Geological Survey of Ethiopia/የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ

Geological Survey of Ethiopia/የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Geological Survey of Ethiopia/የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ, Business Center, CMC Road, Addis Ababa.

The objective of the survey shall be to undertake studies and surveys about the earth’s crust and mineral contained in it, applying earth science techniques and to prospect for, explore, and as the case may be, estimate and delineate mineral deposits.

በርዕደ መሬቱ ዙሪያ ሊወሰዱ የሚገባቸው እርምጃዎችና ተግባራት ላይ አቅጣጫ አስቀምጠናል - ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህአዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የርዕደ- መሬት ክስተቶችና ...
10/01/2025

በርዕደ መሬቱ ዙሪያ ሊወሰዱ የሚገባቸው እርምጃዎችና ተግባራት ላይ አቅጣጫ አስቀምጠናል - ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የርዕደ- መሬት ክስተቶችና የተሰጡ ምላሾችን በመገምገም ሊወሰዱ የሚገባቸው እርምጃዎችና ተግባራት ላይ አቅጣጫ አስቀምጠናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
በኦሮሚያና በአፋር ክልሎች በስምጥ ሸለቆ ውስጥ በሚገኙ ሦስት ወረዳዎች የርዕደ-መሬት ክስተት በተመለከተ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ተካሂዷል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ በስብሰባው የሳይንስ ማህበረሰቡ አካላትና የሁለቱ ክልሎች አመራሮችም እንዲሳተፉ መደረጉን ጠቁመዋል።
ከመስከረም 2017 ዓ/ም ጀምሮ የምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ አካል በሆኑ አካባቢዎች የተከሰቱ የርዕደ-መሬትና ንዝረት ስጋቶች በልዩ ትኩረት መከታተል የሚገባን መሆኑን ተግባብተናል ብለዋል፡፡
የክስተቱ ድግግሞሽና ስፋት በአካባቢው በሚኖሩ ዜጎች ላይ ባለው ተፅዕኖ ምክንያት ተገቢውን ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በማመን በጋራ ግብረ ሀይል የተሰሩ የቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን መገምገማቸውንም ነው የገለጹት፡፡
የፌዴራልና የክልል መዋቅሮች የተቀናጀ የአደጋ ስጋት ምላሽ እየሰጡ መሆኑንና የሳይንስ ማህበረሰቡ ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተለ መረጃ የሰጠ መሆኑንም መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በኩል አጋር አካላትና የሚመለከታቸው ዘርፎች የቅድመ መከላከል ስራውን በትኩረት መደገፋቸውን አንስተዋል አቶ ተመስገን፡፡
በአስቸኳይ ስብሰባው የርዕደ- መሬት ክስተቶችና የተሰጡ ምላሾችን በዝርዝር በመገምገም በቀጣይ ሊወሰዱ የሚገባቸው እርምጃዎችና ተግባራት ላይ አቅጣጫ አስቀምጠናልም ብለዋል፡፡
እስካሁን በቅድመ መከላከል ውጤታማ ስራው ለተሳተፉ አካላትንም አመስግነዋል።

የማዕድን ሀብትን በአግባቡ በመጠቀም የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቷል።(GIE)ⵌⵌⵌⵌⵌⵌⵌ(ህዳር 17/2017ዓ/ም)የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ማዕድን ሚኒስቴ...
26/11/2024

የማዕድን ሀብትን በአግባቡ በመጠቀም የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቷል።
(GIE)
ⵌⵌⵌⵌⵌⵌⵌ
(ህዳር 17/2017ዓ/ም)
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ማዕድን ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ የተዘጋጀውን የማዕድን ኤክስፓ ጎብኝኙ።

በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች ውስጥ አንዱ የማዕድን ዘርፍ ነው።

ዘርፉ በለውጡ ሥራዎች ያስገኘው ውጤት የኢትዮጵያን የማንሰራራት ዘመን በጎ ጅማሮ አመላካች ነው።

ለሦስተኛ ጊዜ እየተካሄደ የሚገኘውን የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2024ን ዛሬ ጎብኝተናል፡፡

ኤክስፖው የማዕድን አምራቾችና ላኪዎች፣ የማዕድን ተጠቃሚዎች፣ የቴክኖሎጂ አምራቾችና አቅራቢዎች ምርትና አገልግሎታቸውን በማስተዋወቅ የገበያ ትሥሥር የሚፈጥሩበት መድረክ ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡

እንደ ሀገር ዕምቅ እና ላቅ ያለ የማዕድን ሀብት አለን። ይህን ሀብት በተገቢው መንገድ አልምቶ ወደ ጥቅም ለመቀየርና ዘርፉን ለማሻሻል መንግሥት የተለያዩ ሥራዎችን በመከወን በአጭር ጊዜ ተጨባጭ ለውጥን እያመጣ ይገኛል፡፡
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/GIE2023E
Telegram: - https://t.me/ethiopiangeology

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በጅማ ዞን ሰኮሩና ላሊሳ ቀበሌ ከፍተኛ የመሬት መንሸራተት እንዳለ ተገለፀ፡፡,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,...
28/04/2022

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በጅማ ዞን ሰኮሩና ላሊሳ ቀበሌ ከፍተኛ የመሬት መንሸራተት እንዳለ ተገለፀ፡፡
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት እንደሚታወቀው በተልዕኮ ከሚያከናውናቸው አንዱ በሃገራችን ደረጃውን የጠበቀ ተለያዩ የሥነ-ምድር ጥናቶችን በማካሄድ ጥራት ያለው የጂኦሳይንስ መረጃ በማመንጨት ለተለያዩ ተጠቃሚዎች ማቅረብ መሆኑ ይታወሳለል፡፡
ስለሆነም የተቋሙ የስነ ምድር አደጋዎች ጥናት ዳይሬክቶሬት በተያዘው በጀት ዓመት በተለያዩ የሃገሪቷ ክልሎች ትኩረት በተሰጣቸው የስነ ምድር አደጋዎች ተብለው በሚጠሩት የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የመሬት መንሸራተትና መደርመስ ላይ ጥና እያካሄደ ይገኛል፡፡
ሚያዝያ 2014 ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርስቲ የትሮፒካል እና ተላላፊ በሽታዎች ምርምር ማዕከል በሰኮሩና ላሊሳ ቀበሌ የሥነ ምድር አደጋዎች ጥናት ከፍተኛ የሆነ የመሬት መንሸራተት እንዳለና ለአካባቢው አርሶ አደሮችና ነዋሪዎችም ከእለት ወደ እለት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የስነ ምድር ባለሙያዎች ገልፀዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም በስፍራው በመገኘት ጥናት እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡

"ትናት ባንድራ አሰዘን ሸኝተን የላክነው  ወንድማችንና የስራ ባልደረባችን  ኤሊያስ ዘውዴ  ዛሬ ጄንታውን እያርበደበደ ይገኛል
04/12/2021

"ትናት ባንድራ አሰዘን ሸኝተን የላክነው ወንድማችንና የስራ ባልደረባችን ኤሊያስ ዘውዴ ዛሬ ጄንታውን እያርበደበደ ይገኛል

የሚደረገው የመከላክያ ድጋፉ  ተጠናክሮ ቀጥሏል //////////////////7የኢትዬጵያ ጂኦሎጅካል እንስቲትዩት  ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ከወረ ደመወዛቸው በተጨማሪ ግንባር ድረስ በመሄድ...
01/12/2021

የሚደረገው የመከላክያ ድጋፉ ተጠናክሮ ቀጥሏል
//////////////////7
የኢትዬጵያ ጂኦሎጅካል እንስቲትዩት ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ከወረ ደመወዛቸው በተጨማሪ ግንባር ድረስ በመሄድ ሰራዊቱን እያበረታቱ ይገኛሉ ። ይህ ያንሰብኛል ያሉ ወ/ሮ ሻሚ ሁሴን ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ይድረስልኝ በማለት አምስት ሺ ብር ለተቋሙ ዋና ዳሬክተር ለወ/ሮ እናት ፈንታ መላኩ አስረክበዋል ። ወ/ሮ እናትፈንታ በአሁኑ ስዓት ብዙ ችግር ባለበት ከምንም በላይ ሀገር ይቀድማል በሚል አገራዊ ስሜት የተደረገውን ድጋፍ አመስግነው ገንዘቡን ለመከላከያ ድጋፋ በተከፈተው አካውንት ገቢ ተደርጎ ደረሰኝ እንዲሰጣቸው በማለት በተቋሙ ላሉት የድጋፋ አሰተባባሪዎች ሰጥተዋል ።

“የተቃጣውን ጦርነት በግንባር፤ የኢኮኖሚ ተፅዕኖውን ደግሞ በሃላፊነት እና በሀገራዊ አንድነት አሸንፈን እናልፈዋለን”፦ ኢ/ር ታከለ ኡማ*****************የማእድን ሚኒስትር ኢ/ር ታከ...
23/11/2021

“የተቃጣውን ጦርነት በግንባር፤ የኢኮኖሚ ተፅዕኖውን ደግሞ በሃላፊነት እና በሀገራዊ አንድነት አሸንፈን እናልፈዋለን”፦ ኢ/ር ታከለ ኡማ
*****************

የማእድን ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት “የተቃጣውን ጦርነት በግንባር፤ የኢኮኖሚ ተፅዕኖውን ደግሞ በሃላፊነት እና በሀገራዊ አንድነት አሸንፈን እናልፈዋለን” ብለዋል።

ሚኒስትሩ በሁለቱም ግንባር እናሸንፋለን፤ ባንድ በኩል በሀገር ሕልውና ላይ የተቃጣውን የጦርነት ግንባር፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የኢኮኖሚ ተፅዕኖ በሃላፊነት እና በሀገራዊ አንድነት አሸንፈን እናልፈዋለን ነው ያሉት።

ኢ/ር ታከለ ኡማ "ኢትዮጵያን ማቆየት የሁላችንም ሀላፊነት ነው!" ብለዋል።

ከልጆቸና ከቤተሰቦቸ ሀገሬ ትበልጥብኛለች ያለውን  ወንድማችን  አቶ ኤልያስ ዘውዴ  የእንስቲቲዬቱ ዋና ዳሬክተር ወ/ሮ እናት ፈንታ መላኩ እና ዋና ጅኦሎጅስቱ ዶ/ር ደጀኔ ሃ/ማሪያም  የኢትዬ...
19/11/2021

ከልጆቸና ከቤተሰቦቸ ሀገሬ ትበልጥብኛለች ያለውን ወንድማችን አቶ ኤልያስ ዘውዴ የእንስቲቲዬቱ ዋና ዳሬክተር ወ/ሮ እናት ፈንታ መላኩ እና ዋና ጅኦሎጅስቱ ዶ/ር ደጀኔ ሃ/ማሪያም የኢትዬጵያን ባንዲራ በማስያዝ በድል ተመለስ ብለው መርቀው ሸኝተዋል።።

16/11/2021

የድንጋይ ከሰል ልማት ተጠቃሚዎች በጅማ ዞን

የአሸባራ ቡድን ዓላማ ሀገር ማፍረስ መሆኑን ከሚናገሩት ብቻ ሳይሆን ከድርጊታቸው መረዳት እንደቻሉ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል እንስቲዩት ሰራተኞች  ተናገሩ//////////////////////////...
16/11/2021

የአሸባራ ቡድን ዓላማ ሀገር ማፍረስ መሆኑን ከሚናገሩት ብቻ ሳይሆን ከድርጊታቸው መረዳት እንደቻሉ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል እንስቲዩት ሰራተኞች ተናገሩ
/////////////////////////////////////////////
የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል እንስቲዩት ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ባለፍት 3 ዓመታት የነበረውን ሀገራዊ ሁኔታ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በድሎቻችን የተሳተፍንበት፤ በተግዳሮቶቻችን ደግሞ የተጎዳንበት በመሆኑ በቀላሉ መገንዘብ እንችላለን፡፡ የጦርነቱን ዓላማ ቢሆንም በቀጥታ ከሚነግሩን ብቻ ሳይሆን ከድርጊታቸው በመነሳት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ለማፍረስ እንደሆነ በግልጽ መረዳታቸውን ነው የገለጹት፡፡ ጦርነቱ የህልውና ጦርነት በመሆኑ ከግንባር እስከ ደጀን ድረስ ሁለተናዊ ድጋፋችን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል ፡፡
የእንስቲዩቱ ዋና ዳሬክተር ወ/ሮ እናት ፈንታ መላኩ በውይይቱ ወቅት መከላከያውን በግንባርና በደጀን ከመደገፍ በተጨማሪ ሀገር እንደ ሀገር ልትቀጥል እንድትችል እና ጦርነቱን በድል ለማጠናቀቅ ጠንካራ ኢከኖሚ መገንባት ያስፈልጋል ስለሆነም እንደተቋም ተቆጥሮ የተሰጠን ተግባር ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ፤ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ከቅሬታ የጸዱ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ እንደ ግለሰብ ስንወስደው በቅድሚያ ጦርነቱ የህልውና ጦርነት ነው የተባለበትን አግባባ መረዳት፤ የመኖርና ያለመኖር ፤ እንደ ሀገር የመቀጠልና ያለመቀጠል ጉዳይ እንደሆነ መረዳትና መግባባት ሲቀጥል ኢትዮጵያን እንደሀገር ለማስቀጠል በቁርጠኝነት ከተነሳው መንግስትና የኢትዮጵያ ህዝብጋር ተባባሪ መሆን ፤ለምንጠየቀው ሁለተናዊ ድጋፍ ዝግጁ መሆንና ፈጣን ምላሽ መስጠት፤ፍት ለፍት ከገጠምነው ጠላት ባልተናነሰ የውስጥ ባንዳዎችና ተላላኪዎች እጅግ ክፍተኛ ዋጋ እያስከፈሉን መሆኑን በመረዳት ምክንያታዊ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የእነሱን እኩይ ተግባር ማጋለጥ፤ እራሳችንንን ከተመሳሳይ ድርጊቶች መቆጠብ፤ከሚዲያዎች ጀምሮ የኢትዮጵያን ጠላትና ወዳጅ የሆኑትን በማወቅና የምንከተለውንና የምንሞግተውን በተገቢው መንገድ መለየት ይኖርብናል ሲሉ ለሰራተኞችን በጥብቅ አሳስበዋል ፡፡
የተቋሙሰራተኞች ሙሉደመወዛቸውን በመስጠት፤ ደም በመለገስ፤ በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ግማሽ ሚሊዮብ ብር የሚገመት አልባሳት በመደገፍ በተጨማሪም ከሰራተኞቻችን መካከል ግንባር ድረስ በመሰለፍ እያደረጉት ያለውን ድጋፍ አመስግነው ፡፡ በአሁኑ ስዓትም ወደ ግንባር ለመሄድ ቃል የገቡና ለመሄድ ዝግጅት ላይ ያሉትን የመ/ቤታችን ሰራተኛ አቶ ኤሊያስ ዘውዴን አመስግነው አንተ ለእኛ ሰላም ግንባር ስትሔድ እኛ ደግሞ ለቤተሰቦችህ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ደጀን እንሆናለን ብለዋል ፡፡
አቶ ኤሊያስ ልጆቼና ቤተሰቦቸ በሰላም እንዲኖሩ ድሮም የደማሁላትና የቆሰልኩላት ሀገሬ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ለማስቀጠል በማሰብ ነው ወደ ግንባር ለመሄድ የወሰንኩት ብለዋል ፡፡

Address

CMC Road
Addis Ababa
2302

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Geological Survey of Ethiopia/የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Geological Survey of Ethiopia/የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ:

Share