ECN's ጨረታ እና ሥራ ገጽ Tender & vacancy page

ECN's ጨረታ እና ሥራ ገጽ Tender & vacancy page Your Universal Commercial Solution™
Ethiopian Commercial Networks™HQ Tender page
>https://t.me/etcnhq

Construction Machinery, Vehicle, Property , Material, Supplies, Maintainance, Professionals, Machinery Parking , Logistics/Lowbed Rental And Sales Agent In Ethiopia.

የግንባታ ሥራ ተቋራጮች የፕሮጀክት አፈጻጸም ምዘና መመሪያ 🟡Contractors Construction Project Performance Evaluation Directive     PDFs are ava...
19/09/2026

የግንባታ ሥራ ተቋራጮች የፕሮጀክት አፈጻጸም ምዘና መመሪያ 🟡
Contractors Construction Project Performance Evaluation Directive

PDFs are available on Telegram
https://t.me/etcnhq
Please, subscribe and keep informed.

የጨረታ ማስታወቂያ 🟢በን/ስ/ሳ/ከ/ከ/ወረዳ 09 የሚገኘው የአዲስ አምባ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ቋሚ እቃዎች፤ አላቂ የቢሮ አቃዎች፤ አ...
17/09/2026

የጨረታ ማስታወቂያ 🟢
በን/ስ/ሳ/ከ/ከ/ወረዳ 09 የሚገኘው የአዲስ አምባ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ቋሚ እቃዎች፤ አላቂ የቢሮ አቃዎች፤ አላቂ የትምህርት አቃዎች፤ የፅዳት አቃዎች፤ የደንብ ልብስ፤ የጥገና አቃዎች፤ ቤተ-መጻህፍት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች በሙሉ በጨረታው እንድትሳተፉ አንጋብዛለን፡፡

እቃውን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ብቃት፤ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚህም የተመዘገቡበትን ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 150 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን ከአዲስ አምባ የመ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 05 ከፍል ቀርበው በ 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይገላሉ፡፡
ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች በገዙበት የጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ ዝርዝር መሙያ ላይ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ በሌላ ሰነድ ከሞሉ ተቀባይነት የለውም፡፡
ባቀረቡት ዋጋ ዝርዝር ላይ ቫት (VAT) ማካተት አለባቸው፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 የሥራ ቀን አየር ላይ ውሎ በ10ኛው ቀን 11 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ በ 4 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው ሂደት በተቀመጠው መሰረት ይካሄዳል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን የመወዳደሪያ ዋጋ ሞልተው በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ከጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ደብዳቤ ይዘው የሚመጡ ተጫራቾች ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ ሲያመጡ የተደራጁበትን ዘርፍ ተጠቅሶ ቀጥታ በት/ቤቱ ስም ማናፍ አለበት፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) የሰነድ መግዣ ዋጋ እና የውል ማስከበሪያ በነፃ መውሰድ እንደሚችሉ ተጠቅሶ መናፍ አለበት፡፡
ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- በን/ስ/ሳ/ከ/ከ/ወረዳ 09 የሚገኘው የአዲስ አምባ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አዲስ ሰፈር ድልድይ ወረድ ብሎ አዲስ ሰፈር ጣና ገበያ ፊት ለፊት፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-4-42-04-41 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በን/ስ/ሳ/ከ/ከ/ወረዳ 09 የሚገኘው የአዲስ አምባ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት

ሳሪስ አዲስ ሰፈር

🔴 ጨረታ መዝጊያ መስከረም 11 2019 ዓ/ም

የጨረታ ማስታወቂያ 🟢ታህሰብ የንግድ ሥራዎች አከሲዮን ማህበር በሕንጻ ውስጥ ያለውን የፓርኪንግ ቦታ መሬቱን ልሾ እና በቀለም ለማስዋብ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን አቅርቦ የሚሰራ ባለሙያ አወዳድሮ ...
17/09/2026

የጨረታ ማስታወቂያ 🟢

ታህሰብ የንግድ ሥራዎች አከሲዮን ማህበር በሕንጻ ውስጥ ያለውን የፓርኪንግ ቦታ መሬቱን ልሾ እና በቀለም ለማስዋብ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን አቅርቦ የሚሰራ ባለሙያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት፡-

በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው
የዘመኑን ግብር አጠናቆ ለመከፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ የሚችል
የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
ተጫራቾች ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺ ብር) በመከፈል ዘወትር ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡30 ድረስ አከሲዮን ማህበሩ ገንዘብ ቤት በመቅረብ የጨረታ ሰነድ እና የተጫራቾች መመሪያ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ 11ኛ (አስራ አንደኛው) የሥራ ቀን ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአከሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ /በታህሰብ የንግድ ስራዎች አከሲዮን ማህበር ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
አሸናፊው የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ የስራ ውል መዋዋል አለበት፡፡
ለአከሲዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር 0112-79-30-65
አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኮልፌ አጠና ተራ አዲስ አበባ

🔴 ጨረታ መዝጊያ መስከረም 11 2019 ዓ/ም እስከ ቀኑ 10፡30

ስታንዳርድ የጨረታ ሰነዶች - SBD 🟡በኢፌድሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣንFederal Public Procurement and Property Authority የመንግስት ልማት ድርጅቶች ብ...
17/09/2026

ስታንዳርድ የጨረታ ሰነዶች - SBD 🟡
በኢፌድሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን
Federal Public Procurement and Property Authority
የመንግስት ልማት ድርጅቶች ብሄራዊና አለማቀፍ ስታንዳርድ የጨረታ ሰነዶች
Standard bidding documents - National and International
ሙሉ ሰነዶችን በቀላሉ በቴሌግራም ቻናላችን ላይ በ PDF ማግኘት ይችላሉ።
ሰብስክራይብ በማድረግም የተለያዩ መረጃዎችን ያግኙ።
Full SBDs are available in PDF on our Telegram channel.
https://t.me/etcnhq
🟢 ማንኛውንም ቋሚ ንብረት እና አዲስ ወይም በሥራ ላይ ያሉ የግንባታ የግብርና የማምረቻ አልያም የማዕድን ማውጫ ማሽነሪዎችን ፣ ተሽከርካሪዎችን ፣ ግብዓቶችን መግዛት መሸጥ መከራየት ማከራየት በሎቤድ ማስጫን ሲፈልጉ እንደተለመደው ይደውሉልን።
Stay tuned.
Ethiopian Commercial Networks™የኢትዮጵያ ንግድ ሥራወች አውታር

🔴 ስለ የከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራት አልያምCost sharing አከፋፈል ምን ያህል ያውቃሉ? ሙሉ መረጃውን በቀላሉ በ PDF ማግኘት ይችላሉ። Full information is availabl...
14/09/2026

🔴 ስለ የከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራት አልያም
Cost sharing አከፋፈል ምን ያህል ያውቃሉ?
ሙሉ መረጃውን በቀላሉ በ PDF ማግኘት ይችላሉ።
Full information is available in PDF
Follow this link
የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ ይከተሉ። ወደ ሰነዱ ይመራዎታል።
ያስተውሉ
በሁሉም አማራጮች ቤተሰብ በሆኑ ቁጥር ይበልጥ ተደራሽ ይሆናሉ።
https://t.me/etcnhq
Stay tuned.

🟡 ለኦፕሬተሮች እና ለሹፌሮች የወጣ ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ  • የማመልከቻ ጊዜ እስከ መስከረም 8 2019 ዓ.ም.• ተፈላጊ ጠቅላላ የሰው ኃይል ብዛት 2950• የሥራ ቦታ ቢሸፍቱ የዓለ...
12/09/2026

🟡 ለኦፕሬተሮች እና ለሹፌሮች የወጣ ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
• የማመልከቻ ጊዜ እስከ መስከረም 8 2019 ዓ.ም.
• ተፈላጊ ጠቅላላ የሰው ኃይል ብዛት 2950
• የሥራ ቦታ ቢሸፍቱ የዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክት - አቡሴራ
• ቀጣሪ ድርጅት CCCC LTD.
• ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ያነጋግሩ።
0942441888
0913428635
0972260078
መረጃው ለሌሎችም ይዳረስ ዘንድ ያጋሩ ሼር ያድርጉ።
መልካምነት መልሶ ይከፍላል።
🟢 ያስተውሉ:- ማንኛውንም ቋሚ ንብረት እና አዲስ ወይም በሥራ ላይ ያሉ የግንባታ የግብርና የማምረቻ አልያም የማዕድን ማውጫ ማሽነሪዎችን ፣ ተሽከርካሪዎችን ፣ ግብዓቶችን መግዛት መሸጥ መከራየት ማከራየት በሎቤድ ማስጫን ሲፈልጉ እንደተለመደው ይደውሉልን። እንዲሁም ተቀጥረው በሚሰሩበት ድርጅት አልያም በሥራ አጋሮ ለሽያጭና ኪራይ ሲፈለግ በቀጥታ ያገናኙን ፤ ሥራው በኛ በኩል በስኬት ሲጠናቀቅ አብረው ኮሚሽን ይጠቀማሉ ገቢዎንም ይጨምራሉ።
መልካም የሥራ ዘመን
Ethiopian Construction Network የኢትዮጵያ የግንባታ ሥራዎች አውታር
ቴዲ Teddy.
(ቴዲ™ ቫይበር)

10/09/2026

መልካም አዲስ ዓመት

ጨረታ 🔵ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ምየጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ  አበባ  ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀ...
04/09/2026

ጨረታ 🔵

ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱና የተተው የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሞባይሎች ፣የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት፣ አልባሳት ፣ጫማዎች ፣ ጊርቦክስ እና ሌሎች ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ እና በሃራጅ
ጨረታ ቁጥር 18/2019 በቀን 2/13/2018 ዓ.ም
ጨረታ ቁጥር 19/2019 በቀን 05/13/2018 ዓ.ም
ጨረታ ቁጥር 20/2019 በቀን 04/01/2019 ዓ.ም
ጨረታ ቁጥር 21/2019 በቀን 07/01/2019 ዓ.ም
ጨረታ ቁጥር 22/2019 በቀን 11/01/2019 ዓ.ም
ጨረታ ቁጥር 23/2019 በቀን 14/01/2019 ዓ.ም
ጨረታ ቁጥር 24/2019 በቀን 18/01/2019 ዓ.ም
ጨረታ ቁጥር 25/2019 በቀን 21/01/2019 ዓ.ም
ጨረታ ቁጥር 26/2019 በቀን 25/01/2019 ዓ.ም
ጨረታ ቁጥር 27/2019 በቀን 28/01/2019 ዓ.ም መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ፡-
1. በቅ/ጽ/ ቤቱ ለሚካሄደው ጨረታ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና የዘመኑ ግብር የተከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ስዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት በኃላ ከ7፡00- 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00( አንድ መቶ)/ በመክፈል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ ጉምሩክ መጋዘን ቅጥር ግቢ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል፡፡
3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOMS BRANCH OFFICE ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ካርጎ መጋዘን እና ገርጀ መጋዘን ጳጉሜ 02/2018 ዓ/ም፣ጳጉሜ 05/2018 ዓ/ም፣ መስከረም 04/2019 ዓ/ም፣መስከረም 07/2019 ዓ/ም፣መስከረም 11/2019 ዓ/ም፣መስከረም 14/2019 ዓ/ም፣መስከረም 18/2019 ዓ/ም፣መስከረም 21/2019 ዓ/ም፣መስከረም 25/2019 ዓ/ም፣መስከረም 28/2019 ዓ/ም፣ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በዛው ቀን በ8፡15 የሚከፈት ይሆናል ፡፡
5. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዘው በቀረቡት ቅጸች መሠረት ለመረጡት የዕዋዎች ኮድ የተሰጠ ዋጋ፤ የተጫራቾች ስም ፣ አድራሻ፣ፊርማና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ( cpo ) እና ከላይ በተ.ቁ 1 የተገለጹትን ሰነዶች ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ላይ በመፈረም አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን መግዣ ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል ፡፡
8. የጨረታ አሸናፊዎች ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ በ05 (አምስት) ቀናት ውሰጥ ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለባችው፡፡
9. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለጸው ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ(cpo) ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
10. በተራ ቁጥር 01-09 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማርም በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 18/2019 በቀን 2/13/2018 ዓ.ም ፣ጨረታ ቁጥር 19/2019 በቀን 05/13/2018 ዓ.ም ፣ጨረታ ቁጥር 20/2019 በቀን 04/01/2019 ዓ.ም፣ጨረታ ቁጥር 21/2019 በቀን 07/01/2019 ዓ.ም ፣ጨረታ ቁጥር 22/2019 በቀን 11/01/2019 ዓ.ም ፣ጨረታ ቁጥር 23/2019 በቀን 14/01/2019 ዓ.ም ፣ጨረታ ቁጥር 24/2019 በቀን 18/01/2019፣ዓ/ም ፣ጨረታ ቁጥር 25/2019 በቀን 21/01/2019፣ዓ/ም ጨረታ ቁጥር 26/2019 በቀን 25/01/2019፣ዓ/ም ጨረታ ቁጥር 27/2019 በቀን 28/01/2019፣ዓ/ም ከጥዋቱ በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የምናካሄድ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ አያሳወቅን፣የዕቃዎችን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ እና ካርጎ ውርስ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
11. በሃራጅ ጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100‚000.00/መቶ ሺህ/ ለየዘርፉ CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOMS BRANCH OFFICE ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
12. ለጨረታ የቀረቡት የዕቃዎች ዋጋ ካቫት በፊት የተሰጠ መሆኑ እናሳውቃልን፡፡
13. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች በተናጠል ሳይሆን ለጨረታው ሰነዱ በተሰጠ ኮድ ቁጥር ብቻ የሚሸጥ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
14. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. በቅ/ጽ/ቤት ደረጃ እየተካሄደ ያለውን የጨረታ አድማስ ለማስፋት ፈጣን የዕቃዎች ማስወገድ ሥራ በማከናወን እና ገቢን በወቅቱ ለመሰብሰብ እንዲቻል ጨረታዎችን በወረቀት አልባ(online) አሠራር ለማስኬድ ከኦክሽን ኢትዮጵያ አ.ማ ጋር ለመሥራት በማሰብ ዘወትር ሐሙስ የሚካሄደውን ግልፅ ጨረታ በቀጥታ ሙሉ በሙሉ በኦክሽን ኢትዮጵያ አ.ማ በወረቀት አልባ (online) የሚካሄድ መሆኑን እናሳውቃለን፤
16. የኦክሽን ኢትዮጵያ አ.ማ መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር +251905115511 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፤
ለተጨማሪ መረጃ ቦሌ ኤርፖርት በስልክ ቁጥር 0116684537 እና 0116684193 ደዉለው ይጠይቁ፡፡

የጨረታ ማስታወቂያ
31/08/2026

የጨረታ ማስታወቂያ

🟡 ጨረታ
30/08/2026

🟡 ጨረታ

Address

Home
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ECN's ጨረታ እና ሥራ ገጽ Tender & vacancy page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ECN's ጨረታ እና ሥራ ገጽ Tender & vacancy page:

Shortcuts

Share