ኢስላማዊ ግጥሞችና ጥያቄዎች pag

ኢስላማዊ ግጥሞችና ጥያቄዎች pag Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ኢስላማዊ ግጥሞችና ጥያቄዎች pag, Business service, Addis Ababa.

01/04/2022

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
ጨረቃ ታይታለች። ረመዳን ነገ ይጀመራል ረመዳን ሙባረክ

31/10/2020
24/06/2020

ደሴታዊያን ክህደትን ከአባቶቻቸው የወረሱት ነው!
◈◈◈መረብ ግሩፕ◈◈◈
የውዷን ሀገራችንን የኢትዮጵያን የታሪክ ትርክት ከክርስትና ጋር ብቻ የተሳሰረ አርጎ የመሳል አባዜ የተጠናወታቸው ደሴታዊያን ለአገር ህልውና ሲዋደቁ ዘመናትን ያስቆጠሩ ሙስሊም (ሙጃሂዶችን) ታሪክ ከማጥናት ይልቅ ለማዳፈን ሲጥሩ የቆዩ ተረት ነጋሪዎች ዛሬ ደግሞ ሙስሊሙን ማህበረሰብ በአገር ህልውና መጠርጠራቸው ከዝቅጠታዊነት ውጭ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው እንደማይችል ግልጽ ነው።

ትናት ሙስሊም የአድዋ ጀግኖች ለሀገራቸው ሲሉ ደማቸውን በመገበር ቢሰውም በድን አካላቸውን እውቅና ላለመስጠት በሞቱበት የአሞራ እና የአውሬ እራት እንዲሆን የተደረገው የተንሻፈፉ የታሪክ ትርክቶች በወለዷቸው ዝቅጠታዊ አስተሳሰብ መሆኑ የሚካድ አይደለም። ለነዚህ አስተሳሰቦች መፈጠር ዋነኛ ተጠያቂዎች የታሪክ ምሁራኖችና የሚዲያ አካላት ብሎም ለዘመናት የነበረው የትምህርት ካሪኩለም ፍትሀዊ ያልሆነ እና ለቤተ ክህነት ወገንተኛ የሆነ ስርአተ-ጥናትን መሰረት በማድረጉ መሆኑም የሚዘነጋ አይደለም። ይህ ትክክለኛ ታሪካችንን እንዳናውቅ ከማድረጉም በላይ በውጭ አለም ያለንን ገፅታ ክርስትያናዊ አድርጎ የሳለ በመሆኑ ዛሬ ላይ እየተፈጠሩ ላሉ ችግሮች ምክኒያት ለመሆን ችሏል።

ዛሬም ከዚህ ደሴታዊና ዝቅጠታዊ አስተሳሰብ ያልወጡ የአንድ ወገን ምሁራኖች ግብፅ በአባይ ግድብ የያዘችውን የግል ጥቅመኝነት የአረብ አገራት ጋር ያላትን ወዳጅነት መሰረት በማድረግና የኢትዮጵያን ሙስሊሞችም ከ አረብ ሀገራት ጋር ቅርርብ እንዳላቸው በማሰብ ከግብፅ ጋር ሊቆሙ ይችላሉ የሚል በጥላቻ የደረተ አስተሳሰብ ይዘው ብቅ ጥልቅ ሲሉ እያስተዋልን ነው።

ነገር ግን እንደዚህ አይነት የላሸቁ አስተሳሰቦችና ጠባብ አመለካከቶች ይታረሙ ዘንድ ሁሉም ምሁራን እና የሚዲያ አካላት ተረባርበው መስራት ይጠበቅባቸዋል። በተረተረትና በውሸት ትርክት ተደርተው የተሰሩት ዲሪቶ አስተሳሰቦች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያውያን ጫንቃ ላይ እንዲወገዱ እስካልተደረጉ ድረስ እነዚህ አስተሳሰቦች ኢትዮጵያን እየበከሏት መቀጠሉ የማይቀር ነው።

አሁን በተፋፋመው ውጥረትና አለመግባባት በአረቡ አለም አለማቀፍ ሚዲያዎች ላይ ስለግድቡ የግብፅን ድምፅ ያቀጨጩ ሙስሊም ምሁራንና የቁርጥ ቀን ልጆች ቢሆኑም በዚህ አካሄዳቸው ትናት አደዋ ላይ ሙስሊሙን እንደካዱት ከአባይ ግድብ በኋላም ሙስሊሙ ለአባይ ግድብ እየከፈለ ያለውን መስዕዋትነት መካዳቸው አይቀርም። ይህ የደሴታዊያን ክህደት ከአባተቸው የወረሱት መሆኑን ብናውቅም ለልጆቻቸው እንዳያወርሱት ማድረግ ግን የሁላችንም ሀላፊነት ነው።

ስለሆነም የተደበቁ ታሪኮችን በማውጣት እና የተንሻፈፉትን በማስተካከል ለቀጣይ ትውልድ እውነታውን በማስተላለፍ ከውዝግብ የጸዳ ትውልድ መፍጠር ያስፈልጋል የሚለው የመረብ መልዕክት ነው።





የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል
https://t.me/mereb_2012
https://t.me/mereb_2012

13/05/2020

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢስላማዊ ግጥሞችና ጥያቄዎች pag posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share