዓት መፈፀሙ የኪነጥበብ ባለሙያውን አስቆጭቷል።

➥Ethiopia  ➥ #ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ለሌሎች እንዲደርስ በቅንነት ሼር ሼር ያድርጉ ።               !!👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 #አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ ለመላው ህብረተሰብከ ...
13/08/2020

➥Ethiopia
➥ #ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ለሌሎች እንዲደርስ በቅንነት ሼር ሼር ያድርጉ ።
!!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ ለመላው ህብረተሰብ
ከ ዶ/ር ሊያ ታደሰ የ ቴሌግራም ገፅ

#ካነበባችሁ በሇላ ለሁሉም እንዲደርስ Share ያድርጉ

ሞባይል ስልክ የሚያመጣብን ጣጣ
የአይን ማኩላር እርጅና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እድሜአቸው በገፋ ሰዎች ላይ ብቻ
ነበር የሚታየው።አሁን ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከ30 እስከ 40 አመት የሆኑ ወጣቶች
ሁሉ ‘ማኩላር ዲጀኔሬሽን’ የተባለና ወደ አይነ ስውርነት የሚያደርስ ሕመም
እየተጠናወታቸው መጥተዋል።
ይሄም የሆነበት ማክንያት ብዙ ሰዎች ማታ መብራት ካጠፉ በኋላ ተንቀሳቃሽ ስልክ
እየከፈቱ ያያሉ።በጭለማ ውስጥ ወይም ጨለም ባለ አካባቢ የሞባይል ስልክን ለ30
ደቂቃ እንኳን መጠቀም መታረም የማይችል አደጋ ውስጥ የሚከት ነው።ሕመሙም
ካታራክት አይነት ሕመም ማስከተል ብቻ ሳይሆን የአይን ካንሰርም ያስከትላል።ይህ
ደግሞ መድሃኒት የሌለው በመሆኑ አይን ሲጠፋ ብቻ ቁጭ ብሎ መመልከት ነው ይላሉ
ሃኪሙ።ይህን መልዕክት ያስተላለፉት 254 የሚሆኑ የአይን ስፔሻሊት ሃኪሞች አንድ
ላይ በመሆን ነው።
ብዙ ሰዎች ማታ አልጋቸው ላይ ሆነው መብራት አጥፍተው ወይም ፈዘዝ ባለ መብራት
ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን እንደሚጠቀሙ ስለምናውቅ አደራ፣አደራ፣ራሳችሁን ከማይድን
ሕመም ጠብቁ ብለዋል።
ልብ ያለው ልብ ይበል!!!

ሞባይልን ቻርጅ ላይ አድርገው እንዳይጠቀሙ ተጠንቀቁ ። የአለም ዶክተሮች "
አስጠንቅቀዋል ካንሰር የሚባል ቫይረስ በውስጡ እንዳለ ፈንድቶም ሒወት ሊያጠፋ
እንደሚችል ይመክራሉ ይህ የሞባይል ቫይረስ በዓለማችን ላይ በጣም አደገኛ ቫይረስ
ነው ከፍተኛ የመግደል ፍጥነት አለው። እባካችሁ ይህን በ Telegram ኮንታክት
ዝርዝራችሁ ላይ ላሉ ሰዎች ወይም ለቤተሰብ አጋሩ ሕይወት ወይም ሕይወቶችን
አትረፉ እኔ የኔን ድርሻ ተወጥቻለሁ አሁን የናንተ ተራ ነው ሼር አድርጉ
የእህትህ የወንድምህ
ሀዘን የማያስደስትክ
ከሆንክ/ሽ
ይሄንን ትምህርት ሰጭ ፅሁፍ በየግሩፑ

በማድረግ አስተላልፈው
እናንተም ድርሻችውን
ተወጡ ሜዳውም ፈረሱም ይሄው!!

🎖ዶ/ር ሊያ ታደሰ

በዚህ ወቅት እንዲህም አለ
11/06/2020

በዚህ ወቅት እንዲህም አለ

የአለማችን አደገኛ ሁለት አስቸጋሪ ጉሮሮ ቆልፎች
28/05/2020

የአለማችን አደገኛ ሁለት አስቸጋሪ ጉሮሮ ቆልፎች

03/05/2020

😂😂😂😂😂😂

18/04/2020

አትሌት መሰረት ደፋር 500 ሰዎችን የሚያስተናግድ ሕንጻ ለለይቶ ማቆያነት እንዲውል ፈቀደች

አትሌት መሰረት ደፋር መገናኛ አካባቢ እያስገነባች ያለውን ባለ 12 ወለል ሕንጻ ኮቪድ-19ኝን ለመከላከል ለለይቶ ማቆያነት እንዲያገለግል ማስረከቧን አስታወቀች።

ሕንጻ የተረከቡት የኮቪድ-19 መከላከል የለይቶ ማቆያ የሚኒስትሮች ኮሚቴ አባላትም ሕንጻው በሳምንት ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረግ አመልክተዋል።

ዓለምን እያስጨነቀ የሚገኛውን የኮቪድ-19 ወርርሽኝ ለመቋቋም ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም አትሌቷ በዚሁ ጊዜ ተናግራለች።
(ኢዜአ)

በስጋ ቤቶች (ሉካንዳዎች) የሚተገበሩ 🐂🐂🐂🐂🐂🐂🐂🐂🐂🐂🐂የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝም ሆነ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት ለመከላከል ሲባል በፌደራል ደረጃ አዋጅ መውጣቱ ይታወቃል።በመሆኑም ከዚ...
18/04/2020

በስጋ ቤቶች (ሉካንዳዎች) የሚተገበሩ
🐂🐂🐂🐂🐂🐂🐂🐂🐂🐂🐂
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝም ሆነ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት ለመከላከል ሲባል በፌደራል ደረጃ አዋጅ መውጣቱ ይታወቃል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዴታዎች መፈፀም የበሽታውን ስርጭት ለመግታት አስተዋፅኦ የሚያደርግ በመሆኑ ሁሉም ስጋ ቤት (ሉካንዳዎች) ለተግባራዊነቱ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ጥሪውን ያስተላልፋል።

ዋና ዋና ግዴታዎች

1. ማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ስጋ አስገብቶ ከመሸጡ (አገልግሎት ላይ እንዲውል) ከማድረጉ በፊት ሙሉ ለሙሉ ስጋ ቤቱን እና መጠቀሚያ ቁሳቁሶችን በውሃ ሳሙናና በረኪና በመጠቀም ማጽዳት አለበት፣

2. ማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) የሚያስገባው ስጋ ህጋዊ እና ከታወቀ ቄራ ታርዶ የቀረበ መሆን አለበት፣

3. ማንኛውም በስጋ ቤት (በሉካንዳ) የሚሰራ ሰራተኛ የስጋ ሽያጭ በሚያከናውንበት ጊዜ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (ማስክ)፣ ቆብ እና ጋዎን መጠቀም አለበት፣

4. በማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ገንዘብ የሚቀበልና ስጋ የሚቆርጥ ሰራተኛ መለየት አለበት፣

5. በማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ውስጥ ለሰራተኞች የእጅ ሳሙናና ውሃ ተዘጋጅቶ በየጊዜው እጃቸውን በመታጠብ አገልግሎት መስጠት አለባቸው፣

6. በማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ሽያጭ በሚከናወንበት ወቅት ተገልጋዮች ከመሸጫ መስኮቱ 1 (አንድ) ሜትር ርቀው እንዲቆሙና እንዲገለገሉ መደረግ አለበት፣

7. በማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ድርጅት ውስጥ የተገልጋይ ቁጥር ከሁለት በላይ በሚሆንበት ወቅት ድርጅቱ ተገልጋዮችን እያንዳንዳቸው ርቀታቸውን በየሁለት እርምጃ ጠብቀው እንዲቆሙና እንዲገለገሉ ማድረግ አለበት፣

8. ከምግብ ቤቶች ጋር የተያያዙ ሉካንዳ ቤቶች ውስጥ ያልበሰለ ስጋ (ቁርጥ/ጥሬ ስጋ፣ ያልበሰለ ክትፎ) ለምግብነት ማቅረብ ለበሽታው ስለሚያጋልጥ የተከለከለ ነው፣

መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ነው

ሳምባ ቆልፍም እንደ ሕዳር በሽታ እንዳይሆን!ስለ ህዳር በሽታ ታሪክ፣ነፍሳቸውን ይማረውና፣ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት አንድ ጥናት አላቸው፡፡ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር መጽሔት፣ቅጽ 13፣ቁጥር...
16/04/2020

ሳምባ ቆልፍም እንደ ሕዳር በሽታ እንዳይሆን!

ስለ ህዳር በሽታ ታሪክ፣ነፍሳቸውን ይማረውና፣ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት አንድ ጥናት አላቸው፡፡ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር መጽሔት፣ቅጽ 13፣ቁጥር 2፣1969 ዓ.ም በታተመው ላይ ወጥቷል፡፡ ርዕሱም የ1911ኙ የህዳር በሽታ (The Hedar Bȧseta of 1918) የሚል ነው፡፡ ምንጫቸው ካልተገለጸ በስተቀር ከዚህ ቀጥሎ የሚቀርቡት መረጃዎች ከዚህ ጽሑፍ የተወሰዱ ናቸው፡፡ በመካከል የሚጨመሩ አስተያቶች ግን የግል ናቸው፡፡

ይህ የህዳር በሽታ የአንደኛው ዓለም ጦርነት ማክተሚያ ላይ ተነስቶ እጅግ በጣም ብዙ ሰው ፈጅቷል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የገባው በ1910 ዓ.ም. በበልግ ወራት ነው፡፡ በወርሃ መጋቢት፡፡ ከዚያ በግንቦትም በሰኔም በሽታው መታየቱን የውጭ አገር ሰዎች ዘግበዋል፡፡

በዚህ በስፓኝ ኢንፍሉዌንዛ ወይም በፈረንሳዮቹ አጠራር በግሪፕ ተይዞ በኢትዮጵያ (በአዲስ አበባ) የመጀመሪያው ሟች እንደሆነ በግልጽ የሚታወቀው የ24 ዓመቱ ወጣት ግሪካዊው ስታማቲዎስ ጋኖታኪስ ነው፡፡ የሞተውም ሐምሌ 30 (ኦገስት 7) ነው፡፡ ራስ ተፈሪን ይህ የህዳር በሽታ የጀመራቸው ነሀሴ 21 ቀን ነው፡፡ ትንሽ አገግመው በሕዝብ ዘንድ የታዩት በ1911 መስከረም 20 ነው፡፡

በሽታው ሲደህ ሲደህ ቆይቶ ሕዝቡን ዘዝ የመታው በህዳር ነው፡፡ ከፓንክረስት ጽሑፍ እንደምንረዳው ሁኔታው እጅግ አሳዛኝ ነበር፡፡ መጀመሪያ ወደ ኢትዮጵያ በገባበት ገደማ ብዙ ሰው አላጠቃም፡፡ እየገደለም አልነበረም፡፡ ኋላ ኋላ ግን እንደ ሰደድ እሳት ሆነ፡፡ አንዱ ምስክር እንዳለው ሰዎች እንደ ዝንብ ረገፉ፡፡

በሽታው እየጠነከረ ሲሄድ አዲስ አበባ የሚገኙት ሦስት ፋርማሲዎች ተዘጉ፡፡ መድኃኒት የሚባል ነገር ጠፋ፡፡ ማስታገሻ የሚሆን እንኳን፡፡ በወቅቱ ስምንት ዶክተሮች አዲስ አበባ ነበሩ፡፡ አራቱ መጀመሪያ ገደማ ሞቱ፡፡ የራስ ተፈሪ ሐኪም፣አሳድ ቸይባንም ሞቱ፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ፍርሃት ነገሠ፡፡

አቡነ ማቴዎስ መናገሻ ማርያም ሄደው ተቀመጡ፡፡ የከተማው ከንቲባ፣ወሰኔ ዛማኔልም ከከተማው ወጥተው ሄዱ፡፡ ትንሽ ቆይተው ተመለሱ፡፡ ከንቲባ ወሰኔ እንደፈሩት ህዳር ላይ ሞቱ፡፡ መሥሪያ ቤት ሁሉ ተዘግቷል፡፡ ፖሊስ ሥራ አቁሟል፡፡ ፍርድ ቤትም ዝግ ነው፡፡ ሕግና ሥርዓት የሚያስከብር ጠፋ፡፡ የጣሊያኑ ተወካይ ለአገሩ መንግሥት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት መንግሥትም መንግሥታዊ ሥርዓትም ስለጠፋ እንግሊዝ፣ፈረንሳይና ጣሊያን ኢትዮጵያን ቀድመው መከፋፈል አስበውት በነበረው መንገድ ቢከፋፈሏት ይበጃል ሲል መልእክት ወደ ሮማ ላከ፡፡

ከ1910 ወርሃ መጋቢት ጀምሮ ሲያደባ የቆየው ይህ በሽታ ህዳር ላይ ስለፈነዳና አሰቃቂም ዘግናኝም ነገሮች ስላስከተለ አገሬው የሕዳር በሽታ አለው፡፡ የጉልበት ሠራተኞች ወደ አገራቸው ገቡ፡፡ ባለሥልጣኑም ቤቱን ዘግቶ ተቀመጠ፡፡ ቤተ መንግሥቱም ይዘጋ እንጂ ያልተያ የለም፡፡ እቴጌ መነን፣ነግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱም ታመው እንደነበር መርስኤ ኃዘን ወልደቂርቆስ “የሃያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ” በሚለው መጽሐፍ በህዳግ ማስታወሻ መልክ ተጽፏል፡፡

በየለጋሲዮኑ የሚኖሩት/የሚሠሩት የውጭ አገር ዜጎችም በአያሌው ረገፉ፡፡ መድሃኒት የሚባል በመጥፋቱ ሐኪሞቹ ጭምር ውስኪ ፣ ኮኛክ፣ ወይን ጠጡ እያሉ ይመክሩ ነበር፡፡ በእንግሊዝ ኢምባሲም ስፕራይት ነክ መጠጦችን ለሠራጠኞቹ እንዲጠጡ ያደርጉ ነበር፡፡ አረቄም እንደ መድሃኒት ተወሰደ፡፡ የባህር ዛፍ ቅጠል መታጠን በኢትዮጵያ በሁሉም ቦታ ተሳምቶ ህዝቡ ይታጠነው ጀመር፡፡

በተለይ በህዳር ወር በአንድ ቀን በአንድ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ከ100 እስከ 150 ሰው ድረስ ይቀበር ነበር፡፡

በየቤተክርስቲያኖቹ የመቃብር ቦታ ጠፍቶም ሌላ ቦታ ተቀበረ፡፡ ኋላ ቤተክስርሲያን ተሠራበት፡፡ መቃብር የሚቆፍር ሰው በመጥፋቱ የሟች ቤተሰብ ራሱ ይቆፍርም ነበር፡፡ አንድ ክንድ የማይሆን ርቀት ጫር ጫር አድረገው ስለሚቀብሯቸው ጅቡ፣ጥንብ አንሳው ውሻው አስከሬኑን እያወጣ በላው፡፡ አንዱ ቆፍሮ አስከሬን ሊያመጣ ሲሄድ ሌላው ቀብሮበት ያገኘዋል፡፡ አስከሬን የሚወሰድ ስለሌለ እናት የሞተ ልጇን፣ ልጅ አባቱን፣አባት የልጁን አስከሬን ብቻውን ወስዶ ይቀብራል፡፡

በየቤቱ ሞቶ የቀረው፣በየመንገዱ የተጣለውም ብዙ ነው፡፡ መርስኤ ኃዘን በዚህ መልኩ በየመንገዱ የወደቀው አንድ ሺ ይደርሳል ይላሉ፡፡


በአዲስ አበባ ብቻ ሳይቆም በሰሜን ወደ ደሴ፣ትግራይ፣ኤርትራም ተዛመተ፡፡ ፓንክረስት በወቅቱ ልጅ ሆኖ አድዋ የነበረውን ሲውዲናዊው ዶ/ር ሀሮልድ ኒይስትሮም (የተደበቀው ማስታወሻ የሚለውን በደጃዝማች አያሌው ብሩ ሕይወት ላይ የሚያጠነጥነውን መጽሐፍ የደረሰው) እንደነገራቸው በአድዋ ብቻ ወደ ሁለት መቶ ሰው ሞቷል፡፡ ይሄ አድዋ ብቻ ነው፡፡ በአገሪቱ በምዕራብም፣በደቡብም በምሥራቅም በኩል የብዙ ሰውን ሕይወት ቀጥፏል፡፡

በወቅቱ 50 ሺ ከሚሆነው የአዲስ አበባ ሕዝብ መካከል እንደ ጃንሆይ መረጃ (“ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ“ በሚለው መጽሐፋቸው እንደተገለጸው) ከአስር ሺ ሰው በላይ፣ እንደ መርስኤ ኃዘን 9 ሺ ገደማ ሰው አልቋል፡፡ መርስኤ ኃዘን በአገሪቱ በተቅላላው 40 ሺ እንደሞተ ተገምቷል ይላሉ፡፡

ይህ የህዳር በሽታ በአዲስ አበባ ከህዳር 21 (ጽዮን) ጀምሮ እየቀነሰ ሄደ፡፡ ወዲያውኑ አንድ ቀን ማታ ድብልቅልቅ ያለ ተኩስ አዲስ አበባን ናጣት፡፡ በሽታውን ያመጣውን መንፈስ ለማባረር ሲባል የተደረገ ተኩስ ነበር፡፡ ከዚያ ቀስ ቀስ እያለ ከቸነፈሩ የተረፈው ሰው ወደ መደበኛ ሕይወት መመለስ ጀመረ።

************
ይሄ ኮቪድ 19 (ሳምባ ቆልፍ) አዘናግቶ አዘናግቶ መያዢያ መጨበጫ እንዳያሳጣን ጥንቃቄያችንን እንጨምር፡፡ በህዳር በሽታም ብዙዎች የተረፉት ቤታቸውን ዘግተው ተቀምጠው ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሚዘገበው የሟች ቁጥር በፍጹም ሊያዘናጋን አይገባም፡፡ የሕዳር በሽታም አዘናግቶ አዘናግቶ (ቀስ ቀስ እያለ) ቆይቶ ነው ህዳር ላይ የፈጀን፡፡

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MULU production posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share