Yimi Translation Office

Yimi Translation Office we translate

12/10/2021
01/12/2019

"ምነው ዝም ብላችሁ ብትኖሩ!
ይህ ጥበብ በሆነላችሁ ነበር። "
" If only you would keep quiet, it would be a sign of wisdom!"

12/08/2018
12/08/2018

“በሰው ልጅ ውስጥ በሚገኝ ውበት አምናለሁ”
ም.ፈቱላህ ጉለን
የአምላክ ትሁት አገልጋይ
ላቭ ኤንድ ቶለራንስ ከተሰኘው መጽሐፍ ተወስዶ የተተረጎመ
ትርጉም በይግረማቸው ዶያ

ጅግ የተከበራችሁ ቅዱሳን፤
ሶስት ሀይማኖቶች የተወለዱባት ቦታ እንደሆነች ከምትታወቅና አለምን ለመኖር አመቺ የሆነች ስፍራ የማድረግ ቅዱስ ተልዕኮን በተመለከተ ሙሉ እውቀት ካላቸው ሰዎች ምድር የከበረ ሰላምታችንን እናቀርባለን፡፡ በተጨማሪም ከልባችን የመነጨ ምስጋናን በስራ ከተወጠረ የጊዜ ሰሌዳችሁ በመቁረስ እዚህ ስለተገኛችሁ እናመሰግናለን፡፡ ዛሬ እዚህ የተገኘነው በቅዱስ ሊቀጳጳስ ፖል 11ኛ የተመሰረተው የፖንቲፊካል የሀይማኖቶች ወይይት ምክር ቤት (ፒሲአይዲ) ተቋም ተልዕኮን ቀጣይነት ለማሳካት ነው፡፡ ይህ ተልዕኮ ፍሬ አፍርቶ ለማየት እንመኛለን፡፡ ወደ እናንተ ስንመጣ ምንም እንኳን የተወሰነ ድፍረት ቢኖረንም በትህትና እና ይህንን ትልቅ ዋጋ ያለው ተግባር ስኬታማ ለማድረግ የምንችለውን አስተዋጽኦ እና ድጋፍ ለማቅረብ ነው፡፡
እስላም በተሳሳተ መንገድ ሰዎች የተገነዘቡት እምነት ሲሆን፤ በዚህም በአብዛኛው ተወቃሽ የሚደረጉ ሊሆኑ ችለዋል፡፡ በወቅቱ የሚደረግ ተገቢ ጥረት ይህንን የተሳሳተ ግንዛቤ ለመቀነስ ይረዳል፡፡ የሙስሊሙ አለም ለክፍለ ዘመናት የቆየውን ስለ እስላም ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ለማስወገድ እድል የሚፈጥር ውይይትን ክልቡ ይቀበላል፡፡
የሰው ልጅ ከጊዜ ወደ ጊዜ በሳይንስ ስም ሀይማኖትን እየካደ በሀይማኖት ስም ሳይንስን በመካድ ሁለት እርስ በእርስ የሚጋጩ አመለካከቶች እንዳሉ ይከራከራል፡፡ ሁሉም እውቀት ከአምላክ ሲሆን ሀይማኖትም ከአምላክ ነው፡፡ እንዴት ሁለቱ ነገሮች እርስ በእርሳቸው ሊጋጩ የችላሉ? በዚህ ረገድ በሀይማኖቶች መካከል በሚደረግ ውይይት በሰዎች ዘንድ ያለውን ግንዛቤ እና መቻቻል ለማሻሻል በጋራ የምናደርገው ጥረት ረጅም ርቀት ሊጓዝ ይችላል፡፡
በሀገራችን ውስጥ ከተለያዩ የክርስትና ቤተ እምነቶች ጋር በመሆን እስከ አሁን ድረስ ለተወሰነ ጊዜ ውይይት ስናደርግ ቆይተናል፡፡ እነዚህ አነስተኛ የሆኑ ጥረቶች ፍሬ አልባ እንዳልነበሩ በትህትና እንገልጻለን፡፡ አላማችን በሶስቱ ታላላቅ ሀይማኖቶች መካከል በመቻቻል እና በግንዛቤ አማካኝነት ወንድማማችነት መመስረት ነው፡፡ በመሆኑም በአንድ ላይ በመሆኑ እነዚህ በተሳሳተ አቅጣጫ የሚጓዙ ነፍሶች እና ተቺዎች እንደ ማገጃ በመሆን የስልጣኔዎች ግጭት የሚባለው ነገር እውነት ሆኖ ለማየት የሚሹ ሰዎችን ለመቋቋም ይቻላል፡፡
ባለፈው አመት በስልጣኔዎች መካከል በሚኖር ሰላም እና መቻቻል ዙሪያ ሲምፖዚየም ያዘጋጀን ሲሆን ይህ ሲምፖዚየም የታወቁ አለማቀፍ ምሁራኖች የታደሙበት ነው፡፡ በዚህ ጥረት ረገድ በተገኘው ስኬት በመበረታታት ይህንን ዝግጅት በድጋሚ ለማድረግ እንሞክራለን፡፡ በአሁኑ ወቅት በሶስቱ ታላላቅ ሀይማኖቶች መካከል ጠንካራ የሆነ ግንኙነት እና ትስስር ለመፍጠር የታለመ የሀይማኖቶች የእርስ በእርስ ውይይት ለማዘጋጅ በእንቅስቃሴ ላይ ስንሆን በዚህ ዝግጅት ላይ ቫቲካን ትገኛለች ተብሎ ተስፋ ተደርጓል፡፡
በሚስተር ዴሚረል የቀረበውን አገራችንን እንዲጎበኙ የሚጠይቅ ግብዣ እርስዎ ለመቀበል ፈቃደኛ ቢሆኑ እጅግ ከፍተኛ ክብርና ደስታ የሚሰማን ሲሆን፤ በዚህም መሰረት ቅዱስነትዎ ቱርክ ውስጥ የሚገኙ ቅዱስ ቦታዎችን ለማየት የሚችሉ ይሆናል፡፡ የአናቶሊያ ህዝብ እንግዳ ተቀባይነቱን ለማሳየት ይህንን እድል በታላቅ ጉጉት እየተጠባበቀ ሲሆን ደማቅ አቀባበል ሊያደርግልዎ ዝግጁ ነው፡፡ ከፍልስጤም መሪዎች ጋር በጉዳዩ ላይ ከተወያየን በኋላ የተቀደሰችዋ ከተማ አለምዓቀፍ ቀጠና መሆኗን፤ ክርስቲያኖች፣ ሙስሊሞ እና አይሁዶች ምንም ዓይነት ቪዛ ሳያስፈልጋቸው በነፃነት የሀይማኖት ጉዞ ሊያደርጉባት የሚችሉባት ቦታ እንደሆነች ሊያረጋግጥ የሚችል ጉልህ እርምጃ ተደርጎ የሚወሰደውን በጋራ እየሩሳሌምን ለመጎብኘት የሚያስችለን ግብዣ አግኝተናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ የዓለም ሀገራት በሚገኙ ዋና ከተማዎች ውስጥ በየተራ የሚደረጉ ተከታታይ ኮንፍረንሶችን ለማካሄድ የምንፈልግ ሲሆን፤ የመጀመሪያው ኮንፍረንስ በሶስቱ ታላለቅ እምነቶች መሪዎች ትብብር ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ውስጥ ይደረጋል፡፡ ሁለተኛው ኮንፍረንስ የሚደረግበት ጊዜ ደግሞ ከኢየሱስ ክርስቶስ 2000ኛ የልደት በዓል ጋር የሚገጥም በመሆኑ ዓይነተኛ ሊያደርገው ይችላል፡፡
የተማሪዎች ልውውጥ ፕሮግራም እንዲሁ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ አማኝ የሆኑ ወጣት ሰዎች በአንድ ላይ ለመማር መቻላቸው እርስ በእርሳቸው የሚኖራቸውን ቅርበት ያጠናክረዋል፡፡ በዚህ በተማሪዎች ልውውጥ ማዕቀፍ ውስጥ የስነ-መለኮት ኮሌጅ ኡርፋ ግዛት ውስጥ- የሶስቱ ታላላቅ ሀይማኖቶች አባት ተደርጎ የሚገለጸው ነብዩ አብርሃም የተወለደባት ቦታ፤ ሀራን ውስጥ የሚመሰረት ይሆናል፡፡ ይህ ሀራን ዩኒቨርስቲ ውስጥ የሚገኙ ፕሮግራሞችን በማስፋፋት ወይም የሶስቱንም እምነቶች ፍላጎት የሚያረካ ሁሉን አቀፍ ስርዓተ ትምህርት የያዘ እራሱን የቻለ ዩኒቨርስቲ በማቋቋም ሊሳካ ይችላል፡፡ ቀጥሎ የተገለጸው ከሀገራት ፖሊሲዎች የተነሳ በሚገጥሙ እንቅፋቶች ምክንያት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡
የተጠቀሱት መርሀ-ግብሮች ምንአልባት ተጨባጭ ባልሆነ ጉጉት የተሞሉ ቢመስሉም ነገር ግን ሊሳኩ የሚችሉ ናቸው፡፡ በዓለም ላይ ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ፡ ለሁኔታዎች ራሳቸውን የሚያስገዙና የማያስገዙ፡፡ ራሳቸውን የሚያስገዙት ሰዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ከሚፈጠረው ነገር ጋር ሁሉ ራሳቸውን ለማጣጣም ይሞክራሉ፡፡ የማያስገዙት ሰዎች በሌላ በኩል ማህበረሰቡን ተደጋጋሚ በሆኑ እሴቶችና ተቀባይነት ባላቸው አዲስ ግንባታዎች ሊያስተካክሉ ይሞክራሉ፡፡ በመሆኑም ሁሉም በማህበረሰብ ውስጥ የሚኖሩ እድገቶች ራሳቸውን ለተለመዱ ነገሮች ማስገዛት በማይፈልጉ ሰዎች ምክንያት የሚገኙ ናቸው፡፡ ስለነዚህ ሰዎች አላህ ይመስገን፡፡

14/05/2017
14/05/2017

Read Qua Vadis in Amharic

Address

Addis Ababa Stadium
Addis Ababa
26670/1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yimi Translation Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share