Amen Media & Communication

Amen Media & Communication ለፈጣን መረጃ Media & Communication

 የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር ውሃ ሙሌት ተጠናቋል።Photo Credit : ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ
19/07/2021



የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር ውሃ ሙሌት ተጠናቋል።

Photo Credit : ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ

እንኳን ደስ አለን!ኢትዮጵያዊ 2ኛዉን የውሃ ሙሌት መጀመርዋን ለግብጽ በይፋ አስታወቀች።
06/07/2021

እንኳን ደስ አለን!
ኢትዮጵያዊ 2ኛዉን የውሃ ሙሌት መጀመርዋን ለግብጽ በይፋ አስታወቀች።

የብዙሀን እናትክብርት ዶክተር አበበች ጎበናነብስ ይማር!
04/07/2021

የብዙሀን እናት
ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና
ነብስ ይማር!

03/11/2020
ዜና እረፍት፦ብላክ ፓንተር በተሰኘው ፊልም አለም አቀፍ ተቀባይነትን ያገኘው አፍሪካዊ አሜሪካዊ ተዋናይ ቻድዊክ ቦስማን በአንጀት ካንሰር ህመም ሳብያ በ43 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።
29/08/2020

ዜና እረፍት፦

ብላክ ፓንተር በተሰኘው ፊልም አለም አቀፍ ተቀባይነትን ያገኘው አፍሪካዊ አሜሪካዊ ተዋናይ ቻድዊክ ቦስማን በአንጀት ካንሰር ህመም ሳብያ በ43 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

መልዕክት ከአብነት የህክምና ማዕከል ሜድካል ዳይሬክተርዶ/ር ገ/መስቀልበአሁን ጊዜ እየተስፋፋ የሚገኘው የ ኮረና ኀቫይረስ እጅግ እያሳሰበን ነው።የህብረተሰቡ የጥንቃቄ ጉድለት እና ችላ ባይነት...
04/08/2020

መልዕክት ከአብነት የህክምና ማዕከል ሜድካል ዳይሬክተር
ዶ/ር ገ/መስቀል
በአሁን ጊዜ እየተስፋፋ የሚገኘው የ ኮረና ኀቫይረስ እጅግ እያሳሰበን ነው።
የህብረተሰቡ የጥንቃቄ ጉድለት እና ችላ ባይነት የበለጠ እያሳሰበን እና
እያስጨነቀን ነው።የጤና ባለሙያዎች በበኩላቸው እየከፈለት ያለው የሙያ
ግዴታ ህይወታቸውን የሚያስከፍል እየሆነ ነዉ ።
እባካችሁ ወገኖች ከበፊቱ የበለጠ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው አሁን በመሆኑ
*ሁል ጊዜ እና በየትኛውም ቦታ ማስክ እናድርግ
*ሰዎችን የሚሰበስብ ጉዳዮችን እናከናውን
*በጣም አስፈላጊ ካልሆነ በቀር እቤት እንሁን
*በምናስነጥስ እና በምናስል ሰአት በክንዳችን እንዲሸፈን
*ጤንነት ካልተሰማን በቶሎ ሀኪም እናማክር
*የህክምና ክትትል የነበራችሁ ጥንቃቄ በማድረግ ክትተልዎን ይቀጥሉ
*በጤና ባለሙያዎች የሚሰጠውን የአመጋገብ ፣የንጽህና አጠበበቅ ይተግበር
በጋራ በመሆን አገራችንን እንታደግ
የእያንዳንዳችን አስተዋጽኦ ሁላችንንም ይረዳናል
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ ።

ሁነኛው የቅርስ ባለሙያ አርኪዮሎጂስት ኃይሉ ዘለቀ (1970-2012)ዕረፍታቸውን ተከትሎ ይህን ህያው ምስክርነት የሰጡት ደግሞ የቀድሞው የባለሥልጣኑ የአርኪዮሎጂ ባለሙያና በዩኔስኮም የሠሩት ...
02/08/2020

ሁነኛው የቅርስ ባለሙያ አርኪዮሎጂስት ኃይሉ ዘለቀ (1970-2012)

ዕረፍታቸውን ተከትሎ ይህን ህያው ምስክርነት የሰጡት ደግሞ የቀድሞው የባለሥልጣኑ የአርኪዮሎጂ ባለሙያና በዩኔስኮም የሠሩት አቶ ካሳሁን አባተ ናቸው፡፡

አቶ ኃይሉ በተለይም በኢትዮጵያ ባሉና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ባገኙ ቅርሶች ላይ የሚከናወኑ የጥበቃና እንክብካቤ ፕሮጀክቶችን በበላይነት በመምራትና በማስፈፀም ከፍተኛ ምስጋናን ያገኙ ትጉህ ሰው እንደነበሩ ከመሥርያ ቤታቸው የተገኘው ገጸ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡

ከዓለም አቀፉ የባህል ተቋም ዩኔስኮ ጋር በመተባበር ቅርሶች ለመጠበቅና ለመንከባከብ በተደረጉ ጥረቶች ውስጥ የአቶ ኃይሉ ድርሻ ፕሮጀክቶችን በማዘጋጀት፣ በመተግበርና ውጤታማነታቸውን በማረጋገጥ ረገድ የፈጸሙት ተግባር ተጠቃሽ ያደርጋቸዋል፡፡ ከፕሮጀክታዊ ሥራዎቻቸው መካከል `Lalibela: Bete Gebrael- Rufael Church Conservation and Consolidation Project` አንዱ ነው፡፡ በአኅጉራዊው ተቋም 'አፍሪካን ወርልድ ሄሪቴጅ ፈንድ' የነበራቸው ተሳትፎም ይበልታን የተጎናፀፈ ነው።

በኢትዮጵያ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶች ዙርያ በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች በተዘጋጁ መድረኮች በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎችን ከማቅረብ ባለፈ፣ በታዋቂው የፈረንሳይ ኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል ጆርናል 'Annales D'Ethiopie' ከታተሙት ሥራዎቻቸው መካከል 'Some Notes on the Great Walls of Wolayta and Dawro' ይገኝበታል።

አቶ ኃይሉ ለአዲስ አበባ ቅርሶች በተለይም ለግብረ ሕንፃዎች ከሚቆረቆሩት፣ በ"ልማት ስም" ነባርና ታሪካዊ ሕንፃዎች እንዳይፈርሱ ለመታደግ በቁርጠኝነት ከተንቀሳቀሱት አንዱ ነበሩ። እየተከናወኑ የሚገኙት የልማት ሥራዎች በታሪካዊው ቅርስ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳያስከትሉ “የቅርስ ተፅዕኖ ግምገማ” በማከናወን የልማት ሥራዎቹ ከቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ጋር ተጣጥመው መተግበራቸውን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉም በየጊዜው ድምፃቸውን ከማስተጋባት ቸል እንዳላሉ የሚያውቋቸው ሁሉ የሚያንፀባርቁት ሐሳብ ነው፡፡

ከእናታቸው ከወ/ሮ ከበቡሽ ተሾመና ከአባታቸው ከአቶ ዘለቀ ወልደፃድቅ በ1970 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ፣ ሰባ ደረጃ በሚባለው አካባቢ የተወለዱት አቶ ኃይሉ፣ የመጀመርያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን በደጃዝማች በላይ ዘለቀና በእንጦጦ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ካጠናቀቁ በኋላ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በአርኪዮሎጂ ትምህርት ዘርፍ በ1991 ዓ.ም. የመጀመርያ ዲግሪን፣ በመቀጠልም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በ1997 ዓ.ም. ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡

የቅድመ ምረቃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣንን በመቀላቀል በአርኪዎሎጂ ዘርፍ በሙያቸው አገልግለዋል፡፡ በተለይ ከ2002 ዓ.ም. ጀምሮ በባለሥልጣኑ የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመሆን ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

አቶ ኃይሉ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ42 ዓመታቸው ሐምሌ 17 ቀን 2012 ዓ.ም. አርፈው፣ በማግስቱ ሥርዓተ ቀብራቸው ቃሊቲ በሚገኘው ሳሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡ አቶ ኃይሉ ባለትዳርና የሁለት ልጆች (ሴት እና ወንድ) አባት ነበሩ፡፡

ዘንድሮ አዲስ አበባን በተለያዩ ፕሮጀክቶች የማስዋብ ተግባርን የተመለከቱት አቶ ኃይሉ፣ በተለይ ከአራት ኪሎ ሚያዝያ 27 አደባባይ ወደ ፒያሳ በሚወስደው ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንገድ እስከ ደጎል አደባባይና አራዳ ታሪካዊና ጥንታዊ ግብረ ሕንፃዎች ያሉበት አካባቢ ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረግ የከተማው አስተዳደር ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በማኅ

21/06/2020



Address

Gulel
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amen Media & Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amen Media & Communication:

Share