Saq Besaq

Saq Besaq Verified

24/06/2026

ጊቤ መርከብ መንገድ ጀመረች

ለአምስት ወራት ሻርጃ ወደብ አካባቢ የከረመችው ጊቤ መርከብ ትላንት ማምሻውን የሆርሙዝ ሰርጥን ማለፍ መቻሏ ታወቀ።

አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የሆርሙዝ መተላለፊያ በመዘጋቱ በርካታ መርከቦች የፋርስ ባህረሰላጤ ወደቦች ላይ መህልቅ ጥለው እንዲጠባበቁ ተገደው ነበር።

ከነዚህም መካከል ጊቤ አንዷ ነበረች።

#ቅዳሜገበያ

በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ።

22/06/2026

ቫንስ ምን አስደነገጣቸው?

አሜሪካ ኢራንን ደንብራታለች!

ከስዊዘርላንድ የሚወጡ ቪዲዮዎች ማነጋገራቸውን ቀጥለዋል።

የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ ወደ ድርድሩ ስፍራ ሲመጡ የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝደንት ጄዲ ቫንስ የደነገጡት ድንጋጤ አይጣል ነው።

አሜሪካ ኢራንን ለመፍራቷ አይነተኛ ምልክት ተደርጎ እየታየ ነው።

አባስ ወደ መሰብሰቢያው መጥተው የፓኪስታኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ሰላም ሲሉ ቫንስ ደንግጠው መታየታቸው በማህበራዊ ሚዲያ መነገሪያ ሆኗል።

#ቅዳሜገበያ Abbas Araghchi Official Mian Shehbaz Sharif

18/06/2026

አስገተራሚ!

ብቸኛ ተንቀሳቃሽ አገር!

የ16 ቢሊየን ዶላር ከተማ | Freedom Ship ቅብጠት ወይስ ቢዝነስ?

የመንግስታት አገዛዝ ለሰለቻቸው፣ ህይወትን በነፃነት ለሚሹ 50 ሺህ ሰዎች የተዘጋጀች ልዩ የውሃ ላይ ከተማ ብለዋል ዲዛይነሮቹ።

ለአመታት ተዳፍኖ የቆየው የFreedom Ship ሃሳብ ዳግም ተነስቷል።

እውን ይቻላል? ይሳካል?

#ቅዳሜገበያ


https://youtu.be/kDWH5yOWV-Y?si=XWdxk4QwXPgyISOR
https://youtu.be/kDWH5yOWV-Y?si=XWdxk4QwXPgyISOR

12/06/2026

የነዳጅ ታክስ

ከነዳጅ 235 ቢሊየን ብር ታክስ ለመሰብሰብ ታቅዷል

በ 2019 በጀት አመት መንግስት ቀጠኛ ያልሆነ ታክስ ከነዳጅ ለመሰብበስ ነው ያቀደው።

👉109.6 ቢሊየን ብር ከኤክሳይስ ታክስ

👉126 ቢሊየን ብር ቫት ለመሰብሰብ ነው የታቀደው

👉ይህም በጥቅሉ ወደ ሩብ ትሪሊየን ብር የሚጠጋ ነው

👉ይህም ለመሰብሰብ ከታሰበው ጠቅላላ 1.5 ትሪሊየን ብር ወደ 15.7 በመቶ የሚጠጋ ነው።

ከዘርፉ ቀጥተኛ ያልሆነ ግብር ከ2018 አንስቶ ለመሰብሰብ መታቀዱ የሚታወስ ነው።

ዝርዝሩ በሊንኩ አለ

https://url-shortener.me/N0KF

#ቅዳሜገበያ

https://www.facebook.com/share/1AQ7K64Z6U/?mibextid=wwXIfr
09/06/2026

https://www.facebook.com/share/1AQ7K64Z6U/?mibextid=wwXIfr

የውጭ ምንዛሬ ጨረታው ተሰረዘ

👉ይህ ጨረታ በCSD/ Central Securities Depository መላ ሲደረግ የመጀመሪያው ነው።

ብሄራዊ ባንክ የዛሬውን የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሰረዘ።

ባንኩ 100 ሚሊየን ዶላር ለመሸጥ ትላንት ሰኔ 1 ቀን ለባንኮች ጥሪ አድርጎ ነበር።

ሆኖም በቴክኒክ ጉዳይ ጨረታው ተሰርዟል ሲል አሁን አስታውቋል።

ይህ ጨረታ በCSD/ Central Securities Depository መላ ሲደረግ የመጀመሪያው ነው።

#ቅዳሜገበያ

አልቫሮ ከIMF ኢትዮጵያ ለምን ጥለው ሄዱ❓ማሳሰቢያ  ወይስ አድናቆት❓IMF 468 ሚሊየን ዶላር እለቃለሁ ብሏል❗️ከተገመተው በ200 ሚሊየን የበለጠ ነው❗️ ለምን❓ IMF አድናቆትና ማሳሰቢያ...
07/06/2026

አልቫሮ ከIMF ኢትዮጵያ ለምን ጥለው ሄዱ❓

ማሳሰቢያ ወይስ አድናቆት❓

IMF 468 ሚሊየን ዶላር እለቃለሁ ብሏል❗️

ከተገመተው በ200 ሚሊየን የበለጠ ነው❗️

ለምን❓

IMF አድናቆትና ማሳሰቢያ ሰቷል❗️

በተለይ የግሉ ዘርፍ ጫና እንዲስተተካከል አሳስቧል❗️

የኢትዮጵያ እዳ ጉዳይ በተለያየ ጎን ተወጥሯል❗️

#ቅዳሜገበያ

IMF 468 ሚሊየን ዶላር እለቃለሁ ብሏል። ከተገመተው በ200 ሚሊየን የበለጠ ነው። ለምን? IMF አድናቆ...

ኢትዮጵያ በአበዳሪዎች ተከሳለች ‼️👉የኢትዮጵያ ብድር ቀውስ ወደ ፍርድ ቤት አምርቷል❗️👉 እነ IMF እና ሁለትዮሽ አበዳሪዎቿ እዳዋን መፍትሄ እናብጅለት እያሉ ነው❗️👉 የግል አበዳሪዎች (E...
05/06/2026

ኢትዮጵያ በአበዳሪዎች ተከሳለች ‼️

👉የኢትዮጵያ ብድር ቀውስ ወደ ፍርድ ቤት አምርቷል❗️

👉 እነ IMF እና ሁለትዮሽ አበዳሪዎቿ እዳዋን መፍትሄ እናብጅለት እያሉ ነው❗️

👉 የግል አበዳሪዎች (EuroBond holders) ደግሞ አሁኑኑ ይከፈለን እያሉ ነው❗️

👉 ኢትዮጵያ የእዳ አስተዳደር ከጠየቀች አምስት አመት አለፈ❗️

👉መፍትሄ ከወዴት አለ❓

#ቅዳሜገበያ



የኢትዮጵያ ብድር ቀውስ ወደ ፍርድ ቤት አምርቷል። እነ IMF እና ሁለትዮሽ አበዳሪዎቿ እዳዋን መፍትሄ እና...

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1476072727870318&id=100064028135472
04/06/2026

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1476072727870318&id=100064028135472

ጅቡቲ እስከ 53🥵 የሚደርስ ከፍተኛ ሙቀት እንደምታስተናግድ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

በቀጣዮቹ ጥቆት ቀናት የጅቡቲ ሰሜን እና ምስራቅ አካባቢ ከ46 እስከ 53 ዲግሪ ሴሊሸስ የሚደርስ ሙቀት እንደሚያስተናግድ ተገለፀ።

በመሆኑም በተለይ ከቤት ውጭ የሚሰሩ እና ለፀሀይ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ነው የጅቡቲ ሜትሮሎጂ ተቋም ያስጠነቀቀው።

ነዋሪዎች ባይጠማችሁ እንኳ ውሃ ቶሎ ቶሎ መጠጣት አይዘንጉ ሲል አሳስቧል።

በተጨማሪ ከቀኑ አምስት እስከ 10 ሰዐት ባትወጡ ይመረጣል ነው ያለው።

የአገሪቱ መካከለኛ እና ደቡባዊ የአገሪቱ አካባቢ በተመሳሳይ በቀጣዮቹ ጥቆት ቀናት ከ34 እስከ 40 ዲግሪ ሴሊሸስ ሙቀት እንደሚኖራቸው ነው የተገለፀው።

#ቅዳሜገበያ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Saq Besaq posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Saq Besaq:

Shortcuts

Share