Wanos Mesfin - ዋኖስ መስፍን

Wanos Mesfin - ዋኖስ መስፍን Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wanos Mesfin - ዋኖስ መስፍን, Addis Ababa.

It was a pleasure spending time with the Special Education staff at Harmony Hills Academy. I had the opportunity to shar...
17/01/2026

It was a pleasure spending time with the Special Education staff at Harmony Hills Academy. I had the opportunity to share my experience and deliver a brief training on professional communication in special education. The discussion emphasized practical ways to communicate more effectively with Parents and to build stronger relationships with students, colleagues, and the wider school community.

I am truly grateful to Sonan Daniel (Candidate Doctor) for coordinating and facilitating the program.

❝ Professional communication in special education ensures that no child is misunderstood and no parent is left unheard. ❞

ዋኖስ መስፍን | Wanos Mesfin

በረከት በቀለ፣ ታዳጊ ሔለን ፋንታሁን፣ የአብፀጋ በለጠ እና ዶ/ር ነቢያት ተስፋዬ ከአከርካሪ አጥንት ወይም የነርቭ ዘንግ ክፍተት (Spina bifida) ጋር የሚኖሩ Self-Advocate ኢ...
01/01/2026

በረከት በቀለ፣ ታዳጊ ሔለን ፋንታሁን፣ የአብፀጋ በለጠ እና ዶ/ር ነቢያት ተስፋዬ ከአከርካሪ አጥንት ወይም የነርቭ ዘንግ ክፍተት (Spina bifida) ጋር የሚኖሩ Self-Advocate ኢትዮጵያውያን ናቸው። በማኀበራዊ ሚዲያና በሌሎች መንገዶች ምሳሌ እየሆኑ ይገኛሉ።

ለመሆኑ የአከርካሪ አጥንት ወይም የነርቭ ዘንግ ክፍተት (Spina bifida) ምንድን ነው?

'Spina bifida' ሥርወ-ቃሉ ከላቲን የተወሰደ ሲሆን 'Spina' የሚለው ቃል በእንግሊዝኛ Spine ወይም Backbone የሚል ትርጉም ሲኖረው 'bifida' ደግሞ Split/Divided ነው። በዚህም Split spine የሚል አቻ ትርጉም አለው። የNeural tube defect (NTD) ሌላኛው መጠሪያ ሲሆን በእርግዝና ወቅት የአካርካሪ ወይም የጀርባ አጥንት በአግባቡ አለመዘጋት ነው። በዚህም ምክንያት ከህብለሰረሰር እስከ እግር የሚሄዱ ነርቮች ጉዳት ይደርስባቸዋል። ይህንን የአፈጣጠር ችግር በእርግዝና ወቅት በአልትራሳውንድ ማወቅ ሲቻል፤ የዚህ ክስተት ዋነኛ መንስዔ የፎሊክ አሲድ እጥረት እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ። ሌሎች አጋላጭ ኹኔታዎች ደግሞ የስኳር በሽታ፣ መድኃኒቶች ናቸው።

ምልክቶች፦

ሽንትና ሰገራ መቆጣጠር መቸገር፣ የጀርባ አጥንት ላይ እጢ መሳይ እብጠትና ፀጉሮች፣ የአጥንት መስነፍ፣ የሰውነት ፓራይዝድ መሆን እና የእንቅስቃሴ ችግሮች ዋነኞቹ ናቸው።

ሕክምና፦

በወሊድ ጊዜ በመጀመሪያው 24 ሰዐት በቀዶ ሕክምና፣ የሕክምና ባለሞያዎች ጋር ክትትሎች ናቸው።

የአከርካሪ አጥንት ወይም የነርቭ ዘንግ ክፍተት (Spina bifida) በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ውስጥ በፎሊክ አሲድ እጥረት ምክንያት ከሚወለዱ ከ1000 ውስጥ 4 ሕጻናት ወይም በየዓመቱ ከ30 ሺህ በላይ ህፃናት ከዚህ ከዚህ ችግር ይወለዳሉ። በተጨማሪም 97% የሚሆኑት ህፃናት አጋዥ መሣሪያዎችን (Assisstive Technology) የመጠቀም ዕድልን አያገኙም።

በኢትዮጵያ የሚገኙ አገልግሎት የሚሠጡ ተቋማት፦

1. ሆፕ ኤስ.ቢ.ኤች (HOPE-Spina bifida and Hydrocephalus)
2. የመንግስት ሆስፒታሎች
3. Addis Guzo, Cheshire Ethiopia, Reachanother Foundation and Tumim Foundation

ዋኖስ መስፍን | Wanos Mesfin

የኢትዮጵያ የኦቲዝም ሶሳይቲ የምሥረታ የማስጀመሪያ መርኃ-ግብር በተሳካ መልኩ ተከናውኗል።በሀገራችን በኦቲዝም ዙሪያ ዘርፈ-ብዙ መሻሻል ያመጣል የተባለው የኢትዮጵያ የኦቲዝም ሶሳይቲ (Natio...
31/12/2025

የኢትዮጵያ የኦቲዝም ሶሳይቲ የምሥረታ የማስጀመሪያ መርኃ-ግብር በተሳካ መልኩ ተከናውኗል።

በሀገራችን በኦቲዝም ዙሪያ ዘርፈ-ብዙ መሻሻል ያመጣል የተባለው የኢትዮጵያ የኦቲዝም ሶሳይቲ (National Autism Society of Ethiopia) በኒያ ፋውንዴሽን የሐሳብ ጠንሳሽነት (Initiatives) በትናትናው ዕለት በኤሊሊ ሆቴል የምክክር እና የሽግግር ቦርድ አባላትን በመምረጥ ተከናውኗል።

በዕለቱም የኒያ ፋውንዴሽን - የጆይ ኦቲዝም ሴንተር ሁለት ከኦቲዝም ጋር ለሚኖሩ ታዳጊዎች ለማስተማሪያ የሚያገለግሉ መመሪያዎችን (Manuals) አስተዋውቋል።

እነዚህን መመሪያዎች ለማግኘት በውስጥ መስመር መጠየቅ ትችላላችሁ።



ዋኖስ መስፍን | Wanos Mesfin

ከመምራት ይልቅ አብሮ መጓዝለዐይነ-ስውራን ወይም በሁሉም የዕይታ እክሎች ውስጥ ለሚገኙ (Individuals with Visual Impairments) በመንገዳችን ላይ አግኝተን ስንመራቸው (Gu...
28/12/2025

ከመምራት ይልቅ አብሮ መጓዝ

ለዐይነ-ስውራን ወይም በሁሉም የዕይታ እክሎች ውስጥ ለሚገኙ (Individuals with Visual Impairments) በመንገዳችን ላይ አግኝተን ስንመራቸው (Guide) ማድረግ ስላለብን እና ስለሌለብን ነገሮች 'ምክረ-ሐሳቤን' ላካፍላችሁ ወደድኩ፦

ዐይነሥውራን በተለያዩ ቦታዎች ሲንቀሳቀሱ የማኅበረሰቡ ድጋፍና ቀና ትብብር ያሻቸዋል፤ በተለይም ምቹ ባልሆኑ ቦታዎች የሚደርስባቸው አደጋዎች ብዙዎችን ለአካል ጉዳትና ሌሎች አሰቃቂ ጉዳቶች ሰለባ እያደረገ ይገኛል። ታድያ ዐይነሥውራንን ስንመራ በጥንቃቄ እና በዕውቀት መሆን አለበት።

በመንገዳችን ላይ ዐይነ-ስውራንን መምራት ስንፈልግ፦

፩| በመጀመሪያ መመራት እና መታገዝ እንደሚያስፈልጋቸው ማረጋገጥ፤ ምክንያቱም ሁሉም ዐይነስውራን መምራት ይፈልጋሉ ማለት አይቻልም።

፪| ለመመራት (Guide) ወይም ለመታገዝ እንደሚፈልጉ በአክብሮትና በትህትና በመጠየቅ ለመምራት ሳይሆን አብሮ ለመሄድ/ለመጓዝ እንደምንፈልግ መጠየቅ፤ ነገር ግን ሳያሰፈቅዱ እና ሳይጠይቁ መምራት ተገቢ አይደለም።

፫| ምላሻቸውንና ፍላጎታቸውን መሠረት አድርገን የመኪና ወይም የአደጋ ተጋላጭ ባልሆኑበት አቅጣጫ በጎናችን በኩል ከእነርሱ በጥቂት ወደፊት በመቅደም እጃችንን እንዲይዙ ማድረግ፤ ነገር ግን መጎተት፣ ማቀፍ፣ አላስፈላጊ ንክኪ፣ ክርናቸውን እጃቸውን መሳብና መጎተት፣ የሌሎች ሰዎችን ትኩረት በሚስብ መልኩ (Stereotypical) መምራት፣ ማጣደፍና ማፋጠን ተገቢ አይደለም።

፬| በጉዞ ላይ አስፈላጊ ከሆነ በትራቸውን (Cane) እንዲሠበስቡ ማድረግ፣ ምቾት ተሰምቷቸው በነፃነት እንዲጓዙ ማድረግ፤ ነገር ግን ካለፍቃዳቸው ዕቃቸውን መያዝ፣ ማስጨነቅ እና ማመናጨቅ ተገቢ አይደለም።

፭| በጉዞ ላይ ስለመንገዱ፣ ስለአካባቢው ገፅታ፣ ከፊት ለፊት ምን እንዳለ፣ ምን ያህል እርምጃ/ሜትር እንደሚቀር እና አጠቃላይ ኹኔታዎች እየገለፁ መሄድ፤ ነገር ግን 'አይዞህ፣ ምፅ፣ ስታሳዝን፣ በርታ፣ ጎበዝ ' በማለት ከልክ ያለፈ ሀዘኔታ ማሳየትና የበታችነት/የደካማነት ስሜት ከሚፈጥሩ ንግግሮች መቆጠብ፣ በተጨማሪም መጠየቅ የሌለባቸውን ጥያቄዎችን አለመጠየቅ። ለምሳሌ፦ ማየት የተሳነህ በ .... ምክንያት ነው? ምን ሆነህ ነው? የሚረዳህ የለም? ከቤት ወጥተህ እንዴት መንቀሳቀስ ትችላለህ?

፮| በመንገድ ላይ የሚያደናቅፉ፣ የሚዘለሉ፣ አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ቦታዎችና ኹኔታዎችን አስቀድሞ ማሳወቅና 'ራሳቸው እንዲወጡት (ዘለው እንዲሻገሩ) ማድረግ ጥሩ ነው። ለምሳሌ፦ ከፊት ለፊታችን 1 ሜትር ያህል የሚረዝም የውሃ መተላለፊያ አለ። እግርህን ሰፋ አድርገህ መሻገር ትችላለህ። በተጨማሪም የእግረኛ መሻገሪያ/ዜብራ በምናቋርጥ ጊዜ፣ የተጨናነቀና ግርግር ያለበት ቦታ፣ የተቆፋፈረና ምቹ ያልሆነ ቦታ ሲሆን ንቁ መሆን እና በሁሉም አቅጣጫዎች እየተመለከተ መጓዝ ጥሩ ነው።

፯| ጠባብ መንገዶችና አንድ ሰው ብቻ የሚያሳልፉ ቦታዎችና መተላለፊያዎች ሲያጋጥሙ እነርሱን ከኃላ በማድረግ ሁለት እጅን ወደ-ኃላ በማጠፍ እንዲይዙን ማድረግ አልያም ትከሻችንን በእጃቸው እንዲይዙን በማድረግ በቀስታ መጓዝ።

፰| ሰላማዊ፣ ጤናማና አዎንታዊ በሆነ መንገድ ብሎም ተግባቢ ሆኖ ከእነርሱ ጋር በመጓዝ (በመምራት) መዳረሻቸው/ቦታቸው ሲደርሱ አሳውቆ መለያየት።

ልብ ይበሉ፡ ስንመራቸው አብረን እየተጓዝን እንጂ እየረዳናቸው መሆን የለበትም።



ዋኖስ መስፍን | Wanos Mesfin

አካታችነት በሁሉም ዘርፍ!(የሕዋ ሳይንስ ለልዩ-ፍላጎት)የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ጋር በመተባበር ለዐይነሥውራንና መስማት የተሳናቸው ተማሪዎ...
22/12/2025

አካታችነት በሁሉም ዘርፍ!

(የሕዋ ሳይንስ ለልዩ-ፍላጎት)

የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ጋር በመተባበር ለዐይነሥውራንና መስማት የተሳናቸው ተማሪዎችን ለሚያስተምሩ መምህራን የሕዋ ሳይንስ ዘርፎች ጋር የተያያዙ ትምህርቶችን አካታች በሆነ መንገድ ማስተማር እንዲችሉ የሚያግዝ የአቅም ግንባታ ስልጠና ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ለመጡ 26 መምህራን ለ 2 ቀናት ከታህሳስ 11 እስከ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና መስሪያ ቤት ስልጠና ተሰጥቷል።

እኔ እና ወዳጄ እስራኤል በሥልጠናው ለተገኙ ልዩ-ፍላጎት ያላቸው መስማት የተሳናቸው እና ዐይነሥውር መምህራን ሥልጠናው ለእነርሱ የተመቸ፣ የተስማማ እንዲሆን በምልክት ቋንቋ በማስተርጎም፣ በሥልጠናው የቀረቡ ውስብስብ ሐሳቦችን ለእነርሱ በሚመጥን መልኩ በማብራራት ተካታች እንዲሆኑ ሠርተናል።

ወዳጆቼ | በኢትዮጵያ የፊዚክስ፣ የሕዋ ሳይንስ እና መሠል የአስትሮኖሚ ዘርፍ ትምህርቶች ለዐይነሥውራን 'መሥራት አይችሉም' በሚል ሲመሩ፣ ሲሰለጥኑ አንመለከትም። አልፎም በአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ብሎም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ፊዚክስና መሠል ተያያዥ ትምህርቶች ለዐይነሥውራን አይሠጡም። የሚመለከተው አካል ሊያተኩርበት ይገባል።

#ይቻላል

ዋኖስ መስፍን | Wanos Mesfin

'Welcome to the Club'(The Power of Acceptance)ዛሬ ተወዳጁ ተዋናይ ኪሮስ ኃ/ሥላሴ በሰይፉ በኢቢኤስ (Seifu on ebs) በነበረው ቆይታ እጅግ አንቃዒ እና አንቃ...
07/12/2025

'Welcome to the Club'

(The Power of Acceptance)

ዛሬ ተወዳጁ ተዋናይ ኪሮስ ኃ/ሥላሴ በሰይፉ በኢቢኤስ (Seifu on ebs) በነበረው ቆይታ እጅግ አንቃዒ እና አንቃሂ ሐሳቦች አቅርቧል፦

❝ .. ከሐረር አንድ ወንድሜ ስልክ ደውሎ 'welcome to our club' አለኝ። 'Thank You' አልኩት። አልገባኝም ነበር። ለካ እንደኔ ማየት የተሳነው ሰው ነው። በኃላ.. አዪዪዪ ገና ከጅምሩ ለካ 'ዐይነሥውር' ነኝ ብዬ 'feel' አደረግኹኝ ሳስበው ግን he is right! (ልክ ነው) በቃ! ማየት ተስኖኛል ወደ እሱ Club ገብቻለሁ። ስለዚህ የእሱ Club አባል ሆኜ ተስማምቼ መኖር ነው አይደል? ከዛን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ተስማምቼ እየኖርኩ ነው ለ10 ዓመታት.. ❞

በጨዋታ መካከልም፦

❝ .. እኔ እንደምታውቀው አካል-ጉዳተኛ ሆኛለሁ ዐይኔ አያይም። ስነግርህ ደንግጠህ ነበር። ቃሉን እንድናገረው ስላልፈለግክ ነው የደነገጥከው ግን ነኝ! መቀበል አለብኝ አይደል? አንድ ነገር መቀየር እስከቻልክ ጊዜ ድረስ ብቻ ነው እንጂ የምትንገጫገጨው፤ መቀየር የማትችለው፣ ለውጥ ማምጣት የማትችለው ነገር ከሆነ Accept ማድረግ አለብህ! ከዛም 'ተመስገን' ማለት መቻል አለብህ። ❞

❝ .. አንዳንዴ ምነው አረፈድክ? ሲሉኝ ስደናበር ነዋ እላለሁ ጠያቂዎቹ ይደነግጣሉ። እኔ እራሴ ነው ያልኩት! ሰው በራሱ መቀለድ ከቻለ፤ በራሱ ላይ መሳቅ ከቻለ ጤነኛ ነው። ሰዎች ሲሉት አይከብደውም! ሰዎች ቢናገሩት አይበሳጭም። ❞

የሰይፉ በኢቢኤስ ዝግጅት የግንዛቤ ማስጨባጫ ውብ መርኃ-ግብር ነበር። ስለነሔርና ሶልያና ምን ማለት ይቻላል? እጅን በአፍ የሚያስጭኑ ልበ ብርሃን ናቸው።

ዋኖስ መስፍን | Wanos Mesfin

አሥሩ የምልክት ቋንቋ ገፀ-በረከቶች1. ምሉዕ ቋንቋ ነው!የምልክት ቋንቋ እንደ ማንኛውም ቋንቋ ሰዋስው፣ የቋንቋ መዋቅርና ሕግ አለው፤ በዓለም ላይ ወጥ እና አንድ የምልክት ቋንቋ የለም። ምን...
25/11/2025

አሥሩ የምልክት ቋንቋ ገፀ-በረከቶች

1. ምሉዕ ቋንቋ ነው!

የምልክት ቋንቋ እንደ ማንኛውም ቋንቋ ሰዋስው፣ የቋንቋ መዋቅርና ሕግ አለው፤ በዓለም ላይ ወጥ እና አንድ የምልክት ቋንቋ የለም። ምንም እንኳን በዓለም-አቀፍ ደረጃ ባይኖርም ሀገራትን ከሀገራት የሚያግባባ International Sign language የሚባል ውድድሮችን እና መሠል ዝግጅቶች ላይ ለመግባባት ጥቅም ላይ የሚውል ያለ ሲሆን ነገር-ግን ሁሉም ሀገራት የራሳቸው አሏቸው። ለምሳሌ፦ የኢትዮጵያ የምልክት ቋንቋ/ኢምቋ (Ethiopian Sign Language/ESL)፣ የአሜሪካ የምልክት ቋንቋ/ኢምቋ (American Sign Language/ASL) ወ.ዘ.ተ

2. ስዕላዊ፣ ክዋኔያዊ እና ገላጭ ነው!

የምልክት ቋንቋ እጆቻችንን፣ የፊት አገላለፅንና የአካላዊ እንቅስቃሴዎችን በመጠቀም መልዕክት የምናስተላልፍበት ሲሆን አንዳንዴም ከልሳን ቋንቋ በተሻለ መልዕክትን ለማስተላለፍ የሚረዳ ድንቅ ቋንቋ ነው።

3. ለክዋኔ እና የእይታ ጥበብ ተስማሚ ነው!

የምልክት ቋንቋ ቴአትር፣ የታሪክ ነገራ፣ ግጥም፣ የራሱ ስላቆች/ጨዋታዎች፣ ሙዚቃ ሲኖረው ስሜቶችን ጥበባዊ በሆነ መንገድ ለመግለፅ አስደናቂና ተመራጭ ነው። የማይም የቴአትር ትርዒት አንዱ ማሳያ ነው።

4. በድምፅ/በልሳን ለምንግባባ ሁነኛ መሣሪያዎችን ነው!

የድምፅ ቋንቋ የሚጠቀሙ ሰዎች እጃቸውን አጣጥፈው መናገር አይችሉም። ከተናገሩም ንግግሩ ሳቢ አይሆንም በዚህም ምክንያት ተናጋሪዎች እጃቸውን እያወራጩ ከድምፃቸው ጋር ንግግራቸውን ያሳምራሉ።

5. በተለያዩ ቦታዎች ቋንቋውን ለመጠቀም ያስችላል!

የምልክት ቋንቋ ሁለት ሰዎች በተለያየ ርቀት ቢሆኑ፣ በጫጫታና ግርግር ውስጥ ቢሆኑ፣ በውሃ ውስጥ ቢሆኑ፣ አንዱ ከፎቁ አናት፥አንዱ ከታች ቢሆኑ፣ በመስታወት ቢሆኑ ለመግባባት ቀላልና ተመራጩ ነው።

6. የምልክት ቋንቋ መማር አመሣሥሎሽን ያዳብራል!

የምልክት ቋንቋ አመሣሥሎሽን (Associate)፣ አንድን ነገር የማስታወስ ችሎታን፣ አካባቢን መረዳትን እንድንረዳ ያስችለናል።

7. በዐይን ለዐይን በመተያየት መነጋገርን ያበረታታል!

ሰዎች ሲናገሩ ወደሌላ ቦታ ከማየት ይልቅ አተኩሮ ማዳመጥን፣ በንቃት መመልከትን ምሳሌ ያደረገ ቋንቋ ነው።

8. ሁሉም የሰው ስሞች የራሳቸው ምልክቶች ይኖራቸዋል!

9. የምልክት ቋንቋ ለእንስሳት ጥናት ጠቃሚ ነው!

ከድምፅ/ቋንቋ ይልቅ የምልክት ቋንቋን በመጠቀም የተለያዩ እንስሳትን ለማሠልጠን፣ ለማስተማር እና ጥናቶችን ለማድረግ ጥቅም ላይ ይውላል። ለምሳሌ፦ የጦጣና ዝንጀሮ ዝርያዎች፣ ውሻዎች ወ.ዘ.ተ

10. የአራዳ ቋንቋም አለው!

የምልክት ቋንቋ እንደየማኅበረሰቡ ልዩ ቃላት፣ የወጣቶች የአራዳ ቋንቋም አለው።

ዋኖስ መስፍን | Wanos Mesfin - ዋኖስ መስፍን

24/11/2025

ዛሬ የመጨረሻውን የBasic ABA (Behavior Technician/BT) ሥልጠና በመውሰድ አጠናቀቅን።

ወዳጆቼ George ፣ D/r Meron ፣ Getnet ፣ Kalkidan እና ሌሎቻችሁም አብረን ስለተማርንና የማይረሳ ጊዜ ስላሳለፍን ደስ ብሎኛል።

በሀገራችን የApplied behavior Analysis/ABA እንዲስፋፋ፣ በሳይንስ የተረጋገጡ የድጋፍ አይነቶች እንዲኖሩና እንዲተገበሩ፣ የባለሞያዎች ዕውቀትና ቁጥር እንዲጨምር እና ያለስስት ዕውቀቷን እየለገሰችን የምትገኘውን Mrs. Yodit Reinhold (BCBA, LBA) ከልብ ማመስገን እፈልጋለሁ።

ሰፊ በሆነው የABA መስክ 'አለማወቅን' አንግበን፤ ሁሌም እየተማርን ለልጆቻችን ሁነኛ የመፍትሔ አካል ለመሆን እንጥራለን!

አዎ ABA ይለምልም!

ዋኖስ መስፍን | Wanos Mesfin - ዋኖስ መስፍን

ዛሬ ሔለንን አወራሗት። እንዴት እድለኛ ነኝ! ተዋወቋት!ሔለን ፋንታሁን ትባላለች፤ 5ኛ ክፍል ናት፣ እጅግ ሲበዛ ትሁት፣ ተግባቢ እና ንግግር አዋቂ ናት። ከአከርካሪ/የጀርባ አጥንት ክፍተት (...
15/11/2025

ዛሬ ሔለንን አወራሗት። እንዴት እድለኛ ነኝ!

ተዋወቋት!

ሔለን ፋንታሁን ትባላለች፤ 5ኛ ክፍል ናት፣ እጅግ ሲበዛ ትሁት፣ ተግባቢ እና ንግግር አዋቂ ናት። ከአከርካሪ/የጀርባ አጥንት ክፍተት (Spina Bifida) ጋር የምትኖር ብትሆንም ❝ You don't have to stand up to stand out ❞ እንዲል ሬኔ ኪርቢ ገና በታዳጊነቷ ለብዙዎች ብርሃን እየሆነች ያለች። 'አለመቻል' በመዝገበ-ታሪኳ የሌለ ድንቅ ልጅ ናት። ሔለን ለብዙዎች ተስፋ ነች። ያሉበትን 'ኹኔታ' ዐይተው ከቤት ለተደበቁ ፊያሜታ፤ ካላቸው እምቅ ችሎታና አቅም ይልቅ ችግሮቻቸው ላይ ለሚያተኩሩ አዲስ ዕይታ ነች።

በቲክቶክ ደግሞ አስገራሚ ብቃቷን እያስመከተችን ትገኛለች፦

በዚህ ሊንክ አግኟት፦https://www.tiktok.com/.fantahun0?_r=1&_t=ZM-91QO4xu50XM

ውድ የ8 ዓመት ጓዴ ቃልኪዳን እህትሽን ስላስተዋወቅሺኝ አመሠግናለሁ።



ዋኖስ መስፍን |

❝ መላኩ.. ድንጋይ.. ውሃ.. ❞           “ ሰበረው! „በጉዞ ፊልምስ ተዘጋጅቶ የቀረበው ልጄስ? በተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ 'ምግባሩ' የፊልሙ ዘዋሪ ኾኖ አግኝቼዋለሁ።...
09/11/2025

❝ መላኩ.. ድንጋይ.. ውሃ.. ❞

“ ሰበረው! „

በጉዞ ፊልምስ ተዘጋጅቶ የቀረበው ልጄስ? በተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ 'ምግባሩ' የፊልሙ ዘዋሪ ኾኖ አግኝቼዋለሁ።

ምግባሩ ፀጉረ ራስታ፣ ከማኅበረሰቡ የተገለለ፣ ሰሚ ያጣ ታዳጊ ነው። ከድንጋይ ጋር ደግሞ ጥብቅ ፍቅር አለው። በጣራ ላይ ያለ ድንጋይ ለማንሳት ሞክሮ እስከመጎዳት ያደረሰው ቁርኝት። የሚናገርበት/የሚግባባት የተለየ መኾን የተረዳችው ዶ/ር ሳሮን እንዲህ ስትል ገልፃዋለች፦

❝ ምግባሩ የሚያወራበት ቋንቋ ስለሚለይ ነው እንጂ ማውራት ይችላል ❞

በድራማው ተግባቦት 'Spectrum' እንደሆነ አስተምረውናል።

የጠፋው ልጅ አባት (ገዛኸኝ) ፍለጋውን ሲዠምር (Character Journey) ልጁ መላኩ ተከራይቶ የነበረበትን ቤት በ'ድንጋይ' ሰብሮ ነበር የገባው/የከፈተው። በታሪኩ 'Climax' ላይ ደግሞ ያ ድንጋይ መላኩ የተመታበት ታላቁ ምስጢር እንደሆነ በምግባሩ የ'ሰበረው.. 'መላኩ.. ድንጋይ.. ውሃ'.. ሰሚ ያጣ ንግግር ሊገለጥ ችሏል።

በፊልሙ ላይ ባለኝ መረዳትም የታሪኩ Central plot የተሸከመው ይህ Macguffin (ድንጋይ) ይመስለኛል። ታድያ በድራማው ካሉ የተለያዩ Subplots ምግባሩ ይህንን ሚና መውሰዱ በሌሎች ፊልሞች የምናያቸው የ 'Macguffin/engimatic Character' ጋር ተመሣሣይነት አለው። የምግባሩን ገፀ-ሰብዕ የተጫወተውን ተዋናይ እያደነቅኩ የድራማውን አዘጋጅ ሰማኝጌታ አይችሉህምን እንዲህ ስል ለመጠየቅ ወደድኹ፦

1. የምግባሩ ገፀ-ሰብዕ ልዩ-ፍላጎት ያለው ይመስላል፤ ምናልባት ከኦቲዝም ጋር የሚኖር ይኾን?

2. ስለምግባሩ የገፀባሕርይ አሣሣልና ምርጫ አስተያየት ብትሠጠን?



ዋኖስ መስፍን | Wanos Mesfin
Highlight

🎶 ዘመዷ ዘመዴ | ማን እንደአንቺ | ካለሽበት | አሻም | ሸጌ | ዝም አለ | አሁን | እመኛለሁ | እልል አለች ነፍሴ | ናፍቄ ናፍቄ | አየዋቸሁ | የትም አያደርስ | ሶረኔ  🎶ኃይሉ አ...
02/11/2025

🎶 ዘመዷ ዘመዴ | ማን እንደአንቺ | ካለሽበት | አሻም | ሸጌ | ዝም አለ | አሁን | እመኛለሁ | እልል አለች ነፍሴ | ናፍቄ ናፍቄ | አየዋቸሁ | የትም አያደርስ | ሶረኔ 🎶

ኃይሉ አመርጋ - Hailu Amerga

Wanos Mesfin

29/10/2025

10ሩ የኦቲዝም እውነታዎች | 10 TRUTHS ABOUT AUTISM

1. ኦቲዝም ኅብር (Spectrum) ነው።

ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉም ተመሣሣይና አንድ አይነት አይደሉም። አንዳንዶች የሚያስፈልጋቸው ድጋፍ ከፍተኛ ነው። ሌሎች ደግሞ ያለዕገዛ መኖር የሚችሉ ናቸው። ኦቲዝም ኅብር (Spectrum) እና የተለያየ (Different) ነው።

2. ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ሰዎችም ስሜቶች አላቸው!

እንደ ማንኛውም ሰው መውደድ/ማፍቀር፣ መደሰት/ማዘን፣ መናደድ/መበሳጨትና የተለያዩ ስሜቶች አላቸው።

3. የተግባቦት አይነታቸውም ኅብርና የተለያየ ነው።

አንዳንዶች ቃላትን ተጠቅመው በማውራት ይግባባሉ፣ አንዳንዶች በቴክኖሎጂ ውጤቶች በመታገዝ ሃስብና ስሜታቸውን ይገልፃሉ። ሌሎች ደግሞ አካላዊ አገላለፆችና የምልክት ቋንቋን ይጠቀማሉ፤ ሁሉም አይነት የተግባቦት አማራጮች ከኦቲዝም ጋር ለሚኖሩ ሰዎች ጠቃሚ ናቸው።

4. ኦቲዝም ዘላቂና (Lifelong) እስከ ሕይወት ፍፃሜ አብሮ የሚቀጥል ነው።

ልጆች ካደጉ በኃላ፣ ድጋፍ ከተደረገላቸው በኃላ የሚጠፋ አይደለም። በአዋቂነታቸውም የአዕምሮ/የኒውሮሎጂካል ልዩነታቸው ይኖራል።

5. የዐይን ለዐይን ግንኙነት ማድረግ ግዴታ መሆን የለበትም።

የዐይን ለዐይን ግንኘነት አድርጎ መነጋገር አለመቻላቸው እያዳመጡ እንዳልሆነ ተደርጎ ይታሰባል። ነገር-ግን የመግባቢያ ዘዴያቸው ነው።

6. ስቲሚንግ (Stimming) ጠቃሚ ነው።

ድግግሞሽ ያላቸው አካላዊ እንቅስቃሴዎች እንደ እጅ ማውለብለብ፣ መወዛወዝ፣ እና ሌሎች ስሜቶቻቸውን የሚገሩበት፣ በስሜት ሕዋሶቻቸው የሚገቡ መረጃዎችን የሚቆጣጠሩበት ዘዴያቸው ነው። መከልከል እና ማስቆም ተገቢ አይደለም።

7. ሜልትዳውን (Meltdown) እንደ ታንትረም (Tantrum) አይደለም!

ሜልትዳውን በስሜት ሕዋሶቻቸው የሚገቡ መረጃዎች ሲበዙና ከአቅም በላይ ሲሆን የሚያሳዩት ምላሻዊ ባህርይ ነው። ታንትረም ግን ቅፅበታዊና ድንገተኛ አላስፈላጊ ባህርይ ነው።

8. ኦቲዝም ሕመም ወይም በሽታ አይደለም!

ኦቲዝም የሚድን፣ የሚፈወስ በሽታ አይደለም። እንደ ማንኛውም ሰዋዊ ማንነት ያለው፣ ዓለምን ከሌሎች በተለየ የመመልከት የአዕምሮ ዕድገት ልዩነት ነው።

9. ኦቲዝም ከብዝኃ-ማንነቶችና ከብዝኃ-አዕምሯዊ ኹኔታዎች (Neurodiversity) ውስጥ አንዱ ነው።

10. ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ሰዎችም ጓደኝነት ይፈልጋሉ።

ምንጭ፦ Neurodiversity Perspectives፣ Modern Researches and Lived Experience

#ኦቲዝም

ዋኖስ መስፍን | Wanos Mesfin

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wanos Mesfin - ዋኖስ መስፍን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wanos Mesfin - ዋኖስ መስፍን:

Share