Liverpool fans in ethiopia we will never walk alone

Liverpool fans in ethiopia we will never walk alone Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Liverpool fans in ethiopia we will never walk alone, Business service, Addis Ababa.

በቀላል መንገድ ሁለት ስራ ይስሩ አንድ ስለኮሮና በበጎ ፍቃድ ግንዛቤ መፍጠር ሲሆን ሌላው ደግሞ 1 ሰው በጋበዛችሁ ቁጥር 2 ብር ከአንድ ሰው Ethiopian union እንድ ያስብላቹሀል።በፈ...
16/06/2020

በቀላል መንገድ ሁለት ስራ ይስሩ አንድ ስለኮሮና በበጎ ፍቃድ ግንዛቤ መፍጠር ሲሆን ሌላው ደግሞ 1 ሰው በጋበዛችሁ ቁጥር 2 ብር ከአንድ ሰው Ethiopian union እንድ ያስብላቹሀል።
በፈለጉት ባንክ ማውጣት ይቻላል ቀላል ነው ሁላችሁም ሞክሩት።

ከዛሬ 29 ዓመታት በፊት (ግንቦት 27 ቀን 1983 ዓ.ም) … የጎተራ ግምጃ ቤት ፍንዳታመላውን አዲስ አበባን ያስደነገጠው፣ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው፣ በርካቶችን ያቆሰ...
04/06/2020

ከዛሬ 29 ዓመታት በፊት (ግንቦት 27 ቀን 1983 ዓ.ም) … የጎተራ ግምጃ ቤት ፍንዳታ

መላውን አዲስ አበባን ያስደነገጠው፣ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው፣ በርካቶችን ያቆሰለው … የጎተራ ጦር መሳሪያ ማከማቻ ግምጃ ቤት ፍንዳታ የተከሰተው ከዛሬ 29 ዓመታት በፊት (ግንቦት 27 ቀን 1983 ዓ.ም) ነበር፡፡

- - -

ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ ከአንድ ሳምንት በኋላ የተከሰተው ይህ ፍንዳታ፣ ከጎተራ እስከ ሰሜን ሆቴል የተሰማ … ከአቃቂ እስከ ኮተቤ ድረስ ቀልብን የገፈፈ ክስተት ነበር። ከኢትዮጵያ ጋር ልዩ ቁርኝት የነበረው ታዋቂው ኬንያዊ የፎቶ ጋዜጠኛ መሐመድ አሚን (Mohamed "Mo" Amin) በፍንዳታው አንድ እጁን አጥቷል፡፡ ጆን ማታይ የተባለው ባልደረባው ደግሞ ለሕልፈት ተዳርጓል፡፡

- - -

በወቅቱ የነበረው ጊዜያዊ አስተዳደር ለፍንዳታው ጣቱን በደርግ ሰዎች ላይ ቀሰረ። ‹‹ማከማቸውን ሆን ብለው ያፈነዱት ‹የደርግ ርዝራዦች› ናቸው›› አለ። የሆነው ሆኖ የጎተራው ፍንዳታ በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ሥፍራ ካለው የግንቦት ወር ክስተቶች አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል።

01/06/2020

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ስድስት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ !!

በተያዘው ዓመት ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 605 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

በሚያዚያ ወር ብቻ 79 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡም ታውቋል።

ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቱ እንዳስታወቀው ለግድቡ ግንባታ በያዝነው ዓመት እስካሁን ድረስ 605 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል።

ገንዘቡ የተሰበሰበው በ8100 አጭር የጽሑፍ መልዕክት ገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብርና በቦንድ ሽያጭ ሣምንት መሆኑን የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አብርሃም ገልጸዋል።

የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ እስካሁን 13 ነጥብ 54 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ከጽሕፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ አሁናዊ አፈጻጸም 73 ነጥብ 7 በመቶ መድረሱ ይታወቃል።

ኤፍሬም ስዩም **ግጥምና ፍቅር**:ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2926 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ አምስት (85) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል❗️⚡️በአጠቃላይ በሀገራችን ሻይረ...
01/06/2020

ኤፍሬም ስዩም **ግጥምና ፍቅር**:
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2926 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ አምስት (85) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል❗️

⚡️በአጠቃላይ በሀገራችን ሻይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1257 ደርሷል፡፡

⚡️ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 51 ወንድ እና 34 ሰች ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1ወር እስከ 65 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

⚠️ 72።ሰዎች ከአዲስ አበባ ⚠️

⚡️አራት(4) ሰዎች ከትግራይ ክልል

⚡️ አምስት (5) ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል

⚡️ አንድ (1) ሰው አማራ ክልል

⚡️ሶስት (3) ሰዎች ከሶማሊ ክልል ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የተጋላጭነት ሁኔታ

• የውጭ ሀገር ታሪክ ያላቸው 19

•በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው 18

• የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በሽታ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው 48

31/05/2020

አጫጭር መረጃዎች

~ በፓኪስታን የሚገኝ የመድሃኒት ኩባንያ ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን የሚያግዝ መድሃኒትን ከባንግላዲሽ ሊያስመጣ መሆኑን አስታወቀ፡፡በአሜሪካና ጃፓን ለጽኑ ህሙማን እንዲሰጥ ፍቃድ የተሰጠዉን ረምዲሲቪር የተሰኘዉን መድሃኒት ነዉ፡፡በፓኪስታን ባለፉት 24 ሰዓት ከፍተኛ የተባለዉ የ56 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት ተደርጓል፡፡

~ ክሮሺያ ለ10 ሀገራት ድንበሯን ክፍት እንደምታደርግ አስታወቀች፡፡ሆኖም ወደ ክሮሺያ የሚመመጡ ጎብኚዎች ከኮሮና ቫይረስ ነጻ የተባሉበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

~ ግሪክ ከ17 ቀናት በኃላ ከ29 ሀገራት ለሚመጡ ቱሪስቶች በሯን ክፍት ልታደርግ ነዉ፡፡የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተስፋፋባቸዉ እንግሊዝ፣ፈረንሳይ፣ስፔንና ጣልያን ለጊዜዉ ቱሪስቶች እንዳይመጡ ግሪክ ከልክላለች፡፡

~ በናይጀሪያ የሚገኙ ሆስፒታሎች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋትን ተከትሎ በተለያየ ህመም የሚመጡ ሰዎችን እያገለሉ መሆኑ ተሰማ፡፡ከሆስፒታል በራፍ በርካቶች እየተመለሱ መሆኑን ሪፖርቶች አመላክተዋል፡፡የቫይረሱ ተጠቂዎች በሀገሪቱ 9ሺ ደርሷል፡፡

~ በቻይና የሚደገፈዉ የእስያ የመሰረተልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፊሊፒንስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያሳደረባትን ተጽእኖ ለመከላከል ለምታደርገዉ ጥረት 750 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ብድር ሊሰጣት ነዉ፡፡

~ በ24 ሰዓት ዉስጥ የ232 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት ያደረገችዉ ሩሲያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሀገሪቱ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

~ በቱርክ ከ2 ወራት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬዉ እለት የሰዉ ቁጥር በተገደበበት መልኩ የእምነት ስፍራ ክፍት ተደርጓል፡፡የጁማ የጸሎት ስነስርዓት ተከናዉኗል፡፡ከ160ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ የ4,461 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

21/05/2020

ኢንተርኔት ላይ የምታጠፉትን ግዜ ገንዘብ አግኙበት። በየቀኑ ኢንተርኔት ላይ ከ3―5 ሰአት የምታጠፉ ከሆነ ከ1000―10,000 ብር ማግኘት ትችላላችሁ። የሚከተለውን ሊንክ ተከትላችሁ ተመዝገቡ። በየሳምንቱ የማይቋረጥ ገቢ አግኙ፦

በሌላ የራቁት ዜናስፔናዊው ጋዜጠኛ በቀጥታ ሰርጭት ከቤቱ ቃለመጠይቅ እየተደረገለት ግማሽ እራቁቷን ሆና ከጀርባው የታየችው ሴት ወቀሳን አስከትሎበታል።አልፎንዞ ሜርሎስ የተባለ ስፔናዊው ጋዜጠኛ...
29/04/2020

በሌላ የራቁት ዜና
ስፔናዊው ጋዜጠኛ በቀጥታ ሰርጭት ከቤቱ ቃለመጠይቅ እየተደረገለት ግማሽ እራቁቷን ሆና ከጀርባው የታየችው ሴት ወቀሳን አስከትሎበታል።

አልፎንዞ ሜርሎስ የተባለ ስፔናዊው ጋዜጠኛ ባለፈው አርብ በዪቲዮብ ቻናል በሚተላለፈው ‘State of Alarm’ በተሰኝ ፕሮግራም ላይ አንግዳ ሆኖ ከቤቱ በቀጥታ ስርጭት ላይ ቃለመጠይቅ እያረገ አንዲት ግማሽ እራቁቷን የሆነች ሴት ራቅ ባለ ቦታ ከጀርባው በመታየቷ " ከብር ቢስ " በማለት ሶሻል ሚዲያዎችና ታብሎይድ ጋዜጦች የስድብ ናዳ አውርደውበታል።
ነገሩን ደግሞ የከፋ ያደረገው በቤቱ ውስጥ የታየችው ሴት ፍቅረኛው የቀድሞ የቢግ ብራዘር ተወዳዳሪዋ ማርታ ሎፔዝ ሳትሆን ስፓኒሽ ቲቪ ሾው ላይ ዘጋቢ የሆነችው አሎክስያ ሬቫስ መሆኗ ነው።

በዚህም የተናደደችው ፍቅረኛው ማርታ ሎፔዝ ክስተቱን " አጅግ አፀያፊና አሳፋሪ " በማለት ከጋዜጠኛው ጋር የነበራትን የፍቅር ግንኙነት እንዳቆመች በስፔን ለሚታተሙ ታብሎይድ ጋዜጦች ተናግራለች።

አልፎንዞ ሜርሎስ ፍቅረኛውን ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን ጉዳዩን በዪቲዮብ እና በኢንስታግራም ያቀጣጠሉትን ጋዜጠኞች ግን ወቅሷል ሲል አር ቲ ሚዲያ ዘግቧል።
በቴሌግራም ቻናላችንም ይቀላቀሉን https://telegram.me/yidenek16

የህንዱ ኮከብ ተዋናይ ኢርፋን ካሀን ከዚህች ዓለም በሞት ተለየየ 53 ዓመቱ የህንዱ ኮከብ ተዋናይ ኢርፋን ካሀን በትልቁ አንጀቱ ላይ ኢንፌክሽን ያጋጠመው ሲሆን በሳምንቱ መጀመሪያ ቀናት ወደ ...
29/04/2020

የህንዱ ኮከብ ተዋናይ ኢርፋን ካሀን ከዚህች ዓለም በሞት ተለየ

የ 53 ዓመቱ የህንዱ ኮከብ ተዋናይ ኢርፋን ካሀን በትልቁ አንጀቱ ላይ ኢንፌክሽን ያጋጠመው ሲሆን በሳምንቱ መጀመሪያ ቀናት ወደ ሙምባይ ሆስፒታል ቢወሰድም ሕይወቱን ማትረፍ ግን አልተቻለም፡፡

ዘ ላይ ኦፍ ፒአይ ፣ ዘ ላንች ቦክስ ፣ ጁራሲክ ወርልድና አሜዚንግ ስፓይደር ማን በተሰኙ ፊልሞች ላይ የተወነው ኢርፋን ፤ በ 2018 በኒውሮኢንዶክሪን እጢ ተጠቅቶ ህክምና ማግኘቱም ይታወሳል፡፡ በወቅቱም ቤተሰቦቹ እንደገለፁት በካንሰር ካለበት ጫና የተነሳ በተደጋጋሚ ይናገራት የነበረችው ቃል ‹‹አምናለሁ እጅም ሰጥቻለሁ›› የሚለውን ነበር፡፡ ይሁንና ግን ይህን ካለበት 2 ዓመታትን መዘለቅ ችሎም ነበረ፡፡

በዓለም ዙሪያ ስሙን ያገነነለት ስላምዶግ ሚሊየነር ፊልም ላይም የነበረው ተሳትፎ አይረሴ ነው፡፡

ህንዳዊው ተዋናይ በህንድ ቦሊውድ ፣ በብሪቲሽና በአሜሪካ ሆሊውድ ፊልሞች ላይ ተሳትፏል፡፡ ከ 30 ዓመታት በላይ በፊልሙ የቆየ ሲሆን ከ 50 በላይ ፊልሞች ላይ ተውኗል፡፡በዚህም የብሄራዊና ፊልምዌር አዋርድን ጨምሮ በርካታ ክብሮችን ተቀዳጅቷል፡፡

በገፀ ባህሪዎቹ ላይ በብዙ ዝምታ ውስጥ የሚጥላቸው ቃላት አጠቃቀምና በአይን ገለፃው ማንም ይህን ሰው አይረሳውም፡፡

ኢርፋን ጠንካራ፣እስከመጨረሻው የሚታገልና ለቀረቡት ሁሉ ከፍታን አቅርቦ በማሳየት የሚታወቅ ሰው ነበረ፡፡

ከ 2018 ጀምሮ ግን በትግል ውስጥ ቀሪ ዘመኑን ስለማሳለፉ ሁሌም በዙሪያ የነበሩትና ታላቅና ገናናነቱን ወደኋላ ጥሎ ስለእነርሱ መኖሩን ምስክርነታቸውን የሚሰጡት ቤተሰበኖቹ ይገልፃሉ፡፡

ከ 1995 ጀምሮ ከሱታፓ ሲክዳር ጋር በትዳር መጣመሩ ይታወቃል፡፡
በቴሌግራም ቻናላችንም ይቀላቀሉን https://telegram.me/yidenek16

በቴሌግራም ቻናላችንም ይቀላቀሉን
28/04/2020

በቴሌግራም ቻናላችንም ይቀላቀሉን

ማንነቱን የሚያውቅ አንባቢ ትውልድ ለመፍጠር የተቻለንን በሙሉ እናደርጋለን በዚህም መሠረት ከመፀሐፍት የተወሰዱ ቅንጭቦች እንዲሁም የሀገር ባለውለታውች ይዘከሩበታል ስዕል ግጥሞች .....

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Liverpool fans in ethiopia we will never walk alone posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share