Amazing and Funny life

Amazing and Funny life Ethiopian Online markets Web Design, App Development, IT Consultation, Networking, Search Engine Optimization, Security Camera and so

14/01/2022
11/06/2019

አሁን ያለንበት ሁኔታ‼

09/06/2017
11/06/2016

አረ ሳናውቅ ተቀየረ እንዴ? እስቲ እምታቁት ነገር ካለ?

28/05/2016

ለፈገግታ...!
በዚህ ዘመን የተቃኙ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን :-
- ‹‹ድርቅ መጣ!›› ቢሉት፣ ‹‹በየት በኩል?›› አለ መንግሥት፡፡
- ‹‹የዘንድሮን ልግሥና ይመፃደቁበታል እንጂ አይፀድቁበትም!››
አሉ የጆሲ ተቃዋሚዎች፡፡
- የዘንድሮ ሰበር ዜና፣ ‹‹ታሠሩ፣ ተፈቱ!›› ነው፡፡
- ‹‹ኦባማ መጣ፤ ከቤት እንዳትወጣ!›› አለ መንግሥት፡፡
- «ተኙ እንዴ የተከበሩ?» ቢባሉ
«ኧረ ጭብጨባው በየት በኩል!» አሉ አንድ የፓርላማ አባል፡፡
- የዶሮ ብልት ስንት ነው? አስራ ሁለት፤ ዋጋዋ? ሁለት መቶ
ሁለት፡፡
- ለአንድ ኪሎ ስኳር፣ መቶ ኪሎ አሳር፡፡
- «ራቤን እንደ ጾም ቁጠርልኝ!» አለ የቸገረው፡፡
- ስኳር ሲቀምሱት ይጣፍጥ፣ ሲገዙት ያንቀጠቅጥ፡፡
- ቀበጥ ተመጋቢ፣ «ከቅቤው አታብዙበት» ይላል፡፡
- የዘንድሮ ሁዳዴ ፋሲካ የለውም፡፡
- የዘንድሮ በርበሬ ሲያቃጥል ሁለቴ፤
አንድም ሲገዙት፣ አንድም ሲበሉት፡፡
- ዘፈን ምረጥ ቢሉት፣ «ወይ ዘንድሮ!» ይሁንልኝ አለ፡፡
- ‹‹ምን ብቆፍር፣ ገመድ ልቀብር›› አለ ቴሌ፡፡
- ‹‹ቻይና መንገድ ሠራች!›› ቢሉት፣
‹‹ምን ዋጋ አለው? ጠዋት ምርቃት፤ ከሰዓት እድሳት!››
- ‹‹ዛሬም ለክስ ፍርድ ቤት ተጠራሁ!›› ቢል
‹‹እንዴት ነው ጋዜጠኛ ሆንክ እንዴ!›› አለው፡፡
- ሰልፍ ላማረው፣ ታክሲ ተራ ውሰደው፡፡
- “ምርጫ ደረሰ ቢሉት ኧረ ቆይ ፓርቲ ልመስርት!” አለ
- «ቆሎ እየተከካ፤ ይቺ ናት ፋሲካ!»
- ስኳር ተወደደ ቢሉት፣ «ጠጂቱ ጉድ ሆነች!» አለ
- የዘንድሮ እንጉርጉሮ፣ ‹‹አማሮ!››
- ‹‹የዘመኑ መጥፊያ ምንድነው?›› ቢሉት፣
“ቫት እና ባት” ናቸው አለ ፡፡
- ኮንዶም ተጠቅመው ልጅ አይመኙም!
- ‹‹በገዛ ምላስህ ጉድ እንዳትሆን!›› ቢሉት፤
‹‹ከዚ ኑሮ በላይ ምን ሊመጣብኝ!?›› አለ፡፡
- ‹‹ተመስገን፤ ቅቅሉንስ ጥብሱንስ ማን አየብኝ!?›› አለ በቆሎ
ሸማች፡፡
www.facebook.com/amazfunlife

Ethiopian Online markets

Address

Liberia Street
Addis Ababa
1110

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00

Telephone

+251916844545

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amazing and Funny life posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amazing and Funny life:

Share