Mass Photo & Video

Mass Photo & Video Get quality pictures

Book Your Photoshoot Now!!Call:- +251 911173246                     +251 910886339            +251 919182732Addis Ababa,...
17/06/2022

Book Your Photoshoot Now!!
Call:- +251 911173246
+251 910886339
+251 919182732
Addis Ababa, Ethiopia.

07/06/2022
ቃር (Heartburn)()ቃር ያስቸግርዎታል? ቃር የምንለው ወይንም በህክምና አጠራሩ ሃርትበርን (Heartburn) በመባል የሚታወቀው የህመም አይነት ሲሆን አብዛኞችን የሚያጠቃ እና እጅግ የ...
19/09/2016

ቃር (Heartburn)
()
ቃር ያስቸግርዎታል? ቃር የምንለው ወይንም በህክምና አጠራሩ ሃርትበርን (Heartburn) በመባል የሚታወቀው የህመም አይነት ሲሆን አብዛኞችን የሚያጠቃ እና እጅግ የተለመደም ችግር ነው።
በደረት አካባቢ የማቃጠል ስሜት መሰማት በአብዛኛው ከምግብ በኃላ እና እንቅልፍ ስንተኛ የሚብስ ነው። ይህም የሚከሰተው የጨጓራ ውስጥ አሲድ ወደ ላይኛው የምግብ አስተላላፊ ቱቦ (esophagus) ሲገባ ነው።
✔ ለቃር ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች፦
* ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ
* ሽንኩርት
* ሲትረስ ያላቸው ምግቦች
* ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች
* ቸኮሌት
* የአልኮል መጠጦችን መውሰድ
* ካፊን ያላቸውን መጠጦች መውሰድ
* ከጥጋብ በላይ መመገብ
* ከመጠን ያለፈ ውፍረት
* ነፍሰጡርነት ናቸው።
✔ ሃኪምዎን ማማከር የሚገባው መቼ ነው?
ቃር በአብዛኛው አመጋገብን በማስተካከል እና ቀስቃሽ ሁኔታዎችን በማስወገድ የሚድን ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የደረት ማቃጠል፣ ውጋት፣መጨምደድ ስሜት እና ወደ ትከሻ የሚሰራጭ የህመም ስሜት ከትንፋሽ ማጠር ጋር ከተከሰተ በአፋጣኝ ሃኪም ማማከር ተገቢ ነው ምክንያቱም የድንገተኛ ልብ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ነው።
✔ ከዚህ በተጨማሪ
* በሳምንት ውስጥ ከሁለት ጊዜ በላይ የሚያቅርዎ ከሆነ
* ለመዋጥ የሚችገሩ ከሆነ
* ማቅለሽለሽና ማስመለስ ካልዎት
* የምግብ ፍላጎት በማጣት ወይንም ለመመገብ በመቸገር ምክንያት የሰውነት ክብደትዎ ከቀነሰ ሃኪምዎን ማማከር ይኖርብዎታል።
✔ ቃርን ለማስታገስ መደረግ ያለባቸው የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች
* የሰውነት ክብደትዎን ማስተካከል
* ቃርን የሚይያስነሱ ምግቦችን አለመመገብ
* የአልኮል መጠጦችን አለመውሰድ
* ሲጋራን አለማጤስ
* በመኝታ ጊዜ ጭንቅላትዎን ከፍ ባለ ትራስ ላይ ማሳረፍ ናቸው።
መልካም ጤንነት!!

በተደጋጋሚ ሽንትዎ እየመጣ ያስቸግርዎታል?(በዳንኤል አማረ ©ኢትዮጤና)በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት ማለት ጤናማ ከሚባለው ሽንት የመሽናት ጊዜ በበለጠ የመሽናት ፍላጎትን ሲኖርዎ/ሲለማመዱ ነው፡፡ ...
17/09/2016

በተደጋጋሚ ሽንትዎ እየመጣ ያስቸግርዎታል?
(በዳንኤል አማረ ©ኢትዮጤና)
በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት ማለት ጤናማ ከሚባለው ሽንት የመሽናት ጊዜ በበለጠ የመሽናት ፍላጎትን ሲኖርዎ/ሲለማመዱ ነው፡፡ ይህ ልምድ በቀን ወይም በማታ(ሌሊት) ሊሆን ይችላል አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ማታ ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡ በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት ሥራዎን፣ እንቅልፍዎንና አጠቃላይ ሠላምዎን ሊያስተጓጉል ይችላል፡፡ ስለዚህ የዚህን ችግር መነሻና ህክምናውን ማወቅ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡
✔የዚህ ችግር መነሻ ምንድን ነው?
• የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን (Urinary Tract Infection)
በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ በሆድና ዳሌ አካባቢ ህመም እንዲሁም ትኩሳት ካለብዎ በዚህ ኢንፌክሽን መጠትዎን አመላካች ናቸው፡፡
• የስኳር በሽታ (Diabetes)
በተደጋጋሚ የመሽናት ፍላጎት ካለዎትና በጣም በርከት ያለ ሽንት የሚሸኑ ከሆነ በዓይነት አንድ ወይም ሁለት የስኳር በሽታ ተይዘው ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙ ሽንት የሚሸኑበት ምክንያት ሰውነትዎ ትርፍ ግሉኮስን ለማስወገድ ስለሚሞክር ነው፡፡
• እርግዝና (Pregnancy)
በእርግዝና ወቅት ሽንት ቤትን በተደጋጋሚ መጎብኝት ይስተዋላል፡፡ ይህ ሁኔታ በደንብ የሚስተዋለው ደግሞ ጽንሱ በደንብ እየገፋ ይመጣና የሽንት ፌኛን ስለሚጫነው ነው፡፡
• የፕሮስቴት ችግር (Prostate Problem)
ዩሬትራ ሽንትን ከሰውነታችን የሚያስወግድ ቱቦ ነው፡፡ ነገር ግን ፕሮስቴት በመጠን ይተልቅና ይህን ቱቦ ሊዘጋው ይችላል፡፡ ፕሮስቴት ዩሬትራን ይጫነዋል በተጨማሪም የሽንት ፌኛ ግድግዳን እንዲቆጣ ያደርገዋል ይህም የሽንት ፊኛ እንዲጨማደድ ስለሚያደርገው መያዝ ያለበትን ያክል ሽንት እንዳይዝ ስለሚያደርገው ለመሽናት እንቻኮላለን።
• ኢንተርስቲሺያል ሲስታይቲስ (Interstitial Cystitis)
ይህ ችግር በምን እንደሚከሰት ግልጽ አይደለም ነገር ግን በሽንት ፌኛና ዳሌ አካባቢ ህመም ያስከትላል፡፡ ሽንት ለመሽናት ከመቻኮል በተጨማሪ ሌሎች ምልክቶችን ሊያዩ ይችላሉ፡፡
• ዲውሪቲክ መጠቀም (Diuretic Use)
ከፍተኛ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር የሚወስዷቸው ዲውሪቲክስ መድሃኒቶች በተደጋጋሚ ሽንት እንዲሸኑ ሊደርግዎት ይችላሉ፡፡ እነዚህ መድሃኒቶች ብዙ ውሃ ከኩላሊትና ከሰውነትዎ እንዲወገድ ይረዱናል፡፡
• የነርቭ ጉዳት (Nerve Problems)
ወደ ሽንት ፊኛ የሚያመሩ ማንኛውም የነርቭ ጉዳት ሽንት በተደጋጋሚ እንዲሸኑ እንዲሁም ሽንትዎ በድንገት መቶ እንዲቻኮሉ ያስገድድዎታል፡፡
መልካም ጤንነት!!

ኤም.አር.አይ /MRI/ እና ሲቲ ስካን የህክምና ምርመራዎችን ለማድረግ አቅም ለሌላቸው ጳጉሜ ወር ላይ ነፃ ህክምና ይሰጣል።ይህን ያለው ውዳሴ ዳያግኖስቲክ ማዕከል ሲሆን ላለፉት 6 ዓመታት “...
05/09/2016

ኤም.አር.አይ /MRI/ እና ሲቲ ስካን የህክምና ምርመራዎችን ለማድረግ አቅም ለሌላቸው ጳጉሜ ወር ላይ ነፃ ህክምና ይሰጣል።
ይህን ያለው ውዳሴ ዳያግኖስቲክ ማዕከል ሲሆን ላለፉት 6 ዓመታት “ጳጉሜን ለጤና” በሚል መርህ የዳያግኖስቲክ ህክምና አገልግሎትን በነፃ ሲሰጥ ቆይቷል፤ ዘንድሮም ለ7ኛ ጊዜ ይህን የነፃ አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቻለው ብሏል፡፡
ዘንድሮ ከጳጉሜ 1-5 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ ምርመራ እንዲያደርጉ ከመንግስት ሆስፒታሎች የሃኪም የትዕዛዝ ወረቀት የተሰጣቸውና ህክምናው የሚጠይቀውን ገንዘብ ለመክፈል አቅም የሌላቸው ህሙማን አገልግሎቱን ያገኛሉም ተብሏል፡፡
የውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዳዊት ሃይሉ እንደተናገሩት ማዕከሉ ከመንግስት ሆስፒታሎች ጋር በመተባበር ይህን ነፃ የምርመራ አገልግሎት ይሰጣል፤ ዘንድሮም የሲቲ ስካን እና የኤም.አር.አይ /MRI/ የምርመራ አገልግሎትን በነፃ ለመስጠት ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡
ባለፉት 6 ዓመታት ከ5 ሺህ በላይ አቅም የሌላቸው ዜጎች የሲቲ ስካን እና ኤም.አር.አይ /MRI/ ምርመራን በነፃ ከውዳሴ ዳያግኖስቲክ ማዕከል ያገኙ ሲሆን ዘንድሮ ከ800-1000 ለሚደርሱ ሰዎች ህክምናውን ለመስጠት ታስቧል፡፡
መልካም ጤንነት!!
ምንጭ፦ ዶክተር አለ።
Share Share Share

የሆድ ድርቀት/Constipation(በዳንኤል አማረ ©ኢትዮጤና)የሆድ ድርቀት የአንጀት ጡንቻዎች የእንቅስቃሴ ድግግሞሽ በቁጥር ሲያንስ ወይም ዓይነ ምድራችንን ለማስወገድ/ለማስወጣት መቸገር ሲሆ...
30/08/2016

የሆድ ድርቀት/Constipation
(በዳንኤል አማረ ©ኢትዮጤና)
የሆድ ድርቀት የአንጀት ጡንቻዎች የእንቅስቃሴ ድግግሞሽ በቁጥር ሲያንስ ወይም ዓይነ ምድራችንን ለማስወገድ/ለማስወጣት መቸገር ሲሆን ይህ ሁኔታ ለጥቂት ሳምንት ወይም ከዚያ በላይ ቆይታ ሲኖረው ነው፡፡ በዚህ እንቅስቃሴ መሃል ያለው የጊዜ ልዩነት ከሰዎች ሰዎች ይለያያል፡፡
አንዳንድ ሰዎች በቀን ሶስት ጊዜ እንቅስቃሴ ሲኖራቸው ሌሎች ደግሞ በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ይኖራቸዋል፡፡ ያለምንም የአንጀት ጡንቻዎች እንቅስቃሴ ሶስት ቀን ከሆነ በጣም እረጂምና አደገኛ ሲሆን ከሶስት ቀን በኋላ ዓይነ ምድራችን ስለሚደርቅ ወይም ጠንካራ ስለሚሆን ለማስወገድ/ለማስወጣት አስቸጋሪ ይሆናል፡፡
የሆድ ድርቀትን ጠቅለል ባለ ሁኔታ ለመግለጽ ያክል የአንጀት ጡንቻዎች እንቅስቃሴ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከሶስት ጊዜ በታች/ያነሰ ሲሆን ነው፡፡
በማንኛውም ሰው ላይ የሆድ ድርቀት በአጋጣሚዎች የሚከሰት ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ከባድ የሆድ ድርቀት ያጋጥማቸዋል ይህም የቀን ከቀን ስራቸውን ያስተጓጉላል፡፡
✔የሆድ ድርቀት መነሻዎች
የሆድ ድርቀት በአብዛኛው ጊዜ የሚከሰተው ዓይነ ምድራቸን በምግብ መፍጨት ስርዓት ውስጥ ሲያልፍ በጣም በሚዘገይበት ጊዜ ይፈጠራል ይህም ዓይነ ምድራችን ጠንካራ እና ደረቅ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ የሚከተሉት የሆድ
ድርቀት መነሻዎች ናቸው፦
• በቂ ውሃ አለመጠጣት
• በምግብ ገበታዎ ውስጥ በቂ ያልሆነ ፋይበር አለመኖር
• መደበኛ የምግብ ሠዓት መስተጓጎል(በጉዞ ወቅት)
• በቂ የሆነ እንቅስቃሴ አለማድረግ
• ከፍተኛ መጠን ያለው የወተት ተዋጽዎ መመገብ
• ጭንቀት
• ሃይፖታይሮይዲዝም
• ከመጠን በላይ የዓይነ ምድር ማለስለሻ() መጠቀም
• የአንጀት ወይም ፊንጢጣ መደፈን/መዘጋት
• በአንጀት እና ፊንጢጣ አካባቢ ያሉ ነርቮች ችግር/በሸታ
ፓርኪንሰንስ በሽታ የጀርባ አጥንት ጉዳት ስትሮክ
• ዓይነ ምድር ለማስወጣት መቸገር የዳሌ ጡንቻዎች በተቀናጀ ሁኔታ መጨማደድና መዝናት አለመቻል ደካማ የዳሌ ጡንቻዎች
• የሰውነታችን ሆርሞኖችን የሚጎዱ ሁኔታዎች
የስኳር በሽታ እርግዝና የታይሮይድ ሆርሞን ችግር
• የአንጀት እና ፊንጢጣ ካንሰር
✔የሆድ ድርቀት ምልክቶች
የሆድ ድርቀት ምልክቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦
• የአንጀት ጡንቻዎች እንቅስቃሴ ድግግሞሽ ማነስ
• ደረቅ እና ጠንካራ ዓይነ ምድር
• በመጠን ትንሽ የሆነ ዓይነ ምድር
• የሆድ መነፋት ወይም የሆድ ህመም
• ህመም
• ማስታወክ/ማስመለስ
• በሳምንት ከሶስት ጊዜ በታች መጸዳዳት
• በምንጸዳዳበት ጊዜ ፊንጢጣችንን ከዓይነ ምድር ባዶ አለማድረግ ወይም ጨርሰን አለመጸዳዳት
• ስንጸዳዳ ዓይነ ምድራችንን ለማውጣት እርዳታ መፈለግ ለምሳሌ፦ ዓይነ ምድርን ከፊንጢጣ ለማውጣት ጣትን መጠቀም፡፡
✔የሆድ ድርቀት እንዴት ሊታከም ይችላል?
አብዛኛዎቹ ሰዎች ከባድ የሆነ ምርመራ አያስፈልጋቸውም በጣም ጥቂት የሚባሉት ደግሞ ከባድ የህመም ችግር ስለሚያጋጥማቸው ህክምና ያስፈልጋቸዋል፡፡ ከሁለት ሳምንት በላ የቆየ የሆድ ድርቀት ካጋጠምዎት የህክምና ባለሙያ ማማከር ያስፈልግዎታል፡፡ ይህ የሆድ ድርቀት በአንጀት ካንሰር ከተከሰተ ቅድሚያ ማወቅና መታከም በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
የሆድ ድርቀትን መነሻ ምክንያት ለማወቅ የሚደረጉ ምርመራዎች የሚከተሉትን ያካትታል፦
• የደም ምርመራ፦ የሆርሞኖች አለመመጣጠን የሚጠረጠር ከሆነ
• የባርየም(Barium) ጥናት፦ የአንጀት መዘጋት የሚጠረጠር ከሆነ
• ኮሎኖስኮፒ፦ የአንጀት መዘጋት/መታገድን ለማወቅ ይጠቅማሉ፡፡
✔የሆድ ድርቀት ካጋጠመኝ ምን ማድረግ አለብኝ?
የሆድ ድርቀት ካጋጠምዎት የሚከተሉትን ይሞክሩ፦
• ከሁለት እስከ አራት ተጨማሪ ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ
• ሞቅ ያለ ፈሳሽ ይጠቀሙ በተለይ ጠዋት ላይ
• የምግብ ገበታዎ ላይ ፍራፍሬና አትክልቶች ይጨምሩ
• የጥራጥሬ ውጤቶችን ይመገቡ
• አስፈላጊ ከሆነ በጣም በጥቂቱ የዓይነ ምድር ማለስለሻዎች ይጠቀሙ
ለምሳሌ፦ ሚልክ ኦፍ ማግኒዚያ
• ሃኪምዎን ሳያማክሩ የዓይነ ምድር ማለስለሻ ወይም ላክሳቲቭ ከሁለት ሳምንት በላይ አይጠቀሙ ምክንያቱም ከመጠን በላይ ላክሳቲቭ መጠቀም ምልክቶቹን ያባብሳቸዋል፡፡
✔የሆድ ድርቀትን እንዴት መከላከል ይቻላል?
የሆድ ድርቀትን ለመከላከል የተለያዩ መንገዶች አሉ ከነዚህም መካከል፦
• የተመጣጠኑ ምግቦችን በተለይ ፋይበር በብዛት ያላቸውን ይመገቡ፡፡ ከፍተኛ የፋይበር ይዘት ያላቸው ምግቦች፦ ፍራፍሬዎች፣ አትክልቶች፣ ለጊዩም፣ ዳቦና ጥራጥሬዎችን ይመገቡ፡፡ ፋይበር እና ውሃ አንጀታችን ዓይነ ምድርን በቀላሉ እንዲያሳልፍ ያደርገዋል፡፡
• ከአንድ ሊትር ተኩል እስከ ሁለት ሊትር ተኩል ውሃ እና ሌሎች ፈሳሾችን በቀን መጠጣት ጠቃሚ ነው(ውሃ መጠጣት በሌሎች የህክምና ችግር እስካልተከለከልን ድረስ)፡፡
• ካፌን የያዙ/ያላቸው ፈሳሾች ለምሳሌ፦ ቡና እና ለስላሳ መጠጦች የሰውነት ፈሳሽን የማድረቅ ባህሪ ስላላቸው አጠቃቀማችንን መቀነስ አለብን፡፡ አንዳንድ ሰዎች ወተት ሲጠጡ ስለሚያባብስባቸው ቢቀንሱ ይመረጣል፡፡
• በየጊዜው ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ያድርጉ፡፡
✔ስለ ሆድ ድርቀት ማስጠንቀቂያ
የሚከተሉት ነገሮች የሚከሰቱ ከሆነ ወደ ህክምና መስጫ ተቋም ይሂድ፦
• የሆድ ድርቀት ለእርስዎ አዲስ ችግር ከሆነ
• በዓይነ ምድርዎ ውስጥ ደም ካለ
• የክብደት መቀነስ ካለ
• የአንጀት ጡንቻዎች ህመም ካለ
• የሆድ ድርቀት ችግርዎ ከሁለት ሳምንት በላይ ከሆነ፡፡
መልካም ጤንነት!!

28/07/2016

ሄፓታይትስ ሲ የጉበት ህመምን ከሚያመጡ የጉበት ቫይረስ አይነቶች አንዱ ሲሆን በጉበት ላይ በአጭር ጊዜ ምልክት የሚያሳይ ወይም ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የጉበት ላይ እንፌክሽን እንዲከሰት ያደርጋል፡፡

Ke 6 amet behuwala
24/06/2016

Ke 6 amet behuwala

18/06/2016

Address

Kality
Addis Ababa

Telephone

+251911173246

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mass Photo & Video posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share