Pioneers Ethiopia

Pioneers Ethiopia provide current informative s to foster Ethiopian development. This may include technologies, news o, Job opportunities.

and also other development issues and discussions. https://miggster.com/signup/behailucrowd1

20/11/2025
14/01/2024
03/11/2023

" ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም የፋይናንስ ተቋም ገንዘብ ያስቀመጡ ሰዎች ገንዘባቸው በገንዘብ መድን ፈንድ ዋስትና ያገኛል "

በኢትዮጵያ በባንኮች ገንዘብ ከሚያስቀምጡት አብዛኛዎቹ ወይም 95 በመቶ የሚሆኑት በባንክ ያለው የገንዘብ መጠን ከ100,000 ብር በታች መሆኑ ተገለፀ።

ይህ የተገለፀው ኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ወደ ሥራ መግባቱን በተነገረበት ጊዜ መሆኑን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

በተለያዩ ገንዘብ ተቋማት ላለ ተቀማጭ ገንዘብ ዋስትና የሚሰጥ የገንዘብ መድን ፈንድ ተቋቁሞ ዛሬ በይፋ ስራ ጀምሯል፡፡

ይህ የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነው ተብሏል።

ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም የፋይናንስ ተቋም ገንዘብ ያስቀመጡ ሰዎች ገንዘባቸው በዚሁ ፈንድ ዋስትና ያገኛል የተባለ ሲሆን ጥበቃው የሚመለከተው 100,000 ብር እና ከዚያ በላይ የሆነን ብቻ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ መርጋ ዋቆያ ተናግረዋል።

ይህም በፋይናንስ ዘርፍ ላይ ከተፈፀሙ ለውጦች አንዱ ነው ተብሏል።

ፈንዱ አደረጃጀቱ ምን ይመስላል የሚለውን የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ ተናግረዋል። የፈንዱ ስልጣንና ተግባር በክፍያ ካዝናነት የተገደበ ነው ተብሏል።

አላማው ህዝባዊ ነው የተባለ ሲሆን የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ ፈንድ በመንግስት እንደሚተዳደር ተገልጿል።

ምክትል ገዢው አንድ የፋይናንስ ተቋም የሚወድቅ ከሆነ ኮሽታ ሳያሰማ ህዝቡን ሳይረብሽ ኢኮኖሚውንም ሳይረብሸው እንዲወጣ ፈንዱ ይሰራል ብለዋል።

ይህ በሚሆን ጊዜም በመድን የተሸፈነውን ገንዘብ ለአስቀማጩ ከ 7 ቀን እስከ 90 ቀን ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንደሚመለስ አስረድተዋል።

147 ሀገራት የተቀማጭ ገንዘብ መድን ፈንድ ተቋም አላቸው የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያ 148ተኛ ሀገር ሆናለች።

የዚህ መረጃ ባለቤት ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

30/10/2023
አዲስ በምሽት በፎቶምንጭ ማህበራዊ ሚድያ
30/10/2023

አዲስ በምሽት በፎቶ
ምንጭ ማህበራዊ ሚድያ

በአዲስ አበባ ከተማ በህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማስተካከያ ተደርጓል****************(ኢ.ፕ.ድ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የሚዲ-ባሶች እና የሚኒ-ባስ ታክሲ...
30/10/2023

በአዲስ አበባ ከተማ በህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማስተካከያ ተደርጓል
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የሚዲ-ባሶች እና የሚኒ-ባስ ታክሲዎች የአገልግሎት ታሪፍ ላይ ማስተካከያ ማድረጉን ማምሻውን አስታውቋል፡፡

አዲሱ የታሪፍ ማስተካከያም ከነገ (ጥቅምት 20 ቀን 2016) ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልጿል፡፡

ቢሮው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች አዲስ በተሻሻለው ህጋዊ የታሪፍ ተመን ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስቧል።

ይህንን በሚተላለፉ ላይ እርምጃ አንደሚወሰድም ነው የገለጸው።

ህብረተሰቡ ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ሲያጋጥሙት በአቅራብያው ለሚገኝ የህዝብ ትራንስፖርት ስምሪትና ቁጥጥር ባለሙያዎችና ለትራፊክ ፖሊስ እንዲያመለክት ተጠቁሟል።

እንዲሁም በአቅራቢያ ባለ የትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በአካልና በነፃ የስልክ መስመር 9417 ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል ቢሮው አስታውቋል፡፡

የታሪፍ ማስተካከያው የከተማ አውቶብስን እና የቀላል ባቡርን እንደማይመለከት ተጠቁሟል፡፡
ኢፕድ

Address

ADDIS ABABA
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251984053986

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Pioneers Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Pioneers Ethiopia:

Share