Sixty Nine 69

Sixty Nine 69 Consult , Council & Train!

የልዩ ፍላጎት ትምህርት የልዩ ፍላጎት ትምህርት ማለት ከመደበኛው ትምህርት በተለየ ሁኔታ የልዩ ትምህርት ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች እንደ እውቀታቸው መጠንና እንደ አስፈላጊነቱ በተለየ መልኩ ተ...
01/05/2024

የልዩ ፍላጎት ትምህርት
የልዩ ፍላጎት ትምህርት ማለት ከመደበኛው ትምህርት በተለየ ሁኔታ የልዩ ትምህርት ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች እንደ እውቀታቸው መጠንና እንደ አስፈላጊነቱ በተለየ መልኩ ተዘጋጅቶ የሚሰጥ የትምህርት አይነት ነው።
ልዩ ፍላጎት ትምህርት ራሱን በቻለ በልዩ ትምህርት ቤት ወይም በመደበኛ ትምህርት ቤት ውስጥ በሚገኙ የልዩ ፍላጎት ትምህርት መስጫ ክፍሎች ውስጥ ወይም በመደበኛ ትምህርት ቤት በመደበኛ ክፍሎች ውስጥ በልዩ ፍላጎት ትምህርት መምህር የሚሰጥ የትምህርት አይነት ነው።
ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆች በቤት ውስጥ የሚያስፈልጋቸውን አገዛ እና እርዳታ ለማግኘት ወላጆች ይህን ስልጠና መውሰዳቸው አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው፨ድርጅታችንም ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት የተለያዩ ስልጠናዎችን አዘጋጅቶ ይጠብቃቹዋል፨
ለበለጠ መረጃ
በ 0977696969
ወይም
በ 0113 696969 በመደወል መመዝገብ ይችላሉ፨

ስነ ልቦና ምንድን ነው? ስል ምን ያጠናል?ሳይኮሎጂ የሚለው ቃል ሳይኪ (ψυχή) እና ሎጊያ (λογία) ከሚሉ ሁለት የግሪክ ቃላት የተዋቀረ ነው። ሳይኪ "ነፍስ" ወይም "እስትንፋስ"ን ሲወ...
29/04/2024

ስነ ልቦና ምንድን ነው? ስል ምን ያጠናል?
ሳይኮሎጂ የሚለው ቃል ሳይኪ (ψυχή) እና ሎጊያ (λογία) ከሚሉ ሁለት የግሪክ ቃላት የተዋቀረ ነው። ሳይኪ "ነፍስ" ወይም "እስትንፋስ"ን ሲወክል ሎጎስ ማለት ደግሞ "ጥናት"ን ያመለክታል። ቃል በቃል ሳይኮሎጂ ማለት "ስለ ነፍስ የሚያጠና" የትምህርት ዘርፍ ማለት ነው።

ሰፋ አድርገን በዘመናዊ መነፅር ስናየው ሳይኮሎጂ ስለ ሰዎች (እንስሳትንም ሊያካትት ይችላል) ስሜት (emotion)፣ ባህርይ (behavior) እና አስተሳሰብ (cognition) የሚያጠና የትምህርት ዘርፍ ነው። የሰው ልጅ ሁለመና ብዙ ጊዜ በሶስቱ ነገሮች ይወሰናል (አንዱ ሌላው ላይ ተፅዕኖ ያደርሳል)። ዘርዘር አድርገን እንመልከተው፦

➊ Cognition (ሀሳብ): የተደበቀ የሰዎችኝ ሀሳብ፣ ዕቅድ፣ ማሰላሰል፣ ስልትና የችግር አፈታት ዘዴን ይጠቁማል።

➋ Behavior (ባህርይ)፡ የሀሳብ ተቃራኒ ሆኖ በግልፅ የሚታይ ድርጊትን ይወክላል (ለምሳሌ፦ አረማመድ፣ አበላል፣ አለባበስ፣ አካሄድ፣ መኮሳተር፣ ፈገግ ማለት...ወዘተ)።

➌ Emotion (ስሜት)። ሌላኛው የሳኮሎጂ የጥናት ማዕከል ስሜት ነው። ስሜት የሚሰሙንን ውስጣዊ ሁኔታ የሚገልጽ ነው (ለምሳሌ፦ ደስታ፣ ሀዘን፣ ንዴት፣ ፍርሃት፣ ጭንቀት...ወዘተ)።

የሰውን ልጅ ውድቀት፣ ስኬት፣ ጤናና ህመምን ለመረዳት ባህርይውን፣ አስተሳሰቡን እና ስሜቱን በጥልቀት መረዳት ያስፈልጋል። ሳይኮሎጂም የሚያደርገው ይሄንን ነው። እየቆየን እናብራራለን።

ህፃናት የትምህርት መማሪያ ጊዜያቸው ደርሶ ወደ ትምህርት ቤት ሲገቡ ወይም ካደጉ በኃላ በህይወታቸው በሚደርሱ የተለያዩ ገጠመኞች ምክንያት ትምህርት ቤት መሄድን ሊፈሩና ሊጠሉ ይችላሉ። በተለይ...
24/04/2024

ህፃናት የትምህርት መማሪያ ጊዜያቸው ደርሶ ወደ ትምህርት ቤት ሲገቡ ወይም ካደጉ በኃላ በህይወታቸው በሚደርሱ የተለያዩ ገጠመኞች ምክንያት ትምህርት ቤት መሄድን ሊፈሩና ሊጠሉ ይችላሉ። በተለይ ከፍ እያሉ ሲሄዱ ትምህርት ቤት ውስጥ ሊያጋጥማቸው የሚችል ዝቅተኛ የመሆን ስሜት፣ የአካባቢ መቀየር፣ በወላጅ መሀል የሚደርስ ፍቺ ወይም ሞት ልጆች ትምህርት ቤት መሄድን እንዲጠሉ ሊያደርጋቸው ይችላል። ይህ ሁኔታ ሲያጋጥም ልጆች ፍርሀታቸውን ማሸነፍ እንዲችሉ ምን ማድረግ ይቻላል?
ፍቅረ ሰላም ጌትነት የስምንት አመት እና የአምስት አመት ልጆች እናት ናት። አሁን በትምህርታቸው ጎበዝና ታታሪ የሆኑት ልጆቿ ታዲያ ትምህርት ሲጀምሩ ትምህርት ቤት ላለመሄድ በጣም ያስቸግሯት እንደነበር ታስታውሳለች። በተለይ የመጀመሪያ ልጇ።

የመጀመሪያ ልጇን ያክል አይሁን እንጂ ሁለተኛ ልጇም በተመሳሳይ ትምህርት ቤት ላለመሄድ ጥረት ታደርግ እንደነበር ፍቅረ ሰላም ትናገራለች። በአብዛኛው ይህን ጥላቻቸውን የሚገልፁትም በማልቀስና ትምህርት ቤት ላለመሄድ የተለያዩ ሰበቦችን በመፍጠር ነበር።

በዩናይትድ ስቴትስ ቴክሳስ ግዛት የጋብቻና የቤተሰብ አማካሪ እንዲሁም በዚሁ ዙሪያ ፀሀፊና አሰልጣኝ የሆኑት ዶክተር ሙላቱ በላይነህ እንደሚያስረዱት ይህ አይነቱ በህፃንነት እድሜ ላይ ትምህርት ቤት የመሄድ ፍራቻ ወይም ጥላቻ የሚከሰተው በእንግሊዘኛው ሰፓሬሽን አንዛይቲ ተብሎ በሚጠራው መለየት የሚፈጥረው ጭንቀት ምክንያት ነው።

ትምህርት ቤት የመሄድ ጥላቻ ወይም ፍራቻ በህፃናት ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የእድሜ ክልል ላይ ባሉ ልጆች ላይ ሊደርስ ይችላል። ለዚህ ምክንያቱ እንደየእድሜያቸው እና የአኗኗራቸው ሁኔታ እንደሚለያይ ዶክተር ሙላቱ ያስረዳሉ።

ሌላው ለልጆች ትምህርት ቤት መጥላት ምክንያት የሚሆነው ደግሞ በቤተሰብ መሃል የሚደርስ ግጭት ወይም በትምህርት ቤት ውስጥ የሚያጋጥም የዝቅተኛነት ስሜት በስነልቦናቸው ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ እንደሆነ ዶክተር ሙላቱ ጨምረው ያብራራሉ።

ከዚህም በተጨማሪ በትምህርት ድረጃ ዝቅተኛ መሆንና ከሌሎች ተማሪዎች ጋር አብሮ መሄድ አለመቻልም እንዲሁ ለትምህርት ቤት ጥላቻ አስተዋጽኦ ያደርጋል። በተለይ ወላጆቻቸው ለስራ ወይም ለኑሮ የሚኖሩበትን ቦታ ወይም ሀገር ቀይረው ወደ አዲስ ቦታ ሲሄዱ ይህ አይነቱ ችግር ጎልቶ ሊታይ ይችላል።

ልጆቻቸው ትምህርት ቤት መሄድ የሚያቸግሯቸው ብዙ ወላጆች በቁጣና በቅጣት ልጆችን ወደ ትምርህት ቤት እንዲሄዱ ለማድረግ ይሞክራሉ። ይህ አይነቱ አካሄድ ግን በተቃራኒው ልጆች እንዲርቁና ሌላ መደበቂያ እንዲፈልጉ እንደሚያደርጋቸው የሚያስረዱት ዶክተር ሙላቱ መፍትሄው ለልጆች ግዜ መስጠትና መነጋገር መሆኑን ያሰምሩበታል።

ዶክተር ሙላቱ አክለው ልጆች አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት በትምህርት ቤት እንደመሆኑ መጠን ከትምህርት ቤታቸውና ከመምህራኖቻቸው ጋር የቅርብ ግንኙነት መፍጠር ልጆችን ለመረዳትና ለማገዝ ቁልፍ መሰረት ነው ይላሉ።

ፍቅረሰላምም ልጆቿ ትምህርት ቤታቸውን እንዲለምዱ እና እንዲወዱ ማድረግ የቻለችው፣ በየቀኑ የሚያስጨንቃቸውንና የሚረብሻቸውን እንዲያካፍሉ በግልፅ በማናገርና ከትምህርት ቤታቸውና ከመምህራኖቻቸው ጋር በመነጋገር ነበር። ይህን በማድረጓ ልጆቿ ዛሬ ትምህርት ቤታቸውን ከመውደዳቸው በላይ ከጓደኞቻቸው ተግባቢና ውጤታማ መሆን ችለዋል።

“በሽታን የመፍራት አባዜ” ከልብና ደም ቧንቧ ህመም በላይ ገዳይ መሆኑን ያውቃሉ?***************=======******************በስዊድን ተመራማሪዎች የተደረገ ጥናት ስለጤናቸ...
19/04/2024

“በሽታን የመፍራት አባዜ” ከልብና ደም ቧንቧ ህመም በላይ ገዳይ መሆኑን ያውቃሉ?
***************=======******************
በስዊድን ተመራማሪዎች የተደረገ ጥናት ስለጤናቸው አብዝተው የሚጨነቁና በሽታን አጥብቀው የሚፈሩ ሰዎች እድሜያቸውን እያሳጠሩ ነው ብሏል፡፡
በቅርቡ የተደረገ ጥናት ስለጤናቸው አብዝተው የሚጨነቁ ሰዎች እድሜያቸውን ያሳጥራሉ ብሏል።
የስዊድን ተመራማሪዎች “በሽታ የመፍራት አባዜ” ያለባቸው ሰዎች ላይ ጥናት አድርገዋል።
በህክምናው “ኢልነስ አንዛይቲ ዲስኦርደር” የሚል ስያሜ ያለው ችግር ከተለያዩ ህመሞች አንጻር ገዳይነቱ ከሚታሰበው በላይ መሆኑን ጥናቱ አመላክቷል።

የዚህ ችግር ተጠቂዎች ስለጤናቸው ከልክ በላይ ይጨነቃሉ፤ ምንም በሽታ ሳይኖርባቸውም እንደታመሙ ያስባሉ። በዚህም ምክንያት ምንም ነገር ሳይገጥማቸው ወደ ህክምና ተቋማት በተደጋጋሚ ይመላለሳሉ።

አንዳንዶቹም “ገዳይ በሽታ” እንዳጠቃቸው በባለሙያዎች ይነገረናል በሚል ፍራቻ ወደ ሀኪም ቤት ከመሄድ ቤታቸው ውስጥ ያልያዛቸውን በሽታ ማስታመም ይመርጣሉ።

የፍርሃታቸው አንደኛው መንስኤ ወላጆቻቸውና የቅርብ ቤተሰቦቻቸውን ያጠቃ ከባድ ህመም በዘር ወደኛ ይተላለፋል የሚል ነው።

በዚህ ችግር የሚንገላቱ 1 ሺህ ሰዎችን ጨምሮ በ42 ሰዎች ላይ ለ20 አመታት የተደረገው ጥናትም ስለጤናቸው አብዝተው የሚጨነቁና የህመም ፍርሃት ያለባቸው ሰዎች ራሳቸውን ይበልጥ እየጎዱ እንደሚገኙ ነው ያመላከተው።

ጥናቱ በሽታን የሚሸሹና የሚፈሩት፤ ህመም ሳይጎበኛቸው ጭንቀታቸው ብቻ አካላዊና አዕምሯዊ ጤናቸውን የሚያዛባባቸው ሰዎች በልብ፣ በደም ቧንቧና መተንፈሻ አካላት በሽታዎች ምክንያት ከሚደርስ ሞት በበለጠ ለህልፈት የመዳረግ እድላቸው ከፍ ያለ መሆኑንም አሳይቷል።

በዚህ “ህመም የመፍራት አባዜ” ውስጥ ያሉ ሰዎች ለከፍተኛ ድብርትና ፍርሃት ስለሚጋለጡ ራሳቸውን እንደሚያጠፉም ተገልጿል።

በዚህ ህመምን ይዞኛል ወይም ሊይዘኝ ነው በሚል ከባድ ጭንቀት የሚሰቃዩ ሰዎች ለሌሎች በሽታዎች ተጋላጭ የመሆናቸውና የመሞት ምጣኔያቸውም ጭንቀት ከሌለባቸው ሰዎች እጅግ ከፍ ያለ መሆኑን ጥናቱ አመላክቷል።

የስዊድን ተመራማሪዎች ያደረጉት ጥናት በዚህ ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች ያለ እድሜያቸው የመሞት እድላቸው 84 በመቶ መሆኑንና ችግሩ ከሌለባቸው ሰዎች ከአምስት አመት በፊት ቀድመው እንደሚሞቱ ማሳየቱንም የዋሽንግተን ፖስት ዘገባ ያሳያል።

የድብርት መንስኤዎችበጅማ ዩኒቨርሲቲ የስነ አእምሮ ህክምና ሐኪም የሆኑት ዶክተር ኤሊያስ ገብሩ እንደሚያስረዱት በዘር ከሚተላለፈው የድብርት ሕመም በተጨማሪ ለበሽታው መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ በር...
15/04/2024

የድብርት መንስኤዎች

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የስነ አእምሮ ህክምና ሐኪም የሆኑት ዶክተር ኤሊያስ ገብሩ እንደሚያስረዱት በዘር ከሚተላለፈው የድብርት ሕመም በተጨማሪ ለበሽታው መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ምክንያቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ።

''የሚወዱትን ሰው በሞት ከማጣት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ከባድ ሀዘን፣ የሰውነታችንን ተፈጥሮአዊ አሰራር የሚረብሹ ሕመሞች፣ የአእምሮ ሰላምን የሚነሱ እንደ አካላዊ እና ጾታዊ ጥቃቶችን የመሳሰሉ ጉዳቶች፣ እንዲሁም በአንድም ሆነ በሌለ መንገድ ራስን ከማህበረሰቡ ማግለል ለከፍተኛ የድብርት ሕመም ሊያጋልጠን ይችላል።''

የገንዘብ እጥረትን የመሳሰሉና ሌሎች ማህበረሰባዊ ጫናዎችም ለከፍተኛ ድብርት ሊያጋልጡን እንደሚችሉ ዶክተር ኤልያስ ያስረዳሉ።

በሌላ በኩል ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ሴቶች ላይ ተለይቶ ከልጅ መውለድ ጋር ተያይዞ በእርግዝና ወቅት አልያም ከወሊድ በኋላ ድብርት ሊያጋጥም ይችላል።

የአካል ጉዳተኞች እና ቤተሰቦቻቸውም ቢሆኑ ለድብርት የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ነው።

10 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ወይም ከ 10 ሰዎች አንዱ ድብርት ወይም depression በሚባለው የአዕምሮ በሽታ የተጠቃ ነው፡፡ከነዚህ መካከልም ከግማሽ በላዩ በአስከፊ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡የቁ...
01/04/2024

10 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ወይም ከ 10 ሰዎች አንዱ ድብርት ወይም depression በሚባለው የአዕምሮ በሽታ የተጠቃ ነው፡፡ከነዚህ መካከልም ከግማሽ በላዩ በአስከፊ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡የቁጥሩ ግዙፍነት ሲታይና የማህበረሰቡ ግንዛቢ ሲገመገም ግን ቆም ብለን ማሰብ እንዳለብን ጥቆማ የሚስጥ አይመስላቹም? ስለዚህ ስለ ድብርት አንዳንድ ጠቃሚ መረጃዎቸን መጋራት የወዲታ ግዲታችን ነውና ወደዛው እናምራ
ድብርት ከስነ አእምሮ ህመሞቸ ዋነኛውና ተቀዳሚው ሲሆን አንድ ሰው ድብርት ወይም ጭንቀት በእንግሊዘኛው DIPRESSION በምንልው የስነ ልቦና በሽታ ተጠቅቷል የምንለው ከሁለት ሳምንት እስከ 15 ቀንና ከዚያ በላይ የቆየ የድብርት ስሚት ወይም የፍላጎት ማጣት ሲስተዋልበት ነው፡፡
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ማህበረሰቦች በድባቲ ወይም በጭንቀት ህመም የተጠቃን ሰው እንደ አንድ የጢና እክል እንደገጠመው ሰው ሳይሆን እንደ ግለስቡ ባህሪ በመቁጥር ‘እሱኮ ከሰው መቀላቀል አይወድም” “እሷኮ ምንም ነገር አይጥማትም” “እንደ ወለደች አራስ ከመኝታው አይወጣም” “ተዉት እሱን ባህሪው ነው” በማለት ለችግሩ ስር መስደድ የደረሻቸውን እንደሚያበረክቱ ያሳያል፡፡በዚህ መሃል እነዚህ የህመሙ ተጠቂዎች ችግራቸው ሳይታወቅላቸው እራሳቸውን እስከማጥፋት ሲደርሱ እናያለን፡፡ከቅርብ ግዚ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ብዙ እራሳቸውን ያጠፉ ሰዎችን ዚና መስማት የተለመደ እየሆነ መቷል፡፡ ከዚህም ከፍ ሲል በዚሁ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ነገራቶቸ ምስቅልቅል እንዳለባችው፣ተስፋ እንዳጡና የነሱ በህይወት መሰንበትም ሆነ መሞት የሚፈጥረው ነገር እንዳጡና እራሳቸውን ሊያጠፉ እንደሆነ በመናገር ይህን ባሉ በቀናት ውስጥ የሞታቸውን ዚና መስማት የዕለት ከዕለት ተግባራችን ከሆነ ሰነባብቷል፡፡
ይሂን ስንል የትኛውም አይነት የመጭነቅ ስሚት ሁሉ ደባቲ ወይም DIPRESSION ነው ማለት አይደለም፡፡አንድ ሰው ለሚወዳት ሚስቱ ስጦታ ለመስጠት አስቦ ነገር ግን ምን እንደሚሰጣት ግራ ተጋብቶ ሊጨነቅ ይችላል፡፡ተማሪ ፈተና ሲደርስ ሊጨነቅ ይችላል፡፡አንድ የቀዶ ጥገና ዶክተር ቀጣይ የሚሰራው የቀዶ ጥገና ኪዝ ሊያስጭንቀው ይችላል፡፡እነዚህ ሁሉ ግን የድብርት ህመም አይደሉም፡፡ከዚህ በታች ያሉት የድብርት ህመም ምልክቶች በአንድም በሊላም መልኩ ሲገለጡ ብቻ የድብርት ህመም ማለት እንችላለን፡፡
 አብዛኛውን ሰዐት የሚቆይ ተከታታይ የሆነ የመደበር ስሚት (ከ 12-15 ቀንና ከዚያ በላይ)
 ፍላጎት ወይም ስሚት ማጣት (ያስደስቱ የነበሩ ነገሮች አለማስደሰት)
 የብቸኝነት ስሚት
 የምግብ ፍላጎት ማጣት
 እንቅልፍ ማጣት
 የማስተዋል ችሎታ መቀነስ
 ስራ ላይ ትኩረት አለማድረግ
እነዚህ ምልክቶች መጠናቸው እየጨመረ በመጣ ቁጥር ተስፋ መቁረጥ ፣ ራስን መጥላት ብሎም እራሰን እስከማጥፋት ሊያደርስ ይችላል፡፡
_ _ _ _ _ _
ይቀጥላል

11/03/2024
አንተ ማለት ያልተነካ እምቅ ችሎታና ልብ ያላለቀ ጥንካሬ ያለህ ሰው ነህ፡፡ ይህንን ችሎታና ጥንካሬ አውጥተህ ሳታባክን ከተጠቀምክ   በ አጨር ጊዜ ውስጥ እድሜ ልክህን ስታልመው የኖረከውን ዐ...
24/01/2024

አንተ ማለት ያልተነካ እምቅ ችሎታና ልብ ያላለቀ ጥንካሬ ያለህ ሰው ነህ፡፡ ይህንን ችሎታና ጥንካሬ አውጥተህ ሳታባክን ከተጠቀምክ በ አጨር ጊዜ ውስጥ እድሜ ልክህን ስታልመው የኖረከውን ዐይነት ተምሳሌታዊ ስኬታማ ሰው ሆነህ የእርካታ ህይወት መምራት ትጀምራለህ፡፡
ለዚህም ይረዳህ ዘንድ፡-
1. የህይወት ተምሳሌቶቸ እነማን እንደሆኑ ዘረዝረህ ጻፋቸው፡፡
2. ከስማቸው ጎን ተምሳሌት አድርገህ እንድትወስዳቸው የገፋፋህ ቁም ነገሮቻችን አስቀምጥ
3. የተምሳሌቶቻቸው መልካመ፣ ምግባራትን የህይወትህ መርሆች አድርገህ በቆራጥነት ለመያዝና ለመተግበር ወስነህ ጀምር፡፡
4. በዚህ አጭር ጌዜ ወስጥ ራሰህ ለሌሎች ሰዎች ተምሳሌት የሚሆን ንቃትና ብቃት ተላብሰህ ታገኘዋለህ
ማንኛውም ሰው በሌሎች ውስጥ ያለን ጥንካሬ ጭሎታና በደንብ ማየት ( በጣም ከባድ ስራ ነው) ከታቻለ የራሱን ጥንካሬና ችሎታ ለይቶ ስኬታማ ለመሆን አያዳግተውም፤፤ ሁሌም ራስህ ውስጥ የተሸሸገውን የተለየ የተምሳሌትነት ችሎታና ብቃት በትጋት ፈልፍለህ በማውጣት ስኬታማነትህን አስመስክር፡፡

በራስ የመተማመን ስሜታችንን ባቆለቆለ ቁጥር ስለራሳችን አሁናዊ ሁኔታ ጨለም ብሎ እንዲታየን ያደርገናል እንደነዚህ አይነት አታካችና ውሉ የጠፋ ጥምዝምዝ የህመም ሸለቆ ውስጥ በምንገባበት ጊዜ ...
17/01/2024

በራስ የመተማመን ስሜታችንን ባቆለቆለ ቁጥር ስለራሳችን አሁናዊ ሁኔታ ጨለም ብሎ እንዲታየን ያደርገናል እንደነዚህ አይነት አታካችና ውሉ የጠፋ ጥምዝምዝ የህመም ሸለቆ ውስጥ በምንገባበት ጊዜ ራስን መጥላት ፤ተስፋ መቁረጥ ስልቹነት፤ ራስን አቅመቢስ አድርጎ ማየት፤ወኔ ቢስነት፤ ድብርት፤ወዘተ… የመሳሰሉት ስሜቶች ይጫኑናል፡፡
በመድሃኒቶቹ ራሳችንን በደንብ አክመን ቶሎ መዳን ይኖርብናል፡፡
መድሀኒት 1 - በፊት የነበረንን በራስ የመተማመን የአልበገርነት መንፈስ ደጋግመን ማስታወስ፤
መድሃኒት 2 - አስደሳች መንፈስ በምናባችን ፈጥረንና አምጥቀን በመላበስ ማጣጣም፤
መድሀኒት 3 - ድጋሚ ፈጥረን አምጥቀን በመላበስ ማጣጣም የጀመርነውን ስሜት በውስጣችን እንዳይነቀል አድርጎ በማስረጽ መነሳት፤
መድሃኒት 4 - ከተነሳን በኃላ ድጋሚ እንዳይወርድ አድርጎ መስቀል ናቸው፡፡

በሚገጥማቸው ማንኛውም  አይነት መሰናክሎች  ሳይደናቀፉ በህይወት መንገዳቸው በአይገበሬነትና በጽናት የሚራመዱ ሰዎች  የሚጎናጸፉት ልክ የሌለውን የእርጋታና የመተማመን ስሜት ልብ ብለሀል? አዎ...
10/01/2024

በሚገጥማቸው ማንኛውም አይነት መሰናክሎች ሳይደናቀፉ በህይወት መንገዳቸው በአይገበሬነትና በጽናት የሚራመዱ ሰዎች የሚጎናጸፉት ልክ የሌለውን የእርጋታና የመተማመን ስሜት ልብ ብለሀል?
አዎ የጎደላቸውን አሳንሰው ጸጋቸውን አግዘፈው ያያሉ! ለምስጋና እነጂ ለወቀሳ ትዝ አይላቸውም:: የሚገጥማቸው እንቅፋቶች ሁሉ ወደ ምርኩዝነት ይቀይሩታል::በ ክረምት በበጋ በራሳቸው በሚዘሩት የማይቋረጥ ተነሳሽነት የስኬት አዝመራቸውን ዘወትር ያፍሳሉ፡፡
እርግጥ ነው በህይወታችን ውጣ ውረድ መሃል የማይገፉ ግዙፍ ቋጥኝ የሚመስሉ ደንቃራዎች ሊያጋጥሙን ይችላሉ፡፡ በዚህ አይነት ቅጽበትም ቢሆን ቶሎ ሐሞታችንን ከማፍሰስ ቶሎ መታጠቂያችንን አጥብቀንና በሌላ መንገድ አሳብረን የስኬት አሳንሰራችን ላይ መውጣት አለብን ፡፡
አይነ ህሊናችንን አብርተን እዝነ ልቦናችንን ከፍተን ከተመለከትናት የምንኖርባት አለም በተዓምራት መካከል አንዱና ዋነኛው ራስህ ሆነህ ታገኘዋለክ፡፡ራስህ ተዐምር መስራት ያቅተኛል ብለህ ታስባለህ? በጭራሽ!

እሳቱን በቤንዚን ሳይሆን በውሃ ለማጥፋት ሞክርበቅርቡ የተደረገ አንድ ጥናት እንዳረጋገጠው ሴቶች ስለ አንድ ነገር እያሰቡ ማውራት ወይም እያወሩ ማሰብ ሲችሉ ወንዶች ግን ሁለቱን ነገሮች በተመ...
03/01/2024

እሳቱን በቤንዚን ሳይሆን በውሃ ለማጥፋት ሞክር
በቅርቡ የተደረገ አንድ ጥናት እንዳረጋገጠው ሴቶች ስለ አንድ ነገር እያሰቡ ማውራት ወይም እያወሩ ማሰብ ሲችሉ ወንዶች ግን ሁለቱን ነገሮች በተመሳሳይ ሰአት መከወን አይሆንላቸውም፡፡ ወይ አስበው ያወራሉ አልያም አውርተው ያስባሉ፡፡ በመሆኑም፡-
አንቺ - የህይወት ተጓዳኝሽ የሆነውን ወንድ በተናደደበት ቅጽበት ስሜቱን በዝርዝር ለማስረዳት እንደሚቸገር ተረጂ ( ባይናገረውም ግን በተለያዩ መንገዶች ሊያንጸባርቀው እንደሚችል መዘንጋትም ሳይኖርብሽ )
አንተ - የህይወት ተጓዳኝህ የሆነችውን ሴት ምንም በንዴት በሚንቀለቀል ስሜት ውስጥ ብትሆንም እንኳን ንግግርዋን በደርዝ በደርዙ ስታብራራ ስታያት አያናድድህ፡፡
አንተም አንቺም በመጀመሪያ ተረጋጉ፤ ብረዱ ከዚያም ቁጭ ብላችሁ ተነጋገሩ፤ እንጂ አንዳችሁ በንዴት ተቃጥላችሁ እየነደዳችሁ ሌላኛችሁ በውሀ ፋንታ ቤንዚን እየረጫችሁ ግጭቱን አታፋፍሙት፡፡ ለምን ብትሉ የተሰራችሁበት ገመድ የብረት ካቦ ቢሆንም እንኳን በረመጡ ከመበላት አይድንምና!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sixty Nine 69 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share