Galaqli Daqaarak Gaaroyse Kutbeh Buxa

Galaqli Daqaarak Gaaroyse Kutbeh Buxa ADASWE is a specialized enterprise for carrying out professional study, design and supervision works

ስለ ሰንደቅ ዓለማ ቀን እውነታዎች*************ሰንደቅ ዓላማ ምንድን ነው?ሰንደቅ ዓለማ የሉዓላዊ ሀገር መለያ አርማ እና የህዝቦች ማንነት መገለጫ ነው፡፡ የህዝቦች ታሪክና አንድነት መ...
14/10/2024

ስለ ሰንደቅ ዓለማ ቀን እውነታዎች
*************

ሰንደቅ ዓላማ ምንድን ነው?

ሰንደቅ ዓለማ የሉዓላዊ ሀገር መለያ አርማ እና የህዝቦች ማንነት መገለጫ ነው፡፡ የህዝቦች ታሪክና አንድነት መገለጫ እና የሀገር ምልክትም ነው፡፡ ሰንደቅ ዓለማ የሰላም፣ የድል አድራጊነት እና የስኬት መገለጫ ተደርጎ ከፍ ብሎ ይውለበለባል፡፡ ሀገራት ካላቸው ሀገራዊ ታሪክና ዳራ ጋር አያይዘው ለሰንደቅ ዓለማቸው ያላቸውን ፍቅር እና ክብር በማሳየት ያከብሩታል፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ያሉት ጥንታዊ እና ነጻ ሀገራት የድል ቀናቸውን፣ በቅኝ ግዛት የተያዙት ሀገራት ደግሞ ከቅኝ ግዛትነት ነጻ የወጡበትን ቀን፣ በተለያዩ ምክንያት ዘግይተው ሀገር የሆኑት ደግሞ ነጻና ሉዓላዊ መንግሥት የመሰረቱበት ቀን ለማስታወስ የሰንደቅ ዓለማ ቀን ያከብሩታል፡፡

በዓለማችን 52 ሀገራት የሰንደቅ ዓለማ ቀንን ያከብራሉ፡፡ ኢትዮጵያም በራሷ መንገድ የሰንደቅ ዓለማን ቀንን ሀገራዊ መልክና ይዘት ያላቸው መልእክቶችን ቀርጻ በደማቅ ሁነቶች ታከብራለች፡፡ በዓሉ ጥቅምት በገባ በመጀመሪው ሳምንት ሰኞ ይከበራል፡፡ ኢትዮጵያ ላለፉት 16 ዓመታትም የሰንደቅ ዓለማ ቀንን በተለያዩ መሪ ቃሎች ስታከብር ቆይታለች፡፡ በዓሉ በየዓመቱ በደማቅ ሁኔታ በፌዴራል ደረጃ፣ በክልሎች፣ በከተማ አስተዳደሮች እና በሁሉም የፌዴራልና ክልል ተቋማት ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ ይከበራል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት 16 ዓመታት ቀኑን በሀገር አቀፍ ደረጃ ስታከብር ምን ዓይነት መልእክቶችን ተጠቅማ ነበር? ባለፉት 16 ዓመታት የሰንቅ ዓላማ ቀናት አከባበሮች በሰንደቅ ዓለማው መርሆች እና ለብዘኃነታቸው ባላቸው ትርጉም ዙሪያ ግልጽነት ለመፍጠር፣ ዜጎች በሰንደቅ ዓለማው ትርጎሜ እና ቅርጽ ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲያዳብሩ ለማድረግ፣ የተዛቡ እና አሉታዊ አስተሳሰቦችን ለማቃናት ለማረም የሚያስችሉ መልዕክቶች ተላልፈውባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓለማ አረንጎዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ቀለማት ያሉት ሲሆን መሃሉ ላይ ሰማያዊ ኮከብ መደብ ብሔራዊ አርማ ያለው ሰንደቅ ዓለማችን ልምላሜያችንን፣ ተስፋችን እና ለሀገር ሉዓላዊነት የሚከፈል መስዋእትነት ያንጸባርቃል፡፡

በኢትዮጵያ እስከ አሁን የተከበሩ የሰንደቅ ዓለማ ቀኖችን አስመልክቶ የተንጸባረቁ መሪ ሀሳቦችን በከፊል እናስታውስ፡-

• 7ተኛው "በህዝቦቹዋ ተሳትፎና ትጋት ድህነትን ድል በመንሳት ብሄራዊ ክብራችንና ሰንደቅዓለማችንን ከፍ ከፍ በማድረግ ላይ ያለች ሀገር ኢትዮጵያ!"

• 10ኛው "ራዕይ ሰንቀናል ለላቀ ድል ተነስተናል!"

• 11ኛው "ሰንደቅ ዓላማችን ለዴሞክራሲያዊ አንድነታችን!”

• 12ኛው "ሰንደቅ ዓለማችን የብዙሃን ድምር ውጤት፣ የአንድነታችን ምሶሶ ነው!”

• 13ተኛ "ሰንደቅ ዓለማችን ፣ለሰላማችን፣ ለአንድነታችን፣ ለሀገራዊ ብልጽግናችን!"

• 14ኛ "በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓለማ ከፍታ!"

• 15ኛ "ሰንደቅ ዓላማችን የብዘሃነታችንና የሉዓላዊነታችን ምሶሶ ነው!”

• 16ኛ "የሰንደቅ ዓለማችን ከፍታ ለህብረ ብሄራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው!"

• 17ኛ "ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!”

29/06/2022
15/04/2022
10/04/2022
07/04/2022

ለተደራራቢ ወንጀሎች የቅጣት አወሳሰን ዘዴ
በወንጀል ሕግ
=======================
በተደራራቢ ወንጀሎች ቅጣት አወሳሰን ዙሪያ አዲሱ የወንጀል ሕግ ከቀድሞው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የሚለይባቸው የተለያዩ ጉዳዮች ቢኖሩም መሠረታዊ ተብሎ ሊጠቀስ የሚችለው ልዩነት ግን የተደራረቡ ወንጀሎች በተፈፀሙ ጊዜ ቀደም ሲል ይሰራበት የነበረው መሠረታዊ መርህ መለወጡ ነው፡፡ በዚህም መሠረት በወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ አካሄድ ለከባዱ ወንጀል ቅጣት ከተወሰነ በኋላ ለሌላው ወንጀል እስከ መጀመሪያው (የከባዱ) ወንጀል ማስቀጫ አንቀጽ የቅጣት ጣራ አጋማሽ ድረስ ቅጣት ይጨመር የነበረበት የማክበድ (aggravation) መርህ ቀርቶ ለየቅጣቱ ዓይነት በሕጉ ጠቅላላ ክፍል የተደነገገውን የቅጣት ጣራ እስካላለፈ ድረስ ለሁሉም ወንጀሎች የሚወሰኑ ቅጣቶች እንዲደመሩ ሆኗል፡፡ በተደራራቢ ወንጀሎች ቅጣት አወሳሰን ዙሪያ በአዲሱ የወንጀል ሕግ የተካተቱትን ነጥቦች ቀጥለን በአጭሩ እንመለከታቸዋለን፡፡

1. #ከተደራራቡት ግዙፍ ወንጀሎች ውስጥ ለአንደኛው የሚጣለው ቅጣት የቀሪዎችን ወንጀሎች ቅጣት የሚያጠቃልል በሆነ ጊዜ፣

ከተደራራቢ ወንጀሎች ውስጥ በአንደኛው ምክንያት የሞት ወይም የዕድሜ ልክ እስራት ወይም ወንጀሎቹ ተመሳሳይ ዓይነት የእስራት ቅጣት የሚያስቀጡ ሆኖ በአንደኛው ምክንያት በሕጉ ጠቅላላ ክፍል የተደነገገው ከፍተኛ ቅጣት ከተወሠነ ይህ ውሳኔ ለሌሎች ተደራራቢ ወንጀሎች የሚወሠነውን ቅጣት ሁሉ አጠቃሎ ይይዛል (አንቀጽ 184(1)(ሀ))፡፡ ይህም ማለት ከተደራራቢ ወንጀሎች ውስጥ በአንዱ ምክንያት የሞት ቅጣት ወይም የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት፣ የ25 ዓመት ፅኑ እስራት ወይም የአምስት ዓመት ቀላል እስራት ከተወሠነ በሌሎች ተመሣሣይ ዓይነት ቅጣት በሚያስፈርዱ ወንጀሎች ምክንያት ከተገለፀው ቅጣት በላይ መወሠን አይቻልም፡፡ (በአንቀጽ 184/1//ሀ/ የተደነገገው ሁኔታ ቅጣቱ ቢከብድም ከተደራረቡት ወንጀሎች በአንደኛው ውስጥ በሕጉ ልዩ ክፍል ቅጣቱ ተካትቶ /ተሸፍኖ/ የምናገኝበትን ሁኔታ የሚመለከት ነው)፡፡

ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ከባድ ለሆነው ለአንደኛው ወንጀል የሞት ቅጣት፤ የዕድሜ ልክ እስራት ወይም ለእስራቱ ዓይነት በሕጉ ጠቅላላ ክፍል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት መወሰኑን ትቶ ዝቅ ያለ ቅጣት ከወሠነ፤ በሌሎቹ ተደራራቢ ወንጀሎች ምክንያት በሕጉ ጠቅላላ ክፍል እስከተደነገገው ከፍተኛ ቅጣት ድረስ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን አክብዶ መወሠን ይችላል፡፡ ለምሳሌ አንድ ጥፋተኛ ከሚፈረድበት ወንጀሎች ውስጥ በአንደኛው ምክንያት የሀያ አምስት ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት የሚወሰንበት ከሆነ በሌሎች አነስተኛ ወንጀሎች ምክንያት የእስራት ቅጣት ሊወሰንበት አይችልም፡፡ ምክንያቱም ለፅኑ እስራት በሕጉ ጠቅላላ ክፍል የተቀመጠው ከፍተኛ የቅጣት ጣራ ሀያ አምስት በመሆኑ ከዚያ አልፎ ሰላሳ ዓመት ወይም ደግሞ የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ፍርድ ቤቱ ሊወስን ዓይችልም፡፡ የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ሊወሰን የሚችለው ወንጀለኛው ከፈፀማቸው ወንጀሎች ውስጥ ቢያንስ አንዱ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ሆኖ ከተገኘ ብቻ ነው፡፡ ምንም እንኳን ወንጀለኛው የፈፀመው ከባዱ ወንጀል በሀያ አምስት ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት ሊያስቀጣ የሚችል ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የተለያዩ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት ከቅጣት ጣራው ዝቅ በማድረግ ለከባዱ ወንጀል ቅጣት የሚጥል ከሆነ ሌሎች ጥፋተኛው የፈፀማቸው ወንጀሎች ግምት ውስጥ ገብተው ቅጣቱ እንዲከብድ ይደረጋል፡፡ በዚህ ሁኔታ ለተደራራቢዎቹ ወንጀሎች የሚወሰነው ቅጣትም ለሁሉም ወንጀሎች ለየራሳቸው ቅጣቶችን በመጣል እንዲደመሩ በማድረግ ይሆናል፡፡

2. #በእስራት የሚያስቀጡ ተደራራቢ ግዙፍ ወንጀሎች ሲያጋጥሙ፣

ጥፋተኛው ከፈፀማቸው ተደራራቢ ወንጀሎች ውስጥ የየትኛውም ወንጀል ቅጣት የቀሪዎችን ወንጀሎች ቅጣት የሚያጠቃልል ካልሆነና ወንጀሎቹ በእስራት የሚያስቀጡ ተደራራቢ ግዙፍ ወንጀሎች ከሆኑ ለእያንዳንዱ በተደራራቢነት ለተፈፀመው ወንጀል ተገቢ የሆነው ቅጣት ተወስኖ ሁሉም እንዲደመር ይደረጋል፡፡ ሆኖም ምንጊዜም ቢሆን ለእስራቱ ዓይነት በሕጉ ጠቅላላ ክፍል ከተደነገገው ጣራ ቅጣት ማለፍ አይቻልም/አንቀጽ 184/1//ለ/፡፡

አንድ ሰው የፈፀማቸው ተደራራቢ ወንጀሎች ከፊሎቹ የሚያስቀጡት በቀላል እስራት ከፊሎቹ ደግሞ በፅኑ እስራት የሚያስቀጡ ወንጀሎች በሚሆኑበት ጊዜ የቅጣት አወሳሰኑ በምን ዓይነት መንገድ እንደሚሰላ በአዲሱ የወንጀል ሕግ ላይ በግልፅ ተደንግጓል፡፡ ይኸውም እንዲህ ዓይነት ሁኔታ በሚያጋጥምበት ጊዜ ቅጣቶችን ለመደመር እንዲያመች ሁለት ዓመት ቀላል እስራት እንደ አንድ ዓመት ፅኑ እስራት ይቆጠራል፡፡ ይህ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 184 ላይ በፅኑ እስራትና በቀላል እስራት የሚያስቀጡ ወንጀሎች ተደራርበው /ተቀላቅለው/ ከተገኙ የእስራት ቅጣቶችን ለመደመር እንዴት እንደሚቻል የሚያመለክተው ድንጋጌ በ1949 ዓ.ም የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ላይ ያልነበረ አዲስ የተጨመረ ሲሆን የቀድሞው ሕግ በግልፅ የደነገገው ነገር ባለመኖሩ ምክንያት የነበረውን የተዘበራረቀ አሰራር ወጥ በሆነ አሰራር እንዲተካ የሚያደርግ ነው፡፡

3. #ሁለት ወይም ከዚያ የሚበልጡ በገንዘብ የሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀሎች ሲያጋጥሙ፣ /አንቀጽ 184/1//መ/

አንድ ሰው የፈፀማቸው ተደራራቢ ወንጀሎች በገንዘብ ቅጣት (በመቀጮ) የሚያስቀጡ ተደራራቢ ግዙፍ ወንጀሎች የሆኑ እንደሆነ ወይም ከሌሎች ቅጣት ጋር ተጣምረው ለተደራራቢ ወንጀሎቹ የገንዘብ ቅጣቶች በጥፋተኛው ላይ የሚጣሉ በሚሆንበት ጊዜ ለእያንዳንዱ በተደራራቢነት ለተፈፀመው ወንጀል ተገቢ የሆነው የገንዘብ ቅጣት ተወስኖ ሁሉም ይደመራል፡፡ ሆኖም ወንጀሉ በአፍቅሮ ንዋይ የተፈፀመ ካልሆነ በቀር ምንጊዜም ቢሆን በወንጀለኛው ላይ የሚጣለው የመቀጮ ቅጣት አጠቃላይ ድምር በሕጉ ጠቅላላ ክፍል ከተመለከተው ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ወሠን ማለፍ አይችልም፡፡

የመውረስና የገንዘብ መቀጮ በሚያጋጥምበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ ሊከተለው የሚገባው የቅጣት አወሳሰን ዘዴ ምን ሊሆን ይገባል የሚለውን በተመለከተ በቀድሞውም ሆነ በአዲሱ የወንጀል ሕግ የተካተተው ሀሳብ ተመሳሳይ ነው፡፡ ከተደራራቢዎቹ ወንጀሎች በአንዱ ምክንያት የተቀጪው ንብረት እንዲወረስ ከተወሰነ በሌላው ወንጀል ምክንያት መቀጮ በተጨማሪ ሊወሠን አይችልም /ቁጥር 189(ሠ)፣ አንቀጽ 184(1)(ሠ)/

በዚህም መሠረት ጥፋተኛው ከፈፀማቸው ተደራራቢዎቹ ወንጀሎች ውስጥ በአንደኛው ወንጀል ምክንያት ከሚፈረድበት ከዋናው ቅጣት በተጨማሪ የወንጀለኛው ንብረት እንዲወረስ ከተፈረደበት በሌሎች ተደራቢ ወንጀሎች ምክንያት የገንዘብ መቀጮ መፍረድ አይቻልም ማለት ነው፡፡

4. #ጣምራ ተደራራቢ ወንጀሎች በሚፈፀሙበት ጊዜ
በአዲሱ የወንጀል ሕግ መሠረት አንድ ሰው በአንድ ድርጊት የሚጥሰው አንድን የሕግ ድንጋጌ ብቻ ቢሆንም ቁጥራቸው ከአንድ በላይ በሆኑ ሰዎች መብት ወይም ጥቅም ላይ ጉዳት ካደረሰ ተደራራቢ ወንጀሎችን እንደፈፀመ እንደሚቆጠር በአንቀጽ 6ዐ(ሐ) ላይ ተደንግጓል፡፡ ቅጣቱ የሚወሰነውም በሌላ አኳኋን ካልተደነገገ በቀር ከዚህ በላይ በተጠቀሠው ተደራራቢ ግዙፍ ወንጀሎች በሚፈፀሙበት ጊዜ ቅጣት በሚወሰንበት መንገድ ነው (አንቀጽ 184(2))፡፡
በአንድ ድርጊት የተደራረቡ ጣምራ ወንጀሎች የፈፀመ ቢሆንም የጉዳዩን አካባቢ ሁኔታዎች በመመርመር ፡-
ጣምራ ወንጀሎቹን የፈፀመው ከዚህ በታች ከተጠቀሰው ሁኔታ ውጭ ከሆነ በሕጉ ልዩ ክፍል ለከባዱ ወንጀል የተደነገገውን ከፍተኛ ቅጣት ወሰን ባለማለፍ ፍርድ ቤቱ ቅጣትን አክብዶ ይወስናል (አንቀጽ 187(1))፡፡
ወንጀለኛው አስቦና አቅዶ ሕጉን ጥሶ ከሆነ ወይም ግልፅ የሆነ መጥፎ ፀባይ አሳይቶ እንደሆነ ግን በአንቀጽ 184 መሰረት ማለትም ተደራራቢ ግዙፍ ወንጀሎች በሚፈፀሙበት ጊዜ ቅጣት በሚወሰንበት መንገድ ቅጣቱ ከብዶ ይወሰንበታል፣

ግዙፍ ውጤት የሚያስከትሉ ጣምራ ወንጀሎች ተፈፅመው በተገኙ ጊዜ ግን፡-
ጥፋተኛው ከተደራራቢ ጣምራ ወንጀሎች ውስጥ ቢያንስ አንደኛውን አስቦ ያደረገ እንደሆነ በአንቀጽ 184 መሰረት ማለትም ተደራራቢ ግዙፍ ወንጀሎች በሚፈፀሙበት ጊዜ ቅጣት በሚወሰንበት መንገድ ቅጣቱ ከብዶ ይወሰንበታል (አንቀጽ 187/2/ሀ)፣
ጥፋተኛው ጣምራ ወንጀሎቹን የፈፀመው በቸልተኛነት ከሆነ በሕጉ ልዩ ክፍል ለከባዱ ወንጀል ከተደነገገው ከፍተኛ ቅጣት ወሰን ባለማለፍ ይወሰንበታል (አንቀጽ 187/2/ለ)፣

5. #የተዛመዱ ወንጀሎች በተፈፀሙ ጊዜ

የተዛመዱ ወይም የተቀራረቡ ወንጀሎች ተፈፀሙ የሚባለው አንዱ የተደረገው ሌላው ወንጀል እንዲፈፀም ለማድረግ፤ ወይም ለማመቻቸት ወይም ለሌላው ከለላ እንዲሆን ለማድረግ ታስቦ ሲሆን ነው (አንቀጽ 63)፡፡ በመርህ ደረጃ የተዛመዱ ወንጀሎች በተፈፀሙ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ቅጣትን የሚወስነው በአንቀጽ 184 መሰረት ማለትም ተደራራቢ ግዙፍ ወንጀሎች በሚፈፀሙበት ጊዜ ቅጣት በሚወሰንበት መንገድ ነው /አንቀጽ 185/1//፡፡

ሆኖም አንዳንድ ጊዜ የተዛመዱ ወንጀሎች እንደ አንድ ነጠላ ወንጀል የሚቆጠሩበት ሁኔታ አለ፡፡ ይህም የሚሆነው ወንጀል ፈጻሚው ዋናውን ወንጀል እግብ ለማድረስ ሲል ሌላ ወንጀል የፈፀመ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ሕግ አውጭው አጥፊው ለዋናው ወንጀል ብቻ ተጠያቂ እንዲሆን በሚደነግግበት ጊዜ ወይም ተዛማጅ ወንጀሎችን እንደ አንድ ነጠላ ወንጀል በመውሰድ የሚደነግግ በወንጀል ሕጉ ውስጥ አንድ ድንጋጌ በሚኖርበት ጊዜ ነው፡፡ እንዲህ በሚሆንበት ለምሳሌ እንደ ከባድ ግድያ ወይም ከባድ ውንብድና የመሳሰሉ /የተዛመዱ ተደራራቢ ግዙፍ ወንጀሎች/ ቅጣት የሚያከብዱ አንድ ወንጀልን የሚያቋቋሙ መሆናቸው በሕጉ ልዩ ክፍል በተደነገገ ጊዜ ተፈፃሚ የሚሆነው ለእነዚሁ ወንጀሎች የተመለከቱት ድንጋጌዎች ናቸው፡፡
6. #ተነጣጥለው ተሠጥተው የነበሩ ውሳኔዎችን ስለማጣመር
ጥፋተኛው ተፈርዶበት ቅጣቱን በመፈፀም ላይ ሳለ ወይም ከፈፀመ በኋላ ከፍርዱ በፊት የፈፀመው ተደራቢ ወንጀል መኖሩ ሲደረስበት ተደራቢው ወንጀል አስቀድሞ ቢታወቅ ሊወሰንበት ይችል ከነበረው ቅጣት ሳያልፍ ይወሰናል (አንቀጽ 186(1))፡፡ ከአንድ ፍርድ በፊት የተፈፀመ ሌላ ወንጀል ተደራራቢ ወንጀል በሚለው የሚሸፈን ሲሆን ከፍርድ በኋላ የሚፈፀም ሌላ ወንጀል ግን እንደ ሁኔታው ደጋጋሚ ወንጀለኛ በሚለው ነው ሊሸፈን የሚችለው፡፡

ተጣምረው መታየት የነበረባቸው ወንጀሎች በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ወይም በተለያዩ ችሎቶች ታይተው ውሳኔ አግኝተው ከሆነ የጠቅላላ ቅጣቱ አወሳሰን ከዚህ በላይ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት ይሆናል /አንቀጽ 186//3//፡፡ በተመሳሳይ ወቅት ማለትም ሁለተኛው ወንጀል የተፈፀመው በአንደኛው ወንጀል ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት ከሆነ ወንጀሎችቹ ተደራራቢ ወንጀሎች ናቸው፡፡ ስለዚህ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ወይም በተለያዩ ችሎቶች ታይተው ቢሆን አንኳን በተናጠል ተሰጥቶ የነበረው ውሳኔ እንደገና በአንድነት ታይቶ ተደራራቢ ወንጀሎች በሚወሰኑበት መንገድ ቅጣቱ ሊወሰን ይገባል፡፡

via Tsegaye Demeke - Lawyer

07/04/2022

Maysaxxaga

Qafar rakaakayak gittoyso komoshin gittoyso poliisih aydakaakanah fideraal gittoyso komoshin luk catiimak aban aydakaakanah tahaak gubal yan alhum kibam duuda faxe qadarih baxa aydakaakanah ruubuh bicak gaba kalak kulli rasuh yacen kootak raqte foxoh foyyah gexaamak asaamik raaqe waynuh wagta marak garaya ta,ayrook abbaxuk ilaa 30fan garaytaanam sin essera

1 caddok 5-8 fan barte num aw baritte
2 currik yan num aw tan num
3 kee baxabxsale digaaloolih mangom digaalime wee aw digaalime wayte
4 aw magaala xiinissok makfta aw fanteena mamaxaga gabat le
5 af fiirisah aw firissam dudda
6 baxa yakkem faxximta
7 qaynatih taamak currih yan aw tan axcuh nammayta doorotik curri yakkem aw takkem

Tahaak dagal edde yabne alhumitte kibah yan qafar baxak 28-30 fan gittoyso buxah komoshinil ankutubuk garayraanam sin naysixxige

Gittoyso poliisik 100 kah faxiimam rakaakayaay,4 kaadu fideraal gittoysoh buxah faxiima

Illacaboh garci kaloot kasiisih

Kilbatti rasu
Fanti rasu
Tahak dagal edde yabne namma rasul yan taqabiik ugutak barittoh alhum kee tonnah faximtam geytime waytam hangit haak ilaa caagid misoowam fan baxsale gurral aydakaakan akah culan innah rakaakay komoshin wagta maraluk agaradeemik ugutak akak raaqe waytaanam masakaxxa luk sin essera

Mamaxxaga wagittam qafar xaylo dubuk kinnim kasiisih cabna

Qafar agatih rakaakayak gittoysso komoshini

Samara

saamit ninnih nantifiqay

07/04/2022

ምንጩ ያልታወቀ ሀበብት በራሱ እና በቤተሰቡ ስም ያካበተው ተከሳሽ እህት እና ወንድሙን ይዞ ማረሚያ ወረደ

ምንጩ ባልታወቀ እና ህጋዊ ከሆነ ወርሃዊ ገቢ በላይ ሀብት በማካበት መኖርያ ቤት ሰርተውና በሬሳ ሳጥን ገንዘብ ቀብረው የተገኙ የቤተሰብ አባላት እንደ ወንጀል ተሳትፏቸው በፅኑ እስራትና በገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ሲወሰን የሙስና ወንጀል ፍሬ ሆኖ የተገኘው ከ2 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ደግሞ በመንግስት አንዲወርስ ተደርጓል ።

የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 18ኛ ወንጀል ችሎት ነው ።

1ኛ ማርክነህ አለማየሁ 2ኛ ትዕግስት አለማየሁ እና ብርሃኑ አለማየሁ የተባሉት ተከሳሾች የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ) 684(5) እንዲሁም የወንጀል ህግ ቁጥር 419(1)( ሀ)ን በመተላለፋቸው ነው በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ዐቃቤ ህግ ክስ የተመሰረተባቸው ።

1ኛ ተከሳሽ ማርክነህ አለማየሁ ከጥር 05/1987 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 03/2005 ዓ.ም ባሉት ጊዚያት በመንግስት መስርያ ቤቶች እየተዘዋወረ ሲሰራ ይከፈለው የነበረው ወርሃዊ ገቢው ደግሞ ከ2‚535 እስከ 10‚234 ያልተጣራ ደመዎዝ ይክፈለው ነበር ።

ማህበረሰቡ በግለሰቡ ላይ በሰጠው ጥቆማ መሰረት በተደረገ ፍተሻ ከ2ኛ ተከሳሽ እህቱ ጋር በመመሳጠር እና ወደ ባንክ አካውንቷ ገንዘብ በማስገባት በሐዋሳ ከተማ አላሙራ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ዲያስፖራ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በወቅቱ 2010 ዓ.ም ግምቱ 1‚425‚000 የሚያወጣ መኖርያ ቤት ሲሰሩ 2ኛ ተከሳሽ በባንክ አስቀምጣው የነበረውን 1‚388‚800 በማሸሸሽ በወላይታ ዞን ሶዶ ዙርያ ወረዳ ገጠር መንደር ውስጥ በሚገኘው በ3ኛ ተከሳሽና ወንድማቸው ጋር በመመሳጠር በመኖርያ ቤቱ ውስጥ በአስከሬን ሳጥን አድርገው በመቅበር የተገኙ በመሆኑ በፈፀሙት ምንጩ ባልታወቀ ንብረትና ገንዘብ አካብቶ መገኘት እንዲሁም በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ የማቅረብና የመርዳት ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል ።

ተከሳሾቹ በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 18ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ክሱ ደርሷቸውና ተነቦላቸው የአምነት ክህደት ቃላቸውን ሲጠየቁ ድርጊቱን በፍፁም አልፈፀምንም ወንጀለኛም አይደለንም ሲሉ ክደው ተከራክረዋል ።

ሆኖም ተከሳሾች ዐቃቤ ህግ አጠናቅሮ ያቀረበባቸውን ዝርዝር የሰው እንዲሁም የሰነድ ማስረጃዎች መከላከልና ማስተባበል ባለመቻላቸው የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል ።

በዚህም መሰረት 1ኛ ተከሳሽ በ4 ዓመት ፅኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር߹ 2ኛ ተከሳሽ በ2 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራትና በ500 ብር 3ኛ ተከሳሽ ደግሞ በ2 ዓመት ፅኑ እስራትና በ300 ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ሲወሰን 1 ሚሊየን 425 ሺህ ብር የሚያወጣው መኖርያ ቤትና በአስከሬን ሳጥን ተቀብሮ የተገኘው 1 ሚሊየን 388 ሺህ 8 መቶ ብር መንጩ ሳይታወቅ የካበተ የሙስና ወንጀል ፍሬ ሆኖ በመገኘቱ በመንግስት አንዲወረስ ተደርጓል ።

07/04/2022
29/03/2022

የኢፌዲሪ ወንጀል ህግ አንቀፅ 555፣ 556 እና 560 ተፈፃሚ ስለሚሆኑበት አግባብ

አከራካሪዉ ጉዳይ፡- ከፊሎቹ ባለሞያዎች የእጅ እልፊት ወንጀል የሚፈፀመዉ በእጅ ብቻ ነዉ ብለዉ ሲያምኑ ሌሎቹ ደግሞ የተፈፀዉ የወንጀል ድርጊት የሚለየዉ ከተገኘዉ ወይም ለማስገኘት ከታሰነዉ የወንጀል ዉጤት ላይ በመመርኮዝ ነዉ ብለዉ ያምናሉ፡፡



የወንጀል ድንጋጌዎቹን በአግባቡ በስራ ላይ ለማዋልና በተግባር የሚስተዋሉ የዉሳኔ ልዩነቶች ለመቅረፍ ባለሞያዉ ዉሳኔዎችን በሚሰጥበት ወቅት የሚከተሉትን ነገሮች ከግምት ወስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡



የአንቀፆቹ ይዘት በንፅፅርና በጥልቀት በማየት ለመረዳት እንደሚቻለዉ ሶስቱንም የህግ ድንጋጌዎች የሚለያዩት የደረሰዉን የጉዳት መጠን መሰረት በማድረግ ብቻ ነዉ፡፡ ይህም ሲባል አንድ ግለሰብ በሌላ ሰዉ አካል ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ግለሰቡ ሊከሰስ የሚገባዉ ከሶስቱ የወንጀል ህግ ድንጋጌዎች በየትኛዉ ነዉ የሚለዉ ጥያቄ የሚመለሰዉ የጉዳቱን መጠን መሰረት በማድግ ብቻ ነዉ፡፡ የአንቀፆቹን ይዘት በአግባቡ ለመረዳት የሶስቱንም የወንጀል ህግ ድንጋጌዎች ይዘት ስንመለከት

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 555 መሰረት ከባድ አካል ጉዳት ተፈፀመ የሚባለዉ “የተጎጂዉን ሕይወት በሚያሰጋ ወይም በሰዉነቱም ሆነ በአዕምሮዉ ላይ ለዘወትር ጠንቅ በሚያተርፊ ሁኔታ ጉዳት ካደረሰ ወይም የሌላ ሰዉን አካል ወይም አስፈላጊ ከሆኑት ብልቶቹ ወይም ከህዋሳቶቹ አንዱን የጎደለ ፣ እንዳያገለግሉ ያደረገ ወይም በሚሳሰቅቅና ጉልህ ሆኖ በሚታይ ሁኔታ መልኩን ያበላሸ ወይም በማናቸዉም ሌላ መንገድ ከባድ የሆነ ጉዳትን ያስከተለ እንደሆነ ነዉ” በማለት ሲደነገግ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 556 ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ወንጀል ማለት

“………….በአንቀፅ 555 ከተመለከቱት ሁኔታዎች ዉጪ በሰዉ አካል ወይም ጤና ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ነዉ፡፡” በማለት ይደነግጋል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 560 መሰረት የእጅ እልፊት ተፈፀመ የሚባለዉ ደግሞ

“…..የአካል ጉዳትን ወይም የጤና ጉድለትን ሳያደርስ በሌላ ሰዉ ላይ የእጅ እልፊት ወይም የመጋፋት ወንጀል የፈፀመ እንደሆነ ነዉ፡፡” በማለት የደነገገ ሲሆን አንቀፁ አክሎም “ሰንበሮች፣ የደም መቋጠር ምልክቶች ወይም በቶሎ የሚያልፍ ህመም ወይም ሥቃይ እንደ አካል ጉዳት ወይም እንደ ጤና ጉድለት አይቆጠሩም” በማለት ይደነግጋል፡፡

ከላይ የተገለፁት የወንጀል ድንጋጌዎች የወንጀል ድርጊቱን ሲደነግጉ ጉዳቱን ለማድረስ አገልግሎት ላይ የዋለዉ መሳሪያ ከግምት ዉስጥ ያላስገቡ ቢሆንም ብዙ ግዜ የጉዳቱን መጠን ወደጎን በመተዉ ጉዳቱ የደረሰበትን መሳሪያ ብቻ ከግምት ዉስጥ በማስገባት ክስ ሲመሰርት ይታያል ነገር ግን ሶስቱም የህግ ድንጋጌዎች ከ 556(2) ዉጪ ያሉት የተመሰረቱት በደረሰዉ የጉዳት መጠን እንጂ ጉዳቱን ለማድርስ በተጠቀሙት የመሳሪያ አይነት ላይ አይደለም፡፡ በተለይ ደግሞ የወ/ህ/ቁ 560 ንዑስ አንቀፅ 1 ሶስተኛዉ ዓ.ነገር ላይ

’’ ቀላል የሆኑ ሰንበሮች፣የደም መቋጠር ምልከቶች፣ወይም በቶሎ የሚያልፍ ህመም ወይም ስቃይ እንደ አካል ጉዳት ወይም የጤና ጉድለት አይቆጠሩም”

የሚለዉን አገላፅ የእጅ እልፊት ወንጀል በእጅ ብቻ ሳይሆን በመሳሪያም ሊፈፀም እንደሚችል ለመረዳት ይቻላል፡፡ በሌላ አገላለፅ ጉዳቱን ለማድረስ የተጠቀመዉ መሳሪያ ምንም ይሁን ምንም ድርጊቱ ያስከተለዉ ጉዳት ቀላል የሆኑ ሰንበሮች፣የደም መቋጠር ምልከቶች፣ወይም በቶሎ የሚያልፍ ህመም ወይም ስቃይ እንደሆነ በእጅ እልፊት ስር ሊመደብ እንደሚገባ ለመረዳት ይቻላል፡፡

ሌላዉ ብዙዎች የሚያነሱት መከራከሪያ የወ/ህ/ቁ 560 ርዕሱ የእጅ እልፊት ማለቱ በራሱ ድርጊቱ መፈፀም ያለበት በእጅ መሆኑን ያመለክታል የሚል ቢሆንም ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ ቀላል የሆኑ ሰንበሮች፣የደም መቋጠር ምልከቶች፣ወይም በቶሎ የሚያልፍ የህመም ወይም ስቃይ እንደ አካል ጉዳት ወይም የጤና ጉድለት አይቆጠሩም ማለቱ የእጅ አልፊት የሚለዉ የድንጋጌዉ ርዕስ የሚያደርሰዉ በቀላል የሚያልፍ ህመም መሆኑን እንጂ በእጅ ብቻ መፈፀም እንዳለበት አያመለክትም፡፡

የደረሰዉ የጉዳት መጠን ሳይሆን ጉዳት አድራሹ ለማድረስ ያሰበዉን የጉዳት መጠን አብሮ መመርመር አስፈላጊ ስለመሆኑ፡- ብዙ ግዜ የሚስተዋለዉ ችግር ተከሳሹ ሊያደርሰዉ የፈለገዉ ጉዳት ከነገሮች ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት ለመረዳትና በማስረጃ ለማስደገፍ እየተቻለ በደረሰዉ ጉዳት ላይ ብቻ በመመሰረት ዉሳኔዎችን መስጠት ሌላዉ የችግሩ መንስኤ ሊሆን ይችላል፡፡ ምንም እንኳን የደረሰዉ ጉዳት በእጅ እልፊት ወይም በቀላል አካል ጉዳት ስር የሚሸፈን ቢሆንም ከአጠቃላይ ነባራዊዉ ሁኔታ በመነሳት ማለትም፡ ተከሳሹ ወንጀሉን ለመፈፀም የተጠቀመዉ መሳሪያ ፣ የግል ተበዳዩ የሚገኝበት ሁኔታና የተከሳሹ ያለዉ ግንዛቤ ፣ ተበዳዩና ጉዳት አድራሹ ተነፃፃሪ ጉልበት ፣ የህክምና ምርመራ ዉጤት ፣ ከደረሰዉ በላይ ጉዳት ያልደረሰበት ምክንያት እና የመሳሰሉትን አከባቢያዊ ሁኔታዎችን በጋራ በመመዘን የተከሳሹ ድርጊት በታወቀ ወይም በተለመደ ሂደት (In the normal course of things) ሊያስገኝ የሚችለዉን ዉጤት ግምት ዉስጥ በማስገባት ተገቢ የሆነዉን ወሳኔ መስጠት ተገቢ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ክስ ሲመሰረት ተከሳሹ የተጠቀመው መሳሪያ ብቻ በመመርኮዝ ሳይሆን ከአጠቃላይ ነባሪ ሁኔታ በመነሳት የደረሰውን ወይም ሊያደርስ ያሰበውን ጉዳት ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል፡፡
ምንጭ:- 👉 የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በወንጀል ጉዳዮች የአተረጓጎም ልዩነት ያለባቸውን ድንጋጌዎች ላይ ወጥነት ያለው ትርጉም ለማምጣት እንዲቻል ከተዘጋጀ የሕግ ማብራሪያ ላይ የተወሰደ 🙌
የህጉ ክፍል ከስር ኮመንት ላይ ተያይዟል!!

27/03/2022
27/03/2022



1/

ለአንድ ሀገር የዋጋ ንረት መከሰት በዋነኝነት ሁለት ዓይነት ኢኮኖሚያዊ ገፊ ምክንያቶች ያሉ መሆናቸውን የስነ-ቁጠባ ባለሞያዎች ይገልፃሉ። እነዚህም ከፍላጎት መጨመር የመነጨ የዋጋ ንረት(demand push inflation) እና የማምረቻ ዋጋ መጨመር(cost push inflation) ናቸው። ከእነዚህ ምክንያቶች አንፃር ሲመዘን በሀገራችን የተከሰተው የዋጋ ንረት እዚህ ደረጃ ሊደርስ የሚያስችል ኢኮኖሚያዊ አመክንዮ የለውም ወደሚለው ድምዳሜም ይደርሳሉ ምሁራኑ።

ሀገራችን የምትከተለው የኢኮኖሚ ስርዓት የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ስርዓት ቢሆንም በየትኛውም ሀገር ቢሆን መንግስት ጣልቃ የማይገባበት የገበያ ኢኮኖሚ የለም። መጠኑ ይለያይ እንጂ ነፃ የገበያ ኢኮኖሚ የሚከተሉ የበለጸጉትም ሆኑ ታዳጊ ሀገራት የገበያ ጉድለት ሲያጋጥማቸው መንግስት ጣልቃ ገብቶ ጉድለቱን የሚሞላበት አሰራር አለ። ኢትዮጵያም ከዚህ ነባራዊ ሁኔታ ውጭ ልትሆን አትችልም።

በንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/06 በአንቀፅ 25 ሥር “አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የንግና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የዋጋ ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚገቡ መሰረታዊ የንግድ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ጥናት አድርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አቅርቦ በማስፈቀድ ዝርዝራቸውንና ዋጋቸውን በሕዝብ ማስታወቅያ ሊያሳውቅ ይችላል፡፡” በማለት ተደንግጓል፡፡ በመሆኑም የንግዱ ማሕበረሰብ ይህ አሰራር ያለ መሆኑን ተገንዝቦ በተለይም በእንደዚህ ዓይነት አስቸጋሪ ወቅት ሊተገበር የሚችል በመሆኑ ነቅቶ መከታተልና መተግበር ይጠበቅበታል፡፡ የንግድ ሚኒሰቴርም ለሸማቹ ሕብረተሰብ የራስ ምታት የሆኑትን ምርቶች የዋጋ ቁጥጥር እንዲደረግባቸው እየለየ ሕጉ ባስቀመጠለት ሥልጣንና ኃላፊነት መሰረት እንዲሰራበት ለመጠቆም እንወዳለን፡፡

በአሁኑ ሰዓት በርካታ ወገኖች ካላቸው ጥቂት ነገር ለተቸገረው በማካፈል ለወገን አለኝታነታቸውን በማስመስከር ላይ ይገኛሉ፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ወረርሽኙን እንደመልካም አጋጣሚ በመቁጠር በእጃቸው ላይ ያለን የግድ ዕቃ በሕገ-ወጥ መንገድ በመደበቅ ገበያው ላይ ሰው ሰራሽ ዕጥረት እንዲፈጠር በማድረግ ሸማቹ እንዳይረጋጋና አማራጭ እንዲያጣ ካደረጉ በኋላ ባሻቸው ዋጋ የሚሸጡ፤ በወቅቱ ወደገበያ ያቀረቡትን ዕቃም ቢሆን ተመሳጥረው ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ተመን በመተመን ተገቢ ያልሆነ ትርፍ የሚያጋብሱ ግልሰቦች አሉ፡፡

ነገር ግን ይህ በሀገር እና በወገን ላይ ከፍተኛ ጫና በሚያሳድር መልኩ የሚደረግ የዋጋ ማናር ተግባር ከሐይማኖቶች አስተምህሮም ሆነ ከሞራል አንፃር ብናየው በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለውና አስነዋሪ ድርጊት መሆኑ እርግጥ ነው፡፡ በመሆኑም ይህን ክፉ ጊዜ ተባብረንና ተደጋግፈን ማለፍ የሚገባን ሆኖ ሳለ በሀገርና በወገን ላይ ሌላ ተጨማሪ ችግር መፍጠር የአንድ መልካም ዜጋ መገለጫ አይደለምና በጥብቅ ልናስብበት ይገባል፡፡

2/ / መደበቅ

ዕቃን ማከማቸት እና መደበቅ ሰው ሰራሽ እጥረት በመፍጠር የገቢያ አለመረጋጋት እና የዋጋ ንረትን ከሚያስከትሉ ተግባራት መካከል የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል። በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች የዕቃውን በገበያ ላይ ያለውን ተፈላጊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የአቅርቦት ችግር በሌለበት ሁኔታ የአቅርቦት ችግር ያለ በማስመሰል በግለሰብ ወይም በቡድን ደረጃ ሊያከማቹ እና ሰው ሰራሽ እጥረት ፈጥረው በከፍተኛ ዋጋ የመሸጥ ተግባር ሲፈፅሙ ይስተዋላሉ። ይህ የንግዱ ማህበረሰብም ሆነ ሸማቹ ያለአግባብ የንግድ ዕቃን የማከማቸት ተግባር በዜጎች ላይ ወይም እንደ አጠቃላይ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰው ተፅእኖ በጣም ከባድ ነው።

በበንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ አንቀፅ 24 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት አንድ ነጋዴ ከመደበኛ የግብይት ስርዓት ውጭ ወይም ነጋዴ ያልሆነ ሰው ለግል ወይም ለቤተሰብ ፍጆታ ከሚውል መጠን በላይ በንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በገቢያ ላይ እጥረት ያለበት መሆኑ በወጣ የህዝብ ማስታወቂያ የተገለፀ የንግድ ዕቃን ማከማቸት ወይም መደበቅ ክልክል መሆኑ ተደንግጓል። ነገር ግን ከተገቢው የንግድ አሰራር ውጪ ማከማቸትም ሆነ መደበቅ የማይቻለው በገበያ ላይ ዕጥረት ያለበትን የንግድ ዕቃ ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም የንግድ ዕቃ መሆኑን የአዋጁን አንቀፅ 23(3) እና 24ን በጣምራ በማንበብ መገንዘብ ይቻላል፡፡

ይኼውም በአንቀፅ 23(3) ላይ “ሚኒስቴሩና ቢሮዎች በነጋዴዎች የሚፈፀም የንግድ ዕቃዎች ክምችት ወይም የመደበቅ ተግባር ላይ ቁጥጥር ያደርጋሉ” ተብሎ መደንገጉ ሲታይ የተጠቀሱት ተቋማት በሕገወጥ ነጋዴዎች የሚደረግን የምርት ማከማቸትና መደበቅ እየተቆጣጠሩ የንግድ ሥርዓቱን ሚዛን የማስጠበቅ ኃላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም የንግዱ ማሕበረሰብ ማንኛውንም ዓይነት የንግድ ዕቃ መደበቅ ወይም ማከማቸት ክልክል መሆኑን ተገንዝቦ እራሱን ከእንደዚህ ዓይነት ተግባር መቆጠብ ይጠበቅበታል፡፡

የማከማቸት እንዲሁም የመደበቅ ተግባራት ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን በተመለከተ የአዋጁ አንቀፅ 43 ንዑስ አንቀፅ 4 እና 5 ላይ የተቀመጡ ድንጋጋጌዎች የተከማቸውን እቃ እንዲሁም ማጓጓዣውን መውረስን ጨምሮ እስከ የሚደርስ ፅኑ እስራት እና የገንዘብ ቅጣቶችን አስቀምጠዋል።

“ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ይጠብቅ!”

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Galaqli Daqaarak Gaaroyse Kutbeh Buxa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Galaqli Daqaarak Gaaroyse Kutbeh Buxa:

Share