Aysheshim

Aysheshim I am honest free to discuss on issues and ready to know

04/08/2018

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የህዝቦችን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 28፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፥ ኢትዮጵያ የህዝቦቿን ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ በለውጥ ሂደት ውስጥ እንደሆነች አንስታል።

ለውጡም መላ የኢትየጵያ ህዝቦችን ባሳተፈ እና ባለቤት ባደረገ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል ያለው ሚኒስቴሩ፥ እየተካሄደ ካለው የለውጥ እንቅስቃሴም መላው የሀገሪቱ ህዝቦች ተጠቃሚ በመሆናቸው ተሳትፏቸውን በማጠናከር ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ሆኖም በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች አልፎ አልፎ የብጥብጥና የሁከት ድርጊቶች እንደሚስተዋሉ አስታውቋል።
እነዚህ ህገወጥ ድርጊቶች በሚስተዋሉባቸው አካባቢዎች የጸጥታ ሃይሉ ከህዝቡ ጋር ሆኖ የማረጋጋት ሥራ በማከናወን ላይ እንደሚገኝም ነው የገለፀው።

በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጂግጂጋ ከተማ የተከሰተው ብጥብጥ፣ ቀጥሎም ወደ ሌሎች አንዳንድ የክልሉ ከተሞች የተዛመተው ሁከት በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለውና በፍጥነት ሊገታ እና ሊታረም የሚገባው ድርጊት መሆኑን አስታውቋል።

የአገር መከላከያ ሠራዊታችን ከሌሎች የጸጥታ ሃይሎች ጋር በመሆን የተከሰተውን ሁከት በቅርበት ሲከታተል፣ ሁኔታውን ለመቆጣጠርና ህብረተሰቡን ለማረጋጋት ጥረት እያደረገ የነበረ ቢሆንም ብጥብጡ በተፈለገው ፍጥነት ሊቆም አልቻለም ብሏል።

በመሆኑም በክልሉ የህዝቦቻችን ሰላም እና ደህንነት አደጋ ውስጥ እየገባ ያለበት ሁኔታ በመፈጠሩ የመከላከያ ሃይላችን ሁከትና ብጥብጡን በዝምታ የማይመለከት መሆኑንና የአካባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ መሆኑን በጥብቅ እንደሚያሳስብ ነው የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር በመግለጫው ያስታወቀው።

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል

ከኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ

አገራችን ኢትዮጵያ የህዝቦቿን ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ በለውጥ ሂደት ውስጥ እንደሆነች ይታወቃል። ለውጡም መላ የኢትየጵያ ህዝቦችን ባሳተፈ እና ባለቤት ባደረገ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል። እየተካሄደ ካለው የለውጥ እንቅስቃሴም መላው የአገራችን ህዝቦች ተጠቃሚ በመሆናቸው ተሳትፏቸውን በማጠናከር ላይ ይገኛሉ።

ሆኖም በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች አልፎ አልፎ የብጥብጥና የሁከት ድርጊቶች ይስተዋላሉ። እነዚህ ህገወጥ ድርጊቶች በሚስተዋሉባቸው አካባቢዎች የጸጥታ ሃይሉ ከህዝቡ ጋር ሆኖ የማረጋጋት ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በጂግጂጋ ከተማ የተከሰተው ብጥብጥ፣ ቀጥሎም ወደ ሌሎች አንዳንድ የክልሉ ከተሞች የተዛመተው ሁከት በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለውና በፍጥነት ሊገታ እና ሊታረም የሚገባው ድርጊት ነው።

የአገር መከላከያ ሠራዊታችን ከሌሎች የጸጥታ ሃይሎች ጋር በመሆን የተከሰተውን ሁከት በቅርበት ሲከታተል፣ ሁኔታውን ለመቆጣጠርና ህብረተሰቡን ለማረጋጋት ጥረት እያደረገ የነበረ ቢሆንም ብጥብጡ በተፈለገው ፍጥነት ሊቆም አልቻለም።

በመሆኑም በክልሉ የህዝቦቻችን ሰላም እና ደህንነት አደጋ ውስጥ እየገባ ያለበት ሁኔታ በመፈጠሩ የመከላከያ ሃይላችን ሁከትና ብጥብጡን በዝምታ የማይመለከት መሆኑንና የአካባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ መሆኑን በጥብቅ ያሳስባል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር
ሃምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም.

18/07/2018

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አሸማጋይ ኮሚቴ አባላትን አነጋገሩ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 11 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አሸማጋይ ኮሚቴ አባላትን በፅህፈት ቤታቸው አነጋገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአስታራቂ ኮሚቴ አባላቱ በእርቅና ሰላም ረገድ አርዓያ መሆን እንዳለባቸው ጠቅሰው፥ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሰላም የሀገር ሰላም መሆኑንም ተናግረዋል።

በቀጣዩ ሳምንት በአሜሪካ በሚኖራቸው ቆይታም ለሰላም የሚከፈልን ማንኛውንም ዋጋ በመክፈል የቤተ ክርስቲያኗ ሰላም እንዲመለስ ጥረት እንዲያደርጉም አደራ ብለዋል።

የአስታራቂ ኮሚቴ አባላቱም የእርቀ ሰላሙ ጉዞ ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሱን ጠቁመው፥ በሁለቱም በኩል ያሉ አባቶችን በማስማማት በቅርቡ የሰላም እና የፍቅር ብስራት በኢትዮጵያ ይሆናል ብለዋል።

በኢትዮጵያም ሆነ በአሜሪካ የሚገኙት የሀይማኖት አባቶች ላደረጉላቸው ቀና ትብብርና ለሰጧቸው መልካም ምላሽም የአስታራቂ ኮሚቴው አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አስራ አንዱ የአሸማጋይ ኮሚቴ አባላት በቀጣዩ ሳምንት ወደ አሜሪካ በሚጓዙበት ወቅት የእርቅ ሂደቱን እንደሚቋጩ እና በአሜሪካ የሚገኘውን ሲኖዶስ ወደ ሃገር ቤት ይዘው እንደሚመለሱ ይጠበቃል።

መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ነው።

18/07/2018

የተቋረጠው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በተወሰኑ ቻይናውያን ሰራተኞች አገልግሎት እየሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰራተኞች ጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ምክንያት ዛሬ አገልግሎቱ ተቋርጦ የነበረውን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በጥቂት ቻይናውያን ሰራተኞች ብቻ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

የቀላል ባቡር አገልግሎቱ ዛሬ ማለዳ ላይ ሰራተኞቹ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ በማንሳታቸው አገልግሎት አቋርጦ ቆይቷል።

አሁን ላይም የትራንስፖርት አገልግሎቱ እንዳይስተጓጎል በተወሰኑ ቻይናውያን ሰራተኞች አማካኝነት በ6 ባቡር አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል።

ከቻይናውያን ሰራተኞች ውጭ ግን ኢትዮጵያውያንና ሌሎች ሰራተኞች ያቀረብነው ጥያቄ እስካልተመለሰ ድረስ ወደ ስራ አንገባም ብለዋል።

ሰራተኞቹ ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ኢንጅነር ብርሃኑ በሻህ ጋር ያደረጉት ውይይት ያለ ስምምነት ተጠናቋል።

ይህን ተከትሎም ኮርፖሬሽኑ ለሰራተኞቹ የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ ወደ ስራ የማይመለሱ ከሆነ ሌሎች በዘርፉ የሰለጠኑ ሰራተኞችን ወደ ስራ እንደሚያስገባ ገልጿል።

በዳዊት መስፍን

18/07/2018

The Addis Ababa Light Railway employees strike for a better pay

Address

Addis Ababa

Telephone

+251942525189

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Aysheshim posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Aysheshim:

Share