Rahel Stockholm

Rahel Stockholm we will gonna create a strong tie with our service customers and boost the confidence of customers b

ዝክረ ክቡር ዶ/ር አርቲስት ዓሊ መሐመድ ሙሣ ( ዓሊ ቢራ) ከ50 ዓመታት በላይ በሙዚቃ ዓለም በመቆየት ዘመን ተሻጋሪ የሙዚቃ ስራዎቹን ለሕዝብ በማድረስ ከፍተኛ ዝናና ተቀባይነት ያተረፈውን ...
06/11/2022

ዝክረ ክቡር ዶ/ር አርቲስት ዓሊ መሐመድ ሙሣ ( ዓሊ ቢራ)

ከ50 ዓመታት በላይ በሙዚቃ ዓለም በመቆየት ዘመን ተሻጋሪ የሙዚቃ ስራዎቹን ለሕዝብ በማድረስ ከፍተኛ ዝናና ተቀባይነት ያተረፈውን ድምፃዊ ዓሊ ቢራ (የክብር ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ዓሊ ቢራ የተወለደው መስከረም 15 ቀን 1940 ዓ/ም በድሬዳዋ ከተማ ነው። በህጻንነቱ የተለያዩ የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ሙዚቃዎችን እያደመጠ ያደገው ዓሊ ለትምህርት ቤት ጓደኞቹና ለቤተሰቦቹ በማንጎራጎር ነበር የሙዚቃ ህይወቱን የጀመረው። በድሬደዋ ውስጥ ብዙ ቋንቋዎች መኖር ያልገደበው ዓሊ በዐረብኛ፣ ኦሮምኛ፣ አደርኛና ሶማሊኛ ሙዚቃዎችን ይጫወት ነበር።

ከዚያም በ14 ዓመቱ አፍራን ቃሎ የተባለ የኦሮሞን ሙዚቃ ለማስተዋወቅ አላማ ያደረገ የባህላዊ ሙዚቃ ቡድንን ተቀላቀለ።

የገንደቆሬው ዓሊን ወላጆቹ ያወጡለት ስም ዓሊ መሐመድ ሙሳ ብለው ነው።
በኋላ ዓሊ ቢራ ተባለ። ይኸውም በአፍራን ቃሎ ቡድን ውስጥ ሌላ ዓሊ የተባለ ልጅ በመኖሩ ሁለቱን ለመለየት ዓሊ መጀመሪያ ካዜመው "BIRRAA DHAA BARIHE" "ቢራ ዳ ባሬ" የሚለው ዘፈኑ "ቢራ" የሚለው ተወስዶ "ዓሊ ቢራ" ተባለ። ወደ አዲስ አበባ በመሄድ የተለያዩ ባንዶች ውስጥ የተጫወተው ዓሊ በ1976 ዓ/ም ከስዊድናዊት ዲፕሎማት ባለቤቱ ጋር ከኢትዮጵያ በመውጣት ኑሮውን በውጭ ሃገር አደረገ።

ዓሊ ቢራ የመጀመሪያ ትምህርቱን በመድረሳ ጅዳ እና በልዑል መኮንን ትምህርት ቤት፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በካቴድራል ትምህርት ቤት ተከታትሏል። አሜሪካ በሚገኘው የሳንታ ሞኒካ ኮሌጅም የሙዚቃ ትምህርትም ተከታትሏል።

ዓሊ ቢራ በ1955 ዓ/ም ድሬዳዋ ውስጥ በአፍረን ቃሎ ባንድ አጃቢ ዘፋኝ በመሆን ከሰራ በኋላ በክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራ ተቀጥሮ ለ3 ዓመታት በድምፃዊነት ተጫውቷል። ችሎታው እየጎለበተ ሲሄድም አይቤክስ ባንድን በመቀላቀል ለ8 ዓመታት የሙዚቃ ሥራዎቹን በዲአፍሪክ ሆቴል ሲያቀርብ ቆይቷል።

ዓሊ ቢራ በአጠቃላይ 264 የሚደርሱ ዘፈኖችን የተጫወተ ሲሆን፤ ለህትመት ያበቃቸው የካሤት አልበም ቁጥር ግን 6 ብቻ ነው።
ዓሊ ቢራ በዘፈኖቹ ፖለቲካዊ ጉዳዮች እያነሳ በመጫዎትም ይታወቃል። ስለዚህም ሲናገር
"በቋንቋችን ላይ የነበረው ጫና ትንሽ የበዛ ነበር። እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ግን ደግሞ ኦሮሞም ነኝ። የነበረው ስርዐት ግን ይሄን አይቀበለውም። ከሌሎች በተለየ ኦሮሞ እና ኦሮምኛ ቋንቋ ላይ የተለየ ተፅዕኖ ነበረው። ስለዚህ በወቅቱ የነበረውን ነገር በመንቀፍ እዘፍን ነበር" ብሏል።

ዓሊ ቢራ ከመዝፈንም ባሻገር ፒያኖ፣ ጊታርና ኡድ የመሳሰሉትን የሙዚቃ መሣሪያዎችንም ይጫወታል፣ 8 ያህል ቋንቋዎችንም ይናገራል። ኦሮምኛ፣ አማርኛ፣ ሶማልኛ፣ አፋርኛ፣ ሃረሪኛ፣ ዐረብኛ እና እንግሊዝኛ በዋናነት ይጠቀሳሉ።

ዓሊ ቢራ የኃምሣ ዓመት የሙዚቃ ህይወቱ የወርቅ ኢዮቤልዮ " መማር አሁንም መማር " በሚል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮለታል።

ዓሊ ጤንነቱን በተመለከተ በጭንቅላቱ ላይ በበቀለ ዕጢ ምክንያት የግራ ዐይኑ ማየት እንዳቆመ እና የቀኙም እንደተዳከመበት፣ እግሩም በካንሠር ተጠቅቶ የነበረ ቢሆንም በቀዶ ጥገና ህክምና ድኖለት ነበር።

ዓሊ ቢራ ለራሱ እና ለሌሎች ድምፃውያን በርካታ ግጥም እና ዜማዎችን ደርሷል፡፡ የራሱን ለየት ያለ የአዘፋፈን ስልትም ፈጥሯል፡፡ በሀገራችን ታሪክ ታላላቅ ከሚባሉ የሙዚቃ ቡድኖች ጋርም ሰርቷል፡፡ በሀገር ውስጥ እና በውጪም በዛ ባሉ መድረኮች ላይ ተጫውቷል፡፡ በሙዚቃው ዓለም በቆየባቸው ዘመናት በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የህዝብ ፍቅር እና አክብሮትን ተቀዳጅቷል፡፡ በርከት ያሉ ሽልማቶችንም አግኝቷል፡፡ ከጅማ ዩኒቨርስቲ የተሰጠው የክብር ዶክትሬትም ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ነው፡፡

ክቡር ዶክተር ዓሊ ቢራ ከሙዚቃው ጎን ለጎን “Birra Children’s Education Fund” የተባለ ምግባረ ሰናይ ድርጅት ከባለቤቱ ጋር አቋቁሞ ለህፃንት ትምህርት ድጋፍ ያደረግ ነበር፡፡ ድርጅቱ በድሬዳዋ አካባቢ ባሉ ት/ቤቶች ላይ እየሰራ ሲሆን በመላው የሀገሪቱ ክፍሎች የተጠናከረ ስራ ለመስራት እቅድ ነበረው፡፡

የ73 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋውን ዓሊ ቀደም ብሎ የጂማ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ያበረከተለት ሲሆን የትውልድ ከተማው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ቅዳሜ ሰኔ 29 ቀን 2011 ዓ/ም ተጨማሪ የክብር ዶክትሬት ዲግሬ አበርክቶለት ነበር።


የአንጋፋው የሙዚቃ ሰው የክቡር ዶ/ር ዓሊን ነፍስ ይማር
ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ እና አድናቂዎቹ መፅናናት ይሁን ‼

👏👏👏🇪🇹ቀና በል አዳም ወንድሜ እንኳን ደስ ያለህ የቅንነት ተምሳሌት👐👐❤❤ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም ስለ ሰላም መስበክህን ቀጥልበት። ኢትዮጵያም ታከብርሀለች 🇪🇹🇪🇹🇪🇹❤️❤️❤️🌴🌴🌴
02/11/2022

👏👏👏🇪🇹

ቀና በል

አዳም ወንድሜ እንኳን ደስ ያለህ

የቅንነት ተምሳሌት👐👐❤❤

በምንም ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም
ስለ ሰላም መስበክህን ቀጥልበት።

ኢትዮጵያም ታከብርሀለች

🇪🇹🇪🇹🇪🇹❤️❤️❤️

🌴🌴🌴

🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ለኢትዮጵያ ትልቅ ቀን ነዉ እንኯን ደስ ያላችሁ ሰላም ፈላጊዎችGreat news for all peace loving Ethiopians!!!ሰላም Peace" ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መ...
02/11/2022

🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ለኢትዮጵያ ትልቅ ቀን ነዉ እንኯን ደስ ያላችሁ ሰላም ፈላጊዎች

Great news for all peace loving Ethiopians!!!

ሰላም Peace

" ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ "

በአፍሪካ ህብረት መሪነት በዛሬው ዕለት በፕሪቶሪያ በተደረሰው " የሰላም 🕊 ስምምነት " መሰረት ፦

- በዘላቂነት ግጭት ለማቆም ፣
- ለተቸገሩ ወገኖች ሁሉ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ
- የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነትን ለማረጋጋጥ
- አገልግሎቶችን_ለማስጀመር ስምምነት ላይ ተደርሷል።

እንዲሁም በስርዓት የሚመራ እና ታከታታይ የትጥቅ መፍታት አንዱ ነው።

በአጠቃላይ ፤ ዛሬ የተደረሱትን ስምምነቶች የአፍሪካ ህብረት ቡድን ይከታተላል።



🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🙏🙏🙏❤️❤️❤️

🇪🇹❤️🙏

🌴🌴🌴

 #ነቅታለች መምህር አለባቸውና እህታችን ራሄል በተጋቡ አንድ አመታቸው የመጀመሪያ ልጃቸውን ሲያገኙ በተፈጠረ የህክምና ስህተት ራሄል ከ2ወር በላይ ፅኑ ህሙማን ክፍል ኮማ ውስጥ በስቃይ ቆይታ...
28/10/2022

#ነቅታለች
መምህር አለባቸውና እህታችን ራሄል በተጋቡ አንድ አመታቸው የመጀመሪያ ልጃቸውን ሲያገኙ በተፈጠረ የህክምና ስህተት ራሄል ከ2ወር በላይ ፅኑ ህሙማን ክፍል ኮማ ውስጥ በስቃይ ቆይታ በእናንተ ደጋጎች ፀሎትና እገዛ፣ በየካቲት ሆስፒታል ጀግና የጤና ባለሙያዎች ድጋፍ ደህና ሆና ነቅታለች!

ሲደክምላት የነበረውን በስርዓተ ቤተክርስቲያን ያገባችው የምትወደውን ባለቤቷ አይን ዳግም ማየት ችላለች።

አሁን በሚገርም ሁኔታ ከመተንፈሻው ማሽንም ወጥታ ምግብ ትንሽ ትንሽ መጉረስ ጀምራለች!!

ከአጠገቧ ሳይለይ እየተንከባከባት የሚገኘው ብርቱው
የትዳር አጋሯ አለቤ "ደርሳችሁልኛል። ድንግል ትስጥልኝ እግዚአብሔር ያኑርልኝ" ብሏችኋል!!

ለተጨነቀ ሰው ደርሶ መፍትሄ ከመስጠት በላይ የሚያስደስት ምን ነገር አለ?

ራሄልዬ ከቤቱ ያልጠፋሽው መድሐኒዓለም የበለጠ በምህረቱ ይጎብኝሽ🙏
ትሁቱ መምህር አለቤ አምላክ ድካምህን ይቁጠርልህ🙏 እንኳን ደስ አለህ!
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

ምንጭ፦ ባይሽ ኮልፌ በጎ አድራጎት

😭😭😭* ጊዮናዊት ና ክሪስቲና ያማል😭አሁን እነዚህ ላይ ይጨከናል የኛ ምስኪኖች 😭😭😭🌴🌴🌴
01/09/2022

😭😭😭

* ጊዮናዊት ና ክሪስቲና

ያማል😭

አሁን እነዚህ ላይ ይጨከናል

የኛ ምስኪኖች

😭😭😭

🌴🌴🌴

መልካም ዜና ለኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የባህርዳር ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል ለኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬቱ የተሰጠው በህይወት ዘመኗ በሙሉ ለኢትዮጵያ በከፈለችው ዘመን የማይ...
25/08/2022

መልካም ዜና

ለኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የባህርዳር ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል

ለኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬቱ የተሰጠው በህይወት ዘመኗ በሙሉ ለኢትዮጵያ በከፈለችው ዘመን የማይሽረው ጀግንነቷ እና በአለም አቀፍ አደባባይ የሀገሯን ሰንድቅ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ በማድረጓ ነው

ይህ የክቡር ዶክትሬት ግዜውን የጠበቀና የባህርዳር ዩኒቨርሲቲን የሚያስመሰግን ስራ ነው

እንግዲክ ክቡር ዶ/ ር ኮማንደር ደራርቱ ተብላ ትጠራለች

በፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል  ዳግም ግጭት  ተቀሰቀሰከፌደራል መንግሥት የተገኘ መረጃ እንደሚጠቁመው የጦርነት ጉሰማውን የጀመረው ህወሓት ነው ። በተደጋጋሚ የሚያደርጋቸው ትንኮሳዎ...
24/08/2022

በፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል ዳግም ግጭት ተቀሰቀሰ

ከፌደራል መንግሥት የተገኘ መረጃ እንደሚጠቁመው የጦርነት ጉሰማውን የጀመረው ህወሓት ነው ። በተደጋጋሚ የሚያደርጋቸው ትንኮሳዎች ውጤት ስላላመጡለት ጦርነቱን ፈልጎታል። እንደ ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ለመጮህ እየሞከረ ነው ብሏል።

ኢትዮጵያ ለሰላም ሁሉንም አድርጋለች። ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመደራደር መንግሥት ወስኖ ተግባራዊ እንቅስቃሴ አድርጓል። ሕወሓት ከጦርነት እንጂ ከሰላም ስለማያተርፍ የአፍሪካ ኅብረትን አልተቀበለም፣ ተደራዳሪዎቹን አላሳወቀም፣ ቅድመ ሁኔታ ይደረድራል። (መጀመሪያ 11 ቀጥሎ 5 ቀጥሎ 3)፣ ተኩስ አቁም ፈርሷል ብሎ አውጇል፣ ተደጋጋሚ ትንኮሳ በምዕራብና ደቡብ ግንባር ፈጽሟል ሲል ከሷል።

ኢትዮጵያ ለሰላማዊ መፍትሔ አሁንም ቁርጠኛ ናት። ከተጠቃች ግን ሁሉንም ዐቅም ትጠቀማለች ሲል ለጉዳዩ ቀርበት ያላቸው ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ በሰጠው መግለጫ በፌደራል መንግስት ጦር ተወርሬአለሁ ብሏል።

በደቡባዊ ግምባር በዛ ግምባር ከቆዩትና ከሌሎች አከባቢዎች ያሰባሰባቸው የአማራ ልዩ ሀይል ክፍለጦሮች፤የወሎ ፋኖ እና ሚሊሻዎችን ባለፉት አምስት ቀናት እያዘጋጀ ከቆዬ በኋላ የፌደራል መከላከያ ሀይል አካላት የሆኑት 6ተኛ እና 8ተኛ እግረኛ እዞችና የ2ተኛ 6ተኛ እና 8ተኛ ሜካናይዝድ ክፍለጦሮችን ጨምሮ ዛሬ ነሓሴ 18 ቀን 2014 ዓ/ም ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ በጩቤበር፤ጃኖራ፤ጉባጋላ እና ያሎው አቅጣጫዎች ወደ አላማጣ ባላና ብሶበር ሰፊ የማጥቃት ዘመቻ ጀምረዋል ብሏል።(በድሬቲዩብ ሪፖርተር)
(ፎቶ:-ፋይል ኢንተርኔት)

በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች እየተዘዋወረ የሙዚቃ ዝግጅቱን እያቀረበ የሚገኘው ልጅ ሚካኤል(ፋፍ) ለሚኒሶታ ዝግጅቱ የተወዳጇን ድምጻዊት እጅጋየሁ ሽባባው( ጂጂ) ምስል እና ስም ያረፈበት ቲሸርት...
13/08/2022

በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች እየተዘዋወረ የሙዚቃ ዝግጅቱን እያቀረበ የሚገኘው ልጅ ሚካኤል(ፋፍ) ለሚኒሶታ ዝግጅቱ የተወዳጇን ድምጻዊት እጅጋየሁ ሽባባው( ጂጂ) ምስል እና ስም ያረፈበት ቲሸርት አሰርቶ በመልበስ በአደባባይ ክብሩን እና አድናቆቱን ገልጦላታል።
Lij Michael Faf. 🙏💚💛❤️
Ejigayehu "GiGi" Shibabaw 💚💛❤️

ኢትዮጵያ በሴቶች 5ሺ ሜትር ፍፃሜ የወርቅና  ብር  ሜዳሊያውን ወሰደች*****ኢትዮጵያ በኮሎምቢያው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 5ሺ ሜትር  የፍፃሜ በአትሌት መዲ...
06/08/2022

ኢትዮጵያ በሴቶች 5ሺ ሜትር ፍፃሜ የወርቅና ብር ሜዳሊያውን ወሰደች
*****
ኢትዮጵያ በኮሎምቢያው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 5ሺ ሜትር የፍፃሜ በአትሌት መዲና ኢሳ እናመልክናት ውዱ በተከታታይ የወርቅና ብር ሜዳሊያውን ለአገራቸው አስገኝተዋል፡፡

ኡጋንዳ የነሐስ ሜዳሊያውን ወስዳለች፡፡

ኢትዮጵያ በዛሬው ሌሊት ብቻ በተደረጉ የፍጻሜ ውድድሮች 3 ወርቆች መጥተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአጠቃላይ በዚህ ውድድር ያገኘችው የወርቅ ሜዳሊያ ብዛትም 5 ደርሷል፡፡

« የአልጀዚራ ጋዜጠኛ »ተፈጥሮ ተገዳ ሳይሆን አገሪቱ አስገድዳ እድለኛ አድርገዋለች። ወታደርም መሳሪያም ዘበኛም አያስፈልገውም ። ማንም የምድራችን ሀይለኛ ነኝ የሚል መሳሪያ አይነካውም። ለሱ...
01/08/2022

« የአልጀዚራ ጋዜጠኛ »

ተፈጥሮ ተገዳ ሳይሆን አገሪቱ አስገድዳ እድለኛ አድርገዋለች። ወታደርም መሳሪያም ዘበኛም አያስፈልገውም ። ማንም የምድራችን ሀይለኛ ነኝ የሚል መሳሪያ አይነካውም።



ለሱ የተላከው ቦንቡ አንድ ግድብ ብቻ ነው የሚነካው። ጥቃት የተሰነዘረበት ግድብ ግን ለጥቃቱ የሚሰጠው መልስ ከ40 ሚሊዮን በላይ ዜጎችንና የሁለት አገር ትልልቅ ከተሞችን ማለትም የሱዳንን ዋና ከተማ ካርቱምን ፣ የግብፅን ዋና ከተማ ካይሮን ያለምንም ከልካይ፣ አፍረሶ ወደ አፈር ቀይሮ ከውሀ ጋር ቀላቅሎ ነጭ ባህር ይጨምራል

ማንኛው የአለማችን መሳሪያ ነው ከኢትዮጵያ እስከ ነጭ ባህር ድረስ ከተሞችንና የመሰረተ ልማቶችን ህዝቦችን እየጠራረገ ነጭ ባህር የሚዶለው .? እስካሁን ድረስ ይህ መሳሪያ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ጉባ ተራራ ሸለቆ ላይ የተጠመደ፣ አንድ አፍሪካዊ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ፣ መሳሪያም ወታደርም ዘበኛም የማያስፈልግ እድለኛው የአባይ ግድብ ብቻ ነው።

አዎ አንተ እድለኛ ነህ ....በአለማችን ላይ ከህፃናት እስከ አዋቂዎች ስምህን የሚያውቁት ! ራስን በራስህ ያስከበርክ!!

ሱልጣን አህመድ

ተፈፅሟል።አሁን አባይ ኢትዮጵያ ጉባ ተራራ ላይ ያጠመደችው ኒኩሌር ተሸካሚ ኤሌክትሪክ አመንጭ ግድቧ ነው። የአባይ ሰላም መሆን የምስራቅ አፍሪካ ሰላምታ ነው። የአባይ መቀየም የምስራቅ አፍሪካ...
31/07/2022

ተፈፅሟል።
አሁን አባይ ኢትዮጵያ ጉባ ተራራ ላይ ያጠመደችው ኒኩሌር ተሸካሚ ኤሌክትሪክ አመንጭ ግድቧ ነው። የአባይ ሰላም መሆን የምስራቅ አፍሪካ ሰላምታ ነው። የአባይ መቀየም የምስራቅ አፍሪካ ትልቁ ስጋት ነው። አባይ ጋር መዛመድ ከብረሐን ጋር መዛመድ ነው።

አሁን በአባይ ወንዝ ላይ ሻወር መውሰድ ይቻላል። መብላት መጠጣት መዋኘት ይቻላል እንጅ ወደ አባይ ወንዝ አንዲት ጠጠር መወርወር ከእሳት ጋር መጫወት ነው።
ውድ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሆይ እንኳን ደስ አላችሁ፣ ሦስተኛው ሙሊት ተጠናቆ የተረፈው ውሃ ጉዞን ጀምሯል። ይህ የኢትዮጵያና የህዝቦቿ ትልቁ ድላቸው ነው።

ሱሌማን አብደላ

Address

CmC
Addis Ababa

Telephone

+251911103375

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Rahel Stockholm posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share