13/02/2026
ዋትስአፕ (WhatsApp) የፑቲን በትር አረፈበት
ሩሲያ ከቴሌግራም በመቀጠል በዋትስአፕ መተግበሪያ ላይ እገዳ መጣሏን አስታወቀች። የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ እንደገለጹት፣ እገዳው የተጣለው መተግበሪያው የሩሲያን ህጎች እና እሴቶች ለማክበር ፍቃደኛ ባለመሆኑ ነው።
የሩሲያ መንግስት ተጠቃሚዎች ዋትስአፕን ትተው በሀገር ውስጥ የበለፀገውን "ማክስ" (Maks) የተሰኘ መተግበሪያ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል።
ሩሲያ ከዚህ ቀደም በፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስ (X) ላይ እገዳ የጣለች ሲሆን፣ በቅርቡም በዩቲዩብ እና በአፕል ፌስታይም ላይ ተመሳሳይ ገደቦችን መጣል መጀመሯ ይታወሳል።
ዋትስአፕ በበኩሉ በሰጠው ምላሽ፣ 100 ሚሊዮን የሚጠጉ ሩሲያውያንን ደህንነቱ ከተጠበቀ የመገናኛ ዘዴ ማግለል "ኋላ ቀርነት ነው" ሲል ድርጊቱን ኮንኖታል። ተጠቃሚዎች ከባለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ እገዳዎችን ለመሻገር በቪፒኤን (VPN) ሲጠቀሙ ቢቆዩም፣ አሁን ግን ቁጥጥሩ መጠናከሩ ተገልጿል።
#ሩሲያ #ዋትስአፕ #ቴክኖሎጂ #እገዳ #ቴሌግራም #ዲጂታልሉዓላዊነት