Kefeta Training and Consulting PLC

Kefeta Training and Consulting PLC Kefeta Training and Consulting PLC is dedicated to create outshining entrepreneurs and professionals.

ተነስቻለሁ!ከድህነት  ትቢያ ውስጥ ልትቀብረኝ ሞክረህ ይሆናል፣ በድርቅ ስንጣቂዎች ውስጥ ልታኖረኝ ሞክረህ ይሆናል፣ በመከራ የዘመን ሸክም ውስጥ ልታቀጭጨኝ ሞክረህ ይሆናል፣ እኔ ግን እንደ አ...
10/09/2025

ተነስቻለሁ!
ከድህነት ትቢያ ውስጥ ልትቀብረኝ ሞክረህ ይሆናል፣
በድርቅ ስንጣቂዎች ውስጥ ልታኖረኝ ሞክረህ ይሆናል፣
በመከራ የዘመን ሸክም ውስጥ ልታቀጭጨኝ ሞክረህ ይሆናል፣
እኔ ግን
እንደ አባይ ወንዝ
እነሳለሁ ፣ እነሳለሁ ፣ እነሳለሁ።
ተሰባብሬ ልታየኝ ትፈልጋለህ?
አጎንብሼ እንድኖርልህ ትሻለህ?
ተስፋዬ ሟሽሾ ማየት ትመኛለህ?
አይይይ
አይሆንም!
እኔ! የደጋው ሰው እነሳለሁ!
ዳግም እነሳለሁ!
እንደ አባይ ወንዝ ፣ እታደሳልሁ
በህዳሴ መንፈስ
በረሃውን ላለመልም ፣
ስብራቴን ልጠግን
እነሆ ተነስቻለሁ።
ከማጣቴ ትብያ ውስጥ ፣
በአባቶቼ የጀግንነት ወኔ
እንደ አባይ ወንዘ እታደሳለሁ!
እናም
እነሳለሁ ፣ ተነስቻለሁ
(ከማያ ኤንጄሉ ሐሳብ የተወሰደ)
እንኳን ደስስስስስስስስስ አለን!

06/06/2025

One cannot understand an organization without trying to change it. Burk Lewin

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም በዓል!
06/06/2025

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም በዓል!

የሚያብለጨልጭ ሁሉ ወርቅ አይደለም!🚫
25/05/2025

የሚያብለጨልጭ ሁሉ ወርቅ አይደለም!🚫

🚫 ይጠርጥሩ! - ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር አይቆረጥም! 2. አሜሪካ (USA) ወጣ ወጣና እንደ ሸንበቆ ... ♨️ ክክብር ማማ የተፈጠፈጠው አሜሪካዊው ኩባንያ አሜሪካ ቢዝነስ በመስራትም ሆነ ሰፋፊ ...
22/05/2025

🚫 ይጠርጥሩ! - ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር አይቆረጥም!
2. አሜሪካ (USA)
ወጣ ወጣና እንደ ሸንበቆ ...
♨️ ክክብር ማማ የተፈጠፈጠው አሜሪካዊው ኩባንያ
አሜሪካ ቢዝነስ በመስራትም ሆነ ሰፋፊ የኢንቨስትመንት እድሎችን ለሰፊው ማህበረሰብ በመፍጠር ግንባር ቀደም ሀገር ናት። በተለይም የቢዝነስ ሀሳብ ወደ መሬት በማውረድና ስኬታማ ኢንተርፕራይዝን በመፍጠር እጅግ የተዋጣላት ሀገር ናት። በዚህም የተነሳ "ከስስ ደመና ዝናብ ያዘንባሉ" የተባለላቸው ድንቅ የስራ ፈጣሪዎች ያሏት ፣ ክህዝብ ብዛት አኳያ የበዛ ስራ ፈጣሪዎች ያላት ሀገር በመሆንም ኣለምን በዘርፉ እየመራች ትገኛለች።
በመሆኑም እንደ አፕል ፣ አማዞን ፣ ዎልማርት ፣ ... የመሳሰሉ ግዙፍ ኩባንያዎችን ያበረከተች ሀገርም ናት።
ሆኖም አንዳንዴ በዚህ ልክ የወጡ ድርጅቶች ከስመው የብዙ ሰዎች መዋዕለ ነዋይ መና ሲያስቀሩና ተስፋቸውን ሲያመክኑ የተስተዋላባት ሀገርም ነች።
⚖️ለዛሬ አንዱን እነሆ።
ኢንሮን ይባላል በዋናነት የኃይል አቅርቦት ላይ የሚሰራ የትልቅነት መገለጫ የነበረ ግዙፍ ኩብንያ ሲሆን እ.ኢ.አ በ2000 አከባቢ በሚያሰራቸው ከ30 ሺህ በላይ ሰራትኞች የኛን የኢትዮጵያን የአምናን አመታዊ ጥቅል ምርታችንን የሚገዳደር አመታዊ ሽያጭ ነበረው 100 ቢልዮን ዶላር አከባቢ።
ኢንሮን በገንዘብ (አክሲዮን) ገበያው ላይ ይበልጥ አትራፊ ሆኖ ለመታየት የትርፍ ትንበያን እንደ ዋና መሸጫ መንገድ በማድረግ "ላም አለኝ በሰማይ ..." የሚመስል የሒሳብ አሰራር በመቀመርና "ምናባዊ ወተት" በማሳየት በእርገጥ ካለው ወተት በላይ ወተት አላቢ አስመስሎ የሰዎችን ገንዘብ እየሰበሰበ እውነተኛዎቹ ላሞች እያረጡ ፣ የምናባዊዎቹ ላሞች የተስፋ ወተት እያንደቀደቁ መሐል መንገድ ላይ ተገናኙ። ኢንሮን ከአለማችን 500 ትልቆቹ ኩባንያዎች 7ኛ ሆነ።
በዚህ የተበረታታው አመራር ቴክኖሎጂን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ኢንቨስትመንት ላይ በመግባት የኪሳራ ስጋቱ ከፍ አደረገው። የንግድ ህጉ የላላና ውድድሩ ከፍ ያለበት ሁኔታ እንዲፈጠር በተደረገው ጉትጎታ ፣ ኢንሮን ፣ "ላሞችን ከመንከባከብ ይልቅ ወተት በቅናሽ መሸጥ ላይ ተጠመደ" በተለይም ዋና የገቢ ምንጩ የሆነው የጋዝ ንግዱ ሁነኛ ተጎዳ ፣ የዋጋ ፉክክር ውስጥ የገባው ኢንሮን ድንቅ የፈጠራ ኩባንያ (Most innovative Company) ፣ ምርጥ የሰራተኞች ኩባንያ ... የመሳሰሉ ቅጥያዎችን ቢጎናፀፍም "ፀጉራም ውሻ ...።" እንደሚባለው ከውስጡ ሆነው በተሳሳተ የሒሳብ ስሌትና ፣ የበዛ የኢንቨስትመንት ውሳኒዎች ውስጥ የገቡ አመራሮች ኢንሮንን ከተከበረበት ማማ ተምዘግዝጎ እንዲወድቅ አደረጉ ፣ ኢንሮን ሞቻለሁ ቅበሩኝ አለ 🤔
74 ቢልዮን የሚልቅ የአሜሪካን ዶላር ያፈሰሱ 1.5 ሚልዮን ምስኪን ዜጎች በካሳ መልክ ያገኙት አንድ አስረኛው የማይሞላ 7.2 ቢልዮን ነበር። የሰራትኞች የጡረታ ገንዘብ አመድ ሆኖ ተበትኖ ሲቀር ፣ ኢንሮን እንደዚህ ተንሰራፍቶ ይሰራባቸው የነበሩ ዘርፎም ሆነ ሀገራትን ጥሎ ኩምሽሽ ብሎ ለመጥፋት ቀናቶች በቂው ነበር። የ16 አመታት ልፋት ፣ የ1.5 ሚልዮን ባለድርሻ አካላት መዋዕለ ነዋይ ፣ የ30 ሺህ ሰራተኞች ድካም አመድ አፋሽ አድርጎ ተሰናበተ። ጥቂት አመራሮች ለጊዜያዊ ክብራቸው ሲሉ ያሰሉት ስሌት ብዙኃኑን አናግቶ እንሆ ለመማሪያ በቃ።
ኢንሮን የሚለው ስያሜም በ 275 ዶላር (ወደ 35 ሺህ ብር) ተሽጦ የሚሆነውን እየጠበቅን እንገኛለን።
ይቀጥላል...
+

ይጠንቀቁ! - ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር አይቆረጥም!ሰሞኑን የተለያዩ ሰዎች እየተካሔደ ባለው የኢኮነሚ ለውጥ ፣ በተለይም የካፒታል ገበያን ተከትሎ ብዙ ጥያቄዎች በማቅረብ ላይ ናቸው። በተለይም በአክ...
19/05/2025

ይጠንቀቁ! - ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር አይቆረጥም!
ሰሞኑን የተለያዩ ሰዎች እየተካሔደ ባለው የኢኮነሚ ለውጥ ፣ በተለይም የካፒታል ገበያን ተከትሎ ብዙ ጥያቄዎች በማቅረብ ላይ ናቸው። በተለይም በአክስዮን ማህበር አደረጃጀትና ከማህበረሰብ ሰፊ ካፒታል በሚሰበሰቡ የንግድ ተቋማት ላይ ጥያቄዎች እየቀረቡ ይገኛል። በነዚህ እና በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ የሚፈጥሩ ሐሳቦች የማቅረብ ስራ እንሰራለን። ለመንደርደርያ ያህል ግን የአለም ተሞኩሮ ምን እንደሚመስልና በዚህ ረገድ የገጠሙ አስተማሪ የሚባሉ ክስተቶች ቅድሚያ በመስጠት በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ምስል እንዲኖረን ማድረጉ ተገቢ ነው።
1. ቻይና
አነቃቂው ቡና አደንዝዞ ሲያስበላ!
በቻይናዋ ዋና ከተማ ቤይጂንግ የተቋቋመው ላኪን ኮፊ (Luckin Coffee) “እድል ይግጠመኝ” ለማለት ይመስል መልከ ጥፉ ... እንዲሉ ስሙን ከኢንግሊዝኛው Luck - ዕድል ጋር አገናኝቶ ወደ ስራ የገባው። እንደተመኘውም "ቻይናዊው ዕድል ቡና" ዕድል ገጠመው። በጊዜው ውድ የሚባሉ የቡና ማሽኖችና መሸጫ ቤቶች በመያዝ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ በሚጠይቅ አሰራር ላይ የተጠመዱ እንደ ስታር ባክስ (Starbucks Coffee) አይነቶቹ ግዙፍ ኩባንያዎችን የሚገዳደር የቢዝነስ ሞዴል (Business Model) (ስለ ቢዝነስ ሞዴል ሌላ ሰፊ አምድ የሚኖረን መሆኑን ላማሳወቅ እንወዳለን) በመቀየስ "ትንንሽ መሸጫ ቦታዎች በአነስተኛ መዋዕለ ነዋይ የሚሰሩ ካፌዎች እንዲሁም በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የሽያጭ ስራ" ላይ መስራቱን ተያያዘው። ኩባንያውም በትክክል አሸናፊ የቢዝነስ ሞዴል በመከተሉ ብትንሽ መዋዕለ ነዋይ ብዙ ቅርንጫፎችና አመርቂ ሽያጭን ማጣጣም ችሏል። ይህን ስኬቱን ይበልጥ ለማስቀጠል "ቻይናዊው ዕድል ቡና" ከ300,000 በላይ ከሚሆኑ የአሜሪካ ዜጎች ከግማሽ ቢልዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ሰብስቦ ትልቅ ስኬትን ተጎናፅፏል።
ሆኖም ዕድለኛው ኩባንያ ዕድሉ ላይ ከመገንባት ይልቅ በሰው ሜዳ የሰበሰበውን መዋዕለ ነዋይ ይዞ "ቁልቁል" መጓዝን መረጠ ፣ ከፍተኛ አመራሮቹ ቃላቸውን አጥፈው የግል ጥቅማቸውን አስቀደሙ።
ይቀጥላል...

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የትንሳኤ በዓል እንመኛለን!ከፍታ ስልጠናና ማማከር!
20/04/2025

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የትንሳኤ በዓል እንመኛለን!
ከፍታ ስልጠናና ማማከር!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮችእንኳን ለለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ፣ እንኳን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!መልካም በዓል! ከፍታ ስልጠናና ማማከር!
18/04/2025

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ፣ እንኳን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል!
ከፍታ ስልጠናና ማማከር!

በአስቸኳይ ይታረም ❎ ያስተምሩ ሰዎችን ግን አያታልሉ!"ያለምንም መነሻ ገንዘብ ዶላር የሚያስገኝ ቢዝነስ⁉️" ሰሞኑን "ያለምንም መነሻ ገንዘብ ዶላር የሚያስገኝ ቢዝነስ" በሚል በebs Tv  ...
29/01/2025

በአስቸኳይ ይታረም ❎
ያስተምሩ ሰዎችን ግን አያታልሉ!
"ያለምንም መነሻ ገንዘብ ዶላር የሚያስገኝ ቢዝነስ⁉️"
ሰሞኑን
"ያለምንም መነሻ ገንዘብ ዶላር የሚያስገኝ ቢዝነስ" በሚል በebs Tv የተሰራጨው አደገኛና አሳሳች መልዕክት ከአንድ ኃላፊነት ሊወስድ ከሚገባው ሚድያ(Mainstream Media) የሚጠበቅ አይደለምና ቶሎ እርምት ሊወሰድበት ይገባል።

Commercial እንደመሆኑ ሚድያው የአንድን ድርጅት አገልግሎትም ሆነ ምርት ማስታወቂያ መስራቱ ችግር ባይኖረውም ከእውነታው እንዲሁም ከሀገራችን ህጋዊ ማዕቀፍ ጋር የሚቃረን ሐሳብ ለኅብረተሰቡ በዚህ ሁኔታ መልቀቁ ግን አግባብ የሌለው መሆኑ መታወቅ አለበት።

ይህ ማስታወቂያ አሳሳች እንዲሁም ከእውነታው የራቀ ሲሆን አንድን ውስብስብ ጉዳዮች (Trading, investment, crypto,....) ለ2 ወር በሚሰጥ ቁንፅል ስልጠና እንደ አስተማማኝ የገቢ መንገድ አስመስሎ መሳልና በዚህ ሚድያ መተላለፉ ልክ አይደለም።

ለማታወቂያ በሚመስል ሁኔታ የተዘጋጀው ፕሮግራም የዘነጋቸው ዋና ዋና ጉዳዮች በአጭሩ ለማስቀመጥ ያህል፦

1. ያለ ካፒታል የሚደረግ ምንም ንግድ አለመኖሩ፡
ልክ እንደ ማንኛውም ንግድ ካፒታል የሚፈልግ መሆኑና ይልቁንስ ሰፊ ልምምድና የስሜት ብስለት የሚጠይቅ እንዲሁም ሰዎችን በቀላሉ ወደ ስሜት ስለሚከት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ብዙ ጊዜ ለኪሳራ ሊዳርግ የሚችል አደገኛ ቢዝነስ መሆኑ።

2. ከፍተኛ የመክሰር አደጋ ያለበት ዘርፍ መሆኑ

ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከ80% ጀማሪዎች በመጀመርያ አመታቸው እንደሚከስሩና ዘርፉ የአጭር ጊዜ ትርፍ ሳይሆን ረጅም ጊዜ ሀብት እሳቤን ለተላበሱ ጥቂት ኢንቨስተሮች(ዋረን ባፌቶችን (Warren Buffets)) የሚመች መሆንና በተለይም እንደ crypto, forex, የመሳሰሉ ግምታዊ(Speculative) ገበያዎች አደጋቸው የከፋ በመሆኑ።

3. ዘርፉ ላይ የሰፋ ማጭበርበርና ማሳሳት ያለ መሆኑ።

የኦንላይን ንግድ በብዙ አሳሳች ደላሎች ፣ የውሸት ሐተታ ሰጪዎች ፣ ስካመሮች ... የሞሉበት በመሆኑና ዘርፉ በባህሪው ከፍተኛ የሆነ ስሜትን የመቆጣጠር ክህሎትና የዳበረ የቢዝነስ ትንተና የሚጠይቅ ስለሆነ ለመጭበርበር የተጋለጠ መሆኑ።

4. ህጋዊነት ያልተከተለ እንዲሁም ስነ ምግባርን የጣሰ

እስክ አሁን ባለን መረጃ የክሪፕቶም ሆነ ሌላ የኦንላይን የግብይት ስራ ጥንቃቄ የተሞላበትና ከህግ አኳያ ጥብቅ ክትትል የሚደረግበት መሆኑ በተለይ እንደ Crypto አይነቶቹ የንግድ እንቅስቃሴዎች በህግ በጥብቅ የተከለከሉ መሆናቸውንና በኢትዮጵያ ህጎች (የሸማቾች ጥበቃም ሆነ የብሔራዊ ባንክ ደንብ) በሚከለክለው መልኩ የቀረበና ስነ ምግባርን የጣሰ መሆኑ ታውቆ እንዲታረም ለማለት እንፈልጋለን።

ምናልባት ይህ ዝግጅት በሌሎች ማኅበራዊ ሚድያዎችና በግለሰቦች የቀረበ ቢሆን ኖሮ ማኅበረሰቡን የማሳሳት አቅሙ (ማህበራዊ ሚድያውን ከመጠራጠር የተነሳ) አነስተኛ ስለሚሆን ይህን የእርምት ፅሑፍ ማውጣት ላያስፈልግ ይችል ነበር ሆኖም ebs የእውነት ግዴታ (Obligation to the Truth) ያለበት ሚድያ በመሆኑ እኛም እንደአንድ ከሙያው ጋር ተያያዥ እንደሆንን ሰዎች እንዲታረም አቅጣጫ መስጠቱ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘነው ነው።
🤔🤔🤔🤔
በዚሁ አጋጣሚ በአሁኑ ወቅት በተለይም በአጭር ጊዜና በትንሽ ወጪ ትልቅ ትርፍና ገቢ የሚገኝበትን መንገድ አለ በሚል የተስፋ ዳቦ እየሰጡ በየማኅበራዊ ሚድያ የሚለቀቁ ማስታወቂያዎች በሚገባ ማጣራትና ተገቢ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳንረሳ ለማሳሰብ እንወዳለን።
💥💥💥

ለመላው የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!አደረሰን! መልካም በዓል!
19/01/2025

ለመላው የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!አደረሰን!
መልካም በዓል!

To all our friends and partners who are celebrating this 2025 New Year,We would like to extend our warmest wishes for a ...
01/01/2025

To all our friends and partners who are celebrating this 2025 New Year,
We would like to extend our warmest wishes for a year filled with joy, prosperity, and meaningful experiences.
Happy New Year!

14/05/2024

2101 likes, 146 comments. “ 📸 🎥 ”

Address

22 Town Square Mall, 8th Floor Office No 805
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kefeta Training and Consulting PLC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Kefeta Training and Consulting PLC:

Share