Global Sport

Global Sport Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Global Sport, Business service, Addis Ababa.

09/03/2021
ሴኔጋላዊው አማካይ ፓፓ ቦባ ዲዮፕ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ--------------ሴኔጋላዊው አማካይ ፓፓ ቦባ ዲዮፕ  በ42 አመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ቢቢሲ ዘግቧል።አማካዩ ረዘም ላለ...
30/11/2020

ሴኔጋላዊው አማካይ ፓፓ ቦባ ዲዮፕ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
--------------
ሴኔጋላዊው አማካይ ፓፓ ቦባ ዲዮፕ በ42 አመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

አማካዩ ረዘም ላለ ጊዜ በነበረበት በሽታ ምክንያት ህይወቱ ማለፉም ነው የተሰማው።

ቦባ ዲዮፕ በፈረንጆቹ 2002 የዓለም ዋንጫ የማይረሳ ጊዜ ያሳለፈው የሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን አባልና ከወሳኝ ተጫዋቾች መካከል አንደኛው እንደነበር የሚታወስ ነው።

በወቅቱ ሃገሩ ሴኔጋል በውድድሩ ሩብ ፍጻሜ ድረስ ላደረገችው ጉዞ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉም አይዘነጋም።

ከዚህ ባለፈም በውድድሩ ሴኔጋል ከፈረንሳይ ጋር ባደረገችው የምድቡ የመክፈቻ ጨዋታ ብቸኛዋንና የማሸነፊዋን ጎል በማስቆጠር ባለ ታሪክም ነበር።

ዲዮፕ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፖርትስማውዝና ፉልሃምን ጨምሮ በሌሎች ክለቦች በነበረው ቆይታ ከ120 በላይ ጨዋታዎችን አድርጓል።

በፈረንጆቹ 2008 በሃሪ ሬድናፕ ከሚሰለጥነው ፖርትስማውዝ ጋር የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ ያሸነፈው ቡድንም አባል እንደነበር ይታወሳል።

ሮናልድ ኪዩመን ባርሴሎናን በአሰልጣኝነት ተረከበ--------------- የስፔኑ ባርሴሎና ሮናልድ ኪዩመንን አሰልጣኙ አድርጎ ሾሟል፡፡የካታላኑ ክለብ የቀድሞ አሰልጣኙ ኪኬ ሴቲዬንን ከቻምፒየን...
19/08/2020

ሮናልድ ኪዩመን ባርሴሎናን በአሰልጣኝነት ተረከበ
---------------
የስፔኑ ባርሴሎና ሮናልድ ኪዩመንን አሰልጣኙ አድርጎ ሾሟል፡፡

የካታላኑ ክለብ የቀድሞ አሰልጣኙ ኪኬ ሴቲዬንን ከቻምፒየንስ ሊጉ ሽንፈት በኋላ አሰናበቷል፡፡

ይህን ተከትሎም የቀድሞው የክለቡን ተጫዋች ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡

ኪዩመን የኔዘርላንድስ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የአፍሪካ ከፍተኛውን የስፖርት ሽልማት አሸነፉ---------------------የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የአፍሪካ ብሄራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር...
08/08/2020

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የአፍሪካ ከፍተኛውን የስፖርት ሽልማት አሸነፉ
---------------------
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የአፍሪካ ብሄራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር /አኖካ/ ለኦሎምፒክ ስፖርት ዕድገት ድጋፍ ላደረጉ መሪዎች እና ታዋቂ ሰዎች የሚሰጠው ሽልማት አሸናፊ ሆኑ።

ለኢትዮጵያ ስፖርት እና ለኦሎምፒክ ንቅናቄ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ይህ በአፍሪካ በስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የሆነው ሽልማት ተሸላሚ መሆናቸውን አኖካ አስታውቋል።

Manchester United win over Sheffield United
25/06/2020

Manchester United win over Sheffield United

Highlights Manchester United 3 0 Sheffield United Premier League

የሊዮኔል ሜሲ ምትሃተኛ እግሮች/Lionel Messi skills 2020/
25/06/2020

የሊዮኔል ሜሲ ምትሃተኛ እግሮች/Lionel Messi skills 2020/

Global sport Ethiopia ግሎባል ስፖርት ኢትዮጵያ new sporting breaking news, transfer gossip, analysis will be provided to our audience.

የሊዮኔል ሜሲ ምትሃተኛ እግሮች/Magical Skills of Lionel Messi!
25/06/2020

የሊዮኔል ሜሲ ምትሃተኛ እግሮች/Magical Skills of Lionel Messi!

Global sport Ethiopia ግሎባል ስፖርት ኢትዮጵያ new sporting breaking news, transfer gossip, analysis will be provided to our audience.

የሜዳ ቴንስ ኮከቡ ጆኮቪች በኮሮና ተያዘ------------------የዓለም ቁጥር አንድ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ሰርቪያዊው  ኖቫክ ጆኮቪች በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተሰማ።ሮይተርስ እንደዘገበው ከሆ...
23/06/2020

የሜዳ ቴንስ ኮከቡ ጆኮቪች በኮሮና ተያዘ
------------------
የዓለም ቁጥር አንድ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ሰርቪያዊው ኖቫክ ጆኮቪች በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተሰማ።

ሮይተርስ እንደዘገበው ከሆነ የሜዳ ቴንስ ኮከቡ በኮሮና ቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።

ለበጎ አድራጎት ድጋፍ ማሰባሰቢያ የሜዳ ቴኒስ ላይ የተሳተፈው ዲሚትሮቭ  የኮሮና  ቫይረስ ተገኘበት--------------------------------በወንዶች የሜዳ ቴኒስ ቀዳሚ በሆነው ኖቫክ...
22/06/2020

ለበጎ አድራጎት ድጋፍ ማሰባሰቢያ የሜዳ ቴኒስ ላይ የተሳተፈው ዲሚትሮቭ የኮሮና ቫይረስ ተገኘበት
--------------------------------
በወንዶች የሜዳ ቴኒስ ቀዳሚ በሆነው ኖቫክ ጃኮቪች አስተባባሪነት በተዘጋጀው የበጎ አድራጎት ድጋፍ ማሰባሰቢያ ላይ ከተሳተፈ በኋላ ነው ቡልጋራዊው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ቫይረሱ የተገኘበት።

የበጎ አድራጎት ዝግጅቱን ያዘጋጀው ኖቫክ ጃኮቪችም ተገቢው ጥንቃቄ ያልተደረገበት ዝግጅት በማዘጋጀቱ ወቀሳ እየቀረበበት ይገኛል።

ይህ ዝግጅትም ዲሚትሮቭ ቫይረሱ ከተገኘበት በኋላ መሰረዙ ተነግሯል።

ዲሚትሮቭ በኢንስታግራም ገፁ ለአድናቂዎቹ ባስተላለፈው መልዕክት ጎደኞቼ እና አድናቂዎቼ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘብኝ እንዲያውቁ እፈልጋለሁ ብሏል።

ላስከተልኩት ማንኛውም ጎጂ ነገር ይቅርታ እጠይቃለሁ ያለው ተጫዋቹ ለድጋፋችሁም አመሰግናለሁ ሲል ለአድናቂዎቹ መልዕክት ማስተላለፉን አልጀዚራ የዘገበው።

Address

Addis Ababa
1000

Telephone

+251966791088

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Global Sport posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Global Sport:

Share