Trading Edge

Trading Edge Welcome to Trading Edge, your trusted source for precision market insights and trading education.
(1)

Note:
We're not financial advisor..!
:
:
Trading is risky business, before investing try to consultant your financial advisor! Forex እና Crypto trading... Forex በአለም ላይ በቀን ከ 5.3 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ከሚንቀሳቀስበት የፋይናንስ ማዕከል ነው።

15/01/2026
01/01/2026

Happy New Year

🎊2026🎊

15/12/2025

ቀልድ የሚመስል ግን የትራዲንግ እውነታ....!

የዚህን ያህል ልዩነት ያለው ለምን ይመስላችኋል ?

ከላይ የተመለከትናቸው በቴክኒካል ጥናቶች ላይ ከከፍተኛ ሰዓት እስከ ዝቅተኛ ሰዓት አንድ ላይ በተሻለ ሁኔታ የሚጣጣሙ ጊዜያት  ናቸው....ከፍተኛ ጊዜያት ( Higher Time Frame(HTF...
12/12/2025

ከላይ የተመለከትናቸው በቴክኒካል ጥናቶች ላይ ከከፍተኛ ሰዓት እስከ ዝቅተኛ ሰዓት አንድ ላይ በተሻለ ሁኔታ የሚጣጣሙ ጊዜያት ናቸው....

ከፍተኛ ጊዜያት ( Higher Time Frame(HTF) ) ወሳኝ የሆኑ ቁልፍ ቦታዎችን የምንለይበት( Key level) ሲሆን ዝቅተኛ ጊዜያት ( Lower Time Frame (LTF)) ደግሞ ወደ ትሬድ መግቢያ ማረጋገጫዎችን የምንፈልግበት ( Confirmation) ነው።

በ HTF ( ጊዜው ከፍ ሲል) የምናገኘው መረጃ ጠንካራ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው።

:
:


👨‍💻 "Trading will expose every weakness you have been hiding from life."✍Trading ከህይወት ስትደብቃቸው የነበሩትን እያንዳንዱን ድክመቶችህን  ያ...
10/12/2025

👨‍💻 "Trading will expose every weakness you have been hiding from life."

✍Trading ከህይወት ስትደብቃቸው የነበሩትን እያንዳንዱን ድክመቶችህን ያወጣል።

🤔 ይህ አባባል 'Trading' (እንደ አክሲዮን፣ ፎሬክስ ወይም ክሪፕቶ የመሳሰሉትን መገበያየት) የሰውን ስነ-ልቦና እና ባህሪ ምን ያህል እንደሚፈትን የሚያሳይ ነው።

✍ገንዘብ አደጋ ላይ በሚወድቅበት ጊዜ፣ ሰዎች በሌሎች የህይወት ዘርፎች የሚደብቋቸው ወይም የሚያስወግዷቸው ባህሪያት በግልጽ ይወጣሉ፡

▫️ ፍርሃት እና ስግብግብነት (Fear and Greed):
ገንዘብ ለማጣት የሚፈራ ሰው በትክክለኛው ሰዓት ግብይት ውስጥ መግባት ይፈራል ወይም በተቃራኒው በጣም ስግብግብ ሆኖ ከመጠን በላይ ይገበያያል።

▫️ትዕግስት ማጣት (Impatience): ፈጣን ትርፍ የማግኘት ፍላጎት አጓጉል ውሳኔዎችን እንዲወስን ያደርጋል።

▫️ ስርዓት/ዲሲፕሊን ማጣት (Lack of Discipline):
አንድ ሰው ያወጣውን የግብይት ህግጋትና ስትራቴጂ ሳይከተል በስሜት መነሳሳት ሲወስን።

▫️ ኩራት (Ego):
ስህተት እንደሰራ አለመቀበል እና ትርፍ የማያመጣውን ግብይት ለረጅም ጊዜ መያዝ።

👨‍💻በአጭሩ፣ ንግድ(Trading) አንድ ሰው በገንዘብ እና በውጥረት ውስጥ እራሱን እንዴት እንደሚቆጣጠር የሚፈትሽ ጠንካራ ፈተና ነው፣ ስለዚህም የውስጥ ድክመቶች ሁሉ ይገለጣሉ።

🎊መልካም ቀን 🎊

❇️ የቢትኮይን ገበያ ዑደት▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️🔰ገበያ በቴክኒካል ና ፈንዳሜንታል እንዲሁም በገበያው ዑደት ( market cycle) ጥናቶች ካልተከተልነው ትርፋማ የመሆን እድላችን አናሳ...
01/12/2025

❇️ የቢትኮይን ገበያ ዑደት
▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️

🔰ገበያ በቴክኒካል ና ፈንዳሜንታል እንዲሁም በገበያው ዑደት ( market cycle) ጥናቶች ካልተከተልነው ትርፋማ የመሆን እድላችን አናሳ ነው።



✍የቢትኮይን ከፍተኛ ዋጋ መመዝገብ በየአራት አመቱ የሚከሰት ሲሆን ከዚህ ቀደም 4 ጊዜ halving የተከናወነ ሲሆን ከፍተኛ ዋጋዎችም ተከናውኗል የዘንድሮው ባይቋጭም።

✍ከፍተኛ ዋጋ የሚመዘገብባቸውም ወራት
October----November---December ነበሩ/ናቸው።

👨‍💻ከታች በምስሉ ላይ የተመለከትነው አረንጓዴ ቋሚ መስመር December 01 ለማመልከት ነው ( ዛሬ ያው ዴሴምበር አንድ አይደል 😂)

✍የቢትኮይንን ከፍተኛ ዋጋ ለመመልከት ያህል:

🔰ዋና ዋናዎቹን የቅርብ ጊዜያት ብንመለከት 2017, 2021 እና ያልተቋጨው 2025 ነው።

📊በትሬዲንግ ቴክኒካላዊ ጥናት ና በክሪፕቶ የ4 አመት የዋጋ ከፍታ ና ዝቅታ ዑደት ( market cycle) መሰረት ከባለፉት አመታት አንፃር የዘንድሮውን ስንመለከት:
Bullrun አለቀ እንዴ ? ያስብላል...! 😂

☑️በዘንድሮው ( 2025) የጣመ Alt season አልተመለከትንም ከተዋሰኑ ኮይኖች ውጪ...!

ጥሩ የዋጋ ጭማሬ ካሳዩት መካክል "BNB" ተጠቃሽ ነው።

ቢትኮይን በ Oct. 06-2025 ከፍተኛ ዋጋ ( $126K ) ካስመዘገበ በኋላ የቁልቁለት ጉዞውን ተያይዞታል።

▫️2017 የተመዘገበው ከፍተኛው ዋጋ:
በDec. 17-2017 ሲሆን ( $19,600)

▫️2021 የተመዘገበው ከፍተኛ ዋጋ:
Nov. 10-2021 ሲሆን ዋጋውም $69,000

🥸የሁለቱን አመታት ስንመለከት የ አንድ ወር መሸጋሸግ ( መቅደም) ይታይበታል..!

▫️2025 ( ዘንድሮ) እስከ አሁን ባለው ሁኔታ ከፍተኛ ዋጋ የተመዘገበው:
በ Oct. 06-2025 ሲሆን ዋጋውም $126K ነው።

👨‍💻በፊት ከነበሩት አመታት የወር ከፍተኛ ዋጋ መመዝገብ ጋር ስናነፃፅረው ይኽኛውም የአንድ ወር መሸጋሸግ ( መቅደም) አሳይቷል....
ከከፍታው በኋላም በፍጥነት እየቀነሳ ይገኛል....!
( አሁናዊ ዋጋ: $86K)

✍ከላይ በተመለከትነው መሰረት የዘንድሮው (2025) Bullrun አለቀ ወይስ ከወትሮው በተለየ ዘግይቶ ይሆን ?
የሚል ጥያቄ ይነሳል....!

🙋‍♂እናንተ ምን ታስባላችሁ ?

ምልከታችሁን አካፍሉን

:
:

🎊መልካም ቀን🎊

NO TRADE DAY....!CME ዝግ በመሆኑ እና Thanksgivingday ( yesterday) ገበያው ጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለም...!እንደዛሬ አይነት ቀናቶችን ከትሬድ መታቀብ ጥሩ ነው..!...
28/11/2025

NO TRADE DAY....!

CME ዝግ በመሆኑ እና Thanksgivingday ( yesterday) ገበያው ጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለም...!

እንደዛሬ አይነት ቀናቶችን ከትሬድ መታቀብ ጥሩ ነው..!

not to trade is a part of trade...!

please preserve your capital...!

Experience will teach you a lot...!
24/11/2025

Experience will teach you a lot...!

24/11/2025

What is your perspective ?

( የእናንተ እይታ ምንድነው ? )

በትሬዲንግ ከባዱ ነገር ራስን ማሸነፍ ነው...!-------------------------------------------------------የትሬዲንግ ፅንሰ ሃሳብ፣ ቴክኒካል ና ፈንዳሜንታል ጥናቶ...
24/11/2025

በትሬዲንግ ከባዱ ነገር ራስን ማሸነፍ ነው...!
-------------------------------------------------------

የትሬዲንግ ፅንሰ ሃሳብ፣ ቴክኒካል ና ፈንዳሜንታል ጥናቶችን በአጭር ጊዜ ( በወራት) ተምራችሁ ልትረዱ ትችላላችሁ። ነገር ግን ራሳችሁን ለማሸነፍ አመታትን ሊወስድባችሁ ይችላል።

ራስ ለእራስ ጠላት የሚሆንበት ስፍራ ነው ....!

እንዴት ?

በትሬዲንግ ትልቁ ና ፈታኙ ክፍል የትሬዲንግ ስነ-ልቦና ( Trading Psychology/mindset) ነው።

ውስጣችሁ ያለ ፍላጎት ና እስከ ዛሬ ይዛችሁት የመጣችሁት ባህሪ ና ስሜት ለትሬዲንግ ምቹ ላይሆን ይችላል።

ለትሬዲንግ ወደሚሆን ማንነት ለመቀየር በጣም ከባድ ነው። ውስጣችን የተጫነውን ሃሳብ፣ ባህሪ መቀየር በጣም ትልቅ ስራ ይጠይቃል።

የትሬዲንግ ህግ አውጥታችሁ አታከብሩም፣
በቋሚነት መስራት ወይም መከተል የፈለጋችሁትን ሂደት አትከተሉም...!

ውስጣችሁ ብዙ ሰዎች( ማንነት) ይፈጠራል...!
ሰው ነግሯችሁ አትሰሙም፣ እናንተም ደርሶባችሁ ቶሎ አትረዱም ወይም በቃኝ አትሉም።

አብዛኛው ሰው በትሬዲንግ ያሳለፈውን ውጣ ውረድ ሲናገር ተመሳሳይ ነው....! አንዳንዴ እናንተ የሌሎችን ተሞክሮ ስትሰሙ ሸምድደው ነው እንዴ ? ልትሉ ሁሉ ትችላላችሁ...!

ብዙዎች ሲናገሩም ስለእናንተ የሚያወሩም ይመስላችኋል...!

ለምን ይመስላችኋል ?
መልሱ ለእናንተ ልተወው...!

በትሬዲንግ ውጤታማ ለመሆን በደንብ መስራት ያለብን የትሬዲንግ ስነልቦና ውቅር ላይ ነው...!

በስነ ልቦና ጥሩ ካልሆናችሁ ስንትም አመት ብትሰሩ ምንም ውጤት የለውም ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ነው...!

አንድ አመት ሙሉ የሰራችሁትን በአንድ ደቂቃ ታጡታላችሁ...!

የሰው ልጅ ፍላጎት ያለተገደ መሆኑ እና ገበያው የሚሰጠን እድል እንዲሁ ገደብ አልባ መሆን በነጋዴዎች ላይ ያለው ስነልቦና ተደማምሮ ጢባ ጢቤ ይጫወትባቸዋል።

*ስለዚህ እናንተም በትሬዲንግ ውጤታማ መሆን ከፈለጋችሁ ትሬዲንግ ስነ-ልቦና ( psychology) ላይ በደንብ ስሩ...።

ስትራቴጂ ትንሽ ቦታ ነው ያለው።

80% ስነ-ልቦና፤
20% ክህሎት

ስነልቦናችሁ ጥሩ ካልሆነ ክህሎታችሁን ታጠፉታላችሁ!
( አውቆ አላዋቂ ትሆናላችሁ)

አንድ ምሳሌ ልስጣችሁ:
ትሬድ ገብታችሁ ያንን ትሬድ ብትከስሩ ውስጣችሁ መጥፎ ስሜት ተሰምቷችሁ፡ የከሰራችሁትን ለማስመለስ ሌላ ትሬድ ከገባችሁ በስነልቦና ስለምትጎዱ እውቀታችሁ ዋጋ ላይኖረው ይችላል።

በትሬዲንግ እንዲሁም በህይወት ፍፁማዊነት ( perfection) የለም...!

it is probabilistic game...!

መልካም ቀን

21/11/2025

✅Tradingveiw discount
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔺Black Friday

☑️ -70% ቅናሽ ዛሬ ጀምሯል!

መግዛት የምትፈልጉ እድሉን ተጠቀሙበት!

Only 7 days

Just for information😂

Address

Addis Ababa

Telephone

+251910011004

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Trading Edge posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Trading Edge:

Share