Biftu Law office

Biftu Law office translation & legal services translating languages English Amharic& Oromic, and legal works

08/09/2021

አዲሱ የንግድ ሕግ ሁለት አዳዲስ የንግድ ማኅበር ዓይነቶችን አካቷል።

አዋጅ ቁ. 1243/2013

📌 1) አንደኛው ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማኅበር በመባል የሚታወቅ ነው። ይህ ዓይነቱ የሽርክና
ማኅበር ሁለት ወይም ከዛ በላይ የሆኑ ሰዎች የሙያ ለሙያ ደጋፊ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት የሚያቋቁሙት ማኅበር ነው። ለምሳሌ የኦዲት፣ የሕግ እና መሰል አገልግሎቶች በሌላው የዓለም ክፍል የሚሰጡት በዋናነት በዚህ መልክ በተደራጀ
ማኅበር ነው::

📌 2) ሌላው በተቀረው ዓለም እየተለመደ የመጣው አዲስ አደረጃጀት ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት (one man company) ነው።
አዋጁን በ pdf የምትፈልጉ inbox ያድርጉን

አዲሱ የብር ኖቶች መመሪያ
29/09/2020

አዲሱ የብር ኖቶች መመሪያ

14/08/2020

ጋብቻን ለመፈጸም መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

መሰረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች

1.ፈቃደኝነት

የሚጸና ጋብቻ ተፈጸመ የሚባለው ተጋቢዎቹ ለመጋባት ነፃና ሙሉ ፈቃዳቸውን ሲሰጡ ብቻ እንደሆነ የፌዴራል ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 6 ላይ ተገልፆል፡፡

2. እድሜ
ተጋቢቹ ለጋብቻው ፈቃዳቸውን በነፃ መስጠት መቻል አለባቸው፡፡ የፌዴራል ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 7(1) ላይ ወንዱም ሆነ ሴቷ አስራ ስምንት አመት ሳይሞላቸው ጋብቻ መፈጸም እንደማይችሉ ይገልፀል፡፡ ነገር ግን በልዩ ሁኔታ ይህ እድሜ ሳይሞላ በፍትህ ሚኒስቴሩ ከመደበኛ እድሜ ሁለት ዓመት ያልበለጠ ጊዜ በመቀነስ እንዲጋቡ ሊፈቅድ ይችላል፡፡ ይህ የሚሆነው ከባድ ምክኛት ሲያጋጥም ብቻ ነው፡፡

3.ዝምድና
ከህብረተሰቡ ሞራልና ከጤና ምክኛት የተነሳ ተጋቢዎች የቅርብ ዘመድ (የስጋም ሆነ የጋብቻ ዘመድ) መሆን እንደሌለባቸው እሙን ነው፡፡ የፌዴራል ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 8 እና 9 ላይ ክልከላው በግልጽ የተቀመጠ ነው፡፡

4.በጋብቻ ላይ ጋብቻ
የፀና ጋብቻ ያለው አንድ ሰው ይህ ጋብቻ ጸንቶ እያለ ሌላ ጋብቻ መፈጸም እንደማይችል የፌዴራል ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 11 ክልከላ ጥሎበታል፡፡

5. በብቸኝት ለመኖር የተወሰነ ጊዜ
አንዴት ሴት አስቀድሞ የነበራት #ጋብቻ ከቀረ በኋላ አንድ_መቶ_ሰማኒያ ቀን ካላለፈ በቀር ሌላ ጋብቻ መፈጸም አትችልም ::

ነገር ግን ይህ 180 (አንድ መቶ ሰማኒያ) ቀን ሳይደርስ
1, የወለደች እንደሆነ:
2, ጋብቻ የምትፈጽመው ከቀድሞ ባሏ ጋር ከሆነ:
3, ዕርጉዝ አለመሆኗ በህክምና ከተረጋገጠ :
4, ይህን ጊዜ እንዳትጠብቅ ፍ/ቤት የወሰነ እንደሆነ :

የ 180 (አንድ መቶ ሰማኒያ) ቀን ክልከላን ሳትጠብቅ ጋብቻ ልትፈጽም እንደምትችል የፌዴራል ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 16 (2) ያመለክታል ::

02/12/2019

ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት : ካሣ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰዉ የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ አዋጅ 1161/2011 👍 👍 🇪🇹. ⚖

ሊንኩን በመጫን ; አዋጁን 'Download' ያድርጉ 👍 🇪🇹

Join. t.me/lawyersamuel

01/11/2019

Bigamy

በጋብቻ ላይ ጋብቻ በገጠሩም ሆነ በከተማው እየተስፋፋ የመጣ ሕገ ወጥ ተግባር ነው ፡፡ ባልና ሚስት በፍርድ ቤት ውሳኔ ሳይሆን በራሳቸው ፈቃድ ትዳራቸውን ካፈረሱ በኋላ በነገሩ ላይ ድርድር አድርገው አንተም አግባ እኔም ላግባ ተባብለው የራሳቸውን ትዳር የሚመሩት በቁጥር ቀላል የሚባሉ አይደሉም ፡፡ ይህም ማለት ላንካሰስ ነገር ግን በስምምነት የየግላችንን ኑሮ እንኑር አይነት ነገር ነው ፡፡ በመሆኑም እንደ እነዚህ አይነት ግለሰቦች ጉዳዩ የወንጀል ድርጊት መሆኑን የሚያውቁና ምንም እንኳን ህግን አለማወቅ ከማስጠየቅ የማያድን ቢሆንም በጋብቻ ላይ ጋብቻ / የመጀመሪያው ህጋዊ ጋብቻ በ በፍርድ ቤት ሳይፈርስ / ሁለተኛ ጋብቻ የሚፈጽሙ ግለሰቦች ይገኙበታል ፡፡
በተሻሻለው የፌደራል መንግስት የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 11 እንደሚለው ፡ ማንኛውም ሰው አስቀድሞ በጋብቻ ላይ የታሰረ ከሆነ ፡ ይኸው ጋብቻው ፀንቶ ባለበት ጊዜ ሌላ ጋብቻ መፈፀም ክልክል መሆኑን በግልፅ ይደነግጋል ፡፡ በአንቀፅ 33/1/ መሰረት ጋብቻ ላይ ሌላ ጋብቻ ተፈፅሞ የተገኘ እንደሆነ በመጀመሪያው ወይም በሁለተኛው ተጋቢው ወይም በዐቃቤ ህግ ጥያቄ እና አመልካችነት የኋለኛው ጋብቻ እንዲፈርስ የሚደረግ ሲሆን በ ንዑስ 2 ላይ የመጀመሪያው ተጋቢ በሞት ከተለየ ደግሞ የተፈፀመውን ጋብቻ እንዲፈርስ ማድረጉ አስፈላጊ አይሆንም ፡፡ በዚሁ በተሻሻው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 75/ሀ/ ጋብቻ ከሚፈርስባቸው ምክንያቶች አንዱ ከተጋቢዎች አንዱ በፍርድ ቤት የመጥፋት ውሳኔ ሲሰጥ መሆኑ ግልፅ ሆኖ እያለ በአንቀፅ 33/2/ ላይ የመጀመሪያው ተጋቢ በሞት የተለየ እንደሆነ የኋለኛው ጋብቻ እንዲፈርስ መጠየቅ አስፈላጊ አለመሆኑን እንጅ አንደኛው ተጋቢ በፍርድ ቤት የመጥፋት ውሳኔ ሲሰጥበት እና ሌላ ጋብቻ ቢፈጽም በጋብቻ ላይ ጋብቻ መሆኑን ወይም አለመሆኑን ድንጋጌው በዝምታ አልፎታል ፡፡
እርግጥ የ ፍትሐ ብሄር ህግ አንቀፅ 163 የጠፋ ሰው ጋብቻ የመጥፋቱ ማስታወቅ ፍርድ የመጨረሻ በሆነበት ቀን እንዲፈርስ ፤ አንድ ሰው የጠፋና ከሁለት አመት ወዲህ ወሬውን ያልሰጠ እንደሆነ ማናቸውም ባለጉዳይ ቢሆን የሰውየውን መጥፋት በዳኞች እንዲነገር በማድረግ በአንቀጽ 164 መሰረት ደግሞ የጠፋው ሰው እንደሞተ ተቆጥሮ ምንም እንኳ ወራሾች ዋስትና በማስያዝም ቢሆን ውርሱ እንደሚከፈት የሚደነግግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ባሏ በፍርድ የጠፋ ሰው የተባለች ሴት ሌላ ባል ብታገባ በጋብቻ ላይ ጋብቻ ልንለው አንችልም ፡፡ ሲጀመር በፍርድ የመጥፋት ውሳኔ ከተሰጠ ለጋብቻ መፍረስ ምክንያት በመሆኑ ከዚህ በኋላ የሚመሰረተውን ጋብቻ ተደራቢ ጋብቻ ሊባል አይችልም ፡፡

27/10/2019

ይርጋ

ይርጋ ሰዎች በውል ወይም በህግ መሰረት ያገኙትን መብት ለመጠየቅ ግዴታ ካለበት ሰው የሚጠይቁበት የጊዜ ገደብ ነው ፡፡ አንድ ሰው በውል ወይም በህግ መሰረት ያገኘውን መብቱን በ ህጉ ላይ ወይም በውሉ ላይ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የማይጠቀመው ከሆነ መብቱ ቀሪ ይሆናል፡፡

ይርጋ በሁለት ክፍሎች የሚከፈል ሲሆን እነዚህም የመሰረታዊ ህግ ይርጋ እና የስነ-ስርዓት ህጎች ይርጋ ናቸው ፡፡

የመሰረታዊ ህግ ይርጋ አንድ ሰው በውል ወይም በህግ ያገኘውን መብት እንዲፈጠምለት ከተዋዋለው ሰው ላይ አሊያም ህግ ግዴታ ከጣለበት ሰው ላይ የሚጠይቅበት ጊዜ ሲሆን የስነ-ስርዓት ህግ ይርጋ በአንጻሩ አንድ ሰው በፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ ሊያስከብረው የሚችለውን መብቱን የሚያቀርብበት የጊዜ ገደብ ነው ፡፡ የስነ-ስርዓት ህግ ይርጋ ማንም ሰው የስነ-ስርዓት ህጎች ወይም ሌሎች መሰረታዊ ህጎች የሚያስቀምጡትን የክስ ማቅረቢያ ጊዜ አክብሮ ለፍርድ ቤት ክስ የማቅረብ መብት ያለው መሆኑን ሆኖም ይህ በህግ ላይ የተቀመጠው ጊዜ ካለፈ መብቱን በራሱ ፈቃድ ሆን ብሎ የተወው እንደሆነ የሚገመት ስለሆነ ክስ የማቅረብ መብቱን እስከወዲያኛው ያጣዋል ማለት ነው ፡፡
በመሆኑም ፡ በውል ህጋችን ላይ (ፍትሐ ብሄር ህግ ቁጥር 1845) ፤ አንድ ሰው በአንድ ውል መሰረት ያገኘውን ግዴታ እንዲፈጸምለት የሚጠይቀው እስከ መቼ ነው የሚለውን በግልጽ ደንግጓል ፡፡ ( ህግ በሌላ አኳኋን ካልወሰነ በቀር ውሉ እንዲፈጸምለት ወይም ካለመፈፀሙ የተነሳ ስለሚደርስ ጉዳት ወይም ውሉ እንዲፈርስ የመጠየቅ መብቱ በ (10) አስር ዓመት ይርጋ ይቀራል ፡፡ እንግዲህ ከዚህ ድንጋጌ ይዘት የምንረዳው አንድ በውል መሰረት መብት ያገኘ ሰው ይህንን ያገኘውን መብት ለማስፈጸም መብቱን መጠየቅ ያለበት በ አስር ዓመት ውስጥ ይሆናል ፡፡ ነገር ግን በውል ውስጥ ያለውን መብቱን በ አስር አመት ጊዜ ውስጥ ካልተጠቀመ ፤ መብቱ እንደሌለ ተቆጥሮ ቀሪ ይሆናል ማለት ነው ፡፡

😂😂😂😂
20/10/2019

😂😂😂😂

Lawyers should never ask a Georgia grandma a question if they aren't prepared for the answer 😁

In a trial, a Southern small-town prosecuting attorney called his first witness, a grandmotherly, elderly woman to the stand.

He approached her and asked, 'Mrs. Jones, do you know me?'

She responded, 'Why, yes, I do know you, Mr. Williams. I've known you since you were a boy, and frankly, you've been a big disappointment to me. You lie, you cheat on your wife, and you manipulate people and talk about them behind their backs. You think you're a big shot when you haven't the brains to realize you'll never amount to anything more than a two-bit paper pusher. Yes, I know you.

The lawyer was stunned. Not knowing what else to do, he pointed across the room and asked, 'Mrs. Jones, do you know the defense attorney?'

She again replied, 'Why yes, I do. I've known Mr. Bradley since he was a youngster, too. He's lazy, bigoted, and he has a drinking problem. He can't build a normal relationship with anyone, and his law practice is one of the worst in the entire state. Not to mention he cheated on his wife with three different women. One of them was your wife. Yes, I know him.'

The defense attorney nearly died.

The judge asked both counselors to approach the bench and, in a very quiet voice, said,
'If either of you idiots asks her if she knows me, I'll send you both to the electric chair.
🤣🤣🤣

08/10/2019

Address

Lideta
Addis Ababa

Telephone

+251910899775

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Biftu Law office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Biftu Law office:

Share